በቤይሩት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 164 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
_
( ጥር 05 ቀን 2017 ዓ.ም.አዲስ አበባ):-በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ እና ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያ ዛሬ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ።በዛሬው ዕለት ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 164 ነው።
አሜሪካ መግታት በተሳናት የሎስ አንጀለሱ የሰደድ እሳት የሟቾች ቁጥር 24 ደረሰ። በአካባቢው ተጠናክሮ የቀጠለው ከባድ ንፋስ የሰደድ እሳቱን ሊያጠናክረው እንደሚችል መስጋታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የሰደድ እሳቱ ባደረሰው አደጋ እስካሁን ከሞቱት በተጨማሪ በአስራዎቹ የሚቆጠሩ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ። በአደጋው እስከ 180 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት እና ንብረት ወደ አመድነት ተቀይሯል ነው የተባለው።
በአሜሪካ ሁለተኛ ትልቋን ከተማ ለአንድ ሳምንት ያህል እያቃጠለ የሚገኘው እሳቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እና ህንጻዎችን ወደ አመድነት ቀይረዋል፤ ከ100 ሺ በላይ ሰዎችን ደግሞ ከመኖሪያቸው አፈናቅሏል ።
አሜሪካን እያሳሳበ የመጣው እስካሁን የደረሰው ውድመት እና ጥፋት ሳይሆን ከዚህ በኋላ ከባዱ ነፋስ እሳቱን አስፋፍቶ ከዚህም የከፋ ውድመት እንዳያደርስ ነው።
የሀገሪቱ ብሄራዊ ሜትሮሎጂ ትንበያ እንዳመለከተው ከነገ ማክሰኞ ጥር 6 ጀምሮ በሰዓት 110 ኪ/ሜ የሚገሰግስ ከባድ ንፋስ ሊከሰት ይችላል።
የዓለም ቱጃሮችን ያስነባው ሰደድ እሳት !!!
ከባለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስአንጀለስ የተከሰተው ሰደድ እሳት በፍጥት በመዛመት ከፍተኛ ውድመት እና ጉዳት እያስከተለ ቀጥሏል፡፡
እስካሁን 10 ሺህ ውድና ቄንጠኛ ቪላዎች አመድ ሆኑ። ዕውቅ እና ቱጃር የሆሊውድ ተዋንያን ውድ ንብረቶች እንዳልነበሩ ሆኑ። ከአንድ ታዳጊ ሀገር ዓመታዊ በጀት በላይ የሆነ 150 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ተቃጥሎ አመድ ተዛቀ።
እሳቱ አሁንም እያወደመ ቀጠለ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ግዙፍ ህንፃዎች የእሳት እራት ሆኑ። በሺህ የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ዕምቢ ብሏቸው 900 ዕስረኞች ከማረሚያ ወጥተው በእሳት ማጥፋት ስራ ቢሰማሩም ሰደድ እሳቱ ከውቅያኖስ በሚመጣ አደገኛ ንፋስ ሃይል እያገኘ በሁለት አቅጣጫ በፍጥነት እየተዛመተ ነው። በወርቅ የተንቆጠቆጡ የሚመስሉ ቤቶች ጋዩ።
የማያልቅ የሚመስለውን ውድ ሀብታቸውን ያጡት ሀብታም የሆሊውድ አክተሮች ዕምባ አውጥተው አለቀሱ። ታዋቂው ሀብታሙ የሆሊውድ አክተር ጀምስ ውድ ሀብቱ ተቃጥሎበት ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቃለመጠይቅ በዕምባ ታጥቦ ዕምባውን መቆጣጠር ሲያቅተው ቃለመጠይቁን አቋረጠ። ልቤ ተሰበረ አለ።
በዓለም ከእግዚአብሔር በቀር ምንም እንደማያስመካ በግልጽ ለሁሉም ታይቷል ። የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ያልገባቸው ይህን የሚያውቁበት ክስተት በልዕለ ሃያሏ ሀ
በእሳት እና በረዶ የተፈተነችው ልዕለ ኃያል ሀገር
የዓለማችን ልዕለ ኃያል ሀገር አሜሪካ ከሰሞኑ እሳት እና በረዶ ለጥፋት አብረውባት ሰንብታለች፡፡
ሀገሪቱ በአንድ በኩል ያገኘውን ሁሉ በሚበላ ከባድ ሰደድ እሳት፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጥንትን በሚሰረስር በረዶ ተፈትናለች፡፡
በሎስ አንጀለስ ከተማ የተነሳው ሰደድ እሳቱ እስካሁን የ10 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ከ170 ሺህ የሚበልጡ ሰዎችም መኖሪያቸውን ለቀው ለመሸሽ በተጠንቀቅ እንዲያሳልፉ አድርጎ ነበር፡፡
በከባድ ሙቀት እና ኃይለኛ ንፋስ የታጀበው ሰደድ እሳቱ ከ10 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን፣ ህንጻዎችን እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን አውድሟል፡፡
በአሜሪካ ሎሳንጀለስ የተከሰተው ሰደድ አሳት ዙሪያ ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ?
በአሜሪካ ሎሳንጀለስ ዙሪያ የተቀሰቀሰው ከባድ የሰደድ እሳት አደጋ ትናንት ምሽት ጀምሮ ወደ ሆሊውድ ኮረብታዎች እየተስፋፋ መሆኑ ተገልጿል።
ከባለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በርካታ ቦታዎችን በፍጥነት ያዳረሰው በደረቅ ንፋስ እየተፋፋመ ያለው እሳት የማጥፋት ዘመቻውን ያከበደው ሲሆን ከ100 ሺ በላይ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ከ57 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚገመት ተገልጿል።
በአፋር ክልል፣ ሳጋንቶ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየወጡ ነው
*****
በአፋር ክልል፣ ዱለሳ ወረዳ በተከሰት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየተፈጠሩ ይገኛሉ።
በወረዳው በሳጋንቶ ቀበሌ የደረሰውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በስፍራው በአካል በመገኘት የመስክ ምልከታ ያደረገ የኢቢሲ ሪፖርተር በቀበሌው በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየወጡ መሆኑን መታዘቡን ገልጿል።
በቀበሌው በተለይ በዶፈን ተራራ ላይ የመሬት መንቀጥቀጡ በመጠኑም በድግግሞሹም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን በዚህም ሳቢያ ተራራው እየተናደ እንደሆነ ገልጿል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በፈጠረው ግፊት በቀበሌው እንፋሎት አዘል ፍል ውሃ እና ቅባት አዘል ጥቁር ውሃ ከመሬት እየፈለቀ መሆኑንም ጠቅሷልል።
በቀበሌው የሚኖረው አርብቶ አደር ማህበረሰብ ከሥፍራው ተነስቶ በሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፍር እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።
በመሬት መንቀጥቀጡ ሳቢያ በፈንታሌ እና በዶፈን ተራራ መካከል የተፈጠረው የመሬት ስንጥቅ ክፍተቱ እየጨመረ መሆኑንም አክሏል።
አራተኛው አርኪ የሪል ስቴት ኤክስፖ በስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ
የቤት ሻጮችና ገዢዎች፣ እንዲሁም ገንቢዎች የተለያዩ ተቋማትን ለማገናኘትና ለማስተሳስር ዕድል ይሰጣል የተባለለት አራተኛው አርኪ ሆምስ ኤክስፖ በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በይፋ ተከፍቷል።
ከዛሬ ታህሳስ 25 እስከ ታህሳስ 27/2017 በሚካሄደው በዚህ ኤክስፖ በርካታ የቤት አልሚዎች እየገነቡት ስላለው ቤት ግንባታዉ ያለበት ደረጃ፣ ሊገነቡት ስላቀዱት ቤት፣ ቤቶቹን ዋጋ፣ ስለሚፈልጉት እቃ እና አገልግሎት ከኤክስፖ ተሳታፊዎችና ከጎብኚዎች ጋር መረጃና ልምድ ይለዋወጣሉ ተብሏል።
ወቅቱ የበዓል እንደመሆኑ በርካታ ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ በመሆኑ የኤክስፖውን ሳይጎበኙ ቤት እንዳይገዙ በሚል ሙሉ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት ልዩ የገና በዓል ቅናሽ መኖሩም ተገልገልፃል።
አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ያዘጋጀው ይሄ ኤክስፖ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ የቤት አልሚ ድርጅቶች እና አጋር አካላት እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ኤክስፖው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ፤ አንድ ላይ በማቀናጀት በከተማ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊሰሩ የታሰቡ መዋቅራዊ ቅንጅቶችን ለመፍጠር ምቹ ዕድል የሚፈጥር ገዥና ሻጭን በአንድ ላይ በማገናኘት በቀጥታ የሚፈልጉትን የቤት ዓይነት የሚመርጡበት ስለአጠቃላይ ሂደት በግልፅ መረጃ የሚለዋወጡበት በርካታ አማራጮች ያ
በአፋር ክልል ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የተከሰተው የቮልካኖ ፍንዳታ
እአአ በ1967 በስድስት ቀናት ጦርነት እስራኤል በሶሪያ ኃይሎች ከዚህ ተራራማ አካባቢ ጥቃት ተፈጽሞባታል።
እስራኤል በመልሶ ማጥቃት ወደ 1,200 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሆን ቦታ በቁጥጥሯ ሥር አስገብታለች።
በአውሮፓውያኑ 1973 በተደረገው 'ዮም ኪፑር' ጦርነት ሶሪያ ግዛቱን መልሳ ከእስራኤል ለመውሰድ ሞክራ አልተሳካላትም።
ሙሉ መረጃውን ተከታተሉት።
የ4 አመት ሚስቴ ኩላሊቴን ሰጥቻት ከዳችኝ ከድህነት ጎዳና ወድቄያለሁ
ሩሲያ ለበሽር አል አሳድ እና ለቤተሰቦቻው ጥገኝነት መስጠቷ ተነገረ
የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽል አል አሳድ ሰልጣን ከለቀቁ በኋላ ወደ ሩሲያዋ መዲና ሞስኮ መኮብለላቸውን አዲስ የወጡ መረጃዎች አመላከተዋል።
በሽር አል አሳድ ስልጣናቸውን ለቀው ከደማስቆ ከወጡ በኋላ ወዴት ተሰደዱ? የሚለው ለበርካቶች ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል።
የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽል አል አሳድ እና ቤተሰቦቻቸው ሞስኮ ውስጥ እንደሚገኙ የሩሲያው የዜና ምንጭ ታስ የክሬምሊን ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
የበሽር አላሳድ አገዛዝ ተገረሰሰ።
የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ወደቀ።
የታጠቁ የሶሪያ አማጺያን የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄዱ ነበር።
በተለይም በሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ አማፂያን ከረዥም ዓመታት በኋላ የአገሪቱ ጦር ላይ ድንገታዊ ጥቃት ከከፈቱ በኃላ ብዙ ቦታዎችን በፍጥነት ይዘዋል።
ከሳምንት በፊት ነው አሌፖን ዘልቀው የገቡት።
ከዛ በኃላ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የመንግስት መከላከያዎች በአስደናቂ ፍጥነት ፈራርሰዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የአማጽያኑን ምት መቋቋም ከብዷቸው ድንበር አቋርጠው ኢራቅ ለመግባትና ጥገኝነት ለመጠየቅ ተገደዋል።
አማጽያኑ በቀናት ውስጥ እጅግ በርካታ ቁልፍ ከተሞችን እና ቦታዎችን ከአላሳድ አገዛዝ ነጻ ያደረጉ ሲሆን ለሊቱን የአሳድ መቀመጫ ወደ ሆናችው ደማስቆ መግባታቸው ታውቋል።
አላሳድ ከደማስኮ ወጥተው ሄደዋል ተብሏል።
የፕሬዜዳንቱን ከደማስቆ መልቀቅ ሁለት ከፍተኛ የጦር አመራሮች ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።
አሁን ላይ አሳድ የት እንደገቡ የሚታወቅ ነገር የለም።
የታጠቁት ተቃዋሚዎች ባወጡት መግለጫ ፤ " ጨቋኙ በሽር አላሳድ ከደማስቆ ለቀው ሄደዋል " ብለዋል።
" ደማስቆን ከጨቋኙ በሽር አላሳድ ነጻ አውጥተናል " ሲሉም ገልጸዋል።
በሽር አላሳድ ሀገሪቱን ለቀው መጥፋ