Minber Tv/ሚንበር ቲቪ

Minber Tv/ሚንበር ቲቪ ሚንበር ቲቪ
ሁለንተናዊ ከፍታ!
(6)

በዱባይ ጎርፍ ጉዳት የደረሰበት ኢትዮጵያዊ እንደሌለ ተነገረዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 10 - 2016 | ሸዋል 9 – 1445 | ሚንበር ቲቪዱባይ ባለፉት 75 ዓመታት ካስመዘገበችው ከፍተኛ የተባለ ...
18/04/2024

በዱባይ ጎርፍ ጉዳት የደረሰበት ኢትዮጵያዊ እንደሌለ ተነገረ

ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 10 - 2016 | ሸዋል 9 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

ዱባይ ባለፉት 75 ዓመታት ካስመዘገበችው ከፍተኛ የተባለ የዝናብ መጠን ባስከተለው ጎርፍ የተጎዳ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ ተነግሯል፡፡ ዱባይ ከሰኞ እኩለ ሌሊት ጀምሮ አስተግዳ በጎርፍ ተጥለቅልቃ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዱባይ የተመዘገበው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የዐረብ ባህር ገብ መሬቶችንም ጭምር በማካለል ለሰው ነፍስ መቀጠፍና ለንብረት ውድመት ምክንያት የሆነ ነው።

በዱባይ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰምቻለሁ ብሎ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ በከተማዋ የጣለውን ዝናብ የተከተለው ጎርፍ የአንድ ግለሰብ መኪና ወስዶ የአሽከርካሪው ሕይወት ቢያልፍም፣ በኢትዮጵያውያን ላይ የሕይወት ጉዳት አልደረሰም፡፡

የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ባለሥልጣናት ትናንት ረቡዕ ከቀትር በኋላ በሰጡት መግለጫ ሰኞ እና በማግሥቱ ማክሰኞ የተመዘገበው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በዱባይ እና ሌሎችም አካባቢዎች ጋብ በማለቱ ቀጣዮቹ ቀናት መደበኛ የአየር ሁኔታ ያስተናግዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል። እስከዚያው ድረስ ዛሬ እና ነገ አየሩ ጭጋጋማ ሆኖ እንደሚቆይ የሜትሮሎጂ ባለሞያዎች ተናግረዋል።

በዱባይ ከተማ የተመዘገበው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ መኖሪያ ቤቶችንና የገበያ ማዕከላትን በማጥለቅለቅ ትምህርት ቤቶችም ዝግ እንዲሆኑ ያስገደደ ነበር። ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተከትሎ የትምህርት አሰጣጡ በኦንላይን እየተከናወነ ይገኛል። መደበኛ ያልሆነው ይህ አሠራር በዱባይ፣ ሻርጃህ እና በኤምሬቶች ዋና መዲና አቡደቢ እስከ ነገ ዐርብ የሚቀጥል ነው።

የተመዘገበው ከፍተኛ የዝናብ መጠን እንደ ዱባይ ባይሆንም በአካባቢው የሚገኙትን ባህሬን፣ ኦማን፣ ኳታር እና ሳዑዲ ዐረቢያንም አዳርሷል። በኦማን ቀደም ብለው በወጡ መረጃዎች የ19 ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል፡፡

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

!

18/04/2024



ከወርሃ ረመዷን በኋላ በመደበኛ ሰዓቱና ቅርፁ በሚቀርበው የዛሬው ኸሚስ ምሽት ፕሮግራማችን፤ ሸይኻችን በሰዓታቸው ከረመዷን በኋላ ለሸይጣን ወጥመድ የሚያጋልጡንን የተለያዩ እኩይ ተግባራት እያወሱና የማምለጫው ዘዴዎቹን እያመላከቱን ያመሻሉ።
በቢስሚከ ነህያ ንዑስ ፕሮግራማችን ደግሞ ኡስታዝ በድር ሁሴን የመክፈቻይቱን ምዕራፍ (ሱረት አል ፋቲሃ) የገዘፉ ምስጢራት እያወሳና ከቀሪ የቁርኣን አያዎች ጋር እያስተሳሰረ ከአዳዲስ ሃሳቦች ጋር አብሮን ይቆያል።

ምሽት ከ2፡00 ጀምሮ!

!
!

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

!

የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም የተመድ የሙሉ አባልነት ጥያቄ ላይ ድምፅ ሊሰጥ ነው ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 10 - 2016 | ሸዋል 9 – 1445 | ሚንበር ቲቪ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ...
18/04/2024

የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም የተመድ የሙሉ አባልነት ጥያቄ ላይ ድምፅ ሊሰጥ ነው

ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 10 - 2016 | ሸዋል 9 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (የተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት ነገ ዐርብ ሚያዝያ 11/2016 በፍልስጤም የሙሉ አባልነት ጥያቄ ላይ ድምፅ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ የፀጥታው ምክር ቤት ይህ የድምጽ የመስጠት ሂደት ከእስራኤል እና ከአጋሯ አሜሪካ የተቃውሞ ድምጽ የሚሰማበት ነው፡፡

በፀጥታው ምክር ቤት አዲስ የአባልነት ጥያቄ የሚመረምረው ኮሚቴ የፍልስጤምን ጥያቄ ለማየት ባለፈው ሳምንት ለሁለት ጊዜ ስብሰባ ተቀምጧል፡፡

ነገ በሚካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ከምክር ቤቱ 15 አባል ሀገራት ውስጥ ዘጠኙ የይሁንታ ድምጽ ሰጥተው አሜሪካን ጨምሮ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ባላቸው አምስት ሀገራት የተቃውሞ ድምፅ ካልተሰጠ የፍልስጤም የተመድ አባልነት ጥያቄ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሆኖም ግን ከእነዚህ አምስት ሀገራት መካከል የእስራኤል አጋሯ አሜሪካ ከዚህ ቀደም በምታራምደው የፍልስጤም ሀገር የመሆን ጥያቄ መፈታት ያለበት በተመድ አይደለም በሚል አቋሟ ምክንያት ከፍልስጤም ጎን አትቆምም የሚል ግምት እንዲሰጥ አድርጓል፡፡

የተመድ የሙሉ አባልነት ጥያቄዋ የሚታይላት ፍልስጤም ከ12 አመታት በፊት በተመድ የታዛቢነት ቦታ ተሰጥቷታል። ፍልስጤም ሙሉ የተመድ አባል ለመሆን ለመጀመርያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ በ2011 ነበር። የሙሉ አባልነት ጥያቄው ተቀባይነት እንዲያገኝ በተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ፀድቆ የጠቅላላ ጉባኤውን ሁለት ሦስተኛውን ድምጽ ማግኘት አለበት።

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

!

  ከወርሃ ረመዷን በኋላ በመደበኛ ሰዓቱና ቅርፁ በሚቀርበው የዛሬው ኸሚስ ምሽት ፕሮግራማችን፤ ሸይኻችን በሰዓታቸው ከረመዷን በኋላ ለሸይጣን ወጥመድ የሚያጋልጡንን የተለያዩ እኩይ ተግባራት እ...
18/04/2024



ከወርሃ ረመዷን በኋላ በመደበኛ ሰዓቱና ቅርፁ በሚቀርበው የዛሬው ኸሚስ ምሽት ፕሮግራማችን፤ ሸይኻችን በሰዓታቸው ከረመዷን በኋላ ለሸይጣን ወጥመድ የሚያጋልጡንን የተለያዩ እኩይ ተግባራት እያወሱና የማምለጫው ዘዴዎቹን እያመላከቱን ያመሻሉ።
በቢስሚከ ነህያ ንዑስ ፕሮግራማችን ደግሞ ኡስታዝ በድር ሁሴን የመክፈቻይቱን ምዕራፍ (ሱረት አል ፋቲሃ) የገዘፉ ምስጢራት እያወሳና ከቀሪ የቁርኣን አያዎች ጋር እያስተሳሰረ ከአዳዲስ ሃሳቦች ጋር አብሮን ይቆያል።

ምሽት ከ2፡00 ጀምሮ!

!
!

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

!

ልዩ “ኸበር” - የፍልስጤም እስረኞች ቀን መታሰቢያዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 10 - 2016 | ሸዋል 9 – 1445 | ሚንበር ቲቪ በየዓመቱ እ.አ.አ አቆጣጠር ኤፕሪል 17 በእስራኤል ማጎሪያዎች ...
18/04/2024

ልዩ “ኸበር” - የፍልስጤም እስረኞች ቀን መታሰቢያ

ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 10 - 2016 | ሸዋል 9 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

በየዓመቱ እ.አ.አ አቆጣጠር ኤፕሪል 17 በእስራኤል ማጎሪያዎች የሚገኙ ፍልስጤማዊያን እስረኞች ታስበው ይውላሉ። የፍልስጤም ብሔራዊ ምክር ቤት እለቱን ለእስረኞች መታሰቢያ አድርጎ የሰየመው በ1971 ለመጀመርያው ጊዜ ከእስራኤል ጋር በተደረገው የእስረኛ ልውውጥ የተለቀቀውን ሙሐመድ ባክር ሂጃዚ ለማሰብ ነው። በአል ቁድስ የተወለደው ሂጃዚ በጥር 1967 በፋታህ እንቅስቃሴ በመታቀፍ ከእስራኤል ጋር ተታኩሶ በቁጥጥር ስር ሲውል የሞት ፍርድ ተበይኖበት ነበር። ሆኖም ፍርዱ ሳይፀና ከ6 ዓመታት በኋላ በ1971 ነጻ ወጥቷል።

ሙሐመድ በመጋቢት 2021 ከዚህ ዓለም ሕይወት ቢለይም ባለፉት ዓመታት እንደሚደረገው ሁሉ የዘንድሮው የፍልስጤም እስረኞች ቀን ትናንት ሚያዝያ 9/2016 (ኤፕሪል 17) በተመሳሳይ ታስቦ ውሏል። በእለቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በማጎሪያዎች ከፍተኛ ስቃይ እያስተናገዱ የሚገኙ ፍልስጤማዊያን እስረኞች እንዲፈቱ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

መቀመጫውን በዌስት ባንክ ያደረገውና ለእስረኞች ድጋፍ የሚሰጠው “አዳሚር ፕሪዝነር ሰፖርት ኤንድ ሂዩማን ራይትስ አሶሴሽን” እንዳወጣው መረጃ፣ እስከ ማክሰኞ መጋቢት 8/2016 ድረስ ከጋዛ እና ዌስት ባንክ የታፈሱ 9500 ፍልስጤማዊያን በእስራኤል እስር ቤቶች ታጉረዋል። ከእነዚህ እስረኞች መካከል 3,360 ታሳሪዎች ለአንድም ቀን ቢሆን ፍርድ ቤት ቀርበው አያውቁም። በማጎሪያዎቹ የሚገኙትም ሆነ የተለቀቁት የሚሰጧቸው መረጃዎች የሚያመለክቱት ታሳሪዎች በማጎሪያዎቹ ቁም ስቅል ያያሉ።

ስለ ታሳሪዎቹ ሠፋ ያለ ዘገባ ያሠራጨው ሬውተርስ የዜና ወኪል ያናገረው ሱፍያን አቡ ሳላህ “ወደ እስር ቤት በሁለት እግር ገብቼ፤ በአንድ እግሬ ተመለስኩ” ሲል የደረሰበትን በደል በስልክ ተናግሯል። ሱፍያን ስለተፈፀመበት በደል ሲያስረዳ፡- “እግሬ ላይ እብጠት ቢከሰትም [የእስራኤል ባለሥልጣናት] ወደ ሆስፒታል ሊወስዱኝ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ። ከሳምንት በኋላ እብጠቱ ተሠራጭቶ ጋንግሪን ስለሆነ ተቆረጠ” ብሏል።

እስራኤል በፍልስጤም እስረኞች ላይ የምትፈፅመው በደል በዚህ አያበቃም። ከታኅሣሥ 2020 ወዲህ በኮቪድ19 ወረርሽኝ ሰበብ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው ተደርገዋል። ታሳሪዎቹ ወደ ቤተሰብ ስልክ መደወል የሚችሉትም በ2 ሳምንት አንድ ጊዜ ለ10 ደቂቃ ብቻ ነው።

እስራኤም በወረራ በያዘችው የፍልስጤም መሬት ላይ ከአምስት ፍልስጤማዊያን አንዱ ቢያንስ በአንድ አጋጣሚ እስር ሊያጋጥመው እንደሚችል የሚነገርበት ነው። ይህ አሐዝ በወንድ ፍልስጤማዊያን ብቻ ከተሰላ ከፍ ይላል። ከአምስት ፍልስጤማዊያን ወንዶች ሁለቱ ቢያንስ በአንድ አጋጣሚ የእስር ሰለባ ይሆናሉ። በእስራኤል እስር ቤቶች ከሚገኙ ፍልስጤማዊያን ውስጥ ሠላሳ ዓመት የቆዩ ይገኛሉ።

(ለዚህ ጥንቅር ከአልጀዚራ የተገኘ መረጃ ጥቅም ላይ ውሏል)

* የታሳሪዎችን አሐዝ የሚያሳየው መረጃ ምንጭ፡ አዳሚር ፕሪዝነር ሰፖርት ኤንድ ሂዩማን ራይትስ አሶሴሽን

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

!

የበርካታ ኢትዮጵያውያን መዳረሻ የሆነችው ዱባይ የአየር ሁኔታ መሻሻል አሳየ* ዱባይን ጨምሮ በሻርጃህ እና አቡደቢ ትምህርት ቤቶች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎቻቸውን በኦንላይን ያስተምራሉዕለ...
18/04/2024

የበርካታ ኢትዮጵያውያን መዳረሻ የሆነችው ዱባይ የአየር ሁኔታ መሻሻል አሳየ

* ዱባይን ጨምሮ በሻርጃህ እና አቡደቢ ትምህርት ቤቶች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎቻቸውን በኦንላይን ያስተምራሉ

ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 10 - 2016 | ሸዋል 9 – 1445

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች መዲና ዱባይ ከሳምንቱ መጀመርያ ቀን አንስቶ ለሁለት ቀናት የተመዘገበው ከፍተኛ ዝናብ ቀንሶ የአየር ሁኔታው መሻሻል አሳየ።

ዱባይ ባለፉት 75 ዓመታት ካስመዘገበችው ከፍተኛ የተባለ የዝናብ መጠን ከሰኞ እኩለ ሌሊት ጀምሮ አስተግዳ በጎርፍ ተጥለቅልቃ ነበር። በዱባይ የተመዘገበው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የዐረብ ባህር ገብ መሬቶችንም ጭምር በማካለል ለሰው ነፍስ መቀጠፍና ለንብረት ውድመት ምክንያት የሆነ ነው።

የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ባለሥልጣናት ትናንት ረቡዕ ከቀትር በኋላ በሰጡት መግለጫ በዱባይ እና ሌሎችም አካባቢዎች የተመዘገበው የተለየ የአየር ሁኔታ በማብቃቱ ቀጣዮቹ ቀናት መደበኛ የአየር ሁኔታ ያስተናግዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል። እስከዚያው ድረስ ዛሬ እና ነገ አየሩ ጭጋጋማ ሆኖ እንደሚቆይ የሜትሮሎጂ ባለሞያዎች ተናግረዋል።

በዱባይ ከተማ የተመዘገበው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ መኖሪያ ቤቶችንና የገበያ ማዕከላትን በማጥለቅለቅ ትምህርት ቤቶችም ዝግ እንዲሆኑ ያስገደደ ነበር። ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተከትሎ የትምህርት አሰጣጡ በኦንላይን እየተከናወነ ይገኛል። መደበኛ ያልሆነው ይህ አሠራር በዱባይ፣ ሻርጃህ እና በኤምሬቶች ዋና መዲና አቡደቢ እስከ ነገ ዐርብ የሚቀጥል ነው።

የተመዘገበው ከፍተኛ የዝናብ መጠን እንደ ዱባይ ባይሆንም በአካባቢው የሚገኙትን ባህሬን፣ ኦማን፣ ኳታር እና ሳዑዲ ዐረቢያንም አዳርሷል። በኦማን ቀደም ብለው በወጡ መረጃዎች የ18 ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን ተነግሮ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ማለዳ የወጡ ዘገባዎች ተጨማሪ ሞት መመዝገቡን ያመለክታሉ። ጎርፉ ሕይወታቸውን ከነጠቃቸው ውስጥ 10 ሕፃናት ይገኙበታል።

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶችና በዐረብ ባህር ገብ ሀገራት ለተመዘገው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የአየር ንብረት ለውጥ በምክንያትነት ተጠቅሷል።

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

!

የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የምስጋና እና የዕውቅና መድረክ አካሄደዕለተ ረቡዕ ሚያዝያ 9 - 2016 | ሸዋል 8 – 1445 | ሚንበር ቲቪ የ1445ኛው የዒድ አል ፊጥር በዓል ...
17/04/2024

የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የምስጋና እና የዕውቅና መድረክ አካሄደ

ዕለተ ረቡዕ ሚያዝያ 9 - 2016 | ሸዋል 8 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

የ1445ኛው የዒድ አል ፊጥር በዓል በደመቀ መልኩ ተከብሮ እንዲያልፍ አስተዋፅኦ የነበራቸውን
አካላት ዕውቅና ለመስጠት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዛሬ ሚያዝያ 9/2016ዓ.ል በግራንድ ኤሊያና ሆቴል የምስጋና ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

በመድረኩ ሼኽ ሱልጣን አማን ኤባ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት፣ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች የሥራ አሰፈጻሚ አባላት፣ የፌደራል ፓሊስ ተወካይ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ተወካዮች፣ የሚዲያ ተቋማት እንዲሁም በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዕለቱ የም/ቤቱ ፕሬዚዳንት ከዒድ ዋዜማ ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ህዝበ ሙስሊሙ በሰላም በዓሉን እንዲያከብር ለተባበሩ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም ለአ/አ ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት፣ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር፣ ለአ/አ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ፣ ለኢትዮጵያ ሙስሊም የጤና ባለሙያዎች ማህበር እንዲሁም ለተለያዩ ለፕሮግራሙ መሳካት አሻራቸውን ላሳረፉ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶ መርሀግብሩ ተጠናቋል።

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

 የበረሃው ፈርጥሸኽ ያሲን አሕመድ ቃዲ ከአፋር ታላላቅ መሻኢኾች አንዱ ነበሩ። አላህ የጀነት ይበላቸው። ራሳቸውን በዲን እውቀት ለማሳደግ አዝሃር ሄደው እውቃታቸውን አስፍተው ነው የመጡት። ታ...
17/04/2024



የበረሃው ፈርጥ

ሸኽ ያሲን አሕመድ ቃዲ ከአፋር ታላላቅ መሻኢኾች አንዱ ነበሩ። አላህ የጀነት ይበላቸው። ራሳቸውን በዲን እውቀት ለማሳደግ አዝሃር ሄደው እውቃታቸውን አስፍተው ነው የመጡት። ታጋይም ናቸው። ከአፋር ነጻ አውጪዎች ጋር ተቀላቀልው ነፍጠው አንግተው ለሕዝባቸው ነፃነት ታግለዋል። በሸኽነትም ደረሶችን ሰብስበው ማቅራት ብቻ ሳይሆን ቁርአን ተፍሲር በአፋርኛ ሠርተዋል። እኚህ ባለብዙ ክህሎት ሸኽ የዛሬው የሕይወት ገጽ ባለተራ ናቸው። ምሽት 3:00 ጠብቁን።

ዕለተ ረቡዕ ሚያዝያ 9 - 2016 | ሸዋል 8 – 1445

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

በረሃማዋ ዱባይ በ75 ዓመት ውስጥ አስተናግዳው አታውቅም የተባለ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ተጥለቀለቀችዕለተ ረቡዕ ሚያዝያ 9 - 2016 | ሸዋል 8 – 1445 | ሚንበር ቲቪ የተባበሩት ዐረብ...
17/04/2024

በረሃማዋ ዱባይ በ75 ዓመት ውስጥ አስተናግዳው አታውቅም የተባለ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ተጥለቀለቀች

ዕለተ ረቡዕ ሚያዝያ 9 - 2016 | ሸዋል 8 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች መዲና የሆነችው ዱባይ ባለፉት 75 ዓመታት ካስመዘገበችው ከፍተኛ የተባለ የዝናብ መጠን ከሰኞ እኩለ ሌሊት ጀምሮ አስተግዳ በጎርፍ ተጥለቅልቃለች። በዱባይ የተመዘገበው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የዐረብ ባህር ገብ መሬቶችንም ጭምር በማካለል ለሰው ነፍስ መቀጠፍና ለንብረት ውድመት ምክንያት ሆኗል።

ከሥፍራው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በተለይ ዱባይ ከተማ በጎርፍ መጥለቅለቋን ተከትሎ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ተስተጓጉሎ የአውሮፕላን በረራዎችም እንዲዘገዩ ተደርጓል።

ከሰኞ እኩለ ሌሊት እስከ ትላንት ማክሰኞ አመሻሽ በዱባይ የተመዘገበው የዝናብ መጠን ከዚህ ቀደም ከተማዋ በአንድ ዓመት ከመንፈቅ ጊዜ የምታስተናግደው መሆኑንም የሜትሮሎጂ ባለሞያዎች ገልፀዋል።

በዱባይ ከተማ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ መኖሪያ ቤቶችንና የገበያ ማዕከላትን በማጥለቅለቅ ትምህርት ቤቶችም ዝግ እንዲሆኑ አስገድዷል። በከተማዋ ውስጥ የሚገኙት ታዋቂዎቹ የገበያ ማዕከላት ዱባይ ሞል እና ሞል ኦፍ ኤምሬትስም ከጎርፉ መጥለቅለቅ አልተረፉም። የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን በማሰማራት ጎርፉን ለማስመጠጥ ሙከራ ሲያደርግ፣ የኤምሬቶች ብሔራዊ የሜትሮሎጂ ማዕከል የዱባይ ነዋሪዎችን በቻላችሁት አቅም ሁሉ እራሳችሁን በጎርፉ ከተጥለቀለቁ አካባቢዎች አርቁ የሚል የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ መልዕክት አስተላልፏል።

የተመዘገበው ከፍተኛ የዝናብ መጠን እንደ ዱባይ ባይሆንም በአካባቢው የሚገኙትን ባህሬን፣ ኦማን፣ ኳታር እና ሳዑዲ ዐረቢያንም አዳርሷል። የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በኦማን የ18 ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን ዘግቧል። ጎርፉ ሕይወታቸውን ከተጠቃቸው ውስጥ 10 ሕፃናት ይገኙበታል።

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶችና በዐረብ ባህር ገብ ሀገራት ለተመዘገው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የአየር ንብረት ለውጥ በምክንያትነት ተጠቅሷል። ለዚህ የአየር ንብረት ለውጥ መነሻ ነው የሚባሉት ሰው ሰራሽ ችግሮች መሆናቸውን ባለሞያዎች ያነሳሉ።

በጎርፍ ከተጠቁት መካከል በበረሃማዋ ዱባይ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ የተለመደ ባለመሆኑ ለጎርፍ መውረጃ የሚያገለግል ቦይ በሥፋት ቀድሞ ስላልተገነባ አደጋውን አስከፊ እንዳደረገው ተነግሯል።

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

!

የሚንበር “ጉርሻ”የደጉ አዛውንት ሥንብትሶሪያዊው አዛውንት ለሐጅ እና ዑምራ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በሚጓዙ ምዕመናን ዘንድ በነጻ ግብዣቸው የሚታወቁ ናቸው። ተጓዦች መዲና ሲያቀኑ “አርሒቡ” ብለው...
16/04/2024

የሚንበር “ጉርሻ”

የደጉ አዛውንት ሥንብት

ሶሪያዊው አዛውንት ለሐጅ እና ዑምራ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በሚጓዙ ምዕመናን ዘንድ በነጻ ግብዣቸው የሚታወቁ ናቸው። ተጓዦች መዲና ሲያቀኑ “አርሒቡ” ብለው ሻይ፣ ቡና እና ቴምር ሲያቀርቡ ኖረዋል። ለአቅርቦታቸው ግን አምስት ሳንቲም የሚቀበሉ አይደሉም።

የደጉ አዛውንት ሥም ሸይኽ ኢስማኤል አልዘይን አቡ አልሰባ ነው። ለ40 ዓመታት በመዲና ነጻ ግብዣ ሲያቀርቡ የኖሩትን የ96 ዓመቱ አዛውንት ከዚህ በኋላ አናገኛቸውም። በደግነታነቸው እንደቆዩ ዛሬ ወደ ቀጣዩ ዓለም መሻገራቸው ከከተማዋ ተሰምቷል።

የሚንበር “ጉርሻ”ዕለተ ማክሰኞ ሚያዝያ 8 - 2016 | ሸዋል 7 - 1445 | ሚንበር ቲቪኢራቃዊው ከሠላሳ ዓመት ገደማ በፊት የሰረቀውን ገንዘብ ከይቅርታ ደብዳቤ ጋር መለሰማንነቱን ይፋ ለ...
16/04/2024

የሚንበር “ጉርሻ”

ዕለተ ማክሰኞ ሚያዝያ 8 - 2016 | ሸዋል 7 - 1445 | ሚንበር ቲቪ

ኢራቃዊው ከሠላሳ ዓመት ገደማ በፊት የሰረቀውን ገንዘብ ከይቅርታ ደብዳቤ ጋር መለሰ

ማንነቱን ይፋ ለማድረግ ያልደፈረው ኢራቃዊ ዜጋ ከሠላሳ ዓመት ገደማ በፊት የሰረቀውን ገንዘብ “ይቅርታ አድርጉልኝ” ከሚል የተማጽኖ ደብዳቤ ጋር የመለሰው ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ነው። ይህ ሌባ በኢራቅ ውስጥ በምትገኘው ኩርዲስታን ግዛት ሱለይማኒያህ ከተማ ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት 400 የኢራቅ ስዊስ ዲናር (ቀድሞ የኢራቅ መገበያያ የነበረና አሁን በሌላ የተተካ) የሰረቀው እ.አ.አ ከ1990 እስከ 1998 ባለው ጊዜ ነበር።

ግለሰቡ ሦስት ዐሥርት ከተጠጋ ጊዜ በኋላ ባለፈው ቅዳሜ ገንዘቡን ለመመለስ ወደሰረቀበት መኖሪያ ቤት ሲያመራ ማንነቱን በጭንብል ሸፍኖ ነው። በእጁ ካኪ ወረቀት ይዞ የነበረው ሰው፣ የቤቱን በር በማንኳኳት ለከፈተችለት ሴት ወረቀቱን በማቀበል በፍጥነት ከአካባቢው ተሰውሯል።

በሩን የከፈተችው ከቤቱ ነዋሪዎች መካከል የሆነችው ሂርሲች ከሪም ሰውዬው በጥድፊያ ይህን ሲያደርግ ድንጋጤ እንደፈጠረባት በመግለጽ በጥርጣሬ የተቀበለችውን ካኪ ስትከፍተው ውስጡ 400 ሺህ የኢራቅ ዲናር (300 ዶላር ገደማ) እንዳገኘች ተናግራለች።

የዚያን ጊዜው ሌባ ከገንዘቡ ጋር ባስቀመጠውና በኩርዲሽ ቋንቋ በተጻፈ ደብዳቤው በጊዜው ለስርቆት መነሻ ሆኖኛል ያለበትን ምክንያት አስፍሯል። ግለሰቡ ለስርቆቱ ምክንያት ያደረገው ድርጊቱን በፈፀመበት ጊዜ ምንም ገንዘብ ኪሱ ውስጥ አለመኖሩን ነው። ገንዘብ አለመኖር ብቻ ግን ለስርቆቱ ሰበብ አልሆነውም፤ “[የሰረቅኩት] ገንዘብ በአንገብጋቢ ሁኔታ ያስፈልገኝ ነበር” ብሏል። ግለሰቡ በደብዳቤው ላይ ለሰረቃቸው ሰዎች “ይቅርታ አድርጋችሁልኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ማለቱንም የገልፍ ኒውስ ዘገባ ያመለክታል።

የግለሰቡ ድርጊትና ለይቅርታ የተማፀነበት ደብዳቤው ይፋ ከተደረገ በኋላ ባለፉት ቀናት በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች አንዳንዶች ሲያወድሱት ሌሎች ደግሞ እየወቀሱት መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

 ጛዛ እንደምን ከረመች?ዛሬ ምሽት ከ2:00 ጀምሮ ይጠብቁን!★★★★★ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል ጥራት ለመከታተል👇ፍሪኩዌንሲ:- 11545ሲምቦልሬት:- 45000ፖላራይዜሽን:- ሆሪ...
16/04/2024



ጛዛ እንደምን ከረመች?

ዛሬ ምሽት ከ2:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

የሃይማኖት አባቶች የሰላም እሴቶችን በማስተዋወቅ ቁልፍ ሚና አላቸው ተባለዕለተ ሰኞ ሚያዝያ 7 - 2016 | ሸዋል 6 - 445 | ሚንበር ቲቪየሃይማኖት አባቶች የሰላም፣ የአብሮነትና የመከባ...
15/04/2024

የሃይማኖት አባቶች የሰላም እሴቶችን በማስተዋወቅ ቁልፍ ሚና አላቸው ተባለ

ዕለተ ሰኞ ሚያዝያ 7 - 2016 | ሸዋል 6 - 445 | ሚንበር ቲቪ

የሃይማኖት አባቶች የሰላም፣ የአብሮነትና የመከባበር እሴትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ቁልፍ ሚና አላቸው ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ኸይረዲን ተዘራ ዛሬ በሒልተን ሆቴል በዓለም አቀፉ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባዔ ላይ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የበላይ ጠባቂነት የተዘጋጀ ሲሆን የተዘጋጀበትን ዓላማ ግብ እንደሚመታም ይጠበቃል ተብሏል።

በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ሠላምና ልማትን ማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ ክብርን መጠበቅ፣ አካባቢን መጠበቅ፣ የጥላቻ ንግግርንና መጤ ጠልነትን በጋራ መከላከል የሚያስችል ምክክር ማድረግ የጉባኤው ዋና ዓላማ መሆኑም ተገልጿል።

ወ/ሮ ካትሪን ማርሻል የG20 የሃይማኖቶች ፎረም ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዓለም እምነት ልማት ውይይት ዳይሬክተር (Executive Director of World Faith Development Dialogue)
ከዩናይትድ ስቴትስ እንዲሁም ፕሮፌሰር ሮድሪጎ አልቬስ የG20 የሃይማኖቶች ፎረም በብራዚል ሊቀመንበር እና የዩበርላንድ ፌዴራል ዩኒቨርሲቲ የህግ ፋኩልቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የአህጉራዊ ኮንፍረንሱን ዓላማዎች በተመለከተ ንግግር አድርገዋል።

3ኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት/እምነት ተቋማት የምክክር ጉባዔ በብራዚል እንደሚካሄድም ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመጀመሪያው ጉባኤ ከያዛቸው ዓላማዎች አንዱ የአፍሪካ ኅብረት 55 አባል ሀገራቱን በመወከል የG20 አባል እንዲሆን ምክር ሀሳብ የቀረበበት እና ሀሳቡም ሌሎች አጋሮችና የሀገራት መሪዎች ጭምር ድጋፍ በማግኘቱ መስከረም 2023 በሀገረ ህንድ በነውዴልሂ ከተማ በተካሔደው የቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች መደበኛ ስብሰባ ላይ ምክረ ሀሳቡ ተቀባይነት አግኝቶ ኅብረቱ የቡድን 20 ቋሚ አባል እንዲሆን መወስኑ ይታወሳል፡፡

ይህም ጉባዔው በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ ሳይሆን በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችም ጭምር አወንታዊ ሚናውን ለመወጣት አቅሙ የፈቀደውን ጥረት እያደረገ ለመሆኑ ማሳያ ነውም ተብሏል።

ዓለም አቀፍ ጉባኤው በዋናነት በሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሮ ጠንካራ መሠረት ያለውን የሰላም፣ የአብሮነትና የመከባበር ዕሴትን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ወርቃማውን ሕግ ይበልጥ በማስተዋወቅ፣ ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለሰብኣዊነት፣ ለአካባቢ ጥበቃና ለሃይማኖት እምነት ነፃነት መጠበቅ ያላቸውን ገንቢና አወንታዊ ሚናቸውን እንዲያጠናክሩ እና ከሃይማኖቶች አስተምህሮ ጋር የሚቃረኑ አሉታዊ አስተሳሰቦችንና ሕገ-ወጥ ተግባራትን በተባበረ አቅም ለመከላከል እንዲቻል ሀገራት አስፈላጊ የሆነ የሕግ ማሻሻያዎችን እንዲደርጉ አማራጭ ሀሳቦችን ያቀርባል ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ የምክክር ጉባኤው ሀገራችን በብሔሮችና ሃይማኖቶች እምነቶች ብዝሃነት የተገነባችና "ምድረ ቀደምት" የሚለውን የቱሪዝም መገለጫ በተጨባጭ ማሳያዎች ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚን ከመፍጠሩም ባሻገር ሁነቱ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ፤ የገጽታ ግንባታና ሀገራችንን የቱሪዝም መዳረሻነቷን ለማስፋት የላቀ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክትም ተገልጿል።

ጉባዔው ከተባባሪ አጋሮች ጋር በመሆን እንዲህ ዓይነት ዓለማቀፋዊ መድረኮችን በማዘጋጀት ጠቃሚና ተጨባጭ ልምዶችንና ተሞክርዎችን ከማግኘቱም ባለፈ የሃይማኖት ተቋማት ተልዕኳቸው ድንበር የለሽ ከመሆኑ አንፃር ሁሉንም የሰው ልጆች እንደአንድ ቤተሰብ በማስተሳሰር ኢፍትሐዊነትንና በደልን፣ ኃጢአትንና ኢሃይማኖታዊነትን ለመከላከል ይረዳል ሲሉም ሊቀትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ አክለዋል።

ይህም ጉባኤው ከተቋቋመበት መሠረታዊ መርህና ዓላማ ጋር በእጅጉ የሚስማማ እንደሆነ እንረዳለን ያሉ ሲሆን በመጨረሻም ይህ ዓለም አቀፍ ጉባዔ በዚህ መልኩ እንዲከናወን ልዩ ልዩ ተሳትፎና አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ በተለይም ለG20 Interfaith Forum Association እና ለURI AFRICA በጉባዔው ስም ምስጋና አቅርበዋል።

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

    ምሽት ከ2፡00 ጀምሮ!★★★★★ሚንበር ቲቪን ለመከታተል👇ፍሪኩዌንሲ:- 11545ሲምቦልሬት:- 45000ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል★★★★★   !
15/04/2024





ምሽት ከ2፡00 ጀምሮ!

★★★★★
ሚንበር ቲቪን ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

15/04/2024

በኑን የቁርአን መድረክ ዝግጅት ላይ በታዋቂዎቹ ሱዳናውያን መሻይኾች ሸይኽ አዘይን እና ሸይኽ ሲራጁዲን የቀረቡ ቲላዋዎች በሚንበሩል ቁራእ መቅረብ ጀምረዋል።
🌴
በዚህ ቪድዮ ሸይኽ ሲራጁዲን በኢብን ዓምር አሻሚ ሪዋያ ከሱረቱ አል ካህፍ አያ 27 እስከ 44 ቀርቧል። ኮሜንት ላይ የተቀመጠውን ሊንክ በመንካት ይጋበዙ።

ሁለተኛውን ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛልዕለተ ሰኞ ሚያዝያ 7 - 2016 | ሸዋል 6 - 445 | ሚንበር ቲቪ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከተ...
15/04/2024

ሁለተኛውን ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል

ዕለተ ሰኞ ሚያዝያ 7 - 2016 | ሸዋል 6 - 445 | ሚንበር ቲቪ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ማለትም United Religions Initiative-Africa, G20 Interfaith Forum, AU-Citizens and Diaspora Directorate, AU-ECOSOCC & AU Interfaith Dialogue Forum ጋር በመተባበር ሁለተኛውን አህጉር አቀፍ ኮንፈረንስ ሚያዚያ 7 - 8 ቀን 2016 ዓ.ል "Interfaith Collective Action to Foster Peace, Human Dignity, Development, Prevention of Environment and to Counter Hate Speech, Violence and Xenophobia" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ኮንፍረንሱ የሃይማኖቶች ትብብር እና የዓለም አቀፍ ወርቃማው ሕግ አስተምህሮን ይበልጥ እንዲጠናከርና ሠፊ ተደራሽነት እንደሚኖረው ታሳቢ በማድረግ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔ መሠረት በየዓመቱ April 5 የዓለም አቀፍ ወርቃማው ቀን እንዲሆን በተወሠነው መሠረት ዝግጅቱ ከዕለቱ ጋር ተቀራራቢ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።

ከሀገር ውስጥ የጉባዔው የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ ሚኒስትሮች፥ ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችን ጨምሮ አንድ መቶ ተሳታፊዎች ከተለያዩ የውጪ ሀገራት ዜጎች ተገኝተዋል።

ሚንበር ቲቪ አጠቃላይ መርሃ ግብሩ ምን እንደሚመስል በቦታው ተገኝቶ እየተከታተለ መረጃውን ወደ እናንተ ያደርሳል።

★★★★★
ሚንበር ቲቪን ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

  ወቅፍ በሂጅራ ባንክ ሂጅራ ባንክ ከሚንበር ቲቪ ጋር በመተባበር ዛሬ ምሽት 2:00 በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን ★★★★★ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል ጥራት ለመከታተል👇ፍሪኩዌንሲ:- ...
14/04/2024



ወቅፍ በሂጅራ ባንክ
ሂጅራ ባንክ ከሚንበር ቲቪ ጋር በመተባበር

ዛሬ ምሽት 2:00 በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

በየደረጃው ለሚያሸንፉ ተወዳዳሪዎች ከብር ሁለት መቶ ሺህ እስከ ብር አንድ ሚሊየን ድረስ የሚያሸልመው አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር፤ በሁለተኛው ዙር ዝግጅቱ አዳዲስ ተሳታፊዎችን እያወዳደ...
14/04/2024

በየደረጃው ለሚያሸንፉ ተወዳዳሪዎች ከብር ሁለት መቶ ሺህ እስከ ብር አንድ ሚሊየን ድረስ የሚያሸልመው አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር፤ በሁለተኛው ዙር ዝግጅቱ አዳዲስ ተሳታፊዎችን እያወዳደረ ይገኛል።
ይህ አቢሲንያ ባንክ በአቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኩል የሚያሰናዳውና ልዩ ልዩ የቢዝነስ ዕይታዎችና ችግር ፈቺ የሥራ ፈጠራ ሃሳቦች የሚቀርቡበት አሚን አዋርድ ሁለተኛ ዙር የሥራ ፈጠራ ውድድር መድረክ እሁድ ከ11:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይቀርብላችኋል።

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

እስራኤል በጋዛ ጋዜጠኞችን ኢላማ አድርጋ በሰነዘረችው ጥቃት ሦስት የሚዲያ ባለሞያዎች ላይ ጉዳት ደረሰ ዕለተ ቅዳሜ ሚያዝያ 5 - 2016 | ሸዋል 4 – 1445 እስራኤል ትናንት ዐርብ በጋዛ...
13/04/2024

እስራኤል በጋዛ ጋዜጠኞችን ኢላማ አድርጋ በሰነዘረችው ጥቃት ሦስት የሚዲያ ባለሞያዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

ዕለተ ቅዳሜ ሚያዝያ 5 - 2016 | ሸዋል 4 – 1445

እስራኤል ትናንት ዐርብ በጋዛ ጋዜጠኞችን ኢላማ አድርጋ በሰነዘረችው ጥቃት ሦስት የሚዲያ ባለሞያዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ድንበር የለሽ የጋዜጠኞቸ ቡድን እና የጋዛ የመገናኛ ብዙኃን ጽሕፈት ቤት አስታወቁ፡፡ እስራኤል ጥቃቱን የሰነዘረችው በጋዛ ውስጥ በሚገኘው ኑሰይራት የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ላይ ነው፡፡

በጥቃቱ የቱርኩ ቲ አር ቲ ዐረቢ ባልደረቦች ጉዳት አስተናግደዋል፡፡ ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ ሳሚ ሸሃዳህ የተባለ ጋዜጠኛ እግሩን ማጣቱን የሚሠራበት ቲ አር ቲ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ሌላኛው የጣቢያው ባልደረባ ሳሚ በርሁም በተመሳሳይ ጉዳት ደርሶበት ለሕክምና ወደ ሆስፒታል ተወስዷል፡፡

በባልደረቦቹ ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ቲ አር ቲ ባወጣው መግለጫ በኑሰይራት የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በጋዜጠኞቹ ላይ ጥቃቱ የተሰነዘረው ለዘገባ በዝግጅት ላይ በነበሩበት ሰዓት መሆኑን ገልጿል፡፡ የቴሌቪዥን ጣቢያው ዋና ኃላፊ የሆኑት ዛሂድ ሶባሺ ጥቃቱን የፈጸመችው “የእስራኤል ጭካኔ” በግብረ ገብ፣ በሕግም ሆነ በሰብዓዊነት አንጻር ሲመዘን ድንበሩን ያለፈ ነው ሲሉ ጥቃቱ ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በጋዛ ከተማ በሚገኘው አል አቅሳ ሆስፒታል ሕክምናውን እየተከታተለ የሚገኘው በጥቃቱ አንድ እግሩን ያጣው የቲ አር ቲው ሸሃዳህ ጥቃቱ ሲሰነዘር “አደገኛ ቀጣና” ተብሎ ከተለየው ሥፍራ ውጭ እንደነበሩ በማስታወስ የሞያ ባልደረቦቹን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች “አብረውኝ ነበሩ” ብሏል፡፡ ከተኩሱ በኋላ እግሩ ሲከዳው እንደተሰማው የሚገልጸው ሹሀዳህ፣ ጥቃቱ ጋዜጠኞቹን ኢላማ በማድረግ “ሆን ተብሎ” እንደተፈጸመ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግሯል፡፡ ሹሃዳህ ጥቃቱ ሲሰነዘር የጋዜጠኛ ቆብ እንዲሁም መለያ አጥልቆ እንደነበረ በመጥቀስ፣ “[በዚህም] ጋዜጠኛ እንደሆንኩ ለመለየት ለማንም ቢሆን የሚከብድ አልነበረም” ሲል አክሏል፡፡

የጋዜጠኞቹን መጎዳት ተከትሎ መግለጫ ያወጣው ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የእስራኤልን ጥቃት አውግዞታል፡፡ የቡድኑ የመካከለኛው ምሥራቅ ተጠሪ ጆናታን ዳገር ጋዜጠኛን ኢላማ ያደረገ ጥቃት “እውነትን ለመደበቅ” የሚደረግ ሙከራ አካል መሆኑን በመግለጽ፣ ባለፉት ስድስት ወራት እስራኤል በጋዜጠኞች ላይ የምትፈጽው ጥቃት መደጋገሙን በየእለቱ የሚደርሷቸውን ሪፖርቶች ዋቢ አድርገው አብራርተዋል፡፡

እስራኤል ባለፉት ስድስት ወራት በጋዛ በንጹሐን ፍልስጤማዊያን ላይ በፈጸመችው ተደጋጋሚ ጥቃት ቢያንስ 33 ሺህ ሰዎች ተገድለዋል፡፡

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

!

መንግሥት በባህር ዳርና ሌሎች ከተሞች ሙስሊሞች ላይ “የግፍ ግድያ” ፈጻሚዎችን “በአስቸኳይ” ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪ ቀረበ ዕለተ ዐርብ ሚያዝያ 4 - 2016 | ሸዋል 3 – 1445 የኢትዮ...
12/04/2024

መንግሥት በባህር ዳርና ሌሎች ከተሞች ሙስሊሞች ላይ “የግፍ ግድያ” ፈጻሚዎችን “በአስቸኳይ” ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪ ቀረበ

ዕለተ ዐርብ ሚያዝያ 4 - 2016 | ሸዋል 3 – 1445

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ መንግሥት በአማራ ክልል ዋና መዲና ባህር ዳር እና ሌሎችም የክልሉ ከተሞች ሙስሊሞችን እየለዩ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ መንግሥት ግድያውን “የፈጸሙትንና ያስፈጸሙትን” በማጣራት “አስቸኳይ ለፍርድ በማቅረብ” የሕግ የበላይነትን የማስፈን ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቋል፡፡

ጉባዔው ትናንት ሐሙስ ሚያዝያ 3/2016 ያወጣው መግለጫ የመጣው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) በአማራ ክልል “ሙስሊሞችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶች” ይፈጸማሉ ካለ በኋላ ነው፡፡ መጅሊስ በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ በክልሉ የሚፈጸሙት ጥቃቶች ከዛሬ ነገ ይሻሻላሉ በሚል “በትዕግሥት ለመያዝ ቢሞከርም” ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሱ ሄደዋል ብሎ ነበር፡፡

በባህር ዳር ከተማ መጋቢት 29/2016 በታጣቂዎች ተፈጽሟል በተባለው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ግለሰቦችን ጨምሮ 5 ምዕመናን መገደላቸውን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ቀደም ብሎ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በትናንትናው መግለጫ ላይ በባህር ዳርና ሌሎችም አካባቢዎች የተፈጸመው ጥቃት “ለዘመናት ጠንካራ የመከባበርና የአብሮነት እሴት ባላቸው” እስልምና እና ክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል “የጥላቻ ስሜት በመዝራት በመካከላቸው አለመተማመን እንዲፈጠር ተፈልጎ የሚሠራ” መሆኑን ገልጿል፡፡

ጉባዔው ይህን ተግባር ሁሉም ሊያወግዘው የሚገባ መሆኑን በማስታወስ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ የሁሉንም አካላት ቀና ትብብር ጠይቋል፡፡

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥ ሙስሊሞች የግድያ፣ እገታ፣ መፈናቀል እና ዝርፊያ ሰላባ መደረጋቸውን በመጠቆም በአጠቃላይ በስምንት ወራት ውስጥ 80 ሙስሊሞች እንደተገደሉ ገልጾ ነበር፡፡

ምክር ቤቱ “በታጣቂዎች” ይፈጸማል ያለውን ይህን ግድያ እና ዝርፊያ “የማንንም እምነትና ብሔር የማይወክል” መሆኑንም በመጥቀስ፣ ይህን “እኩይ ተግባር” ለማስቆም መንግሥት፣ የክልሉ ሕዝብ፣ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖች እና የሃይማኖት አባቶች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ዒድ ሙባረክ
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

!

የዒድ ማግሥት ልዩ “ኸበር” ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 3 - 2016 | ሸዋል 2 – 1445 1445ኛው ዓ.ሂ የዒድ አል ፊጥር በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም ትናንት ሚያዝያ 2/2016 ተከ...
11/04/2024

የዒድ ማግሥት ልዩ “ኸበር”

ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 3 - 2016 | ሸዋል 2 – 1445

1445ኛው ዓ.ሂ የዒድ አል ፊጥር በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም ትናንት ሚያዝያ 2/2016 ተከብሮ ውሏል፡፡ በአብዛኞቹ የዓለም ሀገራት በዓሉ ሲከበር በጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማዊያን ግን እንደ ሌሎች የዓለም ሙስሊሞች በቤታቸው ከወዳጅ ዘመድ ጋር ባንድነት ለመደሰት አልታደሉም፡፡ ርሕራሔ በጎደለው መልኩ እሳት ከላይ በሚዘንብበት ጋዛ ውስጥ የዒድ በዓል በዕለቱ እንደነበረው አየር የጨፈገገ ሆኖ አልፏል፡፡ ከጋዛ አቅራቢያ የሚገኘው “ጀበሊያ” የስደተኞች ጣቢያም ከግድያ ቢተርፉም ቤተ ዘመዶቻቸውን በተነጠቁ ፍልስጤማዊያን ሐዘን ያጠላበት እንደነበር ታይቷል፡፡ እንደ ኡሙ ኒዳል አቡ ዑመይራ ያሉ ፍልስጤማዊያን እናቶች ደግሞ የእስራኤል የቦንብ ዝናብ በነጠቃቸው ቤተሰቦች ቀብር ዙርያ እንባቸውን ሲያፈስሱ ለመዋል ተገደዋል፡፡ ኡሙ ኒዳል በሥፍራው ላገኛት የአሶሽየትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ “[ልጆቹ] ‘አባታችን ናፍቆናል፣ የት ነው ያለው?’ ይሉኛል፡፡ እኔም ‘እርሱ በቀጣይ ዓለም ቤቱ ነው ያለው’ የሚል ምላሽ ስሰጣቸው ማልቀስ ስለሚጀምሩ አብሬያቸው አለቅሳለሁ” ብላዋለች፡፡ የኡሙ ኒዳል እንባ የጋዛ የዒድ መልክ ሆኖ አልፏል፡፡

የዘንድሮው የዒድ አል ፊጥር የጋዛ አከባበር በሌሎች የዓለም ሀገራትም ተጋብቷል፡፡ በርግጥ ከበዓሉ አስቀድሞ እንደ ሚቺጋን የኢማሞች ምክር ቤት ዐይነቶች የዒዱን አከባበር ወደ ጎን በመተው ዕለቱን (ሳምንቱንም ጭምር) ለጋዛ ተጎጂዎች ድጋፍ ለማሰባሰብ ውሳኔ ማሳለፋቸውን ቀድመው አሳውቀው ለትግበራው ሲንቀሳቀሱ ነበር፡፡ በአንጻሩ የበዓሉ ድባብ ሳይደበዝዝ ከፍልስጤማዊያን ወንድም እና እሕቶች ጎን መቆማችንንም እናሳያለን ያሉ የበርካታ ሀገራት ምዕመናን በዓሉን ሲያከብሩ አብሮነታችንን ያሳይልናል ያሉትን ሁሉ አድርገዋል፡፡ ይህን የአብሮነት የዒድ ውሎ ካስተናገዱ የዓለም ሀገራት ውስጥ ሦስቱን መርጠናል፡፡

1/ ኬንያ - ናይሮቢ

በኬንያ ዋና መዲና ናይሮቢ በሚገኘው ራሕማ መስጂድ የዒድ ሰላት የታደሙ ምዕመናን ፍልስጤማዊያን ወንድም እና እሕቶቻቸውን ካሰቡት ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ለዒድ ሰላት ለተሰበሰቡት የሀገሬው ዜጎች በጋዛ በፍልስጤማዊያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ ያስታወሱት የመስጂዱ ኢማም ዓብዱራሕማን ሙሳ፣ “በዓሉን ስናከብር የፍልስጤም ወንድም እና እሕቶችንን በፍጹም ልንዘነጋቸው አይገባም” ሲሉ የፍልስጤማዊያን ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኢማም ዓብዱራሕማን “ፍልስጤማዊያን ተወርረው ግፍ እየተፈጸመባቸው ዓለም ምንም እንዳልተፈጠረ በዝምታ እየተመለከተ” እንደሆነ በቁጭት ያነሱት ጉዳይ ነው።

2/ ቱርክ - ኢስታምቡል

በቱርክ ኢስታምቡል ውስጥ በሚገኘው ታሪካዊው ሀጊያ ሶፍያ መስጂድ የሰገዱ ምዕመናን በመስጂዱ ሲገኙ ለፍልስጤማዊያን ድምጻቸውን ማሰማቱን ጎን ለጎን አካሄደዋል፡፡ በሺሕዎች በታደሙበት የዒድ ሰላት ምዕመናን የፍልስጤምን ሰንደቅ አላማ እያውለበለቡ ከጋዛ ተጎጂዎች ጎን መቆማቸውን ባሰሟቸው መፈክሮች ሲያስተጋቡ ነበር፡፡ የቱርካዊያኑ ድጋፍ በሀጊያ ሶፍያ መስጂድ ውስጥ ብቻ የተገደበ አልሆነም፡፡ የሀገራቸው ፕሬዝዳንት ሬሲብ ጠይብ ኤርዶዋንም በዋዜማው ባስተላለፉት የበዓል መልእክታቸው ወቅት ጋዛን ሳያነሱ አላለፉም፡፡ ኤርዶዋን በመልዕክታቸው ከፍልስጤማዊያን ጎን መቆማቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

3/ ኤንዶኔዥያ - ጃካርታ

በርካታ ሙስሊም ነዋሪዎች ባሉባት ኢንዶኔዥያ በዒድ ሰላት የታደሙ ምዕመናን ቁጥር እንደተለመደው ከፍተኛ ሆኖ የተመዘገበበት ነው፡፡ በተለይ በመዲናዋ ጃካርታ የዒድ ሰላት ታዳሚዎች አደባባዮችን እና መስጂዶችን አጥለቅልቀው ታይተዋል፡፡ የከተማዋ ትልቁ መስጂድ የሆነው ኢስቲቅላል በማለዳ የጎረፉ ምዕመናንን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡ በዚህ የሰላት ክፍለ ጊዜ ንግግር ያደረጉት የኢንዶኔዥያ የመሳጂዶች ምክር ቤት የአማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ ጂምሊ አስሺዲቂ፣ በጋዛ እየተካሄደ ያለው የሃይማኖት ጦርነት እንዳልሆነ በመጥቀስ “ይህ ጊዜ ሙስሊሞችም ሆነ ሙስሊም ያልሆኑ ለሰብዓዊነት የምንቆምበት ነው” ሲሉ ለሰው ልጆች ሁሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

[ይህ ጥንቅር ከአልጀዚራ፣ ቲ አር ቲ፣ ዴይሊ ሰባህ፣ ሀፊንግተን ፖስት፣ ከኢንዲያን ታይምስ እና አሶሽትድ በተገኘ መረጃ የተዘጋጀ ነው፡፡]

🎉 ዒድ ሙባረክ ✨
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

   በምዕራፍ ሁለት ልዩ ዝግጅት ምሽት 2:00 ጀምሮ🎉 ዒድ ሙባረክ ✨★★★★★ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል ጥራት ለመከታተል👇ፍሪኩዌንሲ:- 11545ሲምቦልሬት:- 45000ፖላራይዜሽ...
10/04/2024




በምዕራፍ ሁለት ልዩ ዝግጅት
ምሽት 2:00 ጀምሮ

🎉 ዒድ ሙባረክ ✨
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

    በምዕራፍ ሁለት ልዩ ዝግጅት ምሽት 2:00 ጀምሮ🎉 ዒድ ሙባረክ ✨★★★★★ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል ጥራት ለመከታተል👇ፍሪኩዌንሲ:- 11545ሲምቦልሬት:- 45000ፖላራይዜ...
10/04/2024





በምዕራፍ ሁለት ልዩ ዝግጅት
ምሽት 2:00 ጀምሮ

🎉 ዒድ ሙባረክ ✨
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

 በምዕራፍ ሁለት ልዩ ዝግጅት ምሽት 2:00 ጀምሮ🎉 ዒድ ሙባረክ ✨★★★★★ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል ጥራት ለመከታተል👇ፍሪኩዌንሲ:- 11545ሲምቦልሬት:- 45000ፖላራይዜሽን:...
10/04/2024



በምዕራፍ ሁለት ልዩ ዝግጅት
ምሽት 2:00 ጀምሮ

🎉 ዒድ ሙባረክ ✨
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

     በዒድ እለት  መቶ ሺ ብሩ ባለቤቱን አገኘ!  በዕለተ ዒድ ልዩ ዝግጅት ምሽት ከ12:30 ጀምሮ 🎉 ዒድ ሙባረክ ✨★★★★★ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል ጥራት ለመከታተል👇ፍሪ...
10/04/2024




በዒድ እለት መቶ ሺ ብሩ ባለቤቱን አገኘ!



በዕለተ ዒድ ልዩ ዝግጅት ምሽት ከ12:30 ጀምሮ

🎉 ዒድ ሙባረክ ✨
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

    50ኛው ዓመት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአንድነት ንቅናቄ በምዕራፍ አንድ ልዩ ዝግጅት ቀን 7:00 ጀምሮ🎉 ዒድ ሙባረክ ✨★★★★★ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል ጥራት ለመከታተል👇...
10/04/2024




50ኛው ዓመት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአንድነት ንቅናቄ

በምዕራፍ አንድ ልዩ ዝግጅት
ቀን 7:00 ጀምሮ

🎉 ዒድ ሙባረክ ✨
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

   የዑምራው አሸናፊ ማን ይሆን?በምዕራፍ አንድ ልዩ ዝግጅት ቀን 7:00 ጀምሮ🎉 ዒድ ሙባረክ ✨★★★★★ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል ጥራት ለመከታተል👇ፍሪኩዌንሲ:- 11545ሲምቦ...
10/04/2024




የዑምራው አሸናፊ ማን ይሆን?

በምዕራፍ አንድ ልዩ ዝግጅት
ቀን 7:00 ጀምሮ

🎉 ዒድ ሙባረክ ✨
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

   በምዕራፍ አንድ ልዩ ዝግጅት ቀን 7:00 ጀምሮ🎉 ዒድ ሙባረክ ✨★★★★★ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል ጥራት ለመከታተል👇ፍሪኩዌንሲ:- 11545ሲምቦልሬት:- 45000ፖላራይዜሽን...
10/04/2024




በምዕራፍ አንድ ልዩ ዝግጅት
ቀን 7:00 ጀምሮ

🎉 ዒድ ሙባረክ ✨
★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★


!

Address

Piassa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Minber Tv/ሚንበር ቲቪ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Minber Tv/ሚንበር ቲቪ:

Videos

Share