ሰክትኖ የሳርኖ

21/03/2024

GURAGE is a mixture of all religions. Northern politics Gurage is not based on the earth.

እኔም የጉራጌ ሕዝብ አካል ነኝ ለወልቂጤ ከተማ ሰላም ዘብ እቆማለሁ!!!የጉራጌ ሕዝብ ርእስ ከተማ ወልቂጤን አንገት አልባ ለማድረግ የሚደረግ ሸፍጥ ተወጥኖ በህግ አግባብ መፈፀም የነበረበትን ...
27/12/2023

እኔም የጉራጌ ሕዝብ አካል ነኝ ለወልቂጤ ከተማ ሰላም ዘብ እቆማለሁ!!!
የጉራጌ ሕዝብ ርእስ ከተማ ወልቂጤን አንገት አልባ ለማድረግ የሚደረግ ሸፍጥ ተወጥኖ በህግ አግባብ መፈፀም የነበረበትን የወልቂጤ የአስተዳደር ጣልቃ ገብነት ማስቆምን እንደ ውስብስብ ችግር በማስመሰል የጉራጌ ህዝብ ለሰላም በአንድ ድምፅ እዳይነሳ በ3ወር ህግ እናስከብራለን ተባለ፤ በመቀጠልም በካድሬ ምልመላ ሽምግልና የሚል 7 ጊዜ ቴያትር እንዲሰራ ተደረገ፤ ኮማንድ ፖስትም ታወጀ ፤ ከተማዋ ባሳለፍነው ሁለት ወራት በጠላት የተወረርን እስኪመስል ያልቀመስነው መከራና ግፍ የለም አሁን መቼም ጆሮአችን የማይሰማው የለም የጉራጌ ርእስ ከተማ የሆነችውን ወልቂጤ ከአዲስ አበባ መግቢያ በር ላይ ጄ ኤንድ ፒ አካባቢ የጉራጌ ባህል አዳራሽና በርካታ የጉራጌ ዞን ቢሮዎች የሚገኙበት የወልቂጤ ከተማ አንገት የሆነው የከተማው ክፍል የሕገ ወጥ ፅንፈኞች መናገሻ ለማድረግ ሸፍጥ ተይዞ እየተሰራ እንዳለ በገደምዳሜ እየሰማንም እያየንም ነው፡፡
ይህ ከሞራልም ከህግም ከየትኛውም መስፈርት አንፃር የማይሆንና እጅግ እጅግ አደገኛ በመሆኑ እነዚህ ለሕግ ተገዢ ያለመሆን የወንበዴዎች እኩይ እንቅስቃሴዎች መንግስት በቸልታ ሊያየው አይገባም!

እኛ ጉራጌዎች በወልቂጤ ዙሪያ ለሚደረጉ የሕግ ጥሰት እና ውንብድና ፈጻሚ አስፈጻሚ አካላቶችን እንደተለመደው ለሕግ በማቅረብ እና በመጠቆም ከፍትህ አካላት ጎን በመቆም ለዘላቂ የሕዝባችን ሰላም እንታገላለን!!
gurage ለ ጉራጌ -lojdave Shimelis Abdisa House of Federation of Ethiopia The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ Abiy Ahmed Ali Highlight House of Peoples Representatives of FDRE FDRE Government Communication Service-በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት Gurage Zone Government Communication Affairs Department Gogot for Gurage unity and justice party/ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲ Office of the President, Ethiopia Tarekegn Degife Taye Dendea Aredo #ጉራጌ #ወልቂጤ #ኢትዮጵያ

ፍትህ ለጠየቀእስር መፍትሔ ሆኖ አያውቅም!ያለምንም ወንጀል ከየቦታው ለቅማቹ በእየ እስር ቤቱ የታጎሩ ከ250 በላይ የጉራጌ ዘርማዎች እና የጎጎት ፓርቲ የስራ ኃላፊዎች በአስቸኳይ ይፈቱ!! እ...
26/12/2023

ፍትህ ለጠየቀ
እስር መፍትሔ ሆኖ አያውቅም!

ያለምንም ወንጀል ከየቦታው ለቅማቹ በእየ እስር ቤቱ የታጎሩ ከ250 በላይ የጉራጌ ዘርማዎች እና የጎጎት ፓርቲ የስራ ኃላፊዎች በአስቸኳይ ይፈቱ!!
እኛ የጉራጌ ሕዝቦች መንግሥት የሰላም እና የፍትህ መንገዶችን ሁሉ ዝግ አድርጎ በጠመንጃ ኃይል በማስጨነቅ በሚያደርጋቸው አፈናዎች እና ማሳደዶች ተሽብረን ተንበርክከን እንድንቆም ማሰባችሁ የዋህነት ነው። በግዛት ወሰናችን ያለስጋት በነፃነት እና በሰላም መኖር ፈቅ የማንልለት ተቀዳሚ አላማችን ነው እወቁት።
ታላቁ የጉራጌ ሕዝብ ፍትህን ለሚረግጥ ባከበርከው ልክ ለማያከብር አምባገነናዊ ስርዓቶች ሁሉ ቦታ እንደሌለው አሳይቷችኋል አሁንም ግትርነት ያዋጣናል ካላችሁ በባዶ እጁ ያለ ጠመንጃ ያሳያችኋል!!
በቃን እኛ በጉራጌነታችን በውሃ አስጠምታችሁናል ብዙ ቆስለናል ፣ ተወግረናል ፣ ተዘርፈናል ፣ ተገለናል ፣ እንደ ጠላት ኢላማ ተደርገናል።
ሽንፈት የማይሰለቻችሁ የሀገር መሪ ነን ብላችሁ ሳታፍሩ ሕዝብ ወክሎኛል ብላችሁ የምታስቡ የብልጽግና ፓርቲ ደመኛ አመራሮች ሕዝብ በፍትህ ሲያሸንፋችሁ ሕዝብን ከሕዝብ በማቃረን እና ከማጋጨት እና ደም ከማቃባትም በላይ የስልጣን ዘመናችሁን ለማርዘም ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትሉ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አውቋችኋል እኛ እንደ ጉራጌ ሕዝብ የግዛት ወስናችንን ፣ ነጻነታችንን እና ማንነታችንን በሕግ እስከሚከበር ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል።
Highlight Zebidar Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብZebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ ዘቢዳር ቲዩብ Mesfin Gebereyesus gurage ለ ጉራጌgurage ለ ጉራጌ -lojdave Tarekegn Degife House of Federation of Ethiopia Abiy Ahmed Ali Shimelis Abdisa The Federal Supreme Court of EthiopiaThe Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፌዴራል ጠቅላይ The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤትThe Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤትThe Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት

18/10/2023

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251925125125

Website

https://www.facebook.com/hayahulet.twotwo/, https://www.tiktok.com/@gurage.love?_t

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰክትኖ የሳርኖ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሰክትኖ የሳርኖ:

Videos

Share