DebubTimes ደቡብ ታይምስ

DebubTimes ደቡብ ታይምስ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from DebubTimes ደቡብ ታይምስ, አርባ ምንጭ ደቡብ ኢትዮጵያ, Arba Minch'.

20/01/2025
19/01/2025

"ብርሃነ ጥምቀቱ ክርስቶስ የትህትናን ኃያልነት በተግባር ያስተማረበት በመሆኑ፤ በዓሉን ስናከበር በአስተምሮው መሰረት ትህትናን ተላብሰን ዝቅ ብለን ለማገልገል፤ ለመተባበር እንዲሁም ለአንድነትና ለሰላም ለመትጋት ራሳችንን በማዘጋጀት ሊሆን ይገባል። "

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

18/01/2025
18/01/2025
16/01/2025
16/01/2025
15/01/2025
14/01/2025

የሕክምና ባለሙያዎች ‘የተስተካለ’ ወይም ‘ፍጹም’ የሚባል የሴት ልጅ ብልት ዓይነት እንደሌለ ይናገራሉ። ለንደን ውስጥ በሚገኘው ጠጽንስ እና የማህጸን ሮያል ኮሌጅ የሚሠሩት ቤሪን ታዝካን፣ “የሁሉም ሴት ብልት የተለያየ ነው” ይላሉ። “የየትኛዋም ሴት ብልት ከሌላ ሴት ብልት ጋር በቅርፅ፣ በመጠን እና በጠረን የተለያየ ነው” ሲሉም ያስረዳሉ። ታካሚዎች ‘ብልቴ የሆነ ችግር አለበት’ ብለው ወደ ሕክምና እንደሚሄዱ ገልጸው፣ “ታካሚዎች ብልቴ የሆነ ችግር አለበት ብለው ሲመጡ ምንም ችግር እንደሌላቸው እነግራቸዋለሁ። ሰውነታቸው አንዳችም ችግር እንደሌለበት ሲሰሙ 90 በመቶው እፎይታ ይሰማቸዋል” በማለት ያብራራሉ።
https://bbc.in/3PxJ0QV

10/01/2025

“ሀሹ ኮሽ ባር የይዴ” ብሎ በሞቀ ሰላምታ እንግዳ የሚቀበል፤

“ታና ኤኮ ታ አይሻዶ” ብሎ ለወገኑ መከታነቱን የሚገልጽ፤

“ታ ዳባዶ” ብሎ ያለዉን የሚያካፍል፤

አፈሩ የሰጡትን የሚያበቅል፣ ባለ ልዩ ጣዕሙ ባስኬት ቡና፣ የኮሮሪማ፣ የሰሊጥ ተቆጥሮ የማያልቅ በተፈጥሮ ፀጋ የተንበሸበሸ፤

ሾልኣ ካሻ ብሎ ፈጣሪን አመስግኖ ምርቱን የሚቀምስ፣ የድንቅ ባህል ባለቤት፣
በ”ጾስታ” ጥብቅ ደን ዉስጥ የተጣላን የሚያስታርቅ፣

በዛያ፣ በሹልሹላ እና በዚምባ የሙዚቃ መሳሪያዎቹ ደስታን የሚያደምቅ፤ ያዘነን የሚያጽናና፣

የባስኬት ብሄረሰብ የምስጋና ሥነስርዓት በአደባባይ ለሚከበረዉ “ሾልአ ካሻ” በዓል እንኳን አደረሰን፣ አደረሳችሁ!!

ሀሹ ጾስ ኑና ኮሽ ባር የሊሲዴ !!


የባስኬት ብሔረሰብ ሰብል ምርት መድረሱን እንዲሁም ወደ ጎተራ መሰብሰብን አስመልክቶ ፈጣሪን ሳያመሰግን አዲሱን እህል አይቀምስም። ይህንንም ስርዓት ሾልኣ ካሻ ይለዋል፡፡

ሾልኣ ካሻ የባስኬት ብሄረሰብ የኢኮኖሚ፤ የማህበራዊ እና የፖለቲካዊ ተሳትፎ መገለጫ ነዉ፡፡ በኢኮኖሚዉ ያላረሰ፤ ምርት በጎተራዉ ያላጠራቀመ አርሶአደር ስርዓቱን ስለማያካህድ ሾልኣ ማዘጋጀት ስለማይችል ሁሉም አርሶ አደር በርትቶ ያርሳል በጎተራዉ ለዓመት ይቆጥባል፡፡

ይህ አገር በቀልና የስልጡንነት ምሳሌ የሆነዉ የምስጋና በዓል ባህላዊ ይዘቱን ሳይለቅ እንዲቆይ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንድተላለፍ አባቶች ታሪኩን በማስተማር ወጣቶች በመማር እንዲሁም ጠላታችን ድህነትን ለማሸነፍ ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረዉን የብልጽግና ጉዞ ስኬት ድርሻችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁኝ።

በዓሉ የሰላም የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ፡፡

ሀሹ ጾስ ኑና ኮሽ ባር የሊሲዴ!
እንኳን በሰላም አደረሰን!
መልካም በዓል!

ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር

08/01/2025
08/01/2025

መልካም የገና በዓል

07/01/2025

የኢየሱሰ ክርስቶስ የልደት በዓል የብሩህ ተስፋ መገለጫ ነው - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
*************************

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለኢየሱሰ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልእክታቸው፤ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የድኅነት የተሰፋ ቃል የተፈጸመበት፤ ዓመተ ኩነኔ ተደምስሶ፤ ዓመተ ምሕረት የታወጀበት ዕለትን በማሰብ በድምቀት የሚከበር፤ የክርስትና አስተምህሮ መሠረት የሆነ ታላቅ በዓል ነው ብለዋል፡፡

በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ይህ በዓል የብሩህ ተስፋ መገለጫ ነው ያሉት ርዕሰ መስታዳድሩ፤ የክርስቶስ መወለድ ጨለማው በብርሃን የመሸነፉ ምልክት፤ የብሩህ ዘመን ማብሠሪያ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

የዘንድሮው የገና በዓል ስናከብር ለሀገራዊ እና ክልላዊ የሰላምና የብልጽግና ራዕይ ስኬት፤ በሁሉም መስክ በህዝብ ባለቤትነት በተመዘገቡ ውጤቶች የሚጨበጥ ተስፋን ይዘን፤ የመጪዉን ብሩህ ዘመን አሻግረን እያየን ነው ሲሉም አመልክተዋል።

ከትዕቢት ይልቅ ትህትናን ገንዘብ በማድረግ ከጥላቻ እና ከመከፋፈል መንገድ በመላቀቅ በፍቅር፣ በመደመር እንዲሁም በአብሮነት እና በመተጋገዝ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በህዝባችን ዘንድ ለዘመናት የገነባነውን የመቻቻል፣ የአብሮነትና የመደጋገፍ እሴት በማጎልበት፤ ጊዜያዊ ፈተናዎችን በፅናት እያለፍን፤ በጋራ የሰነቅናቸው ግቦችን ዕውን ማድረግ እንደምንችል በማሰብም ጭምር ሊሆን ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል።

አንድነትና ኅብረት፤ መደጋገፍና መረዳዳት በክርስትና ልዩ ስፍራ እንደሚሰጠው የእምነቱ አስተምህሮ ያስረዳል ያሉት አቶ ጥላሁን፤ በመሆኑም በዓሉን በመተሳሰብና በመጠያየቅ፤ ያለንን ለለሌው በማካፈል፤ የተቸገሩ ወገኖችን በዘላቂነት ራሳቸውን እንዲችሉ ለማቋቋም በመተባበር ማክበር እንደሚገባ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡

Address

አርባ ምንጭ ደቡብ ኢትዮጵያ
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DebubTimes ደቡብ ታይምስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share