Berebere Media-በርበሬ ሚዲያ

Berebere Media-በርበሬ ሚዲያ የሀላባ ወቅታዊ መረጃዎችና ዝግጅቶች እንዲሁ ዶክመንተሪዎች?

ሀላባ ሂጅራ መስጂድ
19/04/2024

ሀላባ ሂጅራ መስጂድ

19/04/2024
19/04/2024

እውነታውን ደረስንበት 😂

18/04/2024
በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከተከሰተው የጎርፍ አደጋ በኋላ ፍርስራሹን የማጽዳት ስራ ተጀመረአዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ ...
18/04/2024

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከተከሰተው የጎርፍ አደጋ በኋላ ፍርስራሹን የማጽዳት ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ ከተከሰተው የጎርፍ አደጋ በኋላ ፍርስራሹን የማጽዳት ስራ ተጀምሯል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ የጎርፍ አደጋው የአንድ ሰው ህይወት ማለፍ ምክንያት ሲሆን፥ የመኖሪያ ቤቶችና ንግድ ቤቶች በከባድ አውሎ ንፋስ ጉዳት ደርሶባቸዋልም ተብሏል፡፡

አደጋው ከተከሰተ ከሰዓታት በኋላ የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች በመላ ሀገሪቱ በጎርፍ የተጥለቀለቁ መንገዶችን ለማጽዳት ውሃውን በፍሳሽ ማስወገጃ ለማፍሰስ ሲጥሩ እንደነበርም ነው የተነሳው፡፡

ሆኖም እስካሁን የጉዳቱ መጠን አልተገለጸም።

የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ሪከርድ የሆነ የዝናብ መጠን ማሳየቱንም ነው የሀገሪቱ ሚቲዎሮሎጂ ማዕከል የገለጸው።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከባድ ዝናብን ለመቆጣጠር የሚያስፈልጉ በቂ የውኃ ማስተላለፊያ መሰረተ ልማቶች የሌሏት ሲሆን፤ ይህም የሆነው ብዙውን ጊዜ ዝናብ በዓመት ጥቂት ጊዜ ብቻ የሚጥል በመሆኑ ነው፡፡

በዚህም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የዝናብ መጠንን ለመጨመር በተደጋጋሚ የደመና ማከማቸት ስራዎችን ያደርጋሉ መባሉን የዘገበው ሲጂቲኤን ነው፡፡

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፍርስራሾችን ከመንገድ ላይ ሲያፀዱ ትምህርት ቤቶች ዛሬ በኦንላይን ትምህርት መስጠት እንዲቀጥሉ መንግስት አዟል ነው የተባለው፡፡

የዱባይ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ በበኩሉ፥ የጣለው ከባድ ዝናብ ከፍተኛ መስተጓጎል ፈጥሮ በረራዎች በመዘግየታቸው እና በመቀየራቸው በዱባይ ያሉ መንገደኞች ወደ አውሮፕላን ማረፊያው እንዳይሄዱ መክሯል።

17/04/2024

የ 40 አመት ሰው ያፈቀረችው ታዳጊ ታሪክ

የሀላባ መንገዶች ወግ
16/04/2024

የሀላባ መንገዶች ወግ

እስራኤል በኢራን ላይ በምትወስደው የአጻፋ እርምጃ እጇን እንደማታስገባ አሜሪካ አስታወቀች **********************ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታን...
16/04/2024

እስራኤል በኢራን ላይ በምትወስደው የአጻፋ እርምጃ እጇን እንደማታስገባ አሜሪካ አስታወቀች
**********************

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ በተወያዩበት ወቅት እስራኤል በኢራን ላይ በምትወስደው የአጻፋ እርምጃ እጇን እንደማታስገባ መግለጻቸው ነው የተነገረው።

ለዚህም እስራኤል ለምትወስደው የአጻፋ እርምጃ ጥንቃቄ ልታደርግ እንደሚገባ ማሳሰባቸው ተገልጿል።

ከዚያ ውጭ ባላው ወታደራዊ ድጋፍ ግን እስራኤል የአሜሪካ ድጋፍ እንደማይለያት ተገልጿል።

ኢራን በበኩሏ አሜሪካም የእስራኤልን መልሶ ማጥቃት የምታግዝ ከሆነ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ወታደራዊ ጣቢያዎቿ ላይ ጥቃት እንደሚትፈጽም ማሳሰቧን የሮይተርሰ ዘገባ ያመለክታል።

"የኛው(የዳቦያው) የግላችን ነው የናንተው(የሀላባው) የጋራችን ነው"
15/04/2024

"የኛው(የዳቦያው) የግላችን ነው የናንተው(የሀላባው) የጋራችን ነው"

15/04/2024

ዌራ ወንዝ

ዌራ ወንዝ (ሀላባ ዞን ሀላባ ከተማ ጫምቡላ አከባቢ)
15/04/2024

ዌራ ወንዝ (ሀላባ ዞን ሀላባ ከተማ ጫምቡላ አከባቢ)

15/04/2024

ከመርካቶ ዱባይ ተራ እስከ የበረሃዋ ገነት ዱባይ ድረስ የነገሰ ስም አህመድ

የበርበሬዎቹ ወዳጅ አህመድ ረምዚ

15/04/2024

በልጅ ቅም አይያዝም 😂😂😂

14/04/2024

መግቢያም መውጫም፤
ላኢላሃኢለላህ

15 የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤልን ኔቫቲም ስትራቴጂያዊ መሰረት ማጥቃታቸው ተገለጸ********************የመረጃ ምንጮች እንደዘገቡት ቢያንስ 15 የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤልን ስትራቴ...
14/04/2024

15 የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤልን ኔቫቲም ስትራቴጂያዊ መሰረት ማጥቃታቸው ተገለጸ
********************

የመረጃ ምንጮች እንደዘገቡት ቢያንስ 15 የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤልን ስትራቴጂያዊ አየር ማረፊያን መትተዋል።

ኢራን ቅዳሜ ለሊት በእስራኤል የሚገኘውን ኔቫቲም አየር ሰፈርን በ15 ሚሳኤሎች ኢላማ አድርጋለች ሲሉ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እያስነበቡ ይገኛሉ።

ጥቃቱን ተከትሎም ጣቢያው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት እና ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጪ እንደሆነ ቢገለፅም የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ግን የተተኮሱት ሚሳኤሎች በቦታው ቀላል መዋቅራዊ ጉዳት ማድረሳቸውን ገልጸው ጥቃቱን ተከትሎም ጣቢያው ስራውን ቀጥለዋል ብለዋል ።

የኔቫቲም አየር ማረፊያ በኔጌቭ በረሃ ክልል ውስጥ በእስራኤል ከተያዙት ግዛቶች በስተደቡብ እና በቢየር ሸቫ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን የእስራኤል መንግስት የኤፍ-35 ተዋጊዎች ዋና ጣቢያ ነው።

ጥቃቱ የደረሰባት እስራኤል እና አጋሮቹ ከኢራን የተተኮሱ ሚሳኤሎች ቀጥር በርካታ መሆኑን በማንሳት ከ300 በላይ የሚሆኑትን ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን አደጋ ሳያደርሱ ማክሸፋቸውን አስታውቀዋል።

ቅዳሜ ለሊት ላይ ኢራን በእስራኤል ላይ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የተኮሰቻቸው ባለስቲክ ሚሳኤሎች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ከሞላ ጎደል ያልተሳኩ ነበሩ ሲሉ የእስራኤል እና የአሜሪካ ባለስልጣናት ገልፀዋል።
ከኢራን ግዛት የተተኮሱት ከ300 በላይ ሚሳኤሎች እና ድሮኖች አብዛኛዎቹ እስራኤል ከመድረሳቸው በፊት ተጠልፈዋል ሲል ሲኤንኤን አስነብቧል።

የእስራኤል ጦር እንዳስታወቀው በኢራን የተተኮሰ "99 በመቶ" ሚሳኤሎች በእስራኤል እና በአጋሮቿ የከሸፉ ሲሆን "ጥቂት" የባለስቲክ ሚሳኤሎች ብቻ ወደ እስራኤል ደርሰው ጉዳት አድርሷል።

በአጠቃላይ 170 ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ ከ30 በላይ ክሩዝ ሚሳኤሎች እና ከ120 በላይ የባላስቲክ ሚሳኤሎች ኢራን በአንድ ሌሊት ወደ እስራኤል መተኮሷንም የእስራኤል ጦር አስታውቋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ በስልክ ተናገሩት በተባለው መልዕክት እስራኤል ግብ የሌለውን የኢራን ጥቃት መከላከል በመቻሏ ድል ነው ሲሉ መናገራቸውን አንድ የአሜሪካ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን ለሲኤንኤን ተናግረዋል ።

የአሜሪካ ባለስልጣናት ሚሳኤሎቹን ለመምታት ምን አይነት መከላከያ እንደተጠቀሙበ ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ ከ70 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሶስት ባለስቲክ ሚሳኤሎች በአሜሪካ ባህር ሃይል መርከቦች እና ወታደራዊ አውሮፕላኖች መምከናቸውን ተናግረዋል።

ከጥቃቱ በኋላ መግለጫ ያወጡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ አሜሪካ እስራኤልን ከኢራን ጥቃት ለመከላከል ጥሩ ዝግጅት እንዳደረገች ገልፀዋል።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በሰጡት መግለጫ የእስራኤልን መከላከያ ለመደገፍ ባለፈው ሳምንት ውስጥ የዩኤስ ጦር አውሮፕላን እና የባላስቲክ ሚሳኤል መከላከያ አውዳሚዎችን ወደ ክልሉ አንቀሳቅሳለች።

ብሪታንያም ብትሆን በክልሉ ያላትን የንጉሳውያን አየር ሃይል አውሮፕላኖችን በመጠቀም ጣልቃ ለመግባት መዘጋጀቷን ተናግራለች።

የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይም ፈረንሳይ የኢራንን ጥቃት በመከላከል ላይ ተሳታፊ መሆኗን ተናግረዋል።

በእስራኤል ላይ ከተተኮሰው የጦር መሳሪያዎች መካከል የተወሰኑት የተተኮሱት ከኢራቅ እና የመን መሆኑንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

እስራኤል ሀማስን ለመዋጋት በሚል በጋዛ የጀመረችው ጥቃትን ተከትሎ የአለም ሀገራት በጎራ ተከፍለው ሲቃወሙና ሲደግፉ ተስተውሏል ።
ይህንን የጋዛን ጥቃት ከሚቃወሙና ከእስራኤል ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት ከሌላቸው ሀገራት መካከል የምትጠቀሰው ኢራን በእስራኤል ላይ የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ሀያላኑ ሃገራት ጦራቸውን ስለማንቀሳቀስ እና እስራኤልን ስለመደገፍ እየመከሩ ይገኛሉ ። ይህ ደግሞ ሶስተኛው የአለም ጦርነትን ሊያስከትል ይችላል የሚለውን ስጋት ከፍ አድርጎታል ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል። መዘገቡን ኢቢሲ ዘግቧል።

ኢራን ቅዳሜ ከለሊት እስከ እሁድ ንጋት እስራኤል ላይ ሰው አልባ እና ባላስቲክ ሚሳኤሎችን በማዝነብ እንቅልፍ ነስታት አንግታለች።
14/04/2024

ኢራን ቅዳሜ ከለሊት እስከ እሁድ ንጋት እስራኤል ላይ ሰው አልባ እና ባላስቲክ ሚሳኤሎችን በማዝነብ እንቅልፍ ነስታት አንግታለች።

"ዩስሪ ዳቦና ኬክ" ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች በተጨማሪ ጣፋጭ ዳቦና ድፎ ዳቦ መጀመራችንን ሲንገልጽሎ በታላቅ ደስታ ነው።ለሰርግ ለልደት አሊያ ለዘመድ ጥየቃ ድፎ ዳቦ ይዘው መሄድ ቢያስፈልጎዎ...
13/04/2024

"ዩስሪ ዳቦና ኬክ"
ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች በተጨማሪ ጣፋጭ ዳቦና ድፎ ዳቦ መጀመራችንን ሲንገልጽሎ በታላቅ ደስታ ነው።
ለሰርግ ለልደት አሊያ ለዘመድ ጥየቃ ድፎ ዳቦ ይዘው መሄድ ቢያስፈልጎዎ አያሳስቦዎ ሀሳቦትን እና ላይ ይጣሉ በፈለጉት መጠን ጣፍጭ ዳቦ ደፍተን እናደርስሎታለን ቢቻ ይዘዙን።
አድራሻችን ሀላባ ዞን ዋና አስተዳደር ህንጻ ፊትለፊት ያገኙናል።
ጥራት ከፍጥነት ጋር ዩስሪ ዳቢና ኬክ !ለበለጠ ምውረጃ 0911080824 ሀሎ ይበሉን ሀላባ

13/04/2024

በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን የኢድ ሰላት

12/04/2024

ወልዳ ጥላዉ የሄደችዉን ልጅ ከአረብ አገር ስትመለስ ያጣችዉ ሴት

ወሎ ከሚሴየ1445ኛው ዓ.ሂ የኢድ አል ፈጥር በዓለም አከባበር ስነስርዓት በወሎ ከሚሴ ከተማ!.©ሀሩን ሚዲያ
10/04/2024

ወሎ ከሚሴ

የ1445ኛው ዓ.ሂ የኢድ አል ፈጥር በዓለም አከባበር ስነስርዓት በወሎ ከሚሴ ከተማ!.
©ሀሩን ሚዲያ

አዲስአበባ ስታዲየም የ1445 ዓ.ሒ ዒድ አል‐ፊጥር ሰላት በአዲስ አበባ ስታዲየም!
10/04/2024

አዲስአበባ ስታዲየም

የ1445 ዓ.ሒ ዒድ አል‐ፊጥር ሰላት በአዲስ አበባ ስታዲየም!

ኢድ በሀላባ❤
10/04/2024

ኢድ በሀላባ❤

10/04/2024
09/04/2024


አላሁ አክበር
አላሁ አክበር
ላኢላሀኢልለላህ
አላሁ አክበር
አላሁ አክበር
ወሊላሂል ሐምድ 🙏

እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሂጅራ  የዒድ አልፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ዒድ ሙባረክ
09/04/2024

እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አልፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ

በመጨረሻም ለእንግዶቹ የሀላባ ዞን አስተዳዳር ሽኝት አደረገላቸው
09/04/2024

በመጨረሻም ለእንግዶቹ የሀላባ ዞን አስተዳዳር ሽኝት አደረገላቸው

09/04/2024

በመጨረሻም ለእንግዶቹ ከሀላባ ዞን አስተዳዳር ደመቅ ሽኝት ተደረገላቸው

አላሁ አክበር

09/04/2024

ሱዳየዊ ቃሪዕ ሼኽ አል ዘይን ሙሀመድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ በኑር መስጂድ ተገኝተው የረመዳን 30ኛ ለሊት የተሀጁድ ሰላት አሰገዱ

በመጨረሻም ዱኣ አደረጉ

09/04/2024

ሱዳናዊ ቃሪዕ ሼኽ አል ዘይን ሙሀመድ በሀላባ ቁሊቶ ኑር መስጂድ ተገኝተው ረመዳን 30ኛ ለሊት የተሀጁድ ሰላት ከአሰገዱ በኃላ 🙏

Address

Alaba K'ulito

Telephone

+251919097805

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Berebere Media-በርበሬ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Berebere Media-በርበሬ ሚዲያ:

Videos

Share