ዘንድሮ Times ወቅታዊ እና ተያያዝ ስነ- ልቡናዊ፣ ማኅበራዊ፣ ጤና፣ ባህል፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚክስ እና መሰል ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን፣ የባለሙያ ሀሳቦችን፣ ሂሶችን፣ የመፍትሄ እና አስደናቂ ለውጥ ሀሳቦችን የምንጋራበት፣ የምንለዋወጥበት፣ የምንማማርበት እና ዘንድሮን እንዲሁም መጪውን ጊዜ የተሻለ ለማድረግ የሚጠቅሙ ሁለገብ ጉዳዮች የሚስተናገዱበት መድረክ ነው፡፡
ዘንድሮ የትላንት በአንድ ገፁ የትላንትን አምሳል ነው፡፡ ዘንድሮ የዛሬ የግለሰቦች፣ ማኅበረሰብ እና መንግስት ምርጫና ተግባራዊ እንቅስቃሴ አጠቃላይ ድምር ውጤት ነው፡፡ ዘንድሮ የነገን መልክ በእጅጉ የሚወስን የዛሬ ተግባር ነው፡፡ በአጭሩ ዘንድሮ ትላንት፣ ዛሬ እና ነገ
ነው፡፡ ከዚህ እና መሰል እሳቤዎች በመነሳት ይህ ማኅበራዊ ገፅ (ዘንድሮ) በግለሰብ እና ማኅበረሰብ ደረጃ ትላንትን በቅርበት እና ቀናነት መረዳት የምንችልበትን፣ ዛሬን ከመረዳት ባሻገር የተሻለ እንዲሆን ቁልፍ ሚና የምንጫወትበትን ሙያዊ እና ሀገራዊ ፋይዳ ያለው እውቀት፣ ክህሎት እና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ እና ምናባዊ ጉዳዮችን የምንማርበት፤ ነገ ከትላንት እንዲሁም ከዛሬ በእጅጉ የቀናና የላቀ እንዲሆን ዘንድሮ ምን፣ ለምን እና እንዴት መማር፣ ማወቅ፣ መስራት፣ እና መለወጥ እንደሚገባን የምንነጋገርበት መስክ ነው፡፡
Zendro Times, among other things offers useful and up-to-date news, information's, insights and inputs of great minds across the globe on life, society and the world as we know it and/or as it should be. The page also pushes forward ideas and information's that can be used to bring about positive change on self and the world widely ranging from health to lifestyle.