አማሮች

አማሮች struggle for human being freedom ትሰግሉ በድል እስኪደምቅ አመርረን እንታገላለን።

11/01/2025

ድል አማሮች

08/01/2025

"የልደት በዓል በሰላም ተጠናቀቀ!"
የአማራ ፋኖ በወሎ ላስታ አሳመነዉ ኮር በተቆጣጠራቸዉ ሁሉም ቀጠናዎች የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም ተጠናቅቋል።

በተለይ ደግሞ በዳግማዊት ኢየሩሳሌም የትናንቷ ሮሃ(አዳፋ) የዛሬዋ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ እና ዙሪያዉ ላስታ (የዛጔዬ ስርዎ መንግስት ማዕከል) በየአመቱ የሚከበረው የልደት በዓል የላስታ አሳመነዉ ኮር 7ቱ ክፍለጦሮች ፋኖ የአሳመነዉ ሃይል ሰራዊቱ እና ታላቁ የአማራ ህዝብ በጋራ አክብረዋል። ምንም እንኳን አገዛዙ የሃይማኖታዊ በዓሉን ድባብ ለመቀየር ቢሞክርም እኛ ግን ቅዱሱ፣ ካህኑ እና ንጉሱ ላሊበላ ስንል፣ ከየሀገሩና አህጉሩ ለመጡ ምዕመናን ስንል፣ ለቅርሱ ደህንነት ስንል በዓሉ የተከበረበት ከላሊበላ ከተማ 3 ኪ.ሜ ርቀት ሆነን በዓሉን ከማዶ እየታደምን አሳልፈነዋል።

ደጉ አማራዉ ህዝባችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለሰራዊቱ የበዓል ስጦታዎችን ያበረከተ ሲሆን ግዙፉ ኮራችንም በተቻለ መጠን ለሁሉም ክፍለጦሮች የበዓል ድጎማ በማድረግ ለአማራ ህልዉና ነፃ ታጋይ (የገንዘብ ደሞዝ የሌለዉ) ለሆነው ሰራዊቱ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ጥረት ተደርጓል።

በዓሉም በሰላም ተጠናቅቋል። ስለሆነም በዱር በገደሉ ለአሳመነዉነት ርዕዮት፣ ለአማራ ህዝብ ነፃነት፣ ለፍትህና ለእዉነት እየተጋላችሁ ያላችሁ መላዉ የአሳመነዉ ኮር የክፍለጦሮች አባላት እና ሰራዊቱ እንዲሁም ህዝባችን በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁት ሁለንተናዊ ሥራ በእጅጉ እናመሰግናለን።

"አሳመነዉነት ርዕዮታችን፣ ፋኖነት ክንዳችን"
ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለፋኖ

ታህሳስ 29/2017 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ በወሎ ላስታ አሳመነዉ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል

ነብስህ በሰላም ትረፍ ጓድ!"ቀኝ አዝማች ይታገሱ አዳሙ እንደ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ "በታሪክ ምስክርነት ፣በዓለም የጠበብቶች ብራና በአኩሪ ገድል የሚታወቀው የአፄ ቴዎድሮስ የእጀን አልሰጥም ...
08/01/2025

ነብስህ በሰላም ትረፍ ጓድ!
"ቀኝ አዝማች ይታገሱ አዳሙ እንደ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ "

በታሪክ ምስክርነት ፣በዓለም የጠበብቶች ብራና በአኩሪ ገድል የሚታወቀው የአፄ ቴዎድሮስ የእጀን አልሰጥም ዘላለማዊ ክብር በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ዋና አዛዥ በቀኝ አዝማች ይታገሱ አዳሙ በድጋሜ በሸዋ ምድር መርሀቤቴ አውራጃ ተደገመ። አማሮች

07/01/2025

እንኳ ለገና በዓል አደርሰን። መልካም በዓል።

ክርስቶስ የሰውን ልጆች ሁሉ ለማዳን እደተወለደ ለእኛም ለአማራዎች የፋኖ ትግል ተወልዶልናል !!ለተከበርከው ታላቁ የአማራ ህዝብ ፣በውጪም በሀገር ቤትም ያላችሁ የክርስትና እምነት ተከታዮች እ...
06/01/2025

ክርስቶስ የሰውን ልጆች ሁሉ ለማዳን እደተወለደ ለእኛም ለአማራዎች የፋኖ ትግል ተወልዶልናል !!

ለተከበርከው ታላቁ የአማራ ህዝብ ፣በውጪም በሀገር ቤትም ያላችሁ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2017 ዓ.ም ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በፅናት አደረሳችሁ አደረሰን ።

እንደሚታወቀው አሁን ያለንበት ወቅት የአማራ ህዝብ በፋሽስት አምባገነኖች የጥፋት ጦርነት ታውጆበት ፤በዘመኑ አሉ በተባሉ መሳሪያዎች ከምድር እንዲጠፋ በብዙ ተዋናዮች ጅምላ ፍጅት እየተፈፀመበት ይገኛል። ሆኖም እደሚታወቀው ቆራጥ የአማራ ልጆች እንደህዝብ የተደቀነብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ክርስቶስ ራሱ በፈጠራት አለም ውስጥ ለጠፋው ለሰው ልጅ በከብቶች በረት እደተወለደ ሁሉ ፤የአማራ ህዝብ በፈጠራት ሀገር ውስጥ ተሳዳጅና ባይተዋር በመሆኑ ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን የቁርጥ ቀን ልጆች ጫካ ከገቡ ሁለት አመታት ተቆጥረዋል ።

በታሪክ እንዳየነው ክርስቶስ ከውልደት እስከ ስቅለቱ ባሳለፋቸው ዘመናት ውስጥ የተበላሸ ስርዓትን ለመለወጥ ምን ያህል ፈታኝ ዋጋ እደሚያስከፍል ከቅዱስ መፀሀፍ አንብበናል ።

እኛም ይህን በዓል ስናከብር አባቶቻችን የሰጡንን ጠቃሚ እሴቶችን በመጠበቅ ጎጂ የሆኑ የኛን እሴቶች ሊያጠፉ የሚችሉ ባዕድ የሆኑ ልማዶችን በማስወገድ የራሳችንን እምነት (faith) ማስቀጠልና መጠበቅ አማራዊ የትግል ግዴታችን ነው ።

ለዚህም በዓሉን ስናከብር ሊተገበሩ የሚገባቸውን መመሪያዎች እደሚከተለው እገልፃለን።

፩.በተቆጣጠርናቸው አካባቢዎች ህዝብና በዓሉን ሊረብሹ የሚችሉ የደስታ ተኩሶች ፣ ከልክ ያለፉ የአልኮል መጠቀምና ማወክ ክልክል ናቸው።

፪.በቅርብ ልምድ የመጡ የገና ዛፍ ፣የገና አባት የሚሉ ከአማራ ሕዝብ ማህበራዊ እሴት ዝምድና የሌላቸውን ባዕድ ባህሎች ከማስፋፋት መቆጠብ።

፫.ፋኖ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ሁሉ ያላችሁ የጎበዝ አለቆች ከህዝባችን ጋር ተባብራችሁ የአካባቢያችሁን ፀጥታውን እድታስከብሩ !!

፬.በዓሉን ስናከብር በየአካባቢው የሚገኙ አቅመደካሞችን በመጠየቅና በመረዳዳት እድናሳልፍ!!

፭.ሁሉም ክፍለጦሮች በማዕከላት ያሉትን የተማረኩ የጠላት ሰራዊት አባላት አቅም በፈቀደ መጠን በዓሉን ደስተኛ ሆነው በጋራ እንዲያሳልፉ ያሳስባል !!

፮. እንዲሁም በህልውና ትግሉ ውስጥ ሲታገሉ የቆሰሉና የተሰው ፋኖ አባሎችና ቤተሰቦችን በመጠየቅና በማፅናናት እንድታሳልፉ አማራዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ ሲል የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መልዕክቱን ያስተላልፋል!!

ድል ለአማራ ህዝብ !!
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት !!

አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ !!

ታህሳስ 2017 ዓ.ም

ሸዋ ፣አማራ ፣ኢትዮጵያ አማሮች የሸዋ ፖለቲካ Abebe mulatu/አበበ ሙላቱ/

"በርካታ የአገዛዙ ሠራዊት አባላት የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝን ተቀላቀሉ! ታሕሳስ 26/2017 ዓ.ምየአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በሸዋ ግንባር በበርካታ ቀጠናዎች በተደረገ አ...
04/01/2025

"በርካታ የአገዛዙ ሠራዊት አባላት የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝን ተቀላቀሉ!

ታሕሳስ 26/2017 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ

በሸዋ ግንባር በበርካታ ቀጠናዎች በተደረገ አውደ ውጊያ በርካታ የአገዛዙ ሠራዊት ሲደመሰስ ፤ አገዛዙን የተጠየፉና በአማራ ፋኖ ሀቀኛ ትግል ያመኑ ስርዓቱን ከድተው የወገን ጦርን ተቀላቅለዋል።

በገጠመው ግንባር በሙሉ ሽንፈት የሚደርስበት የብልፅግና አገዛዝ ፤በቂ ወታደራዊ ስልጠና ያልወሰዱ ፣ እድሜያቸው ለውትድርና ግዳጅ ያልረሱ ወጣቶችን ከተለያዩ ከተሞች በማፈስ በግዳጅ አሰማርቶ በየሜዳውና በየጫካው እንዲወድቁ እያደረጋቸው ይገኛል። ከሰሞኑ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሁሉም ክፍለ ጦሮች በጠላት ሠራዊት ላይ በወሰዱት የተቀናጀ እርምጃም ለቁጥር የሚታክት የብልፅግና ሠራዊት ተደምስሷል።

በዚህ ከፍተኛ ድል በተመዘገገበበት አውደ ውጊያ ከመደምሰስ የተረፉት ምርኮ ሲደረጉ ፤ የተቀሩት ደግሞ ከሰላድንጋይ ከተማ ወደ ሳሲት በመሄድ !! እጃቸውን ለወገን ጦር አስቻለው ደሴ ክፍለጦር በሰላማዊ መንገድ እጅ በመስጠት :-

👉 2- ስናይፐር
👉 11-ጥቁር ክላሽንኮቭ እና
👉 4 -ዘመናዊ ምሽግ መደርመሻ ኢነርጋ ይዘው

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተቀላቀሉት የሠራዊት አባላትንም የምርኮኞች አያያዝና ጥበቃ ክፍል ተረክቦ በቂ እንክብካቤ እያደረገላቸው ይገኛል።

በሸዋ 9ኛ ቀኑን የያዘው አውደ ውጊያ ዛሬም በተለያዩ ግንባሮች የቀጠለ ሲሆን ከፍተኛ ተጋድሎ ትንቅንቅ በማድረግ ላይ ይገኛል። "

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል አማሮአማሮች

አርበኛ ፋኖ ደሳለው በክብር ተሰውቷል። ዘላለማዊ ክብር ለተሰው ጓዶች። ድል ለአማሮች አማሮች
02/01/2025

አርበኛ ፋኖ ደሳለው በክብር ተሰውቷል። ዘላለማዊ ክብር ለተሰው ጓዶች። ድል ለአማሮች አማሮች

ፋኖ አዲሱ ብርሃን ከአማራ ዘላለማዊ ጥላቶች ላይ የሳት ክንዱን አሳርፎ ተሰውቷል። አማሮችየአማራ ፋኖ በባህርዳር ንስር ሻለቃ እና በደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ ጣና ገላውዲዮስ ክፍለ ጦር ለግማሽ...
27/12/2024

ፋኖ አዲሱ ብርሃን ከአማራ ዘላለማዊ ጥላቶች ላይ የሳት ክንዱን አሳርፎ ተሰውቷል። አማሮች
የአማራ ፋኖ በባህርዳር ንስር ሻለቃ እና በደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ ጣና ገላውዲዮስ ክፍለ ጦር ለግማሽ ቀን ባደረጉት ኦፕሬሽን የአራዊት ሰራዊቱን የጁላ ጦር ሙትና ቁስለኛ አድርገው ሸኝተውታል። በዚህ ጦርነትን ጥሎ መውደቅ አይቀሬ ነውና የንስር ሻለቃ ፊት አውራሪ የነበረው ጀግናው ወንድማችን አርበኛ አዲሱ ብርሃን የጁላን ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ እሱም እንደ አባቶቹ በክብር ተሰውቷል። ዘላለማዊ ክብር ለፋኖ ሰማዕታት። ታህሣሥ 18/2017 ዓ.ም

አማሮች
21/12/2024

አማሮች

የወንዶቹ ቁናየሚጠሉት የሚመስሉ በውስጣቸው ያከብሩታልበአካሄድ የተለዩት አብረውት ለመጓዝ ይጓጓሉበሀሳብ የማይስማሙት ከርሱ መለየት አይፈልጉምየሚሰድቡት ያዝኑለታልየሚንቁት የሚመስሉት በውስጣቸው...
19/12/2024

የወንዶቹ ቁና

የሚጠሉት የሚመስሉ በውስጣቸው ያከብሩታል

በአካሄድ የተለዩት አብረውት ለመጓዝ ይጓጓሉ

በሀሳብ የማይስማሙት ከርሱ መለየት
አይፈልጉም

የሚሰድቡት ያዝኑለታል

የሚንቁት የሚመስሉት በውስጣቸው ያደንቁታል

የአርበኛ መከታው ማሞ ቀኝ እጅ የቀድሞው የሑርሶ ፓራኮማንዶ ጦር ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ፤  የወታደራዊ የውጊያ ምህንድስና መምህር ፤  የብላቴ ኮማንዶና ልዩ ኃይሎች አዛዥ ፤   የአሁኑ የ...
18/12/2024

የአርበኛ መከታው ማሞ ቀኝ እጅ የቀድሞው የሑርሶ ፓራኮማንዶ ጦር ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ፤ የወታደራዊ የውጊያ ምህንድስና መምህር ፤ የብላቴ ኮማንዶና ልዩ ኃይሎች አዛዥ ፤ የአሁኑ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ምክትል አዛዥና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ምክትል ወታደራዊ አዛዥ የጦር ጠበብቱ ኮሎኔል ማንነገረው መለሰ !!

ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ

ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ፋኖ አዲስ አበባ ። በአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ስር አዲስ አበባ /መናገሻ አንባ ተወርዋሪ ክፋለ ጦር ተቋቁሟል። በቅርቡ የተወርዋሪ ክፋለ ጦሩ መሪና  ይፋ ይደረጋ...
16/12/2024

ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ፋኖ አዲስ አበባ ።

በአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ስር አዲስ አበባ /መናገሻ አንባ ተወርዋሪ ክፋለ ጦር ተቋቁሟል። በቅርቡ የተወርዋሪ ክፋለ ጦሩ መሪና ይፋ ይደረጋል እንዲሁም የዘመቻ መረጃዎች ይቀርባሉ።

ድል ለአማራ ህዝብ !!
ድል ለአማራ ፋኖ !!

ፋኖ ቸርነት አሰፋ በክብር ተሰዋ።ይህ እንቁ  የአማራ ታጋይ እንደሁል ጊዜውም ጦሩን ይዞ ከፊት ለፊት እየመራ ህዳር 27/2017 ዓ/ም  በመንዝ ማማ ሞላሌ ከተማን ለማስለቀቅ በተደረገው ጦርነ...
14/12/2024

ፋኖ ቸርነት አሰፋ በክብር ተሰዋ።
ይህ እንቁ የአማራ ታጋይ እንደሁል ጊዜውም ጦሩን ይዞ ከፊት ለፊት እየመራ ህዳር 27/2017 ዓ/ም በመንዝ ማማ ሞላሌ ከተማን ለማስለቀቅ በተደረገው ጦርነት በርካታ ምሽጎችን ሰብሮ፣ የታጠቀውን ተተኳሽና ቦንብ ጨርሶ የጓደኞቹን ቦንብ ሳይቀር ተቀብሎ በመወርወር ጠላትን በምሽጉ እንድቀበር አድርጓል። የጣላትን አንድ ኮሎኔል አንገቱን ይዞ ረሽኖታል። አንድ ድሽቃና ላንድ ክሩዘር መኪና እንድሁም በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያና ተተኳሽ ከማረከ በኋላ ከጓደኛው ቦንብ ተቀብሎ ጠላት ምሽግ ላይ በመወርወር ለቆመለት አላማ ለአንድያ ነብሱ ሳይሰስት ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በክብር መተኪያ የሌላትን ነብሱን ሰጥቶ አልፏል። ጀግና ሁሌም ስራው ህያው ነውና ወንድማችን ቸርነት አሰፋ እንደነ አበበ አረጋይ፣ እነደነ አበበ ሸንቁጥ፣ እንደነ ፈለቀ እጅጋየሁ ወዘተ ሲታወስ ይኖራል።

ክብር ለትግሉ ሰማዕታት አርበኞች!!

የመብረቁ ተፈራ ብርጌድ ፈርጦች ሻለቃ ተፈራ እና ጓዶቹ የተሰውበት 1ኛ ዓመት ታስቦ ውሏል።እንደ ዛሬው ሺህወችን ሳናስከትል የስርዓቱ ዘቦች ላይ ምላጭ የሳቡት የሞጣወቹ ወንድሞቻችን እነ መዝገ...
02/12/2024

የመብረቁ ተፈራ ብርጌድ ፈርጦች ሻለቃ ተፈራ እና ጓዶቹ የተሰውበት 1ኛ ዓመት ታስቦ ውሏል።

እንደ ዛሬው ሺህወችን ሳናስከትል የስርዓቱ ዘቦች ላይ ምላጭ የሳቡት የሞጣወቹ ወንድሞቻችን እነ መዝገቡ ዋጋ የከፈሉለት የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በትክክለኛ ሐዲዱ ላይ ነው።
© አስረስ ማረ

በተሳቀ ሳቅ ላይዳግመኛ ለመሣቅለካ አለው ወዳጄየሳቅም አሳሳቅ!!!ዘላለማዊ ክብር ለተሰው የፋኖ ጓዶች። ድል ለአማራ።
15/11/2024

በተሳቀ ሳቅ ላይ
ዳግመኛ ለመሣቅ
ለካ አለው ወዳጄ
የሳቅም አሳሳቅ!!!

ዘላለማዊ ክብር ለተሰው የፋኖ ጓዶች። ድል ለአማራ።

የከብር - ሰማዕት ፋኖ ስንታየሁ ማሞ/ራምቦ 1ኛ አመት መታሰቢያ በአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከፍተኛ አመራሮችና በትግል ጓዶቹ ታስቦ ውሏል። የሸዋው የጉዞ አድዋ ድምቀት ፋኖ ስንታየሁ...
15/11/2024

የከብር - ሰማዕት ፋኖ ስንታየሁ ማሞ/ራምቦ 1ኛ አመት መታሰቢያ በአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከፍተኛ አመራሮችና በትግል ጓዶቹ ታስቦ ውሏል።

የሸዋው የጉዞ አድዋ ድምቀት ፋኖ ስንታየሁ ማሞ(ራምቦ) በቀደመው የሰሜኑ ጦርነት ወቅት ቁጭት ከወለደውና ከአማራ ህዝብ የህልውና ደጀን ከሆነው ከቀድሞው ይፋት ፋኖ ጋር በመሰለፍ አኩሪ ገድል ፈጽሟል።

የደፈጣ እስፔሻሊስቱ የውጊያ መሪው ሻለቃ ስንታየሁ ማሞ (ራምቦ) ከቀድሞዎቹ ይፋት ፋኖ እስከ ምስራቅ አማራ ፋኖ መስራችና አመራር የነበረ እንዲሁም በሰሜኑ ጦርነት ውጊያ ታላላቅ ገድል በመፈፀም እና ጥቂቶች ብቻ ሊፈፅሙት የሚችሉትን በብሬን ገድሎ ብሬን ከጠላት ላይ የገፈፈ (የማረከ) ጀብደኛ ተዋጊ ነው ።

ከሰሜኑ ጦርነት ማግስት ከወሎ/ቤተአማራ ወደ ትውልድ ቀዬው ሸዋሮቢት በመመለስ ከሸዋ አርበኞችና ፋኖ አባላት ጋር ተባብሮ የኦነግ ወረራን በመመከት ብዙ ጀብድ የፈፀመ እንዲሁም ወራሪው የብልፅግና ሰራዊት ወደ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ቀጠና ጦሩን ሲያዘምት ከጣርማበር እስከ ሸዋሮቢት ትልልቅ ደፈጣዎችን በመምራትና በማዋጋት ጠላትን ያንቀጠቀጠ ግዙፍ ታሪክ በጀግንነት የፃፈ አርበኛ ነው!!

ከዚህ ባሻገር ከሸዋ እስከ ወሎ ቤተ-አማራ ቀድሞውኑ በተዘረጋው የፋኖ ትስስር ወሎ ቤተ-አማራ ከሚገኙ የፋኖ አደረጃጀትና መሪዎች ጋር በመቀናጀት በደቡብ ወሎ በተለይም በሀይቅ እና በደሴ ዙሪያ የአገዛዙ ሠራዊት እና ባንዳን በመመንጠር ለበርካታ ወራት ከፍተኛ ጀብዶችን የፈፀመው አርበኛው በወሎ ቤተ-አማራ/ሀይቅ ዙሪያ ከአገዛዙ ሠራዊት ጋር በተደረገ ፍልሚያ በመትረጊሱ የጠላትን ጦር ረፍርፎት በተጋድሎ ላይ እያለ በክብር ሰማእትነቱን ተቀብሏል !!

የጠላት ሃይል ራምቦን እጅግ ይፈራውና በስሙ ይደነግጥ ስለነበር በወቅቱ መሰዋዕትነቱን ሲሰማ ደሴና ኮምቦልቻ ላይ ደስታውን ሲገልፅ እንደነበር ተሰምቷል። አስከሬኑ ከደቡብ ወሎ ወደ ትውልድ ከተማው ሸዋሮቢት ከተማ ሲገባም የስርዓቱ ወታደሮች ስርዓተ-ቀብሩን የማስተጓጎል ሙከራ ቢያደርጉም በወቅቱ የሚወደውን ልጁን ያጣው የሸዋ ህዝብ በግፊያ ተሰልፎ አፅሙን በክብር አሳርፏል። ጀግናው ራምቦ በመሰዋዕትነቱ እልፍ ራምቦዎችን ዛሬ ተክቷል !!

ለጀግናው መታሰቢያ በተሰዋበት ወሎ/ቤተ-አማራ የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ራምቦ ክፍለጦር ብሎ ሲሰይምለት በሸዋ የሚገኙት ወንድሞቹና ጓዶቹ የተሰለፉበት የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ክፍለጦር ስር ደግሞ ራምቦ ብርጌድ በስሙ ተሰይሞለታል ።

የጀግናውን አርበኛ ፋኖ ስንታየሁ ማሞ(ራምቦ) አንደኛ አመት የመታሰቢያ ቀን የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዋና አዛዥ አርበኛ መከታው ማሞ እና የዕዙ ወታደራዊ አዛዥ ኮሎኔል ማንነገረውን ጨምሮ በርካታ አመራሮች የክቡር ሰማዕት ስንታየሁ ማሞ/ራምቦ/ 1ኛ አመት መታሰቢያ ቀኑ ተከብሮለታል ።

ዘላለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማዕት አርበኞች !

Address

Addis
Addis Ababa

Website

http://freemedia.tv/

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አማሮች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አማሮች:

Videos

Share