Ye Ethiopia - የኢትዮጵያ

Ye Ethiopia - የኢትዮጵያ Ye Ethiopia
(3)

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው ረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ - ረመዳን ከሪም
22/03/2023

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው ረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ - ረመዳን ከሪም

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ  ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር )የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ  አህጉረ  ...
22/03/2023

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር )የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ መቆየታቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ ከሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ነበሩ፡፡

እንዴት አይነት ክፉ ጊዜ ላይ ደረስን ⁉️"40ሺ ብር እንከፍልሻለን ብለውኝ ነው ይዣት የጠፋውት"   | ከቀናት በፊት በሞግዚቷ ተሰርቃ የተወሰደችው የ2 ዓመቷ ህፃን ሶሊያና ዳንኤል ከብሄራዊ...
22/03/2023

እንዴት አይነት ክፉ ጊዜ ላይ ደረስን ⁉️

"40ሺ ብር እንከፍልሻለን ብለውኝ ነው ይዣት የጠፋውት"

| ከቀናት በፊት በሞግዚቷ ተሰርቃ የተወሰደችው የ2 ዓመቷ ህፃን ሶሊያና ዳንኤል ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ባደረገው ጠንካራ ክትትል ሱሉልታ ከተማ ላይ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የ2 ዓመት ዕድሜ ያላት ህፃን ሶሊያና ዳንኤል ሳሪስ አዲስ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሃሙስ መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ/ም ረፋድ ላይ ቤዛ በቀለ በተባለችው የቤት ሰራተኛቸው ተሰርቃ ስለመወሰዷ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች መረጃው ሲሰራጭ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በህፃኗ ወላጆች የቀረበለትን አቤቱታ ተቀብሎ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀትና ከአዲስ አበባ ውጪ ወደተለያዩ የሃገራችን ከተሞች እና አካባቢዎች በመሄድ ጭምር አስፈላጊ መረጃዎችን በፖሊሳዊ ጥበብ በማሰባሰብ ከፍተኛ ጥረትን የጠየቀ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የክትትል ስራው ቀንና ሌሊት ደጅ ውሎ ማደርን የግድ የሚል እጅግ አድካሚ እንደነበር ያስታወሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ በስተመጨረሻም ቤዛ በቀለ ዛሬ መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ/ም ሱሉልታ ከተማ "ኖኖ መና አቢቹ" ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ህፃን ሶሊያና ዳንኤልን ሸሽጋ በተቀመጠችበት በቁጥጥር ስር መዋሏን አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ እንደተናገረቸው 40 ሺህ ብር ይከፈልሻል ብለው ሰዎች ስላግባቧት ህፃኗን ሰርቃ ልትሰወር ችላለች፡፡

በወንጀሉ ላይ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ከነጉዳቴ ወደ መኖሪያዬ ገብቻለሁ! "እግዚአብሔር ይመስገን በጸሎታችሁና በድምፃችሁ ከነጉዳቴ ወደ መኖሪያዬ ገብቻለሁ። ድምፅ ለሆናችሁኝ በሙሉ አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ይመስገን።"መምህር ታዬ...
22/03/2023

ከነጉዳቴ ወደ መኖሪያዬ ገብቻለሁ!

"እግዚአብሔር ይመስገን በጸሎታችሁና በድምፃችሁ ከነጉዳቴ ወደ መኖሪያዬ ገብቻለሁ።

ድምፅ ለሆናችሁኝ በሙሉ አመሰግናለሁ።

እግዚአብሔር ይመስገን።"

መምህር ታዬ ቦጋለ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912199628

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ye Ethiopia - የኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ye Ethiopia - የኢትዮጵያ:

Videos

Share

YE ETHIOPIA - የኢትዮጵያ

YE ETHIOPIA - የኢትዮጵያ