አረንጓዴ ሐሳቦች - Green Ideas

አረንጓዴ ሐሳቦች - Green Ideas Green Ideas are dedicated to expound nature concerned ideas, so as to pave the way to promote green societies.
(3)

'30 by 30' – now, more than ever, we need to draw attention to the direct and tangible actions that rangers take every d...
30/07/2024

'30 by 30' – now, more than ever, we need to draw attention to the direct and tangible actions that rangers take every day to reach our global 30 by 30 targets, as set out by the Convention on Biological Diversity.


2024


The first Global Cheetah Summit –A Call to Action, convenes 28th – 31st January 2024 in Addis Ababa, Ethiopia. The Summi...
29/01/2024

The first Global Cheetah Summit –A Call to Action, convenes 28th – 31st January 2024 in Addis Ababa, Ethiopia.

The Summit brings together a diverse group of international stakeholders representing governments, universities, NGOs, policy and economy institutes, local and Indigenous communities, and private enterprise from around the world to discuss and act-on the plight of the fastest land animal and the most endangered of the big cats.

During the event it’s expected to address the three major questions: the status of cheetahs worldwide, address threats and pressures impacting cheetahs, and the enablers for
change.

29/01/2024

ሰላም ውድ ተከታዮቻቸን፤ እንድምን ከረማችሁ፡፡
ተመልሰናል!

የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ላይ እየተካሄደ ያለው ህገወጥ እርሻ በአፋጣኝ ውሳኔ ሊሰጠው ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ የዱር ሕይወት ልማትና ጥበቃ ቲንክ-ታንክ ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ አ...
27/09/2023

የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ላይ እየተካሄደ ያለው ህገወጥ እርሻ በአፋጣኝ ውሳኔ ሊሰጠው ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ የዱር ሕይወት ልማትና ጥበቃ ቲንክ-ታንክ ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ አስገቡ።

በአንጋፋ ኢትዮጽያዊያን የዱር ሕይወት ባለሙያዎች የተመሰረተው ቲንክ-ታንኩ መስከረም 16 ቀን በጻፈው ደብዳቤ የመጠለያው ከ140 ሄክታር ለ"Three Apples" የተባለ ድርጅት የእርሻ ኢንቨስትመንት መሰጠቱ ሊያደርስ የሚችለው ተጽዕኖ እንዳሳሰበው ገልጧል።

ቲንክ-ታንኩ ደረሰኝ ባለው መረጃ መሰረት እንደጠቆመው በኢንቨስትመንት ሰበብ እየተከናወነ የሚገኘው ይህ ህገወጥ የደን ጭፍጨፋ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን አስተዳደር ተሳትፎ ስላለው ድርጊቱን በቀላሉ ማስቆም አለመቻሉን ገልጧል። ስለሆነም ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ትኩረት እንዲሰጡትና መፍትሄ ያሳልፉ ዘንድ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

የግልጽ ደብዳቤውን ሙሉ ቃል ከታች ተያይዟል።

Sign this petition!Save the Elephants in the Babile Elephant Sanctuary!👇https://chng.it/sHPTmffvrm 🐘🐘🐘
27/09/2023

Sign this petition!
Save the Elephants in the Babile Elephant Sanctuary!
👇
https://chng.it/sHPTmffvrm
🐘🐘🐘

የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ላይ እየተካሄደ ያለው ህገወጥ እርሻ በአፋጣኝ ውሳኔ ሊሰጠው ይገባል። እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የመፍትሄ አቅጣጫም ሆነ ውስኔ አለመሰጠቱ የጉዳዮን ቸል መባል ያሳያ...
20/09/2023

የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ላይ እየተካሄደ ያለው ህገወጥ እርሻ በአፋጣኝ ውሳኔ ሊሰጠው ይገባል። እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የመፍትሄ አቅጣጫም ሆነ ውስኔ አለመሰጠቱ የጉዳዮን ቸል መባል ያሳያል።
(ከስር የተያያዘው ምስል እውነታውን ያስረዳል!)

የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ውስጥ 260 ሄክታር የፓርኩ አካል በህገወጥ መንገድ ታርሷል። ከዚህ ውስጥ 140 ሄክታር የሚሆነው የመጠለያው ክፍል ሲሆን ቀሪው ደግሞ ደጀን ስፍራ መሆኑን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ በሀገራችን ብቸኛው ዝሆኖችን ለመጠበቅ ሲባል የተቋቋመ መጠለያ ሲሆን በበርካታ ሰው ሰራሽ ጫናዎች ውስጥ የሚገኝ የዱር እንስሳት ጥበቃ ስፍራ ነው።

የሰዎች ህገወጥ ሰፈራ፣ የእርሻ መስፋፋት፣ ደን ምንጣሮ እና ህገወጥ የዝሆኖች አደን መጠለያውን በእጅጉ እየፈተኑት የሚገኙ ጫናዎች ናቸው።

በቅርቡ የተከሰተው ህገወጥ እርሻም የጫናዎቹ አንዱ አካል ሲሆን ምናልባትም የዝሆኖቹን ህልውና ከመፈታተን አልፎ መጠለያውን ወደ ጥፋት ዳር የሚገፋ ተግባር መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል።

አስደሳች ዜና!ዮኔስኮ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዓለም ቅርስነት መዝግቧል።የምዝገባ ጊዜ: 2023 የምዝገባ መስፈርት፤ (vii)(x) የባሌ ተራሮች በሁለት የምዝገባ መስፈርቶች የተመዘገበ ...
18/09/2023

አስደሳች ዜና!

ዮኔስኮ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዓለም ቅርስነት መዝግቧል።
የምዝገባ ጊዜ: 2023

የምዝገባ መስፈርት፤ (vii)(x)

የባሌ ተራሮች በሁለት የምዝገባ መስፈርቶች የተመዘገበ ሲሆን

አንደኛ፤ (vii) የላቀ የተፈጥሮ ስርዓተ-ምህዳር ያለው ውብ ተፈጥሯዊ መስህብነት እና ኪነጥበባዊ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ፤

ሁለተኛ፤ (x) ከሳይንሳዊ የጥበቃ እና ልማት አንጻር የላቀ አለም አቀፋዊ ጠቀሜታ የያዘ በመሆኑና ዝርያቸው የተመናመነ እንስሳት እና ዕጽዋት መዳረሻ በመሆኑ

የተመዘገበው የፓርኩ ይዞታ፤ 215,000 ሄክታር
የተመዘገበ የፓርኩ ደጀን ይዞታ፤ 235,121 ሄክታር
የምዝገባው ሰነድ፤ 111rev

የቅርሱ መገኛ
N6 47 52 E39 44 56

አረንጓዴ ሐሳቦች ተመልሰናል! በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ላይ እየደረሰ ያለው ህገወጥ ተግባር አሳሳቢነት ተመልሰን እንድንገናኝ አድርጓናል! የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ላይ እየደረሰ ያለውን ህገወ...
16/09/2023

አረንጓዴ ሐሳቦች ተመልሰናል!

በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ላይ እየደረሰ ያለው ህገወጥ ተግባር አሳሳቢነት ተመልሰን እንድንገናኝ አድርጓናል!

የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ላይ እየደረሰ ያለውን ህገወጥ ደን ጭፍጨፋ እና እርሻ አስመልክቶ የዱር እንስሳት ባለሙያዎች ተቃውሟቸውን በግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚንስትሩ አቀረቡ።

"የዞን አመራሮች እውቅና የሰጡት ህገወጥ ኢንቨስትመንት በህጋዊ ጥበቃ ስፍራ ውስጥ፤ የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ጉዳይ" በሚል በጉዳዮ ላይ አጽንኦት ሰጥተው አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሻ ገልጠዋል።

የባለሙያዎቹ ደብዳቤ በቅርቡ ከቁጥጥር ውጭ የወጣውን በመጠለያው ላይ እየደረሰ ያለውን ህገወጥ የእርሻ ኢንቨስትመንት መነሻ ያደረገ ሲሆን በመጠለያው ላይ ቀደም ሲል ጀምሮ እየተስተዋለ የመጣውን አሳሳቢ ጉዳዮች አውስተዋል።

ሙሉውን ለማንበብ
👇
https://www.linkedin.com/posts/habte-jebessa-debella-8a316745_activity-7108768202028949505-YdSV?utm_source=share&utm_medium=member_android

12/09/2023
Fetiya Ousman - Awarded for outstanding resoluteness and leadership, as a head ranger and a pioneer for gender equality....
26/07/2023

Fetiya Ousman - Awarded for outstanding resoluteness and leadership, as a head ranger and a pioneer for gender equality.

Fetiya Ousman effectively and successfully leads a team of 60 rangers addressing poaching, encroachment and human wildlife conflict in Babile Elephant Sanctuary; until recently she was the only female member of the team. She has overcome cultural and personal challenges throughout her career and has brought new approaches to peaceably addressing the threats faced by the Sanctuary.

Her quick wit, attention to detail and loyalty to the office have endeared her to her colleagues, and her skilled, powerful communication and fight for gender equality have inspired more female rangers to join the team from the community.

IUCN
Photo by: Berihun Tadele

ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሔር ልድራችን ሕልውና የደከሙ ታላቅ ሰው!
21/03/2023

ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሔር
ልድራችን ሕልውና የደከሙ ታላቅ ሰው!

የአለም እርጥበታማ ቦታዎች ቀን      Feb 2, 2023
02/02/2023

የአለም እርጥበታማ ቦታዎች ቀን



Feb 2, 2023

“በነጭ ሳር  የሜዳ አህያ እየተሸጠ ነው” በሚል ፋስት መረጃ ዶት ኔት የተሰኘ የማህበራዊ ድረ-ገጽ ያሰራጨው መረጃ የሃሰት መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት በአካባቢው ም...
01/02/2023

“በነጭ ሳር የሜዳ አህያ እየተሸጠ ነው” በሚል ፋስት መረጃ ዶት ኔት የተሰኘ የማህበራዊ ድረ-ገጽ ያሰራጨው መረጃ የሃሰት መሆኑን አረጋግጠናል፡፡

ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት በአካባቢው ምንም አይነት በቂ ዝናብ ባለመጣሉ የተነሳ በገላና ወረዳ አካባቢ እና የፓርኩ አዋሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የመጠጥ ውሃ እጥረት እና ድርቅ መከሰቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም የተነሳ በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚኖሩ የዱር እንስሳት ለመጠጥ ውሃ እጥረት ተዳርገዋል፡፡

በመሆኑም አልፎ አልፎ የሜዳ አህዮች ከፓርኩ ክልል በመውጣት ሰዎች ወደሚኖሩባቸው አካባቢዎች በመሄድ ሰዎች በሚያዘጋጇቸው ጉድጓዶችና የውሃ ማቆሪያ ቦታዎች በመገኘት ውሃ ይጠጣሉ፡፡ በተለይም በገላና ወረዳ አካባቢ ያሉ ትምህርት ቤቶችም ውሃ በገንዳ አዘጋጅተው ስለሚያቀርቡላቸው ወደዚው በመሄድ ውሃ ሲጠጡ ይስተዋላሉ፡፡

ከታች በምስሉ የሚታየውም የሜዳ አህያ በገላና ወረዳ አካባቢ በዚሁ መልኩ ውሃ ፍለጋ ወደ ህብረተሰቡ የተጠጋ መሆኑ ሊታወቅ ገባል ሲል የፓርኩ ጽሕፈት ቤት ገልጧል፡፡

በእኛ በኩል፤ በፓርኩ ያለው ጫና ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ እየገለጥን በተለይም ከድርቅ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችም አፋጣኝ መፍትሄ ቢሰጣቸው መልካም ነው እንላለን፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር በድሬዳዋ አንድ የዱር እንስሳት ጥብቅ ክልል የማቋቋም ምክክር መድረክ አካሂዷል። ታሪካዊ ስያሜን የያዘው ቀለዓድ የዱር እንስሳት ጥብቅ ክልል ለድሬዳዋ የመጀመሪያው የዱር ...
28/01/2023

የድሬዳዋ አስተዳደር በድሬዳዋ አንድ የዱር እንስሳት ጥብቅ ክልል የማቋቋም ምክክር መድረክ አካሂዷል።

ታሪካዊ ስያሜን የያዘው ቀለዓድ የዱር እንስሳት ጥብቅ ክልል ለድሬዳዋ የመጀመሪያው የዱር እንስሳት ጥበቃ ስፍራ የቆላ አጋዘን፣ አምባራይሌ፣ ገረኑክ፣ ኢንሹ፣ ጀርባ ጥቁር ቀበሮ እና ጅብን ጨምሮ በጥናቱ ከሰላሳ በላይ አጥቢ የዱር እንስሳት ይገኙበታል።

በተጨማሪም 51 የእጽዋት ዝርያዎች እና 71 የሚደርሱ የአእዋፍ ዝርያዎችም በጥናቱ መኖራቸው ተረጋግጧል።

የጥበቃ ስፍራው ተገቢው ክለላ ከተደረገለት በኋላ ሕጋዊ ሰውነት የሚያገኝ መሆኑ ተገልጧል።

The African Wildlife Foundation (AWF) has announced the call for applications for the Charles R. Wall Leadership Program...
17/01/2023

The African Wildlife Foundation (AWF) has announced the call for applications for the Charles R. Wall Leadership Program.

The program consists of two components — the Charles R. Wall Young African Policy Fellows and the Charles R. Wall Conservation Leadership and Management Fellowship — and aims to build communities of skilled and connected young African professionals that will drive meaningful transformation in conservation in Africa.

የሰጎን ጫጩት አጥንት ውጣ ከሞት ማትረፍ መቻሉን አሰምተናል። በአቢጃታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ የሰጎን ጫጩት አጥንት ውጣ በመታነቋ ለሞት ስታቃትት በፓርኩ ስራተኞች አጥንቱን በማውጣት እን...
12/01/2023

የሰጎን ጫጩት አጥንት ውጣ ከሞት ማትረፍ መቻሉን አሰምተናል።

በአቢጃታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ የሰጎን ጫጩት አጥንት ውጣ በመታነቋ ለሞት ስታቃትት በፓርኩ ስራተኞች አጥንቱን በማውጣት እንድትተርፍ ማድረግ መቻሉን ጽሕፈት ቤቱ ገልጧል።

የቀዶ ህክምና ተግባሩ በፓርኩ ሰራተኞች የተከናወነ ሲሆን በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አረጋግጠዋል። ጫጩቷ በመልካም ጤንነት ላይ እንደምትገኝም ሰምተናል።

ለዚህ ውሳኔያችሁ እና ስኬታማ ሙከራ የፓርኩ ሰራተኞች ተመስግናችኋል።

Happy New Year2023አረንጓዴ ሐሳቦች - Green Ideas
31/12/2022

Happy New Year
2023
አረንጓዴ ሐሳቦች - Green Ideas

የባህር ዳር እና ዙሪያ ወፎችን በማንሳት የተጠመደ “ያ ወፍ የሚቀርጸው ሰውዬ” በሚል በአካባቢው የሚታወቀው ግለሰብ እነሆ::በሀገራችን በተፈጥሮ ፎቶግራፊ እና ቪዲዩግራፊ ዘርፍ የሚታወቁ ግለሰ...
30/12/2022

የባህር ዳር እና ዙሪያ ወፎችን በማንሳት የተጠመደ “ያ ወፍ የሚቀርጸው ሰውዬ” በሚል በአካባቢው የሚታወቀው ግለሰብ እነሆ::

በሀገራችን በተፈጥሮ ፎቶግራፊ እና ቪዲዩግራፊ ዘርፍ የሚታወቁ ግለሰቦች በጣም ጥቂት ናቸው፡፡

በእኔ የረዥም ጊዜ ምልከታ ከመረጥኳቸው ውስጥ ለዛሬ የባህርዳሩን የወፍ ፎቶግራፈር ቲውተር ገጹን ብትወዳጁ በሚል አጋራኋችሁ፡፡

https://twitter.com/BDR_Photography

የዝሆን ግልገል - ኤልሞሌ🐘 አንድ ኤልሞሌ ለ23 ወራት ተረግዛ የምትወለድ ሲሆን ይህም ከአጥቢዎች ሁሉ ረዥሙ የእርግዝ ወቅት ነው🐘 እንደተወለደ 1 ሜትር ቁመት እና የ100 ኪሎ ግራም ክብደት...
29/12/2022

የዝሆን ግልገል - ኤልሞሌ

🐘 አንድ ኤልሞሌ ለ23 ወራት ተረግዛ የምትወለድ ሲሆን ይህም ከአጥቢዎች ሁሉ ረዥሙ የእርግዝ ወቅት ነው

🐘 እንደተወለደ 1 ሜትር ቁመት እና የ100 ኪሎ ግራም ክብደት ይኖረዋል

🐘 ለተከታታይ ሁለት አመታት እናቷን እየተከተለች ጡት የምትጠባ ሲሆን በቀን እስከ ሦስት ጋሎን ወተት ልትወስድ ትችላለች

ከአራት ቀናት መነጠል በኋላ ኤልሞሌው ከእናቱ ጋር መገናኘቱ ታውቋል፡፡ በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ከእናቱ የተለየ ኤልሞሌ በመጠለያው ሰራተኞች ከፍተኛ ጥረት መልሶ ከእናቱ ጋር እንዲቀላቀል ማድረ...
28/12/2022

ከአራት ቀናት መነጠል በኋላ ኤልሞሌው ከእናቱ ጋር መገናኘቱ ታውቋል፡፡

በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ከእናቱ የተለየ ኤልሞሌ በመጠለያው ሰራተኞች ከፍተኛ ጥረት መልሶ ከእናቱ ጋር እንዲቀላቀል ማድረግ መቻሉን መጠለያው ገልጧል፡፡

ኤልሞሌው በድንገት ከመንጋው እና ከእናቱ ተነጥሎ ለአራት ቀናት በሬንጀሮች ጥበቃ ተገቢው እንክብካቤ እየተደረገለት መቆየቱን እና ከእናቱ ጋር ለመቀላቀል ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቶ መሳካቱን ተገልጧል፡፡
EWCA

የኢትዮጵያ ከፍተኛው ስፍራ ስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የራስ ደጀን ተራራ ለጎብኝዎች ክፍት ሆኗል፡፡የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ራስ ደጀን ከፍታን መውጣት ለሚፈልጉ ጎብኝዎች ክፍት መደረጉን...
27/12/2022

የኢትዮጵያ ከፍተኛው ስፍራ ስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የራስ ደጀን ተራራ ለጎብኝዎች ክፍት ሆኗል፡፡

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ራስ ደጀን ከፍታን መውጣት ለሚፈልጉ ጎብኝዎች ክፍት መደረጉን ገልጧል፡፡ ለጊዜው የተወሰኑ ገደቦች እንዳሉ ሆነው ከፍታውን በመውጣት ለሚዝናኑ ጎብኝዎች አማራጩ ክፍት መሆኑን ጽሕፈት ቤቱ በማህበራዊ ሚዲያ ባጋራው መረጃ አሳውቋል፡፡

በስፍራው በሚኖር ጉብኝት ወቅት ፎቶ እና ቪዲዮ ማንሳት ለጊዜው ከተቀመጡ ገደቦች ውስጥ ዋነኛው ነው ተብሏል፡፡

We are delighted to announce that has been opened for visitors with some pre-condition ( no photo). So come and hike to Ras Dejen, and feel the height of Simien Mountains National Park.

Address

Empror Menelik
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አረንጓዴ ሐሳቦች - Green Ideas posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አረንጓዴ ሐሳቦች - Green Ideas:

Share

ድንቅ ተፈጥሮ፤ የላቀ ሐሳብ - We Discuss Grand ideas!

አረንጓዴ ሐሳቦች፤ ከተፈጥሮ ጋር ያለንን ግንኙነት ጤናማ በማድረግ ለማኅበራዊ ሰላም እና ፍትህ መረጋገጥ የሚያግዙ ሐሳቦች ይነሱበታል።

በአካባቢ ጥበቃ፣ አረንጓዴ ልማት እና ከአካባቢ ጋር የተጣጣመ ልማትን ትኩረት በማድረግ በአለም ዙሪያ ያሉ አዳዲስ መረጃዎችና ጥናቶችን በመዳሰስ ተደራሽ ያደርጋል፡፡

የተፈጥሮ ጥበቃ ይዘት ያላቸው የጥበብ ስራዎች፤ ሥነ ጽሑፍ፣ ሙዚቃ፣ ስዕል፣ ቅርጻ ቅርጽ፣ ዳንስ እና ሌሎችም ተፈጥሮን ጉዳያቸው አድርገው የሚነሱ ስራዎች ተተኳሪ ይሆናሉ፡፡