18/12/2025
በ200 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው አዋሽ ካፒታል አ.ማ. በይፋ ሥራ ጀመረ
ታህሳስ 09/2018 (ገበያ ሚዲያ) ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ያገኘነውና በ200ሚሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው አዋሽ ካፒታል አ.ማ. በዛሬው ዕለት በይፋ ሥራ ጀምሯል።
በሥራማስጀመርያ ሥነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የአዋሽ ካፒታል አ.ማ. የቦርድ ሰብሳቢ እናየአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው፤ "ሀገራችን በፋይናንስ ዘርፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አዲስ ምዕራፍበመግባት ዘርፈ ብዙ ለውጦችን እያደረገች በምትገኝበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቋቋሙ ለቢዝነስ ዘርፉትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር ነው" ብለዋል።
የአዋሽ ባንክ ተቀጥላ ኩባንያ የሆነው አዋሽ ካፒታል አ.ማ ሕጉ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶችና መመዘኛዎችበተገቢው ሁኔታ በሟሟላት ሙሉ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ሕዳር 10ቀን 2018 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቀበሉን አሳውቀዋል፡፡
አክለውም አዋሽ ካፒታል አ.ማ ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት በተገቢው ሁኔታ ራሱን በማደራጀት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣትየዝግጅት ምዕራፉን በማጠናቀቅ በ200 ሚሊዮን ካፒታል ሥራ መጀመሩ ገልጸዋል፡፡
አዋሽ ካፒታል አ.ማ. የተለያዩ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎቶችን ማለትም በድርጅት ፋይናንስ እና የማማከር አገልግሎት፥ በዋስትናንግድ እና የማገናኘት ስራ፥ በምርምር እና የገበያ ኢንተሊጀንስ፥ በአረንጓዴ ፋይናንስ እና የESG ወይምከባባዊ፣ ማህበራዊና አስተዳዳራዊ የማማከር አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለፁት ደግሞ፤ የአዋሽ ካፒታል አ.ማ. ዋና ሥራ አስፈጻሚአንዱአለም ኃይሉ (ዶ/ር) ናቸው።
አዋሽ ካፒታል አ.ማ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ፍቃድ የተሰጠቻው የኢንቨስትመንት ባንኮች አራተኛው በመሆን ነው በዛሬው ዕለት ታህሳስ 9 ቀን2018 ዓ/ም በይፋ ሥራ የጀመረው።
በሚሊዮን ሙሴ
#ገበያ #ኢትዮጵያ