Negarit - ነጋሪት

Negarit - ነጋሪት Negarit is a digital social media platform, providing news, information, insiders leaks and analysis for Ethiopian people.

Negarit is an independent and non partisan digital social media platform designed to inform, inspire and engage the people of Ethiopia. Reaching people through high-standard, high-quality and high impact multimedia content available in different formats such as youtube, facebook, twitter and other social media formats. Negarit recognizes and appreciates the efforts that citizens make each day in b

uilding a better Ethiopia for all people. Negarit strives to empower disadvantaged groups such as women, youth and people with disabilities etc. Working within collaboration of all people to enlighten, educate and strengthen citizens in order to expose corruption and to create unity between neighboring countries.

06/12/2024
30/11/2024

የኪውባው ፕሬዝደንት ፊደል ካስትሮ ከመኝታቸው ተነስተው ልብሳቸውን ከለበሱ በኋላ ጫማቸውን ለማድረግ ጎንበስ ሲሉ ፡ ተወልውለው በስርአት በሚቀመጡት ጫማዎቻቸው ላይ አቧራ መሰል ብናኝ ተነስንሶ ተመለከቱ ። ተጠራጣሪው ካስትሮ ጫማቸውን ለማንሳት የተዘረጉ እጆቻቸውን ሰብስበው ከሳቸው ጋር በአንድ ጊቢ የሚኖረውን የልዩ ጥበቃ ሃላፊያቸው ጋር ደወሉ ።........................

የቀድሞዉ የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ ወደ ስልጣን እንደወጡ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኙት አሜሪካንን ነበር ። ሆኖም አሜሪካ ኪውባን እንድትደግፍ እና ስለሁለቱ ሃገራት ወዳጅነት ላይ ለመምከር በነጩ ቤተመንግስት ለተገኙት ካስትሮ የሃገር መሪን ክብር በሚመጥን መልኩ የሚያስተናግዳቸው ፕሬዝደንት ጠፋ ።

የወቅቱ የአሜሪካን ፕሬዝደንት ዴቪድ አይዘአወር የልኡካን ቡድናቸውን እየመሩ አሜሪካንን ለመጎብኘት የሄዱት ካስትሮን ጋዜጠኞች ባልተገኙበትና በዝግ በተካሄደ የአንድ ሰአት የመወያያ ጊዜ ከመስጠት ውጭ በቂ የመነጋገሪያ ጊዜ ሊሰጣቸው ፈቃደኛ አልሆኑም ።

ይባስ ብሎም ከካስትሮ ጉብኝት በኋላም አሜሪካ ለኪውባ የወዳጅነት ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ ካስትሮን ከስልጣን ወይም ከምድር ለማስወገድ በስለላ ድርጅቷ CIA በኩል የኪውባ ስደተኞችን አስታጥቃ የእጅ አዙር ጦርነት ከፈተች ።

ለዚህ የአሜሪካ ተግባር ኪውባም በሃገሯ የሚገኙ የአሜሪካን ኩባንያዎች ዘግታ የቀሩትንም ወረሰች ። አለመግባባቱ ጦዞ አሜሪካ የኪውባን ስደተኞችና ቅጥረኛ ወታደሮችን አሰማርታ መጠነ ሰፊ ወረራ ጀመረች ። ኪውባ ይህን የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት ለመገዳደር ከኮሙኒስት ሃገር ሶቪየት ጋር ወዳጅነቷን ማጥበቅ ነበረባት ።

የካስትሮ መንግስት ከቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ባገኘው የጦር መሳሪያ እርዳታ ተቃዋሚዎቹን ከማጥቃት አልፎ ትላልቅ ድንበር አቋራጭ ሚሳይል ወደ አሜሪካ ከተሞች አነጣጥሮ ጦርነቱን በአሜሪካ በኪውባና በሩሲያ መሃከል እንዲሆን አድርጎ መጠባበቅ ጀመረ ።

የአሜሪካ ከተሞች ከኪውባ በሚሰነዘር የኒውክሊየር ጥቃት ሊፈፀምባቸው እንደሚችል ስጋት በመፈጠሩ አሜሪካ ሶቪየት ህብረትን ኪውባን መርዳት እንድታቆም አለበለዚያ ግን ፀቧ ከኪውባ ሳይሆን ከሶቪየት ህብረት ጋር እንደሆነ ማስጠንቀቅ ያዘች

አሜሪካ የተፋጠጠችው ከድሃዋ ኪውባ ጋር ሳይሆን ከምንጊዜም ተፎካካሪዋ ( ሶቪየት ህብረት ( ሩሲያ ) ጋር መሆኑን ስታውቅ ወደቀልቧ መመለስ ጀመረች ። በሁለቱ ሃያላን ሃገራት መፈራራትም በኪውባ ሊፈፀም የታቀደው የአሜሪካ የእጅ አዙር መጠነ ሰፊ ወረራ እቅድ ተሰረዘ ።

ኪውባ ከጎኗ ቆማ እስኪ የሚነካሽን አያለሁ ባለቻት ሩሲያ አማካኝነት ከአሜሪካን ወታደራዊ ጥቃት ተረፈች ። ይህን የተገነዘቡት የአሜሪካ መሪዎች ኪውባን በኤኮኖሚ አሽመድምዶ እግራቸው ስር ለማንበርከክ ሌላ እቅድ አወጡ ። ማእቀብ መጣል ።

አሜሪካ በኪውባ ላይ ያኔ የጣለችው ማእቀብ ከዛሬ ነገ ኪውባን እጄ ላይ ይጥልልኛል ብላ ብታስብም በፊደል ካስትሮ ጠንካራ አመራርና በህዝቧ ብርታት ማእቀቧ ሊሰራ አልቻለም ። ይህን የተረዱት የአሜሪካ መሪዎች ሁሉም ነገር የሚጠናቀቀው ካስትሮ ከዚህ አለም በሞት ሲሰናበት ነው ብለው በማሰብ ካስትሮን የመግደል ተልእኮ ለስለላ ድርጅቷ ለ CIA ተሰጠው ።

ይህ ተልእኮ በየጊዜው ዩናይትድ ስቴትስን በመሯት ሰባት መሪዎች ሳይቀየር ከስድስት መቶ ጊዜ በላይ ካስትሮን ለመግደል CIA ወገቡን አስሮ ዶላሩን መንዝሮ መሞከር ጀመረ ።.................................................................................................................

ፊደል ካስትሮ በመኖሪያ ቤታቸው በሚገኘው የመዋኛ ገንዳ ውስጥ ጥቂት ደቂቃዎች ለማሳለፍ የመዋኛ ቁምጣቸውን ለብሰው እየሄዱ ሳለ ከብዙ የግድያ ሙከራ ያዳናቸው የልዩ ጥበቃ ክፍል ሃላፊው ካለወትሮው አስቆማቸውና ።
" ውሃውን መመርመር ሳይኖርብን አይቀርምና ጓድ ፕሬዝዳንትእባክህ አረፍ በል " አላቸው ።.........................
የውሃው ናሙና ተወስዶ በላቦራቶሪ ሲታይ በርግጥም የመዋኛ ገንዳው ውሃ ለሞት በሚያደርስ የቆዳ በሽታ በሚያመጣ ፈንገስ ተመርዞ ነበር ።................
የአሜሪካው C.I.A ይህ የግድያ ሙከራ እንደከሸፈ ሲያውቅ botulinum የሚባል አደገኛ ኬሚካል ፕሪዝዳንቱ በሚወዱት ቶስካኖ ሲጋራ ውስጥ በመክተት ወደ ፕሬዝዳንቱ መኖሪያ በስውር አስገብቶ የፕሬዝዳንቱን መሞት መጠበቅ ጀመረ ። ነገርግን ይሀው የጥበቃ ክፍል ሃላፊ በሲጋራዎቹ ላይ ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ ሲጋሮቹ እንደተመረዙ ታወቀ..................
በተለያየ መንገድ ፕሬዝዳንቱን ለመግደል ሳይታክት የሚሞክረው C.I.A ፕሬዝዳንቱ የሚውጡትን አይነት ተመሳሳይ ክኒን በመድሃኒት ብልቃጣቸው ውስጥ በመክተት ለመግደል ያደረገውም ሙከራ ከሸፈ ።..........
በስለላ ድርጅቱ በተመለመለች የሚወዷት ፍቅረኛቸው ተመርዘው ይህችን አለም እንዲሰናበቱ የታሰበውም ሙከራ ሳይሳካ ቀረ ።
ይህ ሙከራ ይሳካል ተብሎ የታሰበው የካስትሮ የቀድሞ ፍቅረኛ በነበረችው በማሪታ ሎሬንዝ ነበር ፡ ካስትሮን ለመግደል ከምትኖርበት አሜሪካ ወደ ኪውባ ሃቫና የተመለሰችውና ድርጊቱን ከፈፀመች በዶላር እንደሚያንበሸብሿት በCIA ሰወች ቃል የተገባላት ማሪታ ሎሬንስ ካስትሮን ለማግኘት ብዙም ችግር አልገጠማትም ነበር ።
ሆኖም ካስትሮን አግኝታ ፊት ለፊቱ ስትቆም ፍቅር አሸነፈና ያንን ክፋት የመፈፀም ወኔዋ ከዳት ። እቅፉ ውስጥ ሆና እያለቀሰች ፊደል አንተን እንድገድል ነው የመጣሁት ነገር ግን ልገድልህ አልችልም። ምንም ያደረከኝ ነገር የለም ብላ የስለላ ድርጅቱን እቅድ ነግራ የታሰበውን እቅድ አከሸፈችው ።
....................
በስለላ ድርጅቱ በልዩ ትእዛዝ ተመርቶ ካስትሮ ቢሮ እንዲገባ ተሞክሮ የነበረው እስክርቢቶም ወደቢሮው ሳይደርስ በቁጥጥር ስር የዋለው ግቡን ሳያሳካ ነበር ። ይህ እስክርቢቶ እጅግ መርዛማ ኬሚካል እንዲያመነጭ ተደርጎ የተሰራ በመሆኑ ፡ ፕሬዝደንቱ በስክርቢቶው መፃፍ ሲጀምሩ ኬሚካሉ መትነን ይጀምርና መተንፈሻ አካላቸውን መርዞ ከመቅፅፈት ለሞት የሚያበቃቸው ነበር ።...............
አንድ ቀን ደግሞ ፕሬዝደንት ፊደል ካስትሮ ከመኝታቸው ተነስተው ልብሳቸውን ከለበሱ በኋላ ጫማቸውን ለማድረግ ጎንበስ ሲሉ ፡ ተወልውለው በሚቀመጡት ጫማዎቻቸው ላይ አቧራ መሰል ብናኝ ተነስንሶ ተመለከቱ ። ተጠራጣሪው ካስትሮ ወዲያውኑ እጆቻቸውን ሰብስበው ከርሳቸው ጋር በአንድ ጊቢ የሚኖረውን የልዩ ጥበቃ ክፍል ሃላፊ ጋር ደወሉ ። ጫማዎቻቸው በጓንት ተይዘው ወደላቦራቶሪ ተልከው የተገኘው ውጤት ልማደኛው CIA ፕሬዝደንቱን በአቧራ መሰል ገዳይ ኬሚካል በጫማቸው ውስጥ በመበተን ያቀደው ሙከራ እንደነበር ታወቀ
....................
ከገዳይ ባክቴሪያ በተሰራ መሃረብ ........................
ለሃቫናው ሂልተን ሆቴል ዌይተር ማባበያ በመስጠት ፕሬዝዳንቱ የሚወዱትን ሚልክ ሼክ በመመረዝ ለመግደል መሞከር...................
በአልሞ ተኳሾች .....................
ለንግግር በሚወጡበት ፖዲየም ስር ፈንጂ በመቅበር..............
እና በሌሎች ብዙ ሙከራዎች በተለያዩ የአሜሪካን ፕሬዝዳንቶች ትእዛዝ ማለትም
በፕሬዝዳንት Eisenhower: 38 ጊዜ
በ Kennedy: 42 ጊዜ
በ Johnson: 72 ጊዜ
በ Nixon: ዘመነ መንግስት 184 ጊዜ
በ Carter: 64
በ Reagan: 197
Bush Sr: 16
በመጨረሻም በ Clinton: 21 ጊዜ የመግደል ሙከራ የተደረገባቸውና ኩባን ለግማሽ ክፍለዘመን የመሩት የኩባው ፊደል ካስትሮ ከተደረገባቸው ከ 600 በላይ ሙከራዎች ተርፈው በ90 አመታቸው በተፈጥሮ ሞት መሞታቸው አስገራሚ ነው ። ኪውባም ለሃምሳ ምናምን አመት በተጣለባት ማእቀብ ሳትበገር ዛሬም ብርቱ ሆና ቀጥላለች ።

Wasihune Tesfaye

አቶ አብነት ገብረመስቀል ከሁለት ቢሊየን ብር በላይ የትርፍ ድርሻ ቢከፈላቸውም በአሁን ሰአት ግን ሰባራ ሳንቲም በባንክ ሒሳባቸው ውስጥ የለም ሲሉ  ሼህ መሐመድ ለፍርድ ቤት ገለፁ ።ሼኩ ይህ...
29/11/2024

አቶ አብነት ገብረመስቀል ከሁለት ቢሊየን ብር በላይ የትርፍ ድርሻ ቢከፈላቸውም በአሁን ሰአት ግን ሰባራ ሳንቲም በባንክ ሒሳባቸው ውስጥ የለም ሲሉ ሼህ መሐመድ ለፍርድ ቤት ገለፁ ።

ሼኩ ይህን የገለፁት አቶ አብነትገብረመስቀል የገንዘብ እግድ ይነሳልእ ብለው ባቀረቡት ማመልከቻ ላይ በሰጡት መልስ ነው ።

አቶ አብነት ገብረመስቀል ከዚህ በፊት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የውል ጉዳዮች ፍታብሔር ችሎት የተጣለብኝ የገንዘብ እግድ ይረሳልኝ ብለው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል ።

አቶ አብነት ገብረመስቀል ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ ም በድጋሚ ፅፈው ባቀረቡት እግድ ይረሳልኝ ጥያቄን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰኞ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓም ተመልክቶቷል ።

ችሎቱ በእለቱ በቀረበው የአቶ አብነት ጥያቄ ላይ ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቆ አራት ገፅ የያዘ የፅሁፍ ምላሽለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል ።

በዚህ ሰነድ ላይ የአቶ አብነት እግድ መነሳት የለበትም ብለው የገለፁት ሼክ መሐመድ አቶ አብነት በናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኋላ የተ የግ ማህበር ከሰጠሆቸው የ አስራ አምስት ፐርሰንት የአክሲዮን ድርሻ በየአመቱ በመቶ ሚሊዮንኖች የሚቆጠር የትርፍ ድርሻ የሚያገኙ እስከአሁን ድረስም ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የወሰዱ ቢሆንም ሰባራ ሳንቲም በባንክ ሒሳባቸው የለም እነዚህ እውነቶች በፍርድ ቤት ጭምር በተሰጡ ትዕዛዞች የተረጋገጡ ናቸው ።

ይህ ገንዘብ የት ደረሰ የሚለውን ምላሽ ከህግ አካላት የምንጠብቀው ይሆናል ። ባሳለፍነው የ2015 እና 2016 ዓ ም ብቻ ከናሽናል ኦይል ጂቡቲ 2 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ብር ከ 250 ሚሊዮን ብር ወደ ባንክ ሂሳባቸው ገቢ የተደረገ ቢሆንም በተመሳሳይ በኘሁን ወቅትም ሰባራ ሳንቲም በባንክ ሂሳባቸው ውስጥ የለም ሲል የሚያብራራው የሼኩ መቃወሚያ ሲቀጥልም

አቶ አብነት ገብረመስቀል ዐቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ተመስክሮባቸው እንደንፁህ የመቆጠር መብታቸው ቀርቶ በፍርድ ቤት ብይን የተሰጠ በመሆኑ ተከላክለው እስካላስተባበሉ ድረስ እንደወንጀለኛ እንዳይቆጠሩ መከላከል ይገባቸዋል ።

መንግስት አቶ አብነት ገብረመስቀል ከፍተኛ ህመም ላይ በመሆናቸው የቀረበባቸውን ክስ ለመከላከል በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ናቸው ብሎ ጤንነታቸው እስኪመለስ ለጊዜው ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጓል ።

ተከሳሹም በዚህ እድል ተጠቅመው ወደ ውጪ ሃገር የሄዱ ሲሆን አሁን ላይ ግን ጤንነታቸው ተስተካክሎ ጊዜአቸውን በኳስ ሜዳ እና እንደ ካሲኖ በመሳሰሉት መዝናኛ ቤቶችበማሳለፍ ላይ የሚገኙ ናቸው ።

አቶ አብነት ገብረመስቀል መንግስት ያደረገላቸውን ትብብር ዋጋ በመስጠት ወደ አገር ቤት ተመልሰው የፍርድ ሒደታቸውን መከታተል ሲገባቸው ይህንን አለማድረጋቸው ሌለላው ቢቀር እንካን ዐቃቤ ህግ ያስመሰከረባቸው በመሆኑ እንደወንጀለኛ እንዳይቆጠሩ ለራሳቸውም ስምና ክብር ሲሉ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት መከላከያ ማስረጃዎቻቸውን በማቅረብ እንደ ንፁህየመገመት ህገመንግስታዊ መብታቸውን ለማስመለስአልፈለጉም ። የሚለው የባለሐብቱ መቃወሚያ ይህንን አለማድረጋቸው አቶ አብነት ግልፅ በሆነ እና በማያሻማ ሁኔታ እራሳቸው እና ገንዘባቸውን ለማሸሽ ተግባር ቅድሚያ የሚሰጡ ስለመሆናቸው አረጋጋጭ በመሆኑ በዚህ የአፈፃፀም ችሎት የተሠጠው ትዕዛዝ የሚነሳበት የህግ ምክንያት የለም ሲል ይቀጥልና
ስለዚህም የተከበረውፍርድ ቤት በዚህ ረገድ ቢሆን የፍርድ ባለዕዳ አቤቱታ የፍሬነገር መሠረት የሌለው መሆኑን ተገንዝቦልኝ አቤቱታቸው ውድቅ እንዲያደርገው አጠይቃለሁ ሲሉ ባለሐብቱ ለፍርድ ቤት ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ አስፍረው ተመልክተናል ።

ፍርድቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሰኞ ህዳር 23 ቀን 2017 አም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን በችሎት ተገኝተን ታዝበናል ።

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Haftom Tesfay Wedi Chichinya, Teddy Yalew, Manche Fergi, ...
28/11/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Haftom Tesfay Wedi Chichinya, Teddy Yalew, Manche Fergi, ባቲ ባቲ, Dabala Bekuma Balilla, Ahmed Mohammed Seyid, Ak Wah, Shafik, Amare Ejigu Tegegne, Tadesse Heta, Gech Yezhh, Kalaeb Yoni, Tomas T

  (አልረሳንም። እናንተን አንረሳም) [ይመጣል ዘመን። ይመጣል ጊዜ። ይደርሳል ወቅቱ] ∞  ∞  ∞  ∞  ∞  ∞"አዳምጠኝ፣ ይታገስን ገደሉብኝ"''አላለቅስም!''        ''አላፈገፍግም!...
21/11/2024

(አልረሳንም። እናንተን አንረሳም)





[ይመጣል ዘመን። ይመጣል ጊዜ። ይደርሳል ወቅቱ]

∞ ∞ ∞ ∞ ∞ ∞

"አዳምጠኝ፣ ይታገስን ገደሉብኝ"
''አላለቅስም!''
''አላፈገፍግም!''
''ይታገስን ጥዬ?''
''ቅዱስ ሚካኤል ምስክሬ ነው።''

''ዘጠኝ ጥለናል።''
''እኛ እየሞትን ነው።''
"ከልጄ ጋር ነበርኩ"
''እኔ እና እሱ ብቻ!''
''ለመንግስት አሳውቅ።''

"መዝግብ ይሄንን፤ #በሰማይ ነው የምቀበልህ "

¤

ደግመህ አንብበውማ፦ ይሄ እኮ ተራ ምልልስ አይደለም። ይሄ ዝም ብሎ ዘራፍ ዘራፌዋ አይደለም። እንዴኤኤኤ! ይሄማ ድክሞ እንጉርጉሮ፣ ውዳቂ ኑዛዜ፣ የማይረባ ብሶት አይደለም። ጌታዬ ይሄ - 'ቻው - እንቶኔን ሰላም በልልኝ' አይነት ስንብት አይደለም። አይደለም። ኧረ አይደለም። ይሄ እንደዛ አይደለም።

¤

(አይደለማ!)

¤

እዚህ ምልልስ ውስጥ ፍልስፍና አለ። ትውፊት ( Mythology) አለ። ቀኖና (Norms) አለ። የልዕልና ንኅፅሮት (Conviction) አለ። ማንነት (Identity) አለ። ምንነት (Meaning) አለ። #ታላቅነት አለ። #ትልቅነት አለ። አንተነት አለ። እኔነት አለ። እኛነት አለ። . . . #ኢትዮጵያዊነት አለ።

ዕምነት-ማተብ አለ።
ታማኝነት አለ።
ደፋርነት አለ።
#ወንድ፣ ወንድነት አለ።

¤

( ተረዳው እሸቴን)

¤

''ለመንግስት አሳውቅ'' ሲልህ Hierarchyን ማወቅ አለ። ስርአትን፣ Stateን ማክበር አለ። Structureን መረዳት አለ። ጨዋነት አለ። የሸዋ ፈሊጥ፣ የሸዋ ብልሃት፣ የሸዋ ደርባባነት አለ። ሸዋ አለ በውስጡ።

¤

(ቃል ኑዛዜውን Decode እናድርገዋ!)

¤

''አላፈገፍግም'' ሲልህ በውስጡ ብዙ ነገር አለ። ሠፊ ነገር አለ። ጥልቅ ነገር አለ። Embedded የሆነ፣ ልገልጸው የማይቻለኝ Value አለ።

መስዋዕትነት አለ።
ሰማዕትነት አለ።
የአገር ፍቅር አለ።
' #እኔ ሞቼ #አንተ ተከብረህ ኑር' አለ።

¤

(ፃፈው ንግግሩን፣ #ንገረው ለልጅህ)

¤

''ይታገስን ጥዬ?'' ሲልህ አባትነት አለ። ፍቅር አለ። ማፍቀር አለ። ታማኝነት አለ።ሎሌነት አለ። ወኔ አለ። ሰብአዊነት አለ። ሰዋዊነት አለ። ክብር አለ። Grace ግርማ ሞገስ አለ።

¤

ይመጣል ዘመን።
ይመጣል ጊዜ።
ይደርሳል ወቅቱ -

እመነኝ! ይመጣል ዘመን፦ ''Where are you from?'' ስትባል፦ ''I am From እሸቴ's Country'' ብለህ በኩራት የምትመልስበት ዘመን ይመጣል ከፊትህ። ይመጣል ጊዜ። ይደርሳል ወቅቱ።

¤

ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ። እሸቴ ሞገስ። ይታገስ እሸቴ።

¤

( !!)

¤

''. . . ከተወለድሁኝ እስታሁን ወንድ እጄን ጨብጦት አያውቅም ነበረ፤ ሰዎች ሲሼሹ ተነስቼ ማራጋት ልማድ ነበረኝ፣ ጨለማ ከለከለኝ፡፡ እንደኔ አያድርጋችሁ፡፡ እንኳንስ የሀበሻ ጠላቴን ኢየሩሳሌም ዘምቼ ቱርኮችን አስለቅቃለሁኝ መስሎኝ ነበር፡፡ ወንድ ያቀፈ ወንድ ተመልሶ አይታቀፍም፡፡”

[አፄ ቴዎድሮስ (Rubenson, Acta II, 354) (ባህሩ ዘውዴ - የኢትዮጰያ ታሪክ ከ1847-1983 ፡ ገጽ45/ 46)]

¤

(ይመጣል ዘመን)

¤

''Where are you from?'' ስንባል፦ ''I am From እሸቴ's Country'' ብለን በኩራት የምንመልስበት ዘመን ይመጣል ከፊት። ይመጣል ጊዜ። ይደርሳል ወቅቱ።
© Eyob Mihreteab Amlesom 🙏🏻🙏🏻🙏🏻
ነፍስህ በሰላም ትረፍ እዬባ💔

Lualawi_ሉዓላዊ-ፕሮፌሰር_ብርሃኑ_ነጋ__የትምሕርት_ሚኒስትር__ከሉዓላዊ_ሚዲያ_ጋር ክፍል 2
12/11/2024

Lualawi_ሉዓላዊ-ፕሮፌሰር_ብርሃኑ_ነጋ__የትምሕርት_ሚኒስትር__ከሉዓላዊ_ሚዲያ_ጋር ክፍል 2

የገዛ ወንድሙን አግቶ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ  በፅኑ  እስራት  ተቀጣ ተከሳሽ የኔው ብርሀኑ የእንጅባራ ከተማ አሰተዳደር  ነዋሪ ሲሆን  በጥቅምት 19/ 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 6.30 ሰዓት...
08/11/2024

የገዛ ወንድሙን አግቶ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

ተከሳሽ የኔው ብርሀኑ የእንጅባራ ከተማ አሰተዳደር ነዋሪ ሲሆን በጥቅምት 19/ 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6.30 ሰዓት ከቢዳ ጀጎላ ት/ቤት የሚማረውን ወንድሙን ስልክ በመደወል የእናታችንን ልብስ ውሰድ ብሎ ከት/ቤት ከአሰወጣ በኋላ የ14 ዓመት ወንድሙን በማገት ከወላጅ ቤተሰቦቹ 1,000,000/አንድ ሚሊዮን ብር/ መጠየቁን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።

በሁኔታው የተደናገጡት የታጋች ቤተሰቦች ወዲያውኑ ለእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ በሰጡት ጥቆማ በተደረገ ብርቱ ክትትልና ቁጥጥር በሶስተኛው ቀን ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ሲሆን ከተደበቀበት ቢዳጀጎላ ቀበሌ ልዩ ስፍራ አማያስቲ ጎጥ ላይ እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል የላከ ሲሆን መዝገቡ የቀረበለት የአዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ የኔው ብርሃኑ በ7 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ሲል አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዋና ክፍል ያደረሰን መረጃ ያሳያል።

From His videos, I learned 4 key lessons about Women 1.  Marriage does not guarantee her loyalty or fidelity.2.  When fa...
06/11/2024

From His videos, I learned 4 key lessons about Women

1. Marriage does not guarantee her loyalty or fidelity.

2. When faced with money, women deny all moral values. Only their interests prevail

3. When they want to get something without making any effort, they are ready to make the worst compromises.

4. Even if she is married, she will always hope to meet a man who is wealthier than her husband. And if, unfortunately, she meets him, she will cheat on you without pity or remorse.

23/10/2024
አፈሩን አቅልጦ ወደ ነዳጅ የቀየረው ልጅ፣ እንዲህ በነዳጅ ጭማሪ ስንሰቃይ የት ሆኖ ነው?አፈር ሳይችግረን በነዳጅ መወደድ እንዲህ ስንገላታ ምነው ዝም ጨከንክ? 😭
17/10/2024

አፈሩን አቅልጦ ወደ ነዳጅ የቀየረው ልጅ፣ እንዲህ በነዳጅ ጭማሪ ስንሰቃይ የት ሆኖ ነው?

አፈር ሳይችግረን በነዳጅ መወደድ እንዲህ ስንገላታ ምነው ዝም ጨከንክ? 😭

የአፄ ዮሃንስ ልጅ የልዑል ራስ አርዓያ እና የአፄ ሚኒሊክ ልጅ የልዕልት ዘውዲቱ የጋብቻ ሽኝት ሥነ ሥርዓት።፣ከዛሬ 138 ዓመት በፊት በጥቅምት ወር 1875 ዓ.ም ፈረንሳዩ ሚስተር ሶለዬ ለን...
25/08/2024

የአፄ ዮሃንስ ልጅ የልዑል ራስ አርዓያ እና የአፄ ሚኒሊክ ልጅ የልዕልት ዘውዲቱ የጋብቻ ሽኝት ሥነ ሥርዓት።

ከዛሬ 138 ዓመት በፊት በጥቅምት ወር 1875 ዓ.ም ፈረንሳዩ ሚስተር ሶለዬ ለንግድ ስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ በነበረበት ጊዜ ሸዋ ላይ በዚያ ጊዜ የሸዋ ንጉሥ ከነበሩት ከንጉሥ ሚኒሊክ ጋር ተገናኝቶ ነበር። በዚህ አጋጣሚም የ 12 ዓመቱን የአፄ ዮሃንስ ልጅን የልዑል ራስ ሣህለ (አርዓያ) ሥላሴን እና የ7 ዓመቷን የንጉሥ ሚኒሊክ ልጅን የልዕልት ዘውዲቱን የጋብቻ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ የመገኘትና የመዘገብ እድል አግኝቶ ነበር።እኔም ባለኝ ትንሽ የፈረንሳይኛ ችሎታ ፈረንሳዊው ሚስተር ሶለዬ የጉዞዬ ማስታወሻ ብሎ ካሳተመው OBOK-LE CHOA-LE KAFFA ከሚለው መፅሃፍ ላይ ይህንን ክፍል ባጭሩ ተርጉሜ ለአንባቢዎች አቅርቤዋለሁ።

"ጥቅምት 9 ቀን 1875ዓ.ም ፦ በጠዋት የንጉሡን ከቤተ መንግስት መውጣት የሚያበስረውን የጥሩንባ እና የነጋሪት ድምፅ ሰማን ። እንደተነገረንና እንደተረዳነው ንጉሥ ሚኒሊክ የልጃቸውን ጋብቻ ምክያት በማድረግ ከጦር አለቆቻቸው አንዱ ከሆኑት ከራስ ጎበና የተላከላቸውን ስጦታ አካባቢው ከሚገኘው ሰፊ ሜዳ ላይ ለመቀበል ነው። እኛም ፈረሶቻችንን ጭነን ግማሽ ሰዓት ያህል ከተጓዝን በኋላ ቀጠሮው ቦታ ደረስን ቦታውም ትልቅ ሰፊ ሜዳ ሲሆን በቁጥቋጦ የተከፈለና አንዳንድ አጫጭር ዛፎች ያሉበት ቦታ ነው።

ንጉሡ አንድ ከሚያምር አመድማ በቅሎ ላይ የተቀመጡ ሲሆን የበቅሎው ኮርቻ በአረንጓዴ ሃር የተሰራና ዘርፈ ወርቅ ነው ። በአንድ ባለባበሱ ያማረ የጦር አዛዥም ታጅበዋል። ስጦታውን የሚያቀርበው የራስ ጎበና ልጅ ባል ሲሆን ስጦታውም 1300 ፈረስ ከዚህ ውስጥ 500 ባለኮርቻ ሲሆን 300 መቶ ደግሞ በብር ያጌጡ ናቸው።እንዲሁም 300 መቶ በቅሎ ከዚህም ውስጥ 100 ከኮርቻ ጋር ሲሆን ወርቅ፥ የዝሆን ጥርስ እና ከጥርኝ የሚገኘውንና ለሽቶ ስራ የሚያገለግለውን ፈሳሽ ነው።

ቀኑ በጣም ደስ የሚል ሲሆን በፀሃይ የሚያብረቀርቀው የፈረሶች ኮርቻና ባማረው ነጭና ቀይ በለበሱት ሰዎች ልብስ ለዓይን ልዩ ድምቀት ሰጥቶት ነበር።

ጥቅምት 10 ፦ የኔ ጓደኛ የሆነው አቶ ሊዮ የፎቶግራፍ ማንሻ ስለነበረው የሚታይ ነገር ፍለጋ በማለት በማለዳ ወጣን ነዋሪዎቹም እኛን ለማየት በሚያደርጉት ግርግር አንዳንድ አስቂኝ ነገሮች ጠፈጠሩ።

ጥቅምት 11 ፦ ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሃንስ የልጃቸውን እጮኛ ለመውሰድ ከመንግሥታቸው ሶስት ራሶችን ጨምሮ ታላላቅ ሰዎችን ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ ወይም ሁለት ሺህ ከሚሆኑ አጃቢዎች ጋር ወደ ንጉሥ ሚኒሊክ በመላካቸው ንጉሡም ዛሬ እነዚህን ሰዎች በክብር ይቀበሏቸዋል።

እኛም የእግር መንገዳችንን ካለንበት ሶስት ወይም አራት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ሰፈሩት የአጼ ዮሃንስ ሰዎች ጋ አደረግን።ይሁን እንጂ ክብርን በሚነካ ሁኔታ ነው የተቀበሉን በግልፅ ለመናገር ሊያስጠጉንም አልፈለጉም የፎቶግራፍ ማንሻችንም እንደ መተተኛ እና ክፉ ነገር እንደምናመጣ ነው ያስቆጠረን።ወደ አራት ሰዓት ግድም እንደተመለስን የንጉሱ ሠራዊት መሳሪያ ታጥቆና ተሰልፎ አገኝነው።

በ 5 ሰዓት የትግራይ ሰዎች በሰልፍ ሆነው ደረሱ ከፊት የተመረጡ ተኳሾች በብር በተጌጡ ፈረሶች ላይ ሆነው ተሰልፈዋል ጸጉራቸውን በክብ የተሰሩና ያንበሳ ጎፈር ያጠለቁ ናቸው።ከበፊተኛው ረድፍ ቀጥሎ ያሉት የተወሰነ ቁጥር ያላቸው የተማረኩ የቀድሞ የግብጽ ወታደር የነበሩ አሁን አጼ ዮሃንስን በማገልገል ላይ ያሉ የሱዳን ወታደሮች ናቸው።

ከዚህ ቀጥሎ ሶስት ራሶች በነጭ በቅሎዎች ላይ ተቀምጠው ይከተላሉ በእድሜው ከፍ ያለውና በመሃል የተቀመጠው ጸጉሩን በክብ ጉንጉን ተሰርቶታል።
ከራሶቹ ቀጥሎ በበቅሎ የተቀመጡ የተከበሩ ሰዎች በደማቅ ሰልፍ ይከተላሉ ከነሱ ጀርባ ብዙ ሰዎች በእግራቸው እየተከተሉ ይዘፍናሉ ጠመንጃቸውንም ወደ ላይ እያነሱ ይፎክራሉ።ራሶቹም ቀድመው ወደፊት ሲያልፉ በሰልፍ ሆኖ የሚጠባበቀው የንጉሡ ሠራዊት ሶስት ጊዜ እስከመሬት ዝቅ ብሎ እጅ በመንሳት ሰላምታ አቀረበላቸው።

ጥቅምት 12 ፦ የቤተ መንግሥቱ እና የከተማው ዋና ስራ የንጉሡን ስጦታ ከራሶቹ ጋር ለመጡት እንግዶች ማዳረስ ነበር ስጦታውም ፈረስ፥ በቅሎ ፥ጠመንጃ ፥ ልብስና ገንዘብ ነበር።በዚህም ስጦታ ተደስተው የትግራይ ሰዎች እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ሲጫወቱ አመሹ ።

ጥቅምት 13 ፦ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ንጉሥ ሚኒሊክ ልጃቸውን ልዕልት ዘውዲቱን የሚሸኙበት ቀን ነው። ከትግራይ የመጡት ራሶች አጼ ዮሃንስ እና የወደፊት ትዳር አጋሯ የሚሆነው ልጃቸው ልዑል ራስ ሣህለ(አርዓያ) ሥላሴ ወደሚጠብቋት ቦታ ወደ ቦሩ ሜዳ ይዘዋት ይሄዳሉ።

ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ሁሉም የሸዋ ሠራዊት እንደትናንቱ የጦር መሳሪያውን ይዞ ተሰልፏል ። ሁሉም ሰው በወርቃማና ብራማ ቀለም ያጌጠ የበዓል ልብስ ለብሰዋል።እኛም ከቤተ መንግሥቱ መውጫ በር በታች በኩል እንጠብቃለን። አጠገባችን ያለች አንዲት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ውድ የተክህኖ ልብስ ለብሰው ሥነ ሥርዓቱን ለመባረክ ወጥተዋል የቆዳ ልብስ የለበሱ መነኩሴዎችም አብረው ተቀላቅለዋል።

እኔ የምገኘው ሚስተር አልፈሪ ካስተዋወቀኝ አርመናዊ ከሆነው ከዶክተር ጎርጉሃስ አጠገብ ነው።አቶ ጎርጉሃስ የተወለደው ቁንስጥንጥኒያ ሲሆን በካይሮ የከረጅም የሙዚቃ መምህርነት በኋላ በትግራይ በኩል እዚህ መጥቶ ለንጉሡ የንግድ፥የጥበብ ውጤቶችንና ፥ የልብስ ስፌት ስራዎችን ይሰራል በተለይም በሃር ጨርቅ በሚሰራቸው ባርኔጣዎች ታዋቂነትን አትርፏል።

በ5 ሰዓት 50 ላይ የሽኝቱ ሥነ ስርዓት ከቤተ መንግሥቱ ተጀመረ በሰልፍ የሚጠብቁት ወታደሮችም ወደ ሰማይ በመተኮስ ሰላምታ አቅርበው ጠመንጃቸውን አፈሙዙን ዘቅዝቀው ትከሻቸው ላይ አሳረፉ ይህም ልዕልቲቱ ተለይታ የመሄዷን ሃዘን ለማሳየት ነው።

የሽኝቱ ሰልፍ በእውነት በጣም ግዙፍ የደመቀና ልዩ ነው የቤዛንታይንን ስርወ መንግሥት የበአል አከባበር ሥርዓትን የሚያስታውስ ነው። ከፊለፊት መጫኛቸው በውድ ያጌጡ 20 በቅሎዎች እያንዳንዳቸው ጨርቅ የለበሱ ሁለት ሁለት ነጋሪት ተጭነዋል።ኢትዮጵያ ውስጥ ነጋሪት የሃይል ማሳያ ምልክት ሲሆን በጦርነት ጊዜ ነጋሪት መያዝ ልክ በአውሮፓውያን ዘንድ ባንዲራ እንደመያዝ ይቆጠራል። ቀጥሎ የመጡት ቆዳ እና ቢጫ ልብስ የለበሱ ካህናት ሲሆኑ ሁሉም የካህናት ምልክት የሆነውን ነጭ ጥምጥም ጠምጥመዋል።

ከዚህ ቀጥሎ የመጡት ደግሞ ማንኛውም የህብረተሰቡ ክፍል ሲሆን ግማሹ በእግር፥በፈረስና በበቅሎ ናቸው። ትልልቆቹ መኳንንት የተለያዩ ቀለም ያላቸው ጃንጥላዎች ተይዞላቸዋል ወታደሮችም ደስ በሚል ዜማ እየዘፈኑ ይጨፍራሉ እንደተረጎሙልኝ በእውነት ወኔ የሚቀሰቅስ ነው።

ልዕልቲቷን በዙሪያዋ የከበቧት አገልጋዮች ወይም እመቤቶች በጨርቅ በተጌጡ በቅሎዎች ላይ ተቀምጠዋል እያንዳንዳቸው እግራቸው ድረስ የሚጎተት ቀሚስ ለብሰዋል። ሁለት ወይም ሶስት መቶ የሚገመቱት ሁሉም አጃቢ ሴቶች ውድ ልብስ ለብሰዋል እያንዳንዳቸውም የሙሽራዋን ቅርጫት ይዘዋል።በዚህ ጊዜ ነው የልብስና የጌጣጌጥ አይነት ሰልፍ ያየነው።

ከነሱ በኋላ ያሉ ሙዚቀኞች ዋሽንትና ጥሩንባ ይዘው ይጫወታሉ። አንድ ሴት የልዕልቲቱን የጸሎት መጽሃፍት በተለያየ ቀለም ባላቸው ክሮች በተሰሩ ቦርሳዎች አንግታ ይዛለች።

ከዚህ ቀጥሎ ሁለት ፊታቸው የተሸፈነ ወጣት ሴቶች ያማረ ወርቃማ ሃር ልብስ ለብሰው ባጌጡ በቅሎዎች ላይ ተቀምጠዋል።አለባበሳቸው ተመሳሳይ ሲሆን የበቅሎ ያዥያቸው ቁጥርም ተመሳሳይ ነው።አንደኛዋ ሶስት ጥላ የተያዘላት ሲሆን ሁለተኛዋ ግን ምንም አልተያዘላትም። እሷም የንጉሡ ማደጎ ልጅ እና የልዕልቲቱ አብሮ አደግ ስትሆን ከልዕልቲቱ የሚለያት ነገር ቢኖር ይኸው ጥላ ለሷ ያለመያዙ ብቻ ነው።

ሌላው ልብ የሚነካው ነገር የሰዎች ሁሉ እኩልነት ነው ታላላቆቹ ሰዎች ሁሉ ወደ አደባባይ ሲወጡ አጅቧቸው እንደሚወጣው እንደማንኛውም ተራ ሰው ነው እኩል ለብሰው የሚታዩት።ንጉሠ ነገሥቱም ቢሆን ልክ እንደ አንዱ መኮንን እንደ ሊቀ መኳሱ ነው ለብሶ የሚታየው።

በበቅሎ ላይ የተቀመጠች አንዲት ልጃገረድ የልዕልቲቱን ቀይ ቀለም ያለውና ጠርዙ በወርቅ ጌጥ የተጌጠውን ጫማ በጀርባዋ አዝላ ትከተላታለች። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኬደው በባዶ እግር ወይም በሰንደል ጫማ ነው ሽፍን ጫማ ነንጉሣውያን ቤተሰቦችና ለቤተክርስቲያን አለቆች ብቻ የተወሰነ ነው። በዚህ የተነሳ ትላልቅ ሰዎች ደረጃቸውን ለማሳየት ሲሉ ይጫሙታል።

ሰልፉ ከትግራይ በመጡት ራሶችና አጃቢዎቻቸው ተጋርዷል ማለት ይቻላል ትንሿ ንግሥት በአጠገባችን ስታልፍ ካህናቱ በከበሮና በጽናጽል ዳዊት በታቦተ ጽዮን ፊት እንዳሸበሽበው እያሸበሸቡና እየዘመሩ የሰማያዊውን ምርቃት ሁሉ አወረዱላት።

ከዚያም ቀጥሎ በጀርባቸው ጠጅና ጠላ የተሞላ እንስራ ያነገቱ ሴቶችና እንዲሁም የወጥ ቤት ሰራተኞች የምግብ መስሪያ እቃዎቻቸውን በብዛት በበቅሎና በአህያ ጭነው ይከተላሉ። ፈታዮችም በአህያና በበቅሎ ከተጫነ ጥጥ ጋር አብረው ይጓዛሉ። ጠቅላላ የሚጓዘው ጭነት ሁለት መቶ በቅሎና አህያ ይሆናል።ለሥጋ የሚሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ከብትም አብሮ ይጓዛል።

ወጣቷ ልዕልትም በዛሬው ምሽት በትግራይ ሰዎች ሰፈር አድራ ነገ በጥዋት የጋብቻው ስነ ሥርዓት ወደሚካሄድበት ወደ ቦሩ ሜዳ ትጓዛለች። የልዕልት ዘውዲቱና የልዑል ራስ ሣህለ (አርዓያ)ሥላሴ ጋብቻ የሚካሄደው በሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓት ነው። ይሁን እንጂ እድሜያቸው ገና የ7 እና 12 አመት ልጆች በመሆናቸው የትዳር ህይወታቸውን የሚጀምሩት ከአመታት በኋላ ይሆናል።"

ከታሪክ እንደምንረዳው አፄ ዮሃንስም ሆኑ አፄ ሚኒሊክ ለአገራቸው ኢትዮጵያ ነፃነት አንድነትና እድገት ይጥሩ የነበሩና በትግራይ እና በአማራ ነገሥታት መካካል ይነሳ የነበረውን የሥልጣን ሽኩቻ በጋብቻ በማስተሳሰር የአማራን እና የትግራይን ማህበረሰብ አንድ ለማድረግ ጥረት ማድረጋቸውን ይህ ጽሁፍ በግልጽ ያስረዳናል። ይሁን እንጂ አለመታደል ሆነና ልዑል ራስ ሣህለ (አርዓያ)ሥላሴ በወጣትነት ዘመኑ ከልዕልት ዘውዲቱ ልጅ ሳያፈራ 21 ዓመቱ በሞት በመለየቱ ልዕልት ዘውዲቱም ወደ ቤተሰቦቿ ተመልሳለች። ከዚህም ጋብቻ የሚወለደው ህፃን ዙፋኑን ወርሶ ሁለቱንም ማህበረሰቦች አንድ አድርጎ ይገዛል የሚለው ሀሳብም ሳይሳካ ቀርቷል።

የዘውዳዊው ሥርዓት መውደቅን ተከትሎ የትግራይን ሕዝብ ከደርግ አገዛዝ ነፃ እናወጣለን ብለው የተነሱት አማፅያንም በትግራይ ማህበረሰብ ሥነ ልቦና ውስጥ ጨርሶ ያልነበረን የአማራ ማህበረሰብን ጠላት ያደረገ ፤የመገንጠልና ዘርን መሠረት ያደረገ የቅኝ ገዥዎች ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በመከተላቸው ዛሬ እንደምናየው ለአገራቸው ነፃነትና አንድነት በጋራ ሲታገሉ የኖሩትን የትግራይና የአማራ ማህበረሰቦችን ለከፍተኛ ቀውስና ችግር ዳርገው ኢትዮጵያንም ለከፍተኛ አደጋ አጋልጠው ሁለቱን ማህበረሰቦች ማቆሚያ ለሌለው የርስ በርስ ጦርነት ዳርገዋቸዋል።

ጌቱ ከፈረንሳይ

ዜና...!ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትን በተመለከተ የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሰርኩላር አስተላልፏል።...
19/08/2024

ዜና...!

ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትን በተመለከተ የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሰርኩላር አስተላልፏል።

በዚህም ሰርኩላር ፥ መንግሥት በቅርቡ ተግባራዊ ባደረገው የተሟላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ምንዛሬ በገበያው አማካኝነት እንዲወስን ማድረጉ እና ይኸው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ መደረጉን አስታውሷል።

ማሻሻያው የገቢ ንግዱን በይበልጥ እንዲያሳልጥ ወደ አገር እንዳይገቡ በሕግ ክልከላ ከተደረገባቸው ዕቃዎች፣ የነዳጅ አውቶሞቢሎች እና ከፀጥታና ከደህንነት ዕቃዎች ውጪ ሌሎች ዕቃዎች ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ወደ አገር እንዲገቡ በመንግሥት የተወሰነ መሆኑና ይኸው ተግባራዊ እንዲደረግ አሳስቧል።

19/08/2024

🇸🇴 🇪🇹 የሶማሊያ መሪ ከኢትዮጵያ ጋር ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እውቅና እስክትሰጥ ድረስ ለመደራደር ፈቃደኛ አልሆኑም።

🗣 "ሙሉ ሉዓላዊነታችንን እስክትቀበል ድረስ ከኢትዮጵያ ጋር በማንኛውም ጉዳይ አንደራደርም" ሲሉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ቅዳሜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መናገራቸውን የዜና ወኪል ዘግቧል።

እንደ ኤጀንሲው ዘገባ ከሆነ፣ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እውቅና ባለመስጠቱ "በቅርብ ጊዜ የተካሄደው ድርድር በአንካራ" እንዲፈርስ ምክንያት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

መግለጫው በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል በተደረገው ድርድር ሁለተኛው ዙር ሰኞ እና ማክሰኞ በአንካራ የተካሄደው በቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን መሪነት ነው።

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን እንደዘገቡት ሶስተኛው ዙር ኢትዮጵያን እና ሶማሊያን ለማስታረቅ ድርድር በአንካራ መስከረም 17 ቀን 2010 ዓ.ም.

ቀደም ሲል ኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ሰሜናዊ ምዕራብ ክፍል የምትገኘው የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ ወደ ቀይ ባህር የምትገባበትን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ከዚያ በኋላ የሶማሊያ ባለስልጣናት በአዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደር አስጠርተው ሼክ መሀሙድ በሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል የተደረገውን ስምምነት የሚፈርስ ህግ ተፈራርመዋል።

በአሶሳና አካባቢዋ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከትናንት ጀምሮ በአሶሳ ከተማ፣ ባምባሲ፣ ቶንጎ፣ መንጌ፣ ሆሞሻ፣ ኩምሩክ እና አካባቢዎቻቸው የተቋረጠውን የኤሌክትሪ...
19/08/2024

በአሶሳና አካባቢዋ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከትናንት ጀምሮ በአሶሳ ከተማ፣ ባምባሲ፣ ቶንጎ፣ መንጌ፣ ሆሞሻ፣ ኩምሩክ እና አካባቢዎቻቸው የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ወደ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከመንዲ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ አሶሳ ከተማ በተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ እያጋጠመው ባለው ተደጋጋሚ ብልሽት ምክንያት ኃይል መቋረጡ ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም እየተከናወነ ያለው የጥገና ሥራ እስከሚጠናቀቅ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች በትግዕስት እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጥሪ አቅርቧል፡፡

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Negarit - ነጋሪት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Negarit - ነጋሪት:

Videos

Share

Category