#ምፓፔ_ማንነቱን_ፈልጎ_የሚያገኝበት_ቦታ
👌 ይህን ውብ የሆነ ቪዲዮ ተመልከቱት በሁለቱ ሁነቶች መካከል 15 አመታት ልዩነት አለ። ግን አርአያው አድርጎ ሲከተለው ከነበረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር በተመሳሳይ ቦታ ፣ ለተመሳሳይ አላማ ፣ ተመሳሳይ ቃላት ፣ ተመሳሳይ ድርጊት በአንድነት ተጋርቷል።
📌 አው ይህ ቪዲዮ ሪያል ማድሪድ አዲሱን ኮከብ ኪልያን ምፓፔን በይፋ በግዙፉ ስታድየም ያስተዋወቀበትን ሁነት ያሳያል
🔮 ፈረንሳዊው ኮከብ ባሎንዶርን ለማሸነፍ ከየትኛውም ክለብ በላይ ቅርብ ወደ ሆነው ቦታ አምርቷል ቀጣዩ ዘመንም ሪያል ማድሪድ እና ምፓፔ በእግር ኳሱ አለም ሲያሸበርቁ ካየን አይገርምም።
እግር ኳስ/The Beautiful Game
#ዋንጫ_ያጣው_ድንቁ_አርሰናል
✅ በቶፕ 6 ቡድኖች ያልተሸነፈ ብቸኛ ቡድን
✅ ቶፕ 6 ቡድኖችን ሁሉንም ያሸነፈ ብቸኛ ቡድን
✅ ብዙ ጎል በማስቆጠር 2ኛው ቡድን
✅ አነስተኛ ጎል የተቆጠረበት ቡድን
✅ ብዙ ጨዋታ ላይ መረቡን ከጎል የታደገ ቡድን
✅ አነስተኛ የጎል ሙከራ ያስተናገደ ቡድን
✅ በቆመ ኳስ ብዙ ጎል ያስቆጠረ ቡድን
✅ በሁለት ነጥብ ብቻ አንሶ እስከ መጨረሻው ቀን ለዋንጫ የተፋለመ ድንቅ ቡድን በማየታቸው ደጋፊዎች ዛሬ ኢምሬትስ ላይ እንዲህ ነበር ለቡድናቸው ታላቅ ፍቅር ያሳዩት
#በአርሰናል_የከነፉት_አነጋጋሪ_አዛውንት
🎤 ከአርሰናል በጣም የሚወዱት ተጫዋች ማን ነው?
🗣 ገብረ እየሱስ
ማነው ቺቺንኮ.... ያናድደኛል
ሙሉውን ዩትዩብ ላይ በ ሸማ ቲቪ ታገኙታላችሁ
👏 የአርሰናሉ ተከላካይ ቲምበር ከረጅም ግዜ የጉልበት ጉዳት በኋላ ትላንት ምሽት ከአርሰናል 21 አመት በታች ቡድን ውስጥ ተሰልፎ ጎል ለማስቆጠር 8 ደቂቃ ብቻ ፈጅቶበታል። ጎሉን ተመልከቱ
✅ በአንድ የአፍሪካ ዋንጫ 4 ተከታታይ ጨዋታ ላይ መረቡን ከግብ በመታደግ የመጀመሪያው ግብ ጠባቂ
✅ በአፍሪካ ዋንጫው ታሪክ በአንድ ጨዋታ 4 የመለያ ምት በማዳን የመጀመሪያው ግብ ጠባቂ
✅ እግር ኳስ ተመልካቹ ፣ እና የስፖርቱ ሚዲያ ሁሉ ዊልያም ስላዳናቸው 4 ፔናሊቲዎች አድናቆቱን እየቸረው ይገኛል። የመለሳቸው ኳሶች ይህን ይመስላሉ 👇
⏰ ገና 4ኛ ደቂቃ ላይ ሴኔጋሎች አዘጋጇ ኮትዲቯር ላይ ያስቆጠሩትን ጎል ተመልከቱ
👌 ማኔ ጥራት ያለው ኳስ ከመስመር ላይ አሻገረ
👌 ዲያሎ በደረቱ አብርዶ በግራ እግሩ አስቆጠረ
🐘🇨🇮 ዝሆኖቹ 0-1 የቴራንጋ አንበሶች 🇸🇳🦁
🇪🇹 ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመሪያዎቹ 22 ደቂቃ ውስጥ በተቆጠሩበት 3 ጎሎች በድሬዳዋ ከተማ የተሸነፈበትን ጎሎች ይመልከቱ
🙆♂ በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ጎሎች ልክ አልነበሩም በግብ ጠባቂ ወይስ በሜዳው እዩና ፍረዱ
❌ ለቅዱስ ጉዮርጊው በውድድር ዘመኑ 3ኛ ሽንፈት
✅ ለድሬዳዋ ከተማ በውድድር ዘመኑ 4ኛ ድል
የቪዲዮ ክሬዲት: ዲኤስቲቪ
42 ሰከንድ የሚፈጀውን ቪዲዮ እዩት
🙆♂ ከጨዋታው በፊት 8 ቢልየን ሕዝብ ባለባት ፕላኔት ውስጥ ኮትዲቯር 4ለ0 ትሸነፋለች ብሎ የሚያስብ 1 ፍጥር እንኳን አይኖርም ምክንያቱም ለዋንጫው ከተገመቱ 3ቱ ውስጥ አለቻ ፣ በዛ ላይ አዘጋጅ ሀገርም ነቻ ፣ በዛ ላይ ተጋጣሚዋን በ39 ደረጃዎች ትበልጣለቻ።
ግን ሆኗል ሚደያዎች በመገረም ዜናውን ተቀባበሉት ፣
ድሮግባ ሀገሩ ላይ እየሆነ ያለውን በምን ስሜት እንደሚገልፀው ግራ ገባው ፣
ደጋፊዎች በአውሮፓ ስታድየሞች ታዋቂ የሆኑት እና የሚየተማመኑባቸው ኮከቦች ሀገራቸውን በሚገባ አላገለገሉም ብለው በማሰብ ከስታድየሙ ሲወጡ ውጪ ቆሞ ያገኙት የቡድኑ ባስ ላይ ንዴታቸውን ተወጡ
ግን እንደዚህ ልጅ የተጎዳ የለም ገና ጨዋታው ሳያልቅ ኢኳቶሪያል ጊኒዎች ደጋግመው የኮትዲቯር መረብ ውስጥ ኳሳን ሲከቱት ማመን አልቻለም ግማሽ ኪሎ የማትሞላው ኳስ አዳላች ፣ ቅስሙን ሰባበረችው ፣ ሀገሩ በገዛ ሜዳዋ አፈረች። የሚያየውን ማመን ያልቻለው ደጋፊ ሜዳውን ለቅሶ ቤት አደረገው ። እንዳንድ የእግር ኳስ ስሜትን ልትፅፈው አትችልም
42 ሰከንድ የሚፈጀውን ቪዲዮ እዩት
🎤 ታሪክን ገነነ መኩሪያ ይተርካት (ማን ይተካው ይሆን? )
📌 ከስራው በላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን ስላስቀደመው ፣ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የካፍ ኢንስትራክተር ፣ የሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ፣ 16 አመት ለጊርጊስ ሲጫወት ደሞዝ ተከፍሎት ስለማያውቀው ኢትዮጵያዊው የእግር ኳስ ባለውለታ 👉 መንግስቱ ወርቁ ጥፍጥ ባለው የገነነ መኩሪያ አቀራረብ በአሻም ቲቪ እንዲህ ተርኮት ነበር።
🙏 ለቤተሰቦቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንመኛለን
" በነገራችን ላይ ተጫዋቾቼ ሞሮኮን ብቻ አይደለም የገጠሙት ብዙ ፈተናዎችን ነው በዚህ ጨዋታ የገጠሙት "
" በዚህ ውጣ ውረድ ውስጥ ይህን ውጤት በማምጣታቸው ተጫዋቾቼን ማመስገን እፈልጋለሁ "
" ተጫዋቾቼ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገው ነበረ "
" እኔ ብቻዬን የምሰራው ነገር አይደለም ተጫዋቾቼ ሊመሰገኑ እና ሊከበሩ ይገባል "
⭕ የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ትላንት የሞሮኮ አቻውን 1ለ0 ቢያሸንፍም ለአለም ዋንጫው ሳያልፉ ቀርተዋል። ለመሆኑ አሠልጣኝ ፍሬው ኃ/ገብርኤል ከጨዋታው በኃላ ከ ጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምን መልስ ሰጠ ?
#እስኪ_ዘና_እንበል
▶ ቪዲዮውን በድጋሚ ሳያይ አንድም ሰው አይመልስም
🥅 ትንሿ ጎል ላይ ለማግባት 12 ኳሶች ተመቱ ግን ከ 12ቱ ታዳጊዎች ውስጥ አንዱ ብቻ ጎል ሆኗል።
❓ የማን ነው ጎል የሆነው? በደንብ እዩት 👁
🇬🇭 የግብፅ ተከላካዮች ሊያቆሙት አልቻሉም ፣ ግብ ጠባቂውም ኳሱን ከማየት ውጪ የሚያድንበት ዕድል አልሰጠውም ሞሐመድ ቁዱስ ግብፅ ላይ ከቦክስ ውጪ ያስቆጠረውን ድንቅ ጎል ተመልከቱ።
የዌስትሀሙ ኮከብ ከጉዳት መልስ ሀገሩ ጋናን በግሩም ጎሉ ተቀላቅሏል