Ethio Media Net

  • Home
  • Ethio Media Net

Ethio Media Net ኢትዮጵያዊነት የአኩሪ ታሪክ ባለቤቶች ለምለም ሀገር ያለን ኩሩኢትዮጵያዊያን ህዝቦች ነን።

አፍህን ዝጋ ከማለት...(አሌክስ አብርሃም) አዞ ምድራችን ላይ ካሉ እንስሳት ሁሉ እጅግ ሀይለኛ የመንከስ አቅም ያለው ፍጥረት ነው። ለምሳሌ የሰው ልጅ በመጨረሻ አቅሙ ቢናከስ 162 PSI (...
18/02/2025

አፍህን ዝጋ ከማለት...
(አሌክስ አብርሃም)

አዞ ምድራችን ላይ ካሉ እንስሳት ሁሉ እጅግ ሀይለኛ የመንከስ አቅም ያለው ፍጥረት ነው። ለምሳሌ የሰው ልጅ በመጨረሻ አቅሙ ቢናከስ 162 PSI ( pounds per square inch) የመንከስ ሀይል አለው። አንበሳ ፣ ጅብ ወዘተ 1000 pSI! ይታያችሁ... በዚህ ንክሻ ነው አጥንት የሚሰባብሩት፣ እንስሳትን የሚገነጣጥሉት! አጅሬው አዞ በአንዴ የሚያሳርፍባችሁ ሀይል 5000 Psi ይደርሳል። የአንበሳን 5 እጥፍ ማለት ነው!

የሚገርመው ታዲያ አዞ ንክሻው እንዲህ ሀይለኛ ቢሆንም የመንጋጋ ጡንቻው ደካማ ስለሆነ አፉን እንዳይከፍት ሰው በእጁ አፍኖ ሊይዘው ወይም በተልካሻ ክር ሊያስረው ይችላል። አንዴ አፉን እንደምንም ከከፈተ ግን የተጠጋውን ሰው ይሁን እንስሳ እንጨት ይሁን ድንጋይ ብትንትኑን ነው የሚያወጣው። በሌላ አባባል አዞ አፉን እንዳይከፍት ማድረግ በጣም ቀላልና ትንሽ አቅም የሚጠይቅ ሲሆን፣ ከከፈተ በኋላ ማዘጋት ግን ህይወትን ጭምር ሊያስከፍል ይችላል።

ምን ለማለት ነው? ለራሳችንም ቢሆን አንዴ የከፈትነውን አፍ ለመዝጋት ከመታገል ይልቅ መጀመሪያውኑ አለመክፈት ቀላሉ መንገድ ነው። አፍ ካለነገሩ ከተከፈተ የሌሎችንም የራሳችንንም አጥንትና ሕይወት ካልሰባበረ በቀላሉ አይዘጋም። እንግዲህ ታዘቡ... በየሶሻል ሚዲያው በየመድረኩ ጨዋ የሚባሉ፣ የፖለቲካ ፣ የእምነት ወዘተ ሰወች አንዴ አፋቸውን መተሳሳተ መንገድ ከከፈቱ ስንቱን የሞራል አጥንት እንደሚሰባብሩት። ከከፈቱት በሰላም አይዘጋም። ራሳቸውንም ሌላውንም በልቶና አባልቶ፣ ደቀው እና አድቅቀው ወይ እንደከፈቱት ያልፋሉ አልያም ክፍታፍነትን መሳሪያቸው፣ ማስፈራሪያና መኖሪያቸው አድርገውት ይቀጥላሉ።
Abreham

ታዋቂው አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ሻኪል ኦኔል፣“ትልቁ  ሻክ” በመባልም ይታወቃል፤ በትውልድ ከተማው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የተማረበትን ትምህርት ቤት ለመጎብኘት ይሄዳል።ሻኪል ኦኔል...
11/02/2025

ታዋቂው አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ሻኪል ኦኔል፣“ትልቁ ሻክ” በመባልም ይታወቃል፤ በትውልድ ከተማው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የተማረበትን ትምህርት ቤት ለመጎብኘት ይሄዳል።
ሻኪል ኦኔል የተማረበትን ትህምርት ቤት ሲጎበኝ የቅርጫት ኳስ መጫወቻው ቦታ ሲደረስ ጎደኛውን ጋሪ ኩፐርን አስታወሰው፤ በጣም ይወደው ነበረ፣ የነበራቸው ፍቅርና አንድነት ትዝ አለው።አሁን ግን የት እንዳለ አያውቅም ።
ሻክ በትህምርት ቤቱ ውስጥ አንድ ያልጠቀው ነገር ገጠመው።
ሻክ የድሮ የትህምርት ቤት ጎደኛውን ጋሪ ኩፐርን አብረው በተማሩበት ትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ አገኘው። ለረጅም ግዜ ስላልተገናኙ ተቃቅፈው ሰላም ተባባሉ።ጋሪ በጣም ተጎሳቅሎና ያለእድሜው አርጅቷል።
ጋሪ እዛው ትህምርት ቤት ውስጥ የ 4ኛ ክፍል አስተማሪ ነበር። ጋሪ በአንድ ታዋቂ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች የመሆን ህልም ነበረው። ምኞቱ ልክ እንደ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪው ጓደኛው ሻኪል ኦኔል መሆን ነበረ ።
ጋሪ በኮሌጅ እየተማረ ከባድ የመኪና አደጋ ጉዳት ስለደረሰበት ታዋቂ የቅርጫት ኳስ ተጨዋች እውን የማድረግ ምኞቱ አከተመ።
ጋሪ ብዙ ችግሮች አጋጥመውታል ፤ንግድ ጀምሮ ከሰረ፣ ትዳሩ ፈረሰ ፣ቤቱን አጣ ። በሚያስተምርበት ትህምርት ቤት መጠላያ ቤት ውስጥ ነው የሚኖረው ።
ሻክ ኦኔል ስለ ድሮው ጎዳኛው ጋሪ የደረሰበትን ችግርና አሁን በትምርህት ቤቱ ውስጥ መጠለያ እንደሚኖር አወቀ።
የጋሪን ሁኔታ ማየቱ የሻክ አይን እንባ አፈሰሰ፣ ጎደኛውን ለመርዳትም ተዘጋጀ ፣ ከጋሪ ስልክ ተቀብሎ ሄደ።
አንድ ቀን ጠዋት የትምህርት ቤቱ መጠለያ ስራ አስኪያጅ የሆነች አንዲት ሴት ድሃ አስተማሪውን ጋሪን በመኪና ይዛ በመውሰድ ወደ አንድ የሚያምር ባለ ሁለት ክፍል አፓርታማ አደረሰችው። ሴትየዋ ለጋሪ ብዙ ቁልፎቹን ሰጥታ አፖርታማው የአንተ ነው በማለት ጠረጴዛው ላይ ወዳለው ፖስታ እየጠቆመች በፈገግታ “ይህም ያንተ ነው” አለችው።
ጋሪ እጆቹ እየተንቀጠቀጡ ፖስታውን ከፈተው። ከፖስታ ውስጥ “ከልጅነት ጓደኛህ ቢግ ሻክ” የሚል ማስታወሻ ነበረ።
ከማስታወሻው ጋር በጋሪ ስም የተመዘገቡ የአፓርታማው ንብረት ሰነዶች እና የ 5 ሚሊዮን ዶላር ቼክ አገኘ።ጋሪ በስሜት ተውጦ ፣ተንበርክኮ እንባው በፊቱ እየፈሰሰ ፣ ሻክን ደውሎ ሲያመሰግነው ሻክም እንዲህ አለው።
"እራስህን ብቻ ተንከባከብ ፣አስታውስ ደውልልኝ ሁሌም ከአጠገብህ ነኝ።"
ጋሪ ኩፐር በቴክሳስ ውስጥ ስኬታማ ነጋዴ ነው፤ ብዙ ጊዜ ህይወቱን ስለለወጠው የሻኪል ኦኔል ደግነትን ያወራል።
የኛትኩረት ከሚል ገጽ

 #ስንብት!! 😭 💔😭በአጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ፦ * ለሶስት ጊዜ በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቆ የወርቅ ሜዳልያ ያጠለቀ። በመጀመሪያ ዲግሪው፣ ስፔሻላይዝ ሲያደርግና ሰብ ስፔሻላይዝ ሲያደርግ።* የሶ...
02/02/2025

#ስንብት!! 😭 💔😭
በአጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ፦
* ለሶስት ጊዜ በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቆ የወርቅ ሜዳልያ ያጠለቀ። በመጀመሪያ ዲግሪው፣ ስፔሻላይዝ ሲያደርግና ሰብ ስፔሻላይዝ ሲያደርግ።
* የሶሊያ እና የመዝገቡ... አባት፣ባለትዳር።
* ከፈጣሪ በታች ለብዙዎች የጤና ፈውስ የሆነ ምርጥ ሀኪም እና የህክምና መምህር።

"...የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥበበ ግዮን ግቢ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር፤ የጉበት፣ የቆሽት፣ የሀሞት ጠጠር መስመር ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም፣ እንዲሁም የልጆች አባት የ37 ዓመቱ ዶ/ር አንዷለም ከሥራ እየተመለሰ ሳለ ተተኩሶበት ተገድሏል።" ተብሏል።

አዳኙ፣ የወርቃማ እውቀት ባለቤት ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ባህርዳር በሚገኘው መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን እሁድ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ/ም ቀብሩ ተፈጽሟል። እንግዲህ ምን ይባላል!? ኪሳራው እንደሀገር ነው።

ነፍስ ይማር ።
ለቤተሰብ፣ለወዳጅ ዘመድ፣ለታካሚዎቹ፣ለተማሪዎቹ መጽናናቱን ይስጣችሁ።

❗️

የእሁድ ውጤትአርሰናል-5 1-ማንቸስተር ሲቲ
02/02/2025

የእሁድ ውጤት
አርሰናል-5 1-ማንቸስተር ሲቲ

እነዚህ ትናንሽ ወፎች ጎጃቸው ውስጥ ደርቀው ሞተዋልምክንያቱ ደግሞ ምግብ ለማምጣት የወጣችው እናታቸው በአንድ ሞገደኛ  ተገድላ ነው። እነርሱም አቅም ኖሯቸው አይበሩም እሷም ከአንድ ጨካኝ እጅ...
02/02/2025

እነዚህ ትናንሽ ወፎች ጎጃቸው ውስጥ ደርቀው ሞተዋል
ምክንያቱ ደግሞ ምግብ ለማምጣት የወጣችው እናታቸው በአንድ ሞገደኛ ተገድላ ነው።

እነርሱም አቅም ኖሯቸው አይበሩም እሷም ከአንድ ጨካኝ እጅ ላይ ወደቀች አልተመለሰችም እና ክንፋቸው ያልጠነከረው መብረር እና የእለት ጉርሳቸውን ማግኘት የማይችሉት ለጋ ልጆቿም እዚሁ በርሀብ ሞተው ደርቀዋል።

አየህ የአንድ ቤትን ዋርካ - ምሰሶ ስትንድ ፤ ከስራው ስታፈናቅል ፣ ከመኖሪያ ቀየው ስታባረው ፣ ህልሙን ስታጨናግፍበት ከጀርባው ያሉ ቤተሰቡ ፣ ልጆቹን እንድህ ነው የምትጎዳው።

🔺🔺የዶክተር አንዷለምም ታሪክ እንዲሁ ነው🔺🔺

በርሱ ሞት : ጨቅላ ልጆቹ : እናቱ : ባለቤቱ : የርሱን የሙያ ድጋፍ የሚሹ እልፍ አዕላፋት እጣ ፋንታቸው እንዲሁ ነው።

ያሳዝናል 🥲🥲
@ዘመን ተሻጋሪው

አቤት ግፍ...አቤት መከራ😭💔ሕፃኗን ደፍ*ረዉ አስ*ክሬኗን ሰቅለዉ ገደ*ሏት😭😭ሲምቦ ብርሃኑ ትባላለች የ8 አመት ታዳጊ ስትሆን ነዋሪነቷ በምዕራብ ሸዋ ሜታ ወልቂጤ ወረዳ ሲሆን የአስ*ገድዶ መ...
31/01/2025

አቤት ግፍ...አቤት መከራ😭💔

ሕፃኗን ደፍ*ረዉ አስ*ክሬኗን ሰቅለዉ ገደ*ሏት😭😭

ሲምቦ ብርሃኑ ትባላለች የ8 አመት ታዳጊ ስትሆን ነዋሪነቷ በምዕራብ ሸዋ ሜታ ወልቂጤ ወረዳ ሲሆን የአስ*ገድዶ መ*ድፈር ወንጀል ከተፈፀመባት በኋላ ህይወቷ ሲያልፍ አ*ስክሬኗን ሰቅለውቶ ሄዷል።

ለታዳጊዋ ሲምቦ ብርሃኑ ፍትህ እየተጠየቀ ይገኛል።

ትራኦሬ‼በ 2 አመት የፕሬዝዳንት ዘመኑ ኢብራሂም ትራኦሬ ለቡርኪና ፋሶ ምን ሰራ?1. የቡርኪና ፋሶ GDP ከ18.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 22.1 ቢሊዮን ዶላር እንድያድግ አድርጓል።2. ከዓለም ...
26/01/2025

ትራኦሬ‼

በ 2 አመት የፕሬዝዳንት ዘመኑ ኢብራሂም ትራኦሬ ለቡርኪና ፋሶ ምን ሰራ?

1. የቡርኪና ፋሶ GDP ከ18.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 22.1 ቢሊዮን ዶላር እንድያድግ አድርጓል።

2. ከዓለም አቀፍ ገንዘብ አበዳሪ እና ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ገንዘብ አልተበደረም ድጋፍም አላገኘም::

3. የሚኒስትሮችን እና የፓርላማ አባላትን ደም እና ወዝ በ30% በመቀነስ የመንግስት ሰራተኞችን ደሞዝ በ50% ጨምሯል።

4. የቡርኪና ፋሶን የሀገር ውስጥ ዕዳ ከፍሏል።

5. በቡርኪና ፋሶ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የቲማቲም ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን አቋቁሟል

6. የአገር ውስጥ የማቀነባበር አቅሞችን ለማሳደግ ዘመናዊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ፋብርካ አስመርቋል።

7. እሴት ያልተጨመረበት የቡርኪና ፋሶ ወርቅ ወደ አውሮፓ እንዳይወጣ አድርጓል

8. የቡርኪና ፋሶ ሁለተኛ ግዙፍ የጥጥ ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ገንብቷል።

9. አርሶ አደሮችን የእደ ጥበብ ስራ ለማበረታታት ለመርዳት ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ለዕደ-ጥበብ ጥጥ ማቀነባበሪያ ከፍቷል።

10. የብሪታንያ ህጋዊ ዊግ እና ጋውንን በአካባቢ ፍርድ ቤቶች እንዳይለብሱ በመከልከል የሀገረው ሰው ባህላዊ የቡርኪናቤ ልብሶችን እንድለብስ አበረታትተዋል።

11. ምርትና ምርታማነትን ለማሳደ እርሻ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ አደርሶ አደሮች ከ400 ትራክተሮች፣ 710 የውሃ ፓምፖች እና 714 ሞተር ሳይክሎች በማከፋፈል ለግብርናውን ነማዘመን ስራ ሰርቷል።

12. የግብርና ምርትን ከፍ ለማድረግ ምርጥ ዘርና ሌሎች የእርሻ ግብአቶችን አቅርቧል።

13. የቡርኪና ፋሶን የቲማቲም ምርት ወደ ስልጣን ስመጣ ከነበረበት 315,000 ሜትሪክ ቶን በ2024 ወደ 360,000 ሜትሪክ ቶን አሳድጓል።

14. የሩዝ ምርት በ2022 ከነበረበት 280,000 ሜትሪክ ቶን በ2024 ወደ 326,000 ሜትሪክ ቶን አሳድጓል።

15. የፈረንሳይ ሚዲያን በቡርኪና ፋሶ አግዷል።

17. የፈረንሳይ ወታደሮችን ከቡርኪና ፋሶ አስወጥቷል።

18. መንግስታቸው አዳዲስ መንገዶችን በመገንባት ነባሮቹን በማስፋት እና የጠጠር መንገዶችን ወደ አስፋልት ደረጃ እያሳደገ ነው።

"አገር ከፖለቲካ ፓርቲዎች በላይ ናት" አቶ ቡልቻ ደመቅሳን ለዜና ግብዐትነት በርካታ ግዜ የማነጋገር እድል ገጥሞኝ ነበር። ግልፅ እና ለቆሙለት አላማ የቻሉትን ያህል የሚሞግቱ ሰው ሰው የሚሸ...
06/01/2025

"አገር ከፖለቲካ ፓርቲዎች በላይ ናት"

አቶ ቡልቻ ደመቅሳን ለዜና ግብዐትነት በርካታ ግዜ የማነጋገር እድል ገጥሞኝ ነበር። ግልፅ እና ለቆሙለት አላማ የቻሉትን ያህል የሚሞግቱ ሰው ሰው የሚሸቱ ፖለቲከኛ ነበሩ።

በአንድ ወቅት ፓላማ ላይ "... እንዴት ኢትዮጵያ ይህን ያህል አደገች ይባላል?" ብለው ሲሞግቱ እንደተለመደው የፓርላማ አባሎች ግርርር ብለው ሲስቁ ብዙዎቻችን አይተናል።

እውነታው ግን እሳቸው እኛ የማናውቀውን አውቀው ስለነበር ነው ብዬ አስባለሁ፣ መረጃ በመንግስታት እንደሚቀነባበር ስለሚገባቸው። የአለም ባንክ የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ሆነው እ.አ.አ ከ1970- 1974 እንደሰሩ ልብ ይሏል።

ነፍስ ይማር!

የለሚ ኩራ ቅ/ ጽ/ቤት ጠጥተው ያሽከረከሩ 6 አሽከርካሪዎቾን  በደንብ መተላለፍ ቀጣ*****************(ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ...
04/01/2025

የለሚ ኩራ ቅ/ ጽ/ቤት ጠጥተው ያሽከረከሩ 6 አሽከርካሪዎቾን በደንብ መተላለፍ ቀጣ
*****************
(ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የለሚኩራ ቅ/ጽ/ቤት የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ደንብ ማስከበር ዳይሬክቶሬት በክፍለከተማው ደራርቱ አደባባይ እና ዙሪያውን ከማዕከል ጋር በመቀናጀት በዛሬው እለት የጠጥቶ ማሽከርከር ቁጥጥር አድርጔል::

በቁጥጥሩም የትንፋሽ ናሙና ከተወሰደባቸው 120 አሽከርካሪዎች በደንቡ የተቀመጠውን ገደብ ያለፉ 6 አሽከርካሪዎች በህጉ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል::

መጪው ጊዜ በዓላት የሚከበሩበት በመሆኑ ከግንዛቤ ስራ በተጔዳኝ መሰል ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከቅ/ጽ/ቤቱ ተጠቁሟል።

@ ቅ/ጽ/ቤቱ

የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል ከፍ ማለት ትርጉሙ ምንድነው?ከዚህ ቀደሞቹ የመሬት መንቀጥቀጦች ከበድ ያለና በሬክተር ስኬል 5.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ታህሳስ 25፤ ለታህሳስ 26 አ...
04/01/2025

የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል ከፍ ማለት ትርጉሙ ምንድነው?

ከዚህ ቀደሞቹ የመሬት መንቀጥቀጦች ከበድ ያለና በሬክተር ስኬል 5.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ታህሳስ 25፤ ለታህሳስ 26 አጥቢያ ከለሊቱ 9:52:21 መከሰቱን ዓለም አቀፍ ተቋማት አስታውቀዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተውም በዓፋር ክልል አዋሽ አከባቢ መሆኑ የገለፁ ሲሆነ ንዝረቱም በአዲስ አበባ የተለያዩ አከባቢዎች ተሰምቷል።

ይኸ ምን ማለት ነው? ከተለያዩ ምንጮች ያገኘናቸው መረጃዎች ይኸን ያሳያሉ።

ቁጥሮቹ ሲተነተኑ (በሬክተር ስኬል):-

💥 ከ4.0 በታች፡-

አነስተኛ ነው፤ ትንሽ ብቻ ነው የሚሰማው። አልፎ አልፎ ጉዳት ያስከትላል።

💥 ከ4.0 - 4.9፡-

ጉዳቱ አብዛኛውን ጊዜ አነስተኛ ነው።

💥 ከ5.0 - 5.9፡-

መጠነኛ ነው። በደንብ ባልተገነቡ ሕንፃዎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።

💥 ከ6.0 - 6.9፡-

ጠንከር ይላል። ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች በተለይም አሮጌ ወይም በደንብ ባልተገነቡ ህንፃዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።

💥 ከ7.0 - 7.9፡-

መሠረተ ልማት እና ሕንፃዎች ሊያፈርስ ይችላል።

💥 8.0 እና ከዚያ በላይ፡-

ብዙ ጊዜ አስከፊ ጉዳት ማለትም የሰው ህይወት መጥፋት እና ውድመት ሊያስከትል ይችላል። በተለይም በተከሰተበት አካባቢ ከባድ ጉዳት ያስከትላል።

***

በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለውን የመሬት መንቀጥቀጥ የአደጋ ሥጋት ተከትሎ ተጋላጭ በኾኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች ወደተሻለ ቦታ የማስፈር እንቅስቃሴ ሊኖር ይገባል)
(አሶሽየትድ ፕሬስ)

አድማስ ዲጅታል ሎተሪ 30ኛ ዙር ዕጣ ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል
03/01/2025

አድማስ ዲጅታል ሎተሪ 30ኛ ዙር ዕጣ ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል

በአዋሽ አካባቢ ዛሬ ምሽት በሬክተር ስኬል 5.0 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ  🔴በዛሬው ዕለት ብቻ ሰባት የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ ከሰሞኑ ከደረሱት...
29/12/2024

በአዋሽ አካባቢ ዛሬ ምሽት በሬክተር ስኬል 5.0 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
🔴በዛሬው ዕለት ብቻ ሰባት የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል

በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ ከሰሞኑ ከደረሱት የመሬት መንቀጠጥ ክሰተቶች በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ ርዕደ መሬት ዛሬ እሁድ ምሽት መከሰቱን የጀርመን የጂኦሳይንስ የምርምር ማዕከል አስታወቀ።

በአካባቢው ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ10 ላይ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በሬክተር ስኬል 5.0 የደረሰ እንደሆነ የማዕከሉ መረጃ አመልክቷል።

በሬክተር ስኬል የመለኪያ መሳሪያ ከ2.5 እስከ 5.4 መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጦች አነስተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደሆኑ በዘርፉ ምርምር የሚያደርጉ ተቋማት ይገልጻሉ።

በዚህ መጠን የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች ንዝረታቸው በበርካታ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባሉ ከተሞች ጭምር የሚሰማ እንደሆነም የተቋማቱ መረጃ ያሳያል። የምሽቱ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ጭምር ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየ ንዝረት አስከትሏል።

ከአዋሽ ከተማ 14 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ ስፍራ የተከሰተው የምሽቱ ርዕደ መሬት፤ በዛሬው ዕለት ብቻ በአካባቢው የተመዘገቡ መሬት መንቀጥቀጦችን ቁጥር ሰባት አድርሶታል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ አሸናፊዎች*******************• የዓመቱ ምርጥ ሜዲካል ኮንቴንት ክሬተር - ዶ/ር ሀረገወይን ሙሴ• የዓመቱ ምርጥ አነቃቂ ኮንቴንት - ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ...
28/12/2024

የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ አሸናፊዎች
*******************

• የዓመቱ ምርጥ ሜዲካል ኮንቴንት ክሬተር - ዶ/ር ሀረገወይን ሙሴ

• የዓመቱ ምርጥ አነቃቂ ኮንቴንት - ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ

• የዓመቱ ምርጥ የስዕል፣ ግጥምና ሌሎች አርትስ ኮንቴንት- ሲሳይ

• የዓመቱ ምርጥ መላ ሽልማት - I store by sophi

• የዓመቱ ምርጥ ኤዲቲንግ ኤንድ ኢፌክት -ሲሳይ

• የዓመቱ ምርጥ ሙዚቀኛ እና ፕሮዲዩሰር - ዮንዚማ

• የዓመቱ ምርጥ ሶሻል ኢምፓክት ኮኒቴንት - ዶ/ር አብይ ታደሰ

• የዓመቱ ምርጥ የንግድ እና ትምህርታዊ ይዘት ተሸላሚ - ሚስ ፈንዲሻ/Miss Fendisha/

• የዓመቱ ምርጥ ዳንስ ኤንድ ፐርፎርማንስ አሸናፊ- ጃዝሚን/jazmin_ hope1/

• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት- ኤላ Review

• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት ልዩ ተሸላሚ- Baes

• የዓመቱ ምርጥ ስፖርት ኤንድ ፊትነስ ኮንቴንት - ቶማስ ሀይሉ

• የዓመቱ ምርጥ ላይቭ ስትሪመር ተሸላሚ - ታኩር ሌጀንድ

• የዓመቱ ምርጥ ላይፍ ስታይል ኮንቴንት ተሸላሚ - Miss leyu

• የዓመቱ ምርጥ ሴት ፈኒየስት ተሸላሚ - ባዚ

• የዓመቱ ምርጥ ወንድ ፈኒየስት ተሸላሚ - ኤላ ትሪክ/Elatick

• የዓመቱ ምርጥ ሚመር አዋርድ ተሸላሚ- I did it በዘነዘና

• የዓመቱ ምርጥ ትራቭል ኮንቴንት አዋርድ- አቤል ብርሃኑ

 " የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል" ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነ...
07/12/2024



" የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል

" ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " ሲል የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ እንዳስታወቀው የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው።

በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩን ገልጿል።

የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ አልተፈታም።

ችግሩ ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት ተጠባበቁ ተብሏል።

የኤሌክትሪክ ኃይል በመላ ሀገሪቱ ተቋርጧል!!በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልዛሬ ህዳር 28/2017 ማምሻውን በ...
07/12/2024

የኤሌክትሪክ ኃይል በመላ ሀገሪቱ ተቋርጧል!!

በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ዛሬ ህዳር 28/2017 ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

አቶ ታየ ደንደዓ ከዕስር ተለቀቁ⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከአንድ ዓመት እስር ቆይታ በኃላ የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደዓ  ከእስር ተለቀው መኖርያ ...
05/12/2024

አቶ ታየ ደንደዓ ከዕስር ተለቀቁ
⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳
ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከአንድ ዓመት እስር ቆይታ በኃላ የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደዓ ከእስር ተለቀው መኖርያ ቤታቸዉ ገብተዋል።

ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተቀላቅለዋል።

ትናንት አመሻሹን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተለቀው ቤተሰቦቻቸውን ሳይቀላቀሉ ከማረሚያ ቤቱ በራፍ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸው ይታወሳል።

በኃልም የተወሰዱት ሜክሲኮ
የወንጀል ምርመራ እነደነበር ታውቋል።

ዛሬ እኩለ ቀን ደግሞ ሜክሲኮ ከሚገኘው የወንጅል ምርመራ ማዕከል ተለቀው ቤታቸው መድረሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ስንታየሁ " ጠዋት ቤተሰብ ሜክሲኮ ምግብ አድርሶላቸው ከተመለሰና ደህንነታው ከጠየቀ በኋላ ዛሬ እኩለ ቀን ምሳ ሰዓት ከማቆያው እንዲወጡ ተወስኖ 7 ሰዓት ግድም መኖራቸው ቤት ደርሰዋል " ብለዋል።

ባለፈው ሰኞ በፍርድ ቤት በ20 ሺህ ብር ዋስትና ክሳቸውን ከውጪ መከታተል እንዲችሉ በታዘዘው መሰረት ትናንት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቢለቀቁም ለምን ወደ ሜክሲኮ የወንጀል ምርመራ ማዕከል እንደተወሰዱ ግን ቤተሰብ እንዳልተረዳ ነው የተነገረው፡፡

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

አድማስ ዲጅታል ሎተሪ 29ኛ ዙር ዕጣ ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በእድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል
04/12/2024

አድማስ ዲጅታል ሎተሪ 29ኛ ዙር ዕጣ ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በእድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል

ማይክ ታይሰን በጄክ ፖውል ተሸነፈኅዳር 7 2017 ዓ.ም ዝነኛው አሜሪካዊ የከባድ ሚዛን ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ራሱን ከፕሮፌሽናል ውድድር ካገለለ ከ19 ዓመታት በኋላ ወደ ውድድር ተመልሶ ከ2...
16/11/2024

ማይክ ታይሰን በጄክ ፖውል ተሸነፈ

ኅዳር 7 2017 ዓ.ም ዝነኛው አሜሪካዊ የከባድ ሚዛን ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ራሱን ከፕሮፌሽናል ውድድር ካገለለ ከ19 ዓመታት በኋላ ወደ ውድድር ተመልሶ ከ27 ዓመቱ ጄክ ፖውል ጋር ቢጋጠምም በቀላሉ ተዘርሯል።

ጄክ ፖውል ጋር በኤቲ ኤንድ ቲ ስታዲየም በተደረገው ፍልሚያ ማይክ ታይሰንን በማሸነፍ በቦክስ ሕይወቱ ትልቁን ድል ማግኘት ችሏል።

የ27 ዓመቱ ፖል ፍልሚያውን ድል በማድረጉ እስካሁን ካደረጋቸው 11 ውድድሮች በአንዱ ብቻ የተሸነፈ ሆኗል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Media Net posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share