ጠቃሚ ንግግሮች/Useful expressions

ጠቃሚ  ንግግሮች/Useful expressions t.me/UsefulExpression ✍️
(1)

  ..✍️
01/01/2025

..✍️

ሰዎች የአለማችን ድሃው ፕሬዝዳንት ብለው ይጠሩኛል እኔ ግን ድሃ እንድሆንኩ አይሰማኝም ድሃዎች የተቀናጣ ህይወት ለመኖር የሚያግበሰብሱ ናቸው ይላሉ የአለማችን በገንዘብ ድሃ የሆኑት የዩራጓይ ...
01/01/2025

ሰዎች የአለማችን ድሃው ፕሬዝዳንት ብለው ይጠሩኛል እኔ ግን ድሃ እንድሆንኩ አይሰማኝም ድሃዎች የተቀናጣ ህይወት ለመኖር የሚያግበሰብሱ ናቸው ይላሉ የአለማችን በገንዘብ ድሃ የሆኑት የዩራጓይ ፕሬዝዳንት ።

እኚህ ፕሬዝዳንት እንደ ሌሎች የሀገራት መሪዎች በተቀናጣ መኖሪያ ቤት አይኖሩም ይልቅኑስ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፌት ይኖሩበት ከነበረ የገጠር መኖሪያ ቤታቸው ከነበረ ነው የሚኖሩት መኪናቸውም ቢሆን ጥይት የማይበሳ ያማረ እና ዘመናዊ ሳይሆን የ1987 ስሪት የሆነውን ቮልስ ቫገን መኪና ናት....

በተጨማሪ እኝህ ፕሬዝዳንት ከፕሬዝዳንትነታቸው ከሚያገኙት ደሞዎዝ 90% ቱን ድሃዎችን ለሚረዱበት የበጎ አድራጎት ይለግሳሉ...

እሳቸው በ አማካኝ እስከ 800 ዶላር በሚደርስ ገቢ ኑሯቸውን ይገፋሉ ይላል አፍሪካ ሊደር ሽፕ መጽሄት ይሄን ያየሁ ጊዜ ሃገሬን ኢትዮጲያን እና መሪዎቿ ሳስብ ቁጭት ተሰማኝ...😌

https://t.me/UsefulExpression ✍️

01/01/2025

..🤔

01/01/2025

ሌላው እንኳን ቢቀር
እውነት እንናገር ..🤔

01/01/2025

እንዴት አደራችሁ መልካም ቀን ..❤🙏

በጃፓን የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ቀዝቀዝ ካለ በኋላ የነብስ አድን ሰራተኞች በአንድ ፍርስራሽ ቤት ሲገቡ የአንዲት ሴትን እሬሳ ተመለከቱ። ሴትየዋ በጉልበቷ  ተንበርክካለች፤ ሰውነቷ ወደ ፊ...
31/12/2024

በጃፓን የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ቀዝቀዝ ካለ በኋላ የነብስ አድን ሰራተኞች በአንድ ፍርስራሽ ቤት ሲገቡ የአንዲት ሴትን እሬሳ ተመለከቱ።

ሴትየዋ በጉልበቷ ተንበርክካለች፤ ሰውነቷ ወደ ፊት ዘንበል ብሎ ነበር፣ ሁለቱ እጆቿ በአንድ ነገር ተደግፎ ነበረ። የፈራረሰው ቤት ጀርባዋ እና ጭንቅላቷ ላይ ወድቋል።

የነፍስ አድን ቡድን መሪው እጁን ወደ ሴቲቱ አካል ለመድረስ በግድግዳው ላይ ባለው ጠባብ ክፍተት ውስጥ እጁን ሴትየዋ ላይ አደረገው።

ሴትየዋ አሁንም በሕይወት ልትኖር እንደምትችል ተስፋ አድርጎ ነበር። ይሁን እንጂ ቀዝቃዛው እና ግትር ሰውነቷ በእርግጠኝነት እንደሞተች ነገረው።

እሱና የተቀሩት የቡድኑ አባላት ከሴትየዋ ቤት ወጥተው ቀጣዩን የፈራረሰውን ሕንፃ ለመፈተሽ ሄዱ።

የቡድን መሪው ግን የሆነ ነገር ተጠራጠረና ወደ ሟቾ ሴት ፍርስራሽ ቤት እንደገና ተመለሰ።

አሁንም ተንበርክኮ ከሬሳው በታች ያለውን ትንሽ ቦታ በእጁ ሲፈትሽ የሆነ ነገር አገኘ።

የነብስ አድን የቡድን መሪው በድንገት እየጮኸ ፣ “ሕፃን! ልጅ አለ! "
አንድ የ3 ወር ሕፃን ልጅ በእናቱ ሬሳ ሥር በአበባማ ብርድ ልብስ ተጠቅልሎ ነበር።

በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ሴትየዋ ልጇን ለማዳን የመጨረሻውን መሥዋዕትነት ከፍላ ነበረ።.

ቤቷ በሚፈርስበት ጊዜ ልጇን ለመጠበቅ ስትል ሰውነቷን ሙሉ ለሙሉ ህፃኑ ልጇ ላይ አድርጋው ነበረ።

የቡድኑ መሪው ህፃኑን ልጅ አንስቶ ሲያየው ህፃኑ በሰላም ተኝቷል።

የሕክምና ቡድን ህፃኑን ልጅ ለመመርመር በፍጥነት ደርሶ ብርድ ልብሱን ሲከፍቱት ብርድ ልብሱ ውስጥ የሞባይል ስልክ ተመለከቱ።

በሞባይል ስክሪኑ ላይ እንዲህ የሚል የጽሑፍ መልእክት አነበቡ።

“ከሞት ከተረፍክ እኔ እንደምወድህ ሁል ግዜም አስታውስ” ይላል።

እንዲህ ነው እናት ለልጇ ያላት ፍቅር !!

https://t.me/UsefulExpression ✍️

31/12/2024

ኑ ጠቃሚውን ውሰዱ ባትወስዱም ኑ TG👇

....🤔
31/12/2024

....🤔

31/12/2024

ለሶስተኛ ግዜ እየተሰማኝ ነው የመሬት መንቀጥቀጥ ..🏃‍♂️😄

✅በልብ ግዘፉ..🤔ሳታስቡት ቀን ይጥላችኋል፣ እንዲሁ ከመቅፅበት ነገሮች ይበላሹባችኋል፣ በአጋጣሚ በሰውም ሆነ በሁኔታዎች ተጎጂ ትሆናላችሁ፣ ብቻችሁን ፊትለፊት መጋፈጥ ላለባችሁ ችግር ትጋለጣላ...
31/12/2024

✅በልብ ግዘፉ..🤔

ሳታስቡት ቀን ይጥላችኋል፣ እንዲሁ ከመቅፅበት ነገሮች ይበላሹባችኋል፣ በአጋጣሚ በሰውም ሆነ በሁኔታዎች ተጎጂ ትሆናላችሁ፣ ብቻችሁን ፊትለፊት መጋፈጥ ላለባችሁ ችግር ትጋለጣላችሁ። አውቃችሁ አልገባችሁበትም ነገር ግን ከዚህ አጣብቂኝ የመውጣት ግዴታ ይኖርባችኋል፣ ፈልጋችሁ አልተፈተናችሁም ነገር ግን ፈተናውን የማለፍ ግዴታ አለባችሁ። ሁሉን ነገር እንደ አመጣጡ የሚመልስ ማንነት በአንዴ አይገነባም፣ ከሁኔታዎች በላይ የሆነ ስብዕና በትንሽ ጊዜ አይመጣም። ልባችሁ ትንሽ ሲሆን በትንሹም በትልቁም ነገር ላይ ለመፍረድ ትቸኩላላችሁ፣ የማስተዋል አቅማችሁ አናሳ ሲሆን ከራሳችሁ በላይ የሰውን ጉድፍና ድክመት መመልከት ትጀምራላችሁ፣ ያልተሰራ ማንነት ሲኖራችሁ ዝቅ ማለትን ትጠየፋላችሁ፣ ንቀትና እብሪት ይነግስባችኋል፣ በሰው ላይ የበላይነታችሁን ለማሳየት ትደክማላችሁ፣ ሁሉም ሰው እንዲወዳችሁና እንዲቀበላችሁ ትጠብቃላችሁ፣ ክፋትን በላቀ ክፋት፣ መጎዳትንም በሌላ ጉዳት ለመመለስና ለመሻር ትሞክራላችሁ። ስታድጉ ሁሉም ነገር ድካም እንደሆነ ይገባችኋል፣ ትንሽ መብሰል ስትጀምሩ ጥሩ ስለሆናችሁ ብቻ የሚወሰድባችሁ ነገር እንደሌለ ትረዳላችሁ።

አዎ! በልብ ግዘፉ፣ በሃሳብ እደጉ፣ ራሳችሁን በማስተዋል አንፁ፣ በትምህርት ከፍ በሉ፣ ለጥበብ ልቦናችሁን ክፈቱ፣ ብስለትን በጊዜ ተለማመዱ። እውቀት ስም ያስጠራል፣ ተፈላጊና ተወዳጅ ያደርጋል፣ ጥበብ ግን ያነግሳል፣ ጥበብ ችግር ፈቺና እንቁ ሰው ያደርጋል። ልባችሁን ለጥበብ ክፈቱ፣ ውስጣችሁን ተነግሮ በማያልቅ መንፈሳዊ እውቀት ሙሉት፣ ሁሉም ሰው የሚመኘውን ፅኑ ማንነት ገንቡ። ማድረግ እየቻላችሁ እናንተን የሚጠቅም ቢሆን አንኳን ሰውን የሚጎዳ ስለሆነ ብቻ የማታደርጉት ነገር ይኑር። ከማንኛውም ሰው ጋር የምትወዳደሩት በሚታየው ስኬት፣ ንብረት ወይም ገንዘብ ሳይሆን፣ በማይታየውና በመልካም ምግባሮች በሚገለጠው ትልቁ ልባችሁ ይሁን። ልባቸው ትልቅ የሆኑ ሰዎች ቅንኖች ናቸው፣ ራሳቸውን የሚያውቁ፣ የሚፈልጉትን የሚያውቁ፣ ህይወትን በተለየ መንገድ የተረዱና እንዴት ክብራቸውን ሳያጡ ከሰው ጋር መኖር እንደሚችሁ የተረዱ ሰዎች ናቸው። ልባችሁን ዘግታችሁ ራሳችሁን አታስጨንቁ፣ ቀለል ብላችሁ ቀላል ህይወት ኑሩ።

አዎ! ጀግናዬ..! በማይሆን መንገድ አዕምሮህን አትወጥረው፣ በአጉል ልክ አልባ የክፋት ሃሳብ ልህን አታስጨንቃት። ትልቅ ሆነህ ትንሽ ስራ አትስራ፣ እያወቅክ በሚያጠፋህ መጥፎ ምግባር አትወጠር። አንተ አሳልፈህ ካልሰጠሀው ያንተን ሰላም የሚቀማህ ሰው የለም፣ አንተ ካልፈቀድክ ማንም ከታላቅነት ማማህ ላይ ሊያወርድህ አይችልም። ለሰው ብዙ አድርገህ ምላሽ የጠበቅበትን ጊዜ አስታውስ፣ አንተ መልካም ሆነ በክፉ ሰዎች የተጎዳህበትን ወቅት አስታውስ፣ ብዙ ሰጥተህ ባዶ እጅህን የቀረበትን ሰዓት አስታውስ። ትልቅ ሰው የሚሰጠው ተቀባዩን ለመጥቀም ሳይሆን ራሱን ለመጥቀም ነው። ካንተ የሆነው ነገር በቅንነት ከሆነ ትልቁ ስጦታህና ሽልማት ውስጣዊ ሃሴት ነው። ልብህ ብሩህ ሆኖ ሳለ የጨለማን ሃሳብ አታስብ፣ ተስፋ እያለህ የተስፋ ቢስ ሰው ተግባርን አትፈፅም። ለሰው ለመድረስ ከመድከምህ በፊት አስቀድመህ ራስህን ከመጥፎ ትርክቶችና ኩናኔዎች አድን። ለራስህ መሆን ሰትችል ለሁሉ መድረስ ትችላለህ፣ ራስህን ሰትጠቅም የምትፈልገውን ሰው መጥቀም ትችላለህ። ያንተ እያረረ የሰው በማማሰል አትጠመድ። ምንምያህል ደግና መልካም ሰው ብትሆን ራስን ከማዳን የሚቀድም ሌላ በጎ ስራ እንደሌለህ አስታውስ።

https://t.me/UsefulExpression ✍️

አሜሪካዊው ቢሊዬነር ስቲቭ ጆብስ በህይወቱ መጨረሻ ሰዓት ላይ ያስተላለፈው አስደናቂ መልዕክት ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።(ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን ህ...
31/12/2024

አሜሪካዊው ቢሊዬነር ስቲቭ ጆብስ በህይወቱ መጨረሻ ሰዓት ላይ ያስተላለፈው አስደናቂ መልዕክት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
(ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን ህይወቱ ያለፈው በካንሰር በሽታ ነው)) … በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻ ከፍታ ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁ፣ ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት አልቻልኩም። በልፋቴ ካከማቸሁት ሃብት ያገኘሁት ደስታ እዚህ ግባ የማይባል ነው፣ አሁን፣በህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት አካባቢ፣አልጋ ላይ ሆኜ ያሳለፍኩትን ነገር ሁሉ ወደሗላ ሳስበው ፣ እኮራበት የነበረው ሀብቴና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም አልባ እንደሆነ ተረድቻለሁ፥
✔አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባልህ ልትቀጥረው ትችላለህ፣ እየተሰቃየህበት ያለውን ህመም እንዲሸከምልህ ግን ልትቀጥረው አትችልም፥
✔ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ ፣ዳግም ሊገኙም ይችላሉ፥ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ ነገር ግን አለ… እርሱም #ህይወትህ ነው፥
✔አንድ ሰው የቀዶ ጥገና ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው የመጽሐፉ ርዕስ "ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር" የሚል ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም፣
✔በየትኛውም የህይወት ከፍታ ላይ ብንሆን የህይወታችን መጋረጃ የሚዘጋበትን ቅጽበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ አይቀርም፣
★ለቤተሰብህ፣ለትዳር አጋርህ እና ለጏደኞችህ የፍቅርን ውርስ አስቀምጥላቸው፣
★ራስህን ተንከባከብ ፣ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ይኑርህ
👉እያደግን ስንሄድና የህይወት ትርጉሙ ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት ፣ ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል
👉በኪሳችን ውድ ቦርሳም ያዝን ርካሽ ቦርሳ ፣በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም ፣
👉የኣንድ ሚሊዮን ብር መኪናም ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና ፣የመንገዱ ርዝመት አይቀየርም፣ አቅጣጫውም ያው አንድ ነው፥የምንደርሰውም ያው እዚያው ቦታ ነው ፣
👉ውድ መጠጥም ጠጣን ርካሽ መጠጥ፣ ስካሩና አድሮ የሚያመጣው ራስ ምታት ለውጥ የለውም፣
👉ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ ቤት፣ ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው፣ …የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ ይገባሃል
👉አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ ፣አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል ቁልቁል ትወርዳለህ፣
✋እውነተኛው ደስታ የሚገኘው ከቤተሰብህ፣ከጓደኞችህ፣ ከዘመዶችህ ጋር በሚኖርህ ውብ ጊዜኣት ብቻ ነው፥፥ ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ ፣በምትጫወተው ጨዋታ፣ በምትዘምረው መዝሙር፣ በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ ፣ 5 ሊካዱ የማይችሉ የህይወት እውነታዎች አሉ …
☝ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ አታስተምራቸው፥፥ ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አስተምራቸው፥፥ ሲያድጉ የነገሮች ዋጋ ሳይሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል፣
☝ምግብህን እንደ መድሃኒት ውሰድ ካልሆነ መድሃኒት እንደምግብ ትወስዳልህ ፣
☝የሚወድህ ሰው በቀላሉ አይለይህም፣ ከኣንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት በማይችልባት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል፣
☝"ሰው ሆኖ በመፈጠር"ና "ሰው በመሆን" መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፥፥ ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው፥
☝ስትወለድ ውድ ነበርክ፣ ስትሞትም ውድ ትሆናለህ፣ በመካከል ያለውን ማስተካከል ያንተ ፋንታ ነው፣
☝በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ሩቅ ለመድረስ ከፈለግህ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ ፣
👉በዓለም ላይ ያሉ ስድስቱ ፈዋሽ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው…
★የፀሃይ ብርሃን
★እረፍት
★ስፖርት
★ጥሩ ምግብ
★በራስ መተማመን እና
★ጓደኛ እነዚህን አጥብቀህ ያዝ
ደስተኛ ህይወትን አጣጥም!! …

https://t.me/UsefulExpression✍️

31/12/2024

እቅድ ዶሮ
ተግባር ሽሮ
አትሁኑ ..😄

ዛሬ ለሊት 6 ሰዓት ላይ "Happy New Year"🙄 ለማለት የተዘጋጃችሁ አስመሳዮች ግን ብታድቡ መልካም ነው...😄
31/12/2024

ዛሬ ለሊት 6 ሰዓት ላይ "Happy New Year"🙄 ለማለት የተዘጋጃችሁ አስመሳዮች ግን ብታድቡ መልካም ነው...😄

ልጄ ሆይ፡1.ያባትህን ምክር ስማ፤የክፉ ቀን ስንቅ ይሆንሃልና!2.ለእናትህ ደግ ታዛዥ ሁን፤የእናት ምርቃት ለምድራዊ በረከት ብቻ ሳይሆን የነፍስ እንጀራም ይሆናልና!3.በጣም አድማጭ፤መጣኝ ተና...
31/12/2024

ልጄ ሆይ፡
1.ያባትህን ምክር ስማ፤የክፉ ቀን ስንቅ ይሆንሃልና!
2.ለእናትህ ደግ ታዛዥ ሁን፤የእናት ምርቃት ለምድራዊ በረከት ብቻ ሳይሆን የነፍስ እንጀራም ይሆናልና!
3.በጣም አድማጭ፤መጣኝ ተናጋሪ ሁን!
4.ስክነት የሕይወት መንገድህን የቀና ያደርግልሃልና፤የሰከነ ማንነት ይኑርህ!
5.ፍትሓዊነት የሕይወትህ መርህ ይሁን፤ለህሊናህ ትራስ፤ለልቡናህ ድጋፍ፤ለነፍስህ ዋስትና ነውና!

https://t.me/UsefulExpression ✍️

30/12/2024

ወደ ኖርዌይ ለልምድ ልውውጥ የሄዱ የሁለት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ወደ ሀገር ሳይመለሱ ቀሩ..😄 ምን አለ ሁላችሁም መንግስትን ጨምሮ በትሄዱልን ...🚶‍♂️

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጠቃሚ ንግግሮች/Useful expressions posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ጠቃሚ ንግግሮች/Useful expressions:

Videos

Share