07/04/2024
እንኳን ለአብይ ጾም እኩሌታ/የደብረ ዘይት/ በዓል ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ።
ከአንድ ሺ ሁለት መቶ ዓመት በላይ እድሜ ባስቆጠረው በምሁር ኢያሱስ ገዳም ከሃገር ውስጥና ከተለያዩ ሃገራት እንግዶች እና ጎብኚዎች የደብረ ዘይት በዓል ሃይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ለማክበር ወደ ጥንታዊውና ታሪካዊ ገዳም እየገቡ ይገኛል።
የምሁር አክሊል ወረዳ ማህበረሰብ ቀድሞ በሚታወቅበት የእንግዳ አቀባበል ስርዓት ዛሬም የብሳቢ/እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ እንግዶችን እየተቀበለ ይገኛል።
መልካም በዓል!