11/08/2022
በልብስ ላይ የሚሰሩ ሲህሮች
በዶ/ር ኡሙ ሚስባህ
አልሀምዱሊላህ አላህም ሲመርጥ ነውና ይህ ኡማውን የማገልገል እድል የሚገኘው ለዚህም አላህን ከልብ ላመሰግነው ወደድኩ!! በዚህም መንገድ ኡማውን ለማገልገል ላሰባሰበን ዶክተር አቡ ፈርሃን አሏህ ረጅም እድሜ አፊያን እንዲሰጥልኝ ጌታዬን ተማፀንኩ፡፡ ነገራቶች ሁሉ በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ሲሆኑ ቢድአዎች ፈጠራዎች በሙሉ ይወገዳሉ ከኢስላም መስመር መውጣት ይቆማልል አልሀምዱሊላህ በቻልነው አቅም እውቀትን እናስጨብጣለን፡፡
በዛሬው እለት በልብስ ላይ ስለሚሰሩ ሲህሮች ለመዳሰስ እንሻለን፡፡ ይህ ሲህር ብዙውን ግዜ በሃገራችን የተለመደ ሲሆን በሁለት መልኩ ይሰራል ፡፡
አንደኛው ልብስን በስጦታ መልክ በመስጠት ሲህር የተሰራበትን ልብስ ከጤነኛው ልብስ ጋር በማቀላቀል፡፡ ሌላኛው ደግሞ ልብስን በመውሰድ ቆርጦም ይሁን ከነአካቴው በመውሰድ፡፡ በሁለቱም መንገድ ሲህር የተሰራባቸው ሰዎች አንደኛው አዲስ ልብስ ከልብሶቹ ጋር መቀላቀሉን ያያል ግን ልብ አይልም ሌላኛው ደግሞ እንደጠፋበት ይረዳል ግን እርሱም ልብ አይልም፡፡ ብዙውን ግዜ ከህክምና በፊት ነገሩን ልብ ብለው የሚነግሩን ልብሶቻቸው የተቆረጡባቸው ሰዎች ናቸው እነርሱም በሌላው ተመልካች ግፊት ነው ‹‹ልብስሽ ምን ሆኖ ተቆረጠ…ልብስህ ምን ሆኖ ተቆረጠ›› በሚል ጥያቄ ተነስተው አስታውሰው ይነግሩናል፡፡ ልብ ሊባል የሚገባው ግን እነኚህ ሲህሮች ሲህር በተሰራበት ሰው ላይ የመርሳት ችግርን ወድያው መፍጠራቸው ነው፡፡ ይህም ከህክምና በፊት ሲህሩ እንዲደበቅ ያደርጉታል፡፡
ምልክቶቹ
1..ማሳከክ
ይህ በሰውነት ላይ የሚፈጠር የመጀመርያው ምልክት ነው፡፡ ትንንሽ የሆኑ ሽፍታዎች ይፈጠራሉ፡፡ እኒህ ሽፍታዎችን በምን ሰአት እንደሚነሳ ለማወቅ የሚጠረጥሩትን ልብስ መልበሱ ብቻ በቂ ነው፡፡ ሰውነት ወድያው ሽፍ ይታል፡፡ መተኛት አይችሉም መቀመጥ ከሰው ጋር ማውራት አይችሉም፡፡ የማሳከኩ ሁኔታ በጣም በጣም አሰቃይ ነው ፡፡ ሰውነታቸውም እስኪደማ ድረስ ሊያኩ ይችላሉ፡፡
2..ማቃጠል
ይህ ስሜት የሚታየው በጭንቅላት ላይ ነው፡፡ ምሳሌው ልክ ውሀና ወደ አፍንጫችን በፍጥነት ስናስገባ አእምሮ እንደሚነደው አይነት ስሜት ይፈጠራል፡፡ ይህም ከእንቅልፍ ሲነቁ ጎንበስ ብለው ወዲያው ቀና ሲሉ ልብሱ ላይ ያለው ጠረን ሲሸታቸው በፍጥነት አእምሯቸው ጭንቅላታቸው ይቃጠላል፡፡
3..ጭንቀት
ሁሌም ቢሆን እንደተጨነቁ ነው፡፡ በተለይም ልብስ በስጦታ መልክ የተሰጣቸው ታካሚዎች ያ ልብስ ያለነበት ስፍራ እስካሉ ድረስ እራሳቸውን በጭንቀት ሊጨርሱ ይደርሳሉ፡፡ አላህም ይጠብቀን ብዙውን ግዜ ማልቀስ መነጫነጭ ይጀምራሉ፡፡
4..የቆዳ መላላጥ
የእግር ቆዳዎች ቅርፊት መስራት፡፡ የእጅ ቆዳዎች ቅርፊት መስራት ይህን ቪታሚኖችን ቢጠቀሙ እንኳ ሰውነታቸው ይፈነዳዳይ ይላላጣል፡፡ እንደ እባብ ቆዳ ሰውነታቸው ይላላጣል፡፡
5..መታፈን
በሚተኙበት ወቅት ብቻ አይደለም ያን ሲህር የተሰራበትን ልብስ ለብሰው መራመድ መንቀሳቀስ አይችሉም ውስጣቸው በጣም የሚያስጠላ ስሜት አለ፡፡ ቢያለቅሱ አይወጣላቸውም ያነጫንጫቸዋል፡፡ አንድ በርሜል ውስጥ ገብተው እንደተዘጋባቸው አይነት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡
6..ተቅማጥና ትውከት
ይህ አይነቱ ምልክት ሲህሩ በተሰራ ሰሞን የሚፈጠር ሲሆን፡፡ በሰገራው ስር ደም የመቀላቀል ባህሪ አለው፡፡ በዚህ ግዜ ወዲያው በራሳቸው ላይ ተስፋ ቆራጮችም ናቸው፡፡ የሚሞቱ ይመስላቸዋል፡፡ ኑሮ በነርሱ ላይ ፊቷን ያዞረች ይመስላቸዋል፡፡ ተስፋ ይቆርጣሉ ያማርራሉ፡፡ ብዙውን ወቅት ከሽንት ቤት ባይወጡ ደስታቸው ነው፡፡
7..መፍራት
ድንጉጦች ናቸው፡፡ ይህን ማወቅ እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ ልባም የሆነ ወንድ ልባም የሆነች ሴት ከሆነ ግዜ አንድቶ ከእንቅልፋቸው ሲነሱ በርግገው ነው ኮሽ ባለ ቁጥር ደንጋጮች ናቸው፡፡ በተለይ የአዛን ድምፅ ሲሰሙ ውስጣቸው ይረበሻል ይጨንቃቸዋል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ፍርሀትን ይወርሳቸዋል፡፡ ከሰው በሙሉ ተለይተው ቢቀመጡ ተደሳቾች ናቸው፡፡
8..መስገድ ማቆም
ሰላት ለነርሱ ጅግ በጣም ከባድ ነው፡፡ የታወቀ ነው ከሸይጧን ግፊት በተጨማሪ እነርሱ ሰላትን መስገድ ሞት መስሎ ይታያቸዋል፡፡ በአስገዳጅ ሁኔታ እንኳ አይሰግዱም፡፡ መሳርያ ደግኖ እነርሱን ማሰገድ ይከብዳል አይደለም በፍቃደኝነተ፡፡ ቤት ውስጥ ሰው ሰላት እየሰገደ ሲያዩ መጭነቅ ከቦታው ቶሎ መሸሽ የነርሱ ባህሪ ነው፡፡ አላህ ይጠብቀንና ከፍርሃቱ ጋር ሰላት መስገድ መጥላት ተውስጥ ጭንቀት ነው፡፡
9..ሰላም ማጣት
የሰው ልጅ ሰላም የሚጣው ችግር ሲደርስበት ሊቆጣጠረው የማይችለው አይነት አደጋ ሲደርስበት ወይም ወደ ችግን እንደሚገባ ሲያውቅ ነው፡፡ ይህን ማሰብ አይከብድም ነጋ ጠባ ጭንቅ ጥብብ ማለት፡፡ ልብ በፍርሃት መሸበር ሰላም ማጣት ሰው ማየት መጥላት፡፡ ባጠቃላይ ሰላምን ማጣት እጅግ ትልቅ ቅጣት ነው፡፡ እመኑም አሏህ ሷሂሮችን ከዚህ በላይ ይቀጣቸዋል፡፡
10.. መሽተት
ሲጀምር ከእግር ከብልት ከብብት ለ,ከአፍ ሉሆን ይችላል የበሽታውን መክፋት ግን የምናውቀው ሙሉ ለሙሉ ሰዎች አጠገባችን መቆም ሲጠሉ ማየት ነው፡፡ ሰዎች ወዲያው ከአጠገባችን ይሸሻሉ!! አጠገባችን ሆነው ቢያወሩ እንኳ አፍንጫቸውን ይዘው ነው፡፡ ይህ ታማሚው ሰውነቱን ቢታጠብ ቢታጠን ከመሽተት ወደኋላ አይልም፡፡
11..መደበር
ይህ ከላይ የጠቀስናቸው ምልክቶች በሙሉ ሲፈጠሩ በስተመጨረሻ እራስን ማግለል መሞት አለብኝ ብሎ ማሰብ እኔ አልጠቅምም ይህ አለም ለኔ ስቃይ ብቻ ነው ያስገኘው ብሎ ሰዎችን መጠርጠር ይጀምራሉ ከዚህም አለም ለመለየት የሚያስቡት ሞት ብቻ ነው፡፡ ሁሌም መቆዘም መደበት የነሱ መገለጫ ይሆናል፡፡
12..አስፈሪ ህልሞችን መመልከት
ከከፍታ ቦታዎች ላይ መውደቅ፡፡ እባቦች ሲነድፏቸው አይጦች ወደነርሱ ሲሮጡ መመልከት ብሎም ጥቁር የሆኑ አስፈሪ ፍጥረታት ሲያፍኗቸው ብቻ ሰላም የማይሰጡ አይነት ህልሞችን መመልከት ይጀምራሉ፡፡
13..የገንዘብ በረካን ማጣት
እነኚህ ሰዎች ከዚህ ፊት አትራፊ ነጋዴ ቢሆኑ እንኳ ብራቸው በረካ የለውም የት እንደሚገባ በምን ላይ እንደሚወጣ ሊያውቁ ይሳናቸዋል፡፡ ሊያስቡ ሲጥሩ አእምሯቸው ይታመማል፡፡
14..የሆድ መነፋት
ሆዶቻቸው ልክ እንደ እርጉዝ ሴት ይነፋሉ፡፡ ለየት የሚያደርገው ሆዳቸው መነፋቱ ብቻ ሳይን በጣም ይወጠራል፡፡ ውስጣቸውም የሚገላበጥ ነገር እንዳለ ይረዳሉ፡፡
ህክምናው
1.ጥዋትና ማታ አላህን ማስታወስ ቁርአን መቅራት፡፡
2.ቤት ውስጥ የሚጠረጥሩትን የልብስ አይነት ማውጣት፡፡
3.ውሃ በብዛት መጠጣት፡፡
4.ቡና ጫት ኮካ ሺሻ አይነት የመሳሰሉ ሱሶችን ማቆም፡፡
5.ባፋጣኝ ሩቅያህ መጀመር እራሳቸውን በኢማን ማጠናከር፡፡
6.ዳእዋዎችን ማዳመጥ!!
ህክምናውም በቀልብ ዶክተር ቴሌግራም ቻናል ላይ ይቀጥላል፡፡
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇......https://t.me/Qallbdoc
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere
👆
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb
👆
የ ዩትዩብ አድራሻችን👇
https://www.youtube.com/c/የቀልብዶክተር