![ሸገር ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቋል!የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሊጉ ከተባለ በኋላ 48ኛው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ያለምንም ግብ አቻ ተጠናቋል።በአጠቃላይ በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ የጨዋታ እንቅ...](https://img3.medioq.com/745/719/1180123157457198.jpg)
02/02/2025
ሸገር ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቋል!
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሊጉ ከተባለ በኋላ 48ኛው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ያለምንም ግብ አቻ ተጠናቋል።
በአጠቃላይ በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ የጨዋታ እንቅስቃሴና ሙከራ ያሳዩት ፈረሰኞቹ ለባለሙያ ውሳኔ የሚተው የፍፁም ቅጣት ምት የጥፋት ጥያቄን አስከትሎ ጨዋታው ተጠናቋል።
በሁለተኛው አጋማሽ ወጣቶቹን ባለተሰጥኦ ተጨዋቾች ኪሩቤል ደሳለኝና ሚኪያስ ፀጋዬን ቀይረው ያስገቡት ኢትዮጵያ ቡናዎች በበረከት ወልዴ ጉዳት የሳሳውን የመሀል ክፍል በመቆጣጠር የተሻለ የጎል እድል መፍጠር ችለዋል።
የጨዋታውን አጠቃላይ እንቅስቃሴና ብዙ መልኮች የነበሩትን ጨዋታና የታክቲክ ፍልሚያ በመደበኛ የባላገሩ ሜዳ ፕሮግራም በዝርዝር እናቀርባለን።
ባላገሩ ስፖርት