What's New/ebs news

What's New/ebs news what's new in the world 813 adis abeba ethiopia
(4)

አሁናዊ መረጃተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ እስራኤል አገር "እብደት በሕብረት" የተሰኘ ቴአትሩን ለማሳየት አውሮፕላን ሊሳፈር ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ...
25/04/2024

አሁናዊ መረጃ

ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ እስራኤል አገር "እብደት በሕብረት" የተሰኘ ቴአትሩን ለማሳየት አውሮፕላን ሊሳፈር ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዶ መታሰሩ ይታወሳል።

ከቤተሰብ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና ያለበት አያያዝ መልካም መኾኑን ገልጸው በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየት መወሰናቸውን ለማወቅ ችያለሁ።

በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት በአገረ እስራኤል ነስ ፅዮና ከተማ ሊካሄድ የነበረው እና ከ750 በላይ ተመልካቾች ሊታደሙበት የነበረው አማኑኤል ሐብታሙ የሚተውንበት "እብደት በሕበረት" ባለ አንድ ሰው ቴአትር መርሐ ግብር ለሌላ ጊዜ እንደተዘዋወረ በመግለጽ አዘጋጆቹ ተመልካቹን አክብረው ይቅርታ ጠይቀዋል።

ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ በአስቸኳይ ከእስር ይፈታ ዘንድ የሚወዱት ሁሉ ምኞት ነው።

አርቲስት አማኑኤል ሐብታሙ ለምን ታሰረ?ወደ አመሻሽ ላይ በስራ ጥድፊያ መሐል ሳለሁ ደወለልኝ።"... አስቸኳይ ነው። ለምን እንደሆነ እንጃ እቃዎቼን መልሰዋቸዋል። እኔንም እንፈልግሀለን ብለው...
24/04/2024

አርቲስት አማኑኤል ሐብታሙ ለምን ታሰረ?

ወደ አመሻሽ ላይ በስራ ጥድፊያ መሐል ሳለሁ ደወለልኝ።

"... አስቸኳይ ነው። ለምን እንደሆነ እንጃ እቃዎቼን መልሰዋቸዋል። እኔንም እንፈልግሀለን ብለው እስከ አሁን ይዘውኛል። የአውሮፕላን መነሻ ሰዓቱም ሊያልፍብኝ ነው"

- እንዴ!.. ለምን?

"እኔ እንጃ ኤርፖርት ውስጥ ነው እስከ አሁን ያለሁት። ጉዞዬ ከደቂቃዎች በኋላ ነው። ግን እስከ አሁን ጠብቅ! ብለው ይዘው እንዳቆዩኝ ነው"

ከአማኑኤል ሐብታሙ ጋር መጠነኛ መረጃዎች ከተቀያየርን በኋላ አንድ አንድ ነገሮችን አጣርቼ በቶሎ መልሼ እንደምደውልለት ከነገርኩት በኋላ ስልኩ ተቋረጠ።

ከደቂቃዎች በኋላ መልሼ ስደውል ስልኩ ተዘግቷል። በተደጋጋሚ ብሞክርም ያው ነው።

ከቤተሰቦቹ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ይህንን ማስታወሻ እስካሰፈርኩበት ሰዓት ድረስ አማኑኤል ፖሊሶች ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ወስደውት በእስር ላይ ይገኛል።

ቤተሰቦቹ ራት እንዳደረሱለት እና በፖሊስ ስለተያዘበት ጉዳይ እርሱም ይሁን በሕግ ስር የዋሉት ፖሊሶች ምንም አይነት መረጃ እንዳልሰጧቸው አረጋግጫለሁ።

አማኑኤል ሐብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘውን ተወዳጅ አዲስ ባለ አንድ ሰው የሙሉ ሰዓት ቴአትሩን እስራኤል አገር ለሚገኙ ተመልካቾች ለማሳየት በጉዞ ላይ ሳለ ዛሬ ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ/ም አመሻሽ ላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በፖሊስ ተይዞ ወደ እስር ቤት ተወስዷል።

ለእስር ያበቃው ጉዳይ ምን እንደሆነ የተገለጸ ነገር ባይኖርም፤ እስራኤል ውስጥ ነስ ጽዮና በተባለ ከተማ ትልቅ ቴአትር ቤት የፊታችን ሐሙስ ትርዒቱን ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቆ አውሮፕላን ለመሳፈር አየር ማረፊያ ደርሶ ነበር።

ከ400 በላይ ተመልካቾች ትኬቱን በቅድሚያ ቆርጠው፣ በጠቅላላው ከ750 በላይ ተመልካቾች የሚታደሙበትን ዝግጅት ለማቅረብ በጉጉት እየተጠበቀ በድንገት ምክንያቱ ባልተገለጸ ሰበብ ለእስር መዳረጉን ለመረዳት ችያለሁ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ "እያዩ ፈንገስ ቁጥር 2"ን ጨምሮ የተለያዩ የኪነጥብ ዝግጅቶች ከመድረክ እንዲወርዱ እና ዕይታቸው እንዲስተጓጎል የተደረገበት አታካች አካሄድ በአዲሱ "እብደት በሕብረት" ተውኔት ላይ ተደርጎ ይሁን አይሁን ለጊዜው የታወቀ ነገር ባይኖርም፤ ተቋማዊ ድጋፍ ሳይደረግለት በግል ጥረት ዘውትር በታላቅ ትግል የሚከወነው የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ትልቅ ጋሬጣ የሚፈጥሩ ተደጋጋሚ ሳንካዎች መከሰታቸው ለጥበብ ሙያተኞች አንገት የሚያስደፋ ሆኗል።

ብዙ ውጪ ወጥቶበት ለዕይታ ለመቅረብ ጫፍ ላይ የደረሰው ይህ ተውኔት በተወዳጁ ተዋናይ ላይ ከደረሰበት ድንገተኛ እስር ባሻገር ተዋናዪን እና አዘጋጆቹን ለኪሳራ የሚዳርግ አጋጣሚ በመፈጠሩ በእጅጉ የሚያሳዝን ሆኗል።

አማንን በቅርብ የሚያውቁ ሁሉ በስነ ምግባር የታነጸ፣ ሙያውን እለት ከዕለት በማሳደግ ምስጉን የኾነ ተዋናይ መኾኑን ይመሰክሩለታል።

በፍጥነት ከእስር ተለቆ ጉዞውን በማካሄድ አክበረውት በጉጉት ከሚጠባበቁት ተመልካቾች ጋር እንደሚገናኝ ተስፋ በማድረግ ባለበት ፈጣሪ እንዲጠብቀው እመኛለሁ።

ግን ለምን?


Via ያሬድ ሹመቴ

🇩🇯 ጅቡቲ :  የ38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አለፈ   | በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ የ 38 ኢት...
09/04/2024

🇩🇯 ጅቡቲ : የ38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አለፈ

| በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ የ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወት አልፏል።

በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ ጎዶሪያ በሚባል የባህር ዳርቻ አቅራቢያ 60 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ 38 ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

በጅቡቲ የኢፌዴሪ ሚሲዮን አደጋው ከደረሰ በኋላ ወደ ስፍራው በመጓዝ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ሚሲዮኑ በዚህ አሳዛኝ ክስተት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ፤ ከጅቡቲ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚደረገው ህገ ወጥ ጉዞ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በየጊዜው የዜጎችን ሕይወት እያሳጣ እንደሚገኝ አስገንዝቧል።

ዜጎች በህገ ወጥ ደላሎች የሀሰት ስብከት በመታለል ውድ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው ሚሲዮኑ፤ የፍትህ አካላትም ከገጠራማ የአገሪቱ አካባቢዎች ዜጎችን በመመልመል ለስደት በሚዳርጉ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪውን አስተላልፏል።

አንጋፍው ሙዚቀኛ እና ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ  ከዚሀ አለም ድካም አርፏል። ነፍስ ይማር። ለቤተሰቡ ለወዳጅ ዘመዶቹና ላድናቂዎች መፅናናትን ይመኛል   muluken melese
09/04/2024

አንጋፍው ሙዚቀኛ እና ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚሀ አለም ድካም አርፏል። ነፍስ ይማር። ለቤተሰቡ ለወዳጅ ዘመዶቹና ላድናቂዎች መፅናናትን ይመኛል
muluken melese

08/04/2024

ዛሬ የታየው የፀሀይ ግርዶሽ እና በኢትዮጵያ ይታያል...........

2ኛ ዙርከ21 ሺህ እስክ 95 ሺህ ብር የወስዱ 😎😎😎ፎቶ ገጭየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፎቶ ለቋል ገንዘቤን ወስደው አልመለሱም ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶ ለቋልአሁንም ገንዘቤን ትመልሱ እንደሆነ መል...
02/04/2024

2ኛ ዙር

ከ21 ሺህ እስክ 95 ሺህ ብር የወስዱ 😎😎😎

ፎቶ ገጭ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፎቶ ለቋል

ገንዘቤን ወስደው አልመለሱም
ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶ ለቋል

አሁንም ገንዘቤን ትመልሱ
እንደሆነ መልሱ ብሏል::

ፎቶአችሁ አለ እንዴ እስቲ ራሳችሁን
ፈልጉ

ሴቶቹ 👁️😮

መልሱ………..

📸 ፎ

🏃🏾‍♂️😎

🌴🌴🌴ምንጭ

27/03/2024

footballer Alelegn Azene
rest in peace

25/03/2024
የቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ከእስር ተለቀቁ   | የቀድሞው የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው፤ ከ...
15/03/2024

የቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ከእስር ተለቀቁ

| የቀድሞው የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው፤ ከአምስት ዓመት ከአራት ወራት እስር በኋላ ዛሬ ከሰዓት ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ሜጀር ጄነራል ክንፈ የተፈቱት፤ በእርሳቸው ላይ ቀርበው የነበሩ ተደራራቢ ክሶች “ለህዝብ ጥቅም” ሲባል በትላንትናው ዕለት መቋረጣቸውን ተከትሎ ነው።

የቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ዛሬ አርብ መጋቢት 6፤ 2016 ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ የተለቀቁት፤ አብዛኛውን የእስር ጊዜያቸውን ካሳለፉበት ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት መሆኑን ጠበቃቸው አቶ ሐፍቶም ከሰተ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ሜጀር ጄነራል ክንፈ ከእስር ሲለቀቁ በቤተሰቦቻቸው አቀባበል እንደተደረገላቸውም አክለዋል።

ሜጀር ጄነራል ክንፈ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው፤ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ህዳር 3፤ 2011 ዓ.ም. ነበር። የቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ከተያዙበት ትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ በሄሊኮፕተር ተጓጉዘው ሲደርሱ፤ በብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ “በሰበር ዜና” እንዲሰራጭ ከተደረገ በኋላ ጉዳያቸው ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ መቆየቱ አይዘነጋም።

ተጠርጣሪው ሜቴክ በሚያስተዳድራቸው እና በሚሳተፍባቸው ፕሮጀክቶች ከተፈጸሙ 37 ቢሊዮን ብር ከሚያወጡ ግዢዎች ጋር በተያያዘ፤ ተደራራቢ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት ሲከታተሉ ቆይተዋል። የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በሜጀር ጄነራል ክንፈ ላይ ያቀረባቸው 13 ክሶች፤ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲታዩ የቆዩት በስድስት መዝገቦች ነበር። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

👏👏👏ታኩር Seifu on EBS እንደዚህ አይነት በራሳቸው unique በሆነ “ Content Video “ እየመጡህብረተሰቡ የሚያዝናኑ እንደ ታኩር አይነት ታዳጊ ቲክቶከሮች በዚህ መዝናኛ ዝግጅ...
10/03/2024

👏👏👏

ታኩር Seifu on EBS

እንደዚህ አይነት በራሳቸው unique በሆነ
“ Content Video “ እየመጡ

ህብረተሰቡ የሚያዝናኑ እንደ ታኩር አይነት ታዳጊ ቲክቶከሮች በዚህ መዝናኛ ዝግጅት ማቅረብ በጣም ደስ የሚያስኝ ና የሚያበረታታ ተግባር ነው::

* ሰይፉ 🙏

* ታኩር ብዙ ስኬቶች ከፊት ለፊትህ
ያለ ጎብዝ ታዳጊ ነህ::

በርታ 👏🥰

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

ቀብር 💔 🖤   | የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጉዲሳ ለገሠ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡  በዋ...
27/02/2024

ቀብር 💔 🖤

| የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጉዲሳ ለገሠ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

በዋና ሥራ አስፈፃሚያችን ድንገተኛ ህልፈት ከፍተኛ ሐዘን ደርሶብናል፡፡

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ አራት ኪሎ በሚገኘው በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መካነ መቃብር ማክሰኞ፣ የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ የሚፈጸም መሆኑን እንገልጻለን፡፡

አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ.

***
Ibsa Gaddaa

Hoji-gaggeessaan Inshuraansii Awaash Obbo Guddisaa Laggasaa dhibee isaan muudaterraa fayyuuf biyya keessaafi biyya alaatti yaalamaa osoo jiranii Guraandhala 18/2016 ALI du’aan addunyaa kanarraa boqotaniiru.

Boqochuu hoji-gaggeessaa dhaabbata keenyaatiin gadda guddaa nutti dhagahame ibsaa, Maatii Obbo Guddisaa Laggasaatiif, Maatii Inshuraansii Awaashiif, firootaafi hiriyoottan isaanii hundaaf jajjabina hawwina.

Sirni awwaalcha isaanii Guraandhala 19/2016 ALI Bataskaana Kaatediraalii Qiddisti Sillaasee naannoo Araat Kiiloo jirutti kan raawwatamu ta’uun beekameera.

Inshuraansii Awaash

***
የሀዘን መግለጫ!
===
የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የስራ አመራርና መላው ሰራተኛ በእህት ኩባንያው አዋሽ ኢንሹራንስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ጉዲሳ ለገሠ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልፃለን፡፡

ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡

Ibsa Gaddaa!
===
Miseensotni Boordii, Hoggantootniifi Hajjettootni Baankii Awaash Hoji-Gaggeessaa Olaanaa Inshuraansii Awaash kan turan Obbo Guddisaa Laggasee du’aan addunyaa kanarraa boqochuu isaaniitiif gadda guddaa nutti dhagahame ibsaa, maatiifi firoottan isaaniif jajjabina hawwina.

ተይዟል👏👏👏ስደተኛው ብሩክ ላይ አሲድ ደፍተው ካቃጠሉት ውስጥ አንደኛው እዛው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተይዟልየደቡብ አፍሪካ ልጆች ልጁንም ይዘውት ይገኛሉየደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን good Jo...
23/02/2024

ተይዟል

👏👏👏

ስደተኛው ብሩክ ላይ አሲድ ደፍተው ካቃጠሉት ውስጥ አንደኛው እዛው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተይዟል

የደቡብ አፍሪካ ልጆች
ልጁንም ይዘውት ይገኛሉ

የደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን
good Job 👏 👏👏

ወንድማችን ብሩክ ፈጣሪ ይማርህ

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

በአሜሪካ የሉዚያና ግዛት ነዋሪ የሆነው Darren James ማታ ሲተኛ የሚያውቀው በባንክ አካውንቱ ውስጥ ያለው ተቀማጭ ገንዘብ መቶምናምን ዶላር እንደሆነ ነበር ። ልክ ሲነጋ ግን ነገሮች ተ...
18/02/2024

በአሜሪካ የሉዚያና ግዛት ነዋሪ የሆነው Darren James ማታ ሲተኛ የሚያውቀው በባንክ አካውንቱ ውስጥ ያለው ተቀማጭ ገንዘብ መቶምናምን ዶላር እንደሆነ ነበር ። ልክ ሲነጋ ግን ነገሮች ተለዋወጡ ፡ ከባለቤቱና ከሁለት ልጆቹ ጋር የሚያገኛትን ደሞዝ አብቃቅቶ የሚኖረው ዳረን በአንድ ሌሊት. .. ሀምሳ ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በማስመዝገብ ፡ የአለም 25 ኛው ቢሊየነር ሰው ሆነ ። ነገሮቹን ሁሉ የለወጠው ከባንክ የተላከለት ቴክስት ነበር ። እና ከባለቤቱ ጋር ሆነው ቴክስቱን ደጋግመው አነበቡት ፡ የተላከው ቴክስት ስካም ወይም ፌክ እንዳልሆነ በደንብ አረጋገጡ ፡ እውነታው አንድ የማያውቁት ሰው በነሱ አካውንት ላይ ሀምሳ ቢሊየን ዶላር አስገብቶላቸዋል ።

በህይወቴ ዘጠኝ ዜሮዎች ያሉት ይቅርና ፡ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ብርም ኖሮኝ አያውቅም ፡ እና አንድ ዘመድ ይህን ብር እንዳስገባልኝ አሰብኩ ፡ ሆኖም ያን ያህል ብር ያለው ሰው ፈፅሞ አላውቅምና ፡ ጉዳዩን ለባንክ ማሳወቅና የተሳሳተ ብር እንደተላከልኝ ለመናገር ወሰንኩ ይላል ። ሆኖም የዳረን ባለቤት ይህን ሀሳብ ተቃውማ ምን አስቸኮለህ የተሳሳተ ከሆነ ራሳቸው ይደውሉልናል ተረጋጋ አለችው ። ዳረን በሀሳቧ አልተስማማም ፡ የገባለትን ገንዘብ ወደሌላ አካውንት ለማዛወርም አልሞከረም እና ወዲያው ወደባንክ ሄደ ፡ እውነቱን ነግሯቸው ለሱ የተላከም ከሆነ ለማወቅ ካልሆነም ፡ ለቢሊየነሩ ሰው መልሶ ምስጋና እና ገንዘቡን ለመለሰበት አንድ አስር ሚሊየን ብር ጉርሻ ሊሰጡት እንደሚችሉ እያሰበ ባንክ ደርሶ ሀምሳ ቢሊየን ብር ወደባንክ አካውንቴ ገብቷል አላቸው ፡ ማናጀሩ ቢሮ ጠርቶ አናገረው ። እና ሁኔታውን እንደሚያጣሩ ነግረውት ከባንኩ ወጥቶ ጥቂት እርምጃ እንደተራመደ ፡ ሌላ ቴክስት በስልኩ ገባ ፡ ቴክስቱን አነበበው ፡ አሁን ያሎት ቀሪ ሂሳብ ( ጥቂት ) መቶ ብር ብቻ ነው ይላል ቴክስቱ ። በድንገት በአካውንቱ ገብቶ ከአለም ቢሊየነሮች ተርታ በ25 ኛ ደረጃ ያስቀመጠው ገንዘብ ፡ ከመቅፅበት ከአካውንቱ ወጥቶ ተሰወረ ። አስገራሚው ነገር ባንኩ ይህን በተመለከተ ምንም አይነት መግለጫም ሆነ ትክክለኛው የገንዘቡ ባለቤት በተመለከተ ምንም አልተናገረም ፡ ይህን በተመለከተ አስተያየት የሰጡ ሰወች ገንዘቡ ከክሪፕቶ ወይም ከህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ተናግረዋል ። ለሰአታት ቢሊየነር ለሆነው ዳረን ጀምስም ጉርሻ ይቅርና ምስጋናም አልተሰጠውም ነՈር::

የነፍስ አድን ስራው ድጋሜ ተጀመረ* በደላንታ ቆሞ የነበረው 20 ማዕድን አውጪዎች ከገቡበት  ፍርስራሽ ውስጥ የማውጣት ስራው ዳግም ተጀመረ።   | የደቡብ ወሎ ኮሙንኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ...
16/02/2024

የነፍስ አድን ስራው ድጋሜ ተጀመረ

* በደላንታ ቆሞ የነበረው 20 ማዕድን አውጪዎች ከገቡበት ፍርስራሽ ውስጥ የማውጣት ስራው ዳግም ተጀመረ።

| የደቡብ ወሎ ኮሙንኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ እያሱ ዮሀንስ እንዳሉት የወጣቶቹን ህይወት ለመታደግ የወረዳው እና የአካባቢው ማህበረሰብ ሌት ተቀን በፈረቃ እየቆፈረ እንደነበር ነገር ግን መልክዓ ምድሩ ለቁፋሮ አመቺ አለመሆኑን ተከትሎ ተጨማሪ ሰው ላለማጣት በሚል ቁፋሮው ከአቅም በላይ ነው ተብሎ ቆሞ እንደነበር ጠቅሰው አሁን ዳግም እንደተጀመረ ተናግረዋል።

ወጣቶቹ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ላይ ማዕድኑን ለማውጣት እየቆፈሩ እያሉ መውጫቸው በዓለት የተዘጋባቸው ሲሆን በአካባቢው በተመሳሳይ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ጉዳዩን ለህዝብ አሳውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀን ጀምሮም ወጣቶቹን ለመታደግ የደላንታ ወረዳ እና የአካባቢው ማህበረሰብ በዘመቻ እየቆፈረ ነው የተባለ ሲሆን ወጣቶቹ ያሉት በግምት 750 ሜትር ርቀት ላይ ይሆናልም ተብሏል፡፡

እስካሁን በተደረገው ጥረትም ከ50 ሜትር በላይ ርቀት ቁፋሮ እንደተቆፈረ የተናገሩት ሀላፊው ቦታው አለታማ እና የቁፋሮ ማሽን ለማስገባት አመቺ አለመሆኑ ጥረቱን ፈታኝ አድርጎታል ሲሉም አክለዋል፡፡

ከሶስት ዓመት በፊት በተመሳሳይ ኦፓል ማዕድን በማውጣት ስራ ላይ የነበሩ ወጣቶች ተማሳሳይ አደጋ አጋጥሟቸው ነበር ያሉት አቶ እያሱ በተደረገው ርብርብ ከ11 ቀናት እልህ አስጨራሽ ቁፋሮ በኋላ ሁሉንም ወጣቶች በህይወት ማግኘት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡

አቶ እያሱ አክለውም ወጣቶቹን በህይወት ለማትረፍ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ተናግረው በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ ሁሉንም ወጣቶች በህይወት ለመታደግ ተስፋ እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡

አል ዐይን

እርዳታው ቀጥሏል በመኪና አደጋ የተነጠቀችውን እናት በቤቷ ተገኝተው አጽናኑ   | ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አንድ ልጇ በመኪና አደጋ የተነጠቀችን እናት በቤቷ ተ...
15/02/2024

እርዳታው ቀጥሏል
በመኪና አደጋ የተነጠቀችውን እናት በቤቷ ተገኝተው አጽናኑ

| ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አንድ ልጇ በመኪና አደጋ የተነጠቀችን እናት በቤቷ ተገኝተው አጽናንተዋል።

ብፁዕነታቸው ኀዘንን በኦርቶዶክሳዊ ልክነት ማድረግ እንደሚገባም አባታዊ ምክር ሰጥተዋል።

በመኪና አደጋ ምክንያት በሞተ ሥጋ የተለየው ስሙ ኦኮቻ የተባለ በቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በአከባቢው ማኅበረሰብም ቅን ታዛዥ እንደነበረም ተገልጿል።

ብፁዕነታቸው ከአደጋው ቀን ጀምሮ በተለያየ መልኩ ኀዘንተኞችን ያጽናኑትን ከጎናቸው ያልተለዩትን ሰዎች አመሰግናው እንዲህ ዓይነቱ ኦርቶዶክሳዊም ሰብአዊም ተግባር በእጅጉ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል።

ብፁዕነታቸው በአባታዊ ቃለ በረከት ከማጽናናታቸው ጎን ለጎን ልጆን ለተነጠቀች እናት የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ሲል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አስታውቋል።

የፕሪቶሪያው ስምምነት ሳይፈጸም ሠራዊታችን ትጥቅ ፈትቶ እንደማይበተን ለመንግሥት አሳውቀናል›› አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት   | የፕሪቶሪያው ስምምነት ተ...
15/02/2024

የፕሪቶሪያው ስምምነት ሳይፈጸም ሠራዊታችን ትጥቅ ፈትቶ እንደማይበተን ለመንግሥት አሳውቀናል››

አቶ ጌታቸው ረዳ፣
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት

| የፕሪቶሪያው ስምምነት ተሟልቶ ሳይፈጸም ‹‹የትግራይ ሠራዊት›› ትጥቅ ፈትቶ እንደማይበተን ለፌዴራል መንግሥት ማሳወቃቸውን፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸምን በአዲስ አበባ ተገናኝተው የገመገሙ ሲሆን፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ሰኞ የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በግምገማው ወቅት ከሁለቱም አካላት የተነሱ ጉዳዮችን አብራርተዋል።

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ሊፈጽማቸው ይገቡ የነበሩ በርካታ ጉዳዮችን አለመተግበሩን፣ ይህንንም በውይይቱ ወቅቱ ማስረዳታቸውን አቶ ጌታቸው በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

‹‹የፕሪቶሪያው ስምምነት አልተፈጸመም፣ ሕወሓት ሕጋዊ ሰውነቱን መልሶ አላገኘም፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው አልተመለሱም፣ የአማራና የኤርትራይ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡ አልተደረገም፤›› ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ይህንንም ለፌዴራል መንግሥት በዝርዝር ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

የፌዴራል መንግሥት በበኩሉ በሕወሓትና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ላይ ካነሳቸው ቅሬታዎች መካከል፣ ‹የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለጊዜ መግዣ እየተጠቀማችሁበት ነው፣ ትጥቃችሁን ለመፍታት ፍላጎት የላችሁም፣ ሠራዊታችሁን ማጠናከር ነው የምትፈልጉት፣ ከኤርትራና ከሌሎች የውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር መንግሥትን ለመጣል እየሠራችሁ ነው› የሚሉት እንደሚገኙበት፣ አቶ ጌታቸው በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ሕወሓትም ሆነ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት ፍላጎት የላቸውም ተብሎ የቀረበባቸውን ክስ በተመለከተ ምላሽ መሰጠቱን የተናገሩት አቶ ጌታቸው፣ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታትና መልሶ በማቋቋም ረገድ ትልቁ ኃላፊነት የፌዴራል መንግሥት ቢሆንም፣ ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ ሊፈጸም እንዳልቻለ ገልጸዋል፡፡

‹‹የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሳይሆን ይህንን ሠራዊት ተበተን የምንልበት ምክንያት የለም። ይህ ሠራዊት መስዋዕትነት የከፈለ፣ ለትግራይ ህልውና የቆመ ሠራዊት ነው፤›› ብለዋል።

አክለውም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ብዙ ችግሮች ያሉበት ቢሆንም፣ ለክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች ሊከፈል የሚገባውን ደመወዝ በመቀነስ ለሠራዊቱ ወጪ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ‹‹ይህንንም መተሳሰብ አለብን፤›› ሲሉም ተደምጠዋል።

የትግራይ ክልል ከ270 ሺሕ በላይ ሠራዊት እንዳለው የጠቀሱት አቶ ጌታቸው፣ ይህ ሠራዊት ወደ ቤቱ የሚመለስ ከሆነ ለዚህ የሚመጥን በጀት ሊመደብ እንደሚገባ፣ ለዚህም የፌዴራል መንግሥት ከውጭ አጋሮቹ ጭምር ገንዘብ ሰብስቦ በማምጣት ሠራዊቱ መልሶ የሚቋቋምበትን ሁኔታ ማቻቸት እንዳለበት ተናግረዋል።

ይህንን ማድረግ ረዥም ጊዜ የሚወስድ እንደመሆኑ መጠን፣ የፌዴራል መንግሥት በካምፕ ውስጥ ለሚገኘው የትግራይ ሠራዊት ስንቅ የማቅረብ ኃላፊነት እንደነበረበት፣ ነገር ግን ይህንን ኃላፊነት እንዳልተወጣ ገልጸዋል።

‹ከኤርትራና ከሌሎች ኃይሎች ጋር በመተባበር መንግሥትን ለመጣል እየሠራችሁ ነው› ተብሎ በፌዴራል መንግሥት የቀረበባቸው ወቀሳን በተመለከተ አቶ ጌታቸው በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹እኛ ፍላጎታችን ሰላም ብቻ ነው ብለን አብራርተን ምላሽ ሰጥተናል፣ እናም የተግባባን ይመስለኛል፤›› ብለዋል።

14/02/2024

ጠንካራ ሴት 💀

የአድዋ መዚየም የምሽት ገፅታLike and share
12/02/2024

የአድዋ መዚየም የምሽት ገፅታ

Like and share

ሰባስቲያን ሃለር - ካንሰርን ድል ከመንሳት እስከ አፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮንነት አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮትዲቯሩ አጥቂ ሰባስቲያን ሃለር ከካንሰር ሕመም በማገገም ሀ...
12/02/2024

ሰባስቲያን ሃለር - ካንሰርን ድል ከመንሳት እስከ አፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮንነት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮትዲቯሩ አጥቂ ሰባስቲያን ሃለር ከካንሰር ሕመም በማገገም ሀገሩ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን እንድትሆን የአንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል፡፡

የቀድሞው የአያክስ እና ዌስትሃም አጥቂ ሰባስቲያን ሃለር የጀርመኑን ክለብ ቦርሺያ ዶርትሙንድ ከተቀላቀለ በኋላ በፈረንጆቹ ሐምሌ ወር 2022 የቴስቲኩላር ካንሰር ሕመም አጋጥሞት ነበር፡፡

ለሕመሙ ከሚሰጠው ሳይንሳዊ ትንታኔ እና በእግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ ከሚፈጥረው የአካል ብቃት ተፅዕኖ አንፃር ብዙዎቹ የኮትዲቯሩን አጥቂ የእግር ኳስ ሕይወት በ28 ዓመቱ እንደሚያበቃ ገምተው ነበር፡፡

የሃለርን የእግር ኳስ ጉዞ በመርሳት ፈጣሪ በሕይወት ብቻ እንዲያኖረው የጸለዩ የእግር ኳስ አፍቃሪያንም አልጠፉም፡፡

ነገር ግን የታሰበው ሳይሆን ሃለር የቀዶ ጥገና እና የጨረር (ኬሞቴራፒ) ሕክምናውን በማጠናቀቅ በፈረንጆቹ 2023 ጥር ወር ሕመሙን ታግሎ በማሸነፍ ሙሉ በሙሉ ከካንሰር ነጻ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ለተጫዋቹ የተሳካ የኬሞቴራፒ ሕክምናም የጀርመን ሐኪሞች ጥረት ከፍተኛ እንደነበር ነው የተነገረው፡፡

ከካንሰር ሕመሙ ካገገመ በኋላ ወደ ማርቤላ የልምምድ ሜዳ በመመለስ በቦርሺያ ዶርትሙንድ የቡድን አጋሮቹን በመቀላቀል በቡንደስሊጋው ድንቅ ጊዜን ማሳለፍ ችሏል፡፡

በ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የእናት ሀገሩን ጥሪ የተቀበለው የ28 ዓመቱ አጥቂ ሰባስቲያን ሃለር ወደ አቢጃን በመመለስ የብሔራዊ ቡድን አጋሮቹን ተቀላቅሏል፡፡

ሃለር ደካማ አጀማመር በማሳየት ከምድብ በምርጥ ሶስተኝነት ያለፈው የኮትዲቯር ብሄራዊ ቡድን በግማሽ ፍጻሜው ዴሞክራቲክ ኮንጎን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ብቸኛዋን ግብ በማስቆጠር ቡድኑን ለፍጻሜ አሳልፏል፡፡

በፍጻሜው ከናይጄሪያ ጋር በነበረው ጨዋታ ኮትዲቯር በቁርጥ ቀን ልጇ ሰባስቲያን ሃለር ሁለተኛ ግብ በመታገዝ ናይጄሪያን 2 ለ 1 በማሸነፍ ያዘጋጀችውን የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማንሳት ችላለች፡፡

52 ጨዋታዎች ተካሂደው 119 ግቦች የተቆጠሩበት 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኮትዲቯር ሻምፒዮንነት ትላንት ምሽት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

14/01/2024

💔 "ሞት እንኳን ጨክኖ..."

😪 ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ህክምናውን ሲከታተል በቆየበት፣ ዲሲ በሚገኘው የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፤ ቅዳሜ በዋሽንግተን አቆጣጠር ከምሽቱ 1:00 ሰአት (በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከለሊቱ 9:00 ሰዓት ) ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል።

ለልጁ ሳምሶን (ጃፒ)፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለጓደኞቹ እና ለሚያውቁት ሰዎች ሁሉ መጽናናት ይሁን።

💔 "ልጄን አደራ!" ...

ወንድማችንና የሥራ ባልደረባችን አስፋው መሸሻ ባደረበት ህመም በህክምና ሲታገዝ ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።የጣቢያችን ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንትና ሰራተኞችም በአንጋፋው የራዲዮና ቴሌ...
14/01/2024

ወንድማችንና የሥራ ባልደረባችን አስፋው መሸሻ ባደረበት ህመም በህክምና ሲታገዝ ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

የጣቢያችን ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንትና ሰራተኞችም በአንጋፋው የራዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን።

አስፋው መሸሻ ረጅም አመታትን በተሻገረ አገልግሎቱ በጣቢያችን ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ይተላለፍ በነበረው ኑሮ በአሜሪካ ከተሰኘው ፕሮግራም እስከ እሁድን በኢቢኤስ መሰናዶ ድረስ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈ ባልደረባችን ነበር።

በህልፈተ ህይወቱ የተሰማንን ልባዊ ሀዘን በድጋሚ እየገለጽን ለቤተሰቦቹ ወዳጅ ዘመዶቹ አድናቂዎቹና የሙያ ባልደረቦቹ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።

ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ልባዊ ሀዘን እንገልጻለን።

የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) መልእክት    | የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ 127ኛው የአድዋ ድል በዓል...
02/03/2023

የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) መልእክት

| የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ 127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ብሔራዊ ኩራት ነው::

የዘንድሮውን የ127ኛው የአድዋ ድል በአልን ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደ ሀገር የመቀጠል እጣዋ ከፍተኛ አደጋ ላይ የወደቀበት ወቅት መሆኑን አፅንኦት በመስጠት እና ቀደምት አባቶቻችን በታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት ያቆዩልንን የጋራ ሀገራችንን ከመቼውም ጊዜ በላቀ የመጠበቅ እንዲሁም ከገጠማት እጅግ ፈታኝ የህልውና አደጋ የመታደግ ታላቅ ታሪካዊ ሃላፊነት እና አደራ በኛ ትውልድ ትከሻ ላይ መውደቁን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊሆን ይገባል::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)

127ኛው የአድዋ የነፃነት ቀን
01/03/2023

127ኛው የአድዋ የነፃነት ቀን

በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖቻችን ትኩረት ይሰጣቸው!በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ላለፉት አምሥት የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ባለመጣሉ ምክንያት የአካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ የውኃ እጥረት አጋጥሞታ...
23/02/2023

በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖቻችን ትኩረት ይሰጣቸው!

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ላለፉት አምሥት የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ባለመጣሉ ምክንያት የአካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ የውኃ እጥረት አጋጥሞታል። ይኽም ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ጠባቂ እንዲኾኑ አድርጓል።

የቦረና ማኅበረሰብ የኑሮ መሠረቱ የኾኑት ከ 2.3 ሚሊየን በላይ ከብቶቹ በዚሁ ድርቅ ምክንያት ሞተውበታል። ድርቁ ያስከተለው ጉዳት እየተባባሰ መጥቶ ሰዎች መሞት መጀመራቸውን መረጃዎች አመላክተዋል። ይኽ ከባድ ድርቅ በደቡብ እና ሶማሊ ክልል አንዳንድ አካባቢዎችም ጉዳት እያደረሰ ነው።

ድርቁ ላስከተለው ሰብዓዊ ጉዳት ምላሽ ለመስጠት የክልልና የፌዴራል መንግሥት ጥረት እያደረጉ ቢኾንም፤ በድርቁ ምክንያት ለርሃብ ከተጋለጡ ሰዎች ብዛት አንፃር በበቂ ሁኔታ ለጉዳዩ ትኩረት አልተሰጠውም።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በድርቅ ምክንያት ለርሀብ የተጋለጡ ወገኖቻችንን ለመታደግ መንግሥት አላስፈላጊ የፖለቲካ ሽኩቻዎች እና መጠላለፎች ላይ የሚያባክነውን ጊዜ እና አቅም ወደጎን ትቶ፤ ለርሀብ ለተጋለጡ ወገኖቻችን ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲሠራ ይጠይቃል። ከተጋረጠው ሰብዓዊ ቀውስ አንፃር አስቸኳይ ብሔራዊ የዕርዳታ ኮሜቴ በማቋቋም መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተባብሮ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን እንዲደርስላቸው እናሳስባለን።

ለረሃብ የተጋለጡ ወገኖችን ለመታደግ ከመንግስት በተጨማሪ መንግስታዊ ያልኾኑ ተቋማት፣ ሲቪክ ማኅበራት፣ የዕርዳታ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት፣ አክቲቪስቶች፣ መገናኛ ብዙኃን፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አርቲስቶች እና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠበቅባችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን።

የፓርቲያችን አባላትም በያላችሁበት አካባቢ ኹሉ ወገኖቻችንን ለመታደግ በሚደረጉ ሰብዓዊ እና ወገናዊ ዘመቻዎች ላይ የተለመደውን ግንባር ቀደም ተሳትፏችሁን እንድታከናውኑ እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
የካቲት 16/2015 ዓ.ም

15/02/2023
ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ(ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ======= #=======እሁድ ታሕሳስ 2 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በበርካታ የአገራችን ፊልሞች ላይ በመሳተፍ የሚታወቀው ወጣቱ ተዋናይ...
11/12/2022

ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ(ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
======= #=======

እሁድ ታሕሳስ 2 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በበርካታ የአገራችን ፊልሞች ላይ በመሳተፍ የሚታወቀው ወጣቱ ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ/ባባ/ በድንገተኛ ህመም ዛሬ ታሕሳስ 2 ቀን 2015 ማለዳ ላይ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ታውቋል።

ላውንደሪ ቦይ፣ 300 ሺ፣ ሹገር ማሚ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ፣ ኢንጂነሮቹ፣ ህይወቴ፣ ወደው አይሰርቁ፣ ከቃል በላይ፣ ህይወት እና ሳቅ፣ ሀገርሽ ሀገሬ፣ እዮሪካ፣ ከባድ ሚዛን፣ ወፌ ቆመች፣ ይመችሽ ያአራዳ ልጅ 2፣ በቁም ካፈቀርሽኝ፣ እንደ ቀልድ፣ እርቅ ይሁን፣ አስነኪኝ፣ ሞኙ ያአራዳ ልጅ 4፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር፣ ወጣት በ97 እና ባሌ ማነቅያ፤ ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ(ባባ) ከተወነባቸው ፊልሞች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው።

በተጨማሪም ተዋናይ ታሪኩ የጉዳዬ ፊልም ደራሲና ዳይሬክተር ሲሆን፤ በ2ተኛው ለዛ አዋርድ፣ በ7ተኛው አዲሲ ሙዮዚክ አዋርድ እንዲሁም በ12 ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ላይ በምርጥ ተዋናይነት አሸናፊ ነበር።

በሰላሳዎቹ የእድሜ አጋማሽ ላይ የሚገኘው ተዋናይ ታሪኩ ተውልዶ ያደገው አዲስ አበባ ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሲሆን፤ የአንድ ልጅ አባትም ነበረ።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ/ባባ/ ባደረበት ድንገተኛ ህመም ምክንያት ዛሬ ታሕሳስ 2/2015 ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

አዲስ ነገር ዜና

ተወዳጁ ድምጻዊ የክብር ዶክተር አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ Ebs News
07/11/2022

ተወዳጁ ድምጻዊ የክብር ዶክተር አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ Ebs News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአራዳ ክፍለ ከተማ በአዲስ መልክ የተገነባውን "15 ሜዳ" መርቀው ከፈቱጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በአዲስ መልክ የተገነ...
27/10/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአራዳ ክፍለ ከተማ በአዲስ መልክ የተገነባውን "15 ሜዳ" መርቀው ከፈቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በአዲስ መልክ የተገነባውን በተለምዶ "15 ሜዳ" ተብሎ የሚጠራውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፈቱ።

23/10/2022

የነደብረጺዮን ከሀገር መውጣት! የመቀሌ መያዝ አሜሪካን ለምን አስፈራት?

Address

Addis Abeba
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when What's New/ebs news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to What's New/ebs news:

Videos

Share