04/11/2024
#✍️በዝግታ ይነበብ
#ከሚከተሉት ምልክቶች አንዱ ከተገኘ እርዳታ ይጠይቁ፡
👉አሁን ያለኝ ስሜት ህይወቴን በተለመደው መንገድ እንዳላከናውን ከለከለኝ።
👉የምኖረውን ወይም አብሬያቸው የምሠራውን ሰዎች አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረኩ እንደሆነ ይሰማኛል።
👉ስሜቴ ለብዙ ሳምንታት እየተለወጠ ነው።
👉ራሴን የመጉዳት ወይም ሌሎችን የመጉዳት ሃሳቦች አሉኝ።
👉በሥራ ቦታ፣ ወይም የቤት ውስጥ ሥራ በምሠራበት ጊዜ፣ ከወትሮው የበለጠ ድካም ይሰማኛል፣ ወይም ያልተለመዱ ስህተቶችን አደርጋለሁ።
👉ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሴን ማግለል እመርጣለሁ
እባክዎ ሌሎችም እዚህ ያልተገለፁ ስለሚኖሩ ኮሜንት ላይ ያስቀምጡልን
ዳዊት አሞኝ
የስነ ልቦና እና ማህበረሰብ ባለሙያ