ሰበር ዜና ኢትዮጵያ Ethiopian Breaking News

ሰበር ዜና ኢትዮጵያ Ethiopian Breaking News ትኩስና ሰበር ዜናዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው። ዩቱዩብ �https://youtube.com/channel/UC-lp8qaD5SOXhR8G91cCvGw

28/11/2024

Hello

የነብይ እዩ ጩፋ ወላጅ እናት የሆኑት ወ/ሮ በየነች ዶጊሶ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው እለት ህዳር 12 ወደጌታ ተሰብስበዋል። ለነብይ እዩ ጩፋ እና ለመላው ቤተሰባቸው እ...
21/11/2024

የነብይ እዩ ጩፋ ወላጅ እናት የሆኑት ወ/ሮ በየነች ዶጊሶ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው እለት ህዳር 12 ወደጌታ ተሰብስበዋል። ለነብይ እዩ ጩፋ እና ለመላው ቤተሰባቸው እግዚአብሔር መፅናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።
ነፍስሽ በሰላም ትረፍ😭

18/10/2024

ቪዲዩውን በቴሌግራም ለቀነዋል! ሊንኩን ተጭነው ይከታተሉ 👉 https://t.me/zenachannel1

ከአራት ኪሎ እስክ ካዛንቺስ ፥ አሌክስን የሚከተለው የልማት ፈረሳ !!  : ከዓመታት በፊት አራት ኪሎ 'ለልማት' ሲፈርስ የመጀመሪያው 'ተነሺ' ነው አሌክስ:: አራት ኪሎን 'አጥቢያ' ብሎ ፅ...
15/10/2024

ከአራት ኪሎ እስክ ካዛንቺስ ፥ አሌክስን የሚከተለው የልማት ፈረሳ !!

: ከዓመታት በፊት አራት ኪሎ 'ለልማት' ሲፈርስ የመጀመሪያው 'ተነሺ' ነው አሌክስ:: አራት ኪሎን 'አጥቢያ' ብሎ ፅፎልን ዛሬም መልኩ ከምናባችን እንዲቆይ አድርጎናል::
አራት ኪሎ ሲፈርስ ትንሽ ዝቅ ብሎ ካዛንቺስ ከተመ:: የካዛንቺስ መናኸሪያ ጌጥ ነው አሌክስ::
ሰው የትም ሁኖ ሲቀጥረው ''እኔም ግማሽ ልምጣና አንተም ግማሽ መጥተህ 'ዓለም ቡና' እንገናኝ" ይላል እያልን እንቀልዳለን:: ዓለም ቡና ደጁ ላይ ነዋ መኖሪያው:: በቀን ሁለቴ ዓለም ቡና የሚገባ ሰው ቢወራረድ ሁለቴም አግኝቶት ያሸንፋል::
"ሳንቡሳቸውኮ... ማኪያቶ አትጠጪም?" ይላል: ሁሉንም ሰው::
"እኔ እሰራው ይመስል ሳንቡሳውን ሲበሉት ደስ ይለኛል" ይላል:: ሌላም ቀን ይሄንኑ ለሌላ ሰው ሲደግም ታገኙታላችሁ::

ደሞ መናኸሪያ ሬስቶራንት በረንዳ ከእኛ ከወዳጆቹ ጋር ማምሻው ናት:: ከየትም ከየትም አምሽቶ በዚያ የሚያልፍ እዛ መናኸሪያ ጋ የሚያወካና የሚከራከር የብዙ ሰዎች ድምፅ ከሰማ 'እኛ' ነን:: ሄኖክ፣ ብሩክ፣ ተስፋሁን፣ ሀይሉ፣ ደምሰው፣ ግርማ፣ ጊፍት... እኔ... ብዙ ብዙ...

የምፅፈው ከቤቱ ውጪ ስለፈጠረልን ዓለም ነው::

የአሌክስ ቤት ነገርማ ምኑ ይወራል? መሰባሰቢያ ነው:: በተለይ እንደአሌክስ አይነት ትልቅ ሰው በቀላሉ ማግኘት ለኔ ትውልድ 'እንዴት ያለ መባረክ ነው?' የሚያስብል:: ማንም ከየትም ቤቱ ገብቶ ያለውን አሳይቶ፣ ተማክሮ.. ስለንባብ ልምዱ አውርቶ.. ልብ ላለው ተቀርፆ የሚሄድበት 'ቤት' ነው አሌክስ::

ፒያሳ 'ሊፈርስ ነው' ሲባል በየቀኑ ይሄድ ነበር ፒያሳ:: 'ትናንትም እዛ አልነበርክ?' ስንለው ''ትንሽ ትዝታ ቀርታኛለች: እስኪፈርስ ልመላለስ" አለ:: የመጨረሻ ቀን 'መግባት አትችሉም' ተብሎ መንገዱ እስኪዘጋ እዛው ሃገር ፍቅር መንደር ነበር ውሎና ማምሻው::

አሁን 'ካዛንቺስ' ፈረሰ:: አሌክስ ምን ሊሰማው እንደሚችል መገመት ቀላል ቢመስልም ግን አይገመትም:: አሁን በቅርብ ርቀት እንኳ እንዳናገኘው የነገ ተረኛ ፈራሽ መንደር የቱ እንደሆነ አይታወቅም::

አሌክስ ሲሆን 'መዳረሻችን' እንደመሆኑ በልዩ ትኩረት ማረፊያ ሊበጅለት ይገባ ነበር:: ሁልጊዜም፣ ስለትናንቶቹ ታላላቆቻችን ስናወራ የምንቆጭበት 'አልቦ ክብር' የማድረግ አባዜያችን ዛሬም በአሌክስ ላይ ተደግሟል:: ሰው እንዳይኖረን፣ ያለንንም እንዳናከብር የተረገምን ነን እኛ በእውነት::

Via: Yiftusira Mitku

14/10/2024

ሰበር መረጃ!

14/10/2024
14/10/2024

👍🤣

🤣
14/10/2024

🤣

14/10/2024

👍

አናጋጋሪው የፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መልእክት - "ፅሁፉ በግል አካውንት ላይ ስለተለጠፈ ቢሯችንን አይመለከትም"- የፕሬዝደንት ጽ/ቤት ኃላፊ    በዛሬው እለት ከአንድ ሰአት በፊት ገደማ...
05/10/2024

አናጋጋሪው የፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መልእክት

- "ፅሁፉ በግል አካውንት ላይ ስለተለጠፈ ቢሯችንን አይመለከትም"- የፕሬዝደንት ጽ/ቤት ኃላፊ

በዛሬው እለት ከአንድ ሰአት በፊት ገደማ በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተረጋገጠ የኤክስ (ትዊተር) አካውንት ላይ የቀረበ አንድ ፅሁፍ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።

ፅሁፉ "እነ ጥላሁን ገሠሠ፣ ቴዲ አፍሮ፣ አሊ ቢራ፣ ማህሙድ አህመድ..ድንቅ ድምጻውያን መካከል ናቸው::"የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው፣ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው"ይላል ማህሙድ "ዝምታ ነው| መልሴ"ን ሲያዜም:: ለአንድ ዓመት ሞከርኩት" የሚል ነው።

ኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ ማጣርያ ዴስክ ጉዳዩን በተመለከተ የፕሬዝደንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑትን አቶ ፍቃዱ ሰቦቃን አነጋግሮ ያገኘውን ምላሽ አስነብቧል።

"የፕሬዝደንት ሳህለ-ወርቅ ኦፊሴላዊ አካውንት አለ፣ እኛ አስተያየት መስጠት የምንችለው በእሱ ዙርያ ነው። የተባለው ፅሁፍ በግል አካውንት ላይ ስለተለጠፈ ቢሯችንን አይመለከትም" በማለት ምላሽ ሰጥተውናል ብሎ የመረጃ ማጣርያው ዘግቧል።

በሌላ በኩል የፕሬዝደንት ፅ/ቤት ባልደረባ በመሆን ያገለገለችው ጋዜጠኛ መቅደስ ጥላሁን በዚህ ዙርያ ከደቂቃዎች በፊት ማህበራዊ ሚድያ ላይ ባጋራችው ጽሁፏ "ኬንያ ናይሮቢ የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ተሳትፎ መልስ፣ መሀሙድን እወደዋለሁ... ዝምታ ነዉ መልሴን ደጋግሜ እየሰማሁት ነዉ የመጣሁት አሉኝ" ብላ ትውስታዋን አጋርታለች።

ይህ የፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ፅሁፍ አሁን ላይ በርካታ ግብረ መልሶችን እና አስተያየቶችን እያስተናገደ ይገኛል፣ አሁንም በአካውንቱ ላይ ይታያል።

ሰበር ዜና======አቶ ጌታቸው ረዳ በዛሬው ቀን በሽሬ ከተማ ከሕዝብ ጋር የሚያደረገው ውይይት በከፍተኛ ሕዝብ ተቃወሞ ተቋረጠ።አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ...
15/09/2024

ሰበር ዜና
======
አቶ ጌታቸው ረዳ በዛሬው ቀን በሽሬ ከተማ ከሕዝብ ጋር የሚያደረገው ውይይት በከፍተኛ ሕዝብ ተቃወሞ ተቋረጠ።

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በዛሬው ቀን በሽሬ ከተማ ከህዝቡ ጋር ለማድረግ ያሰበው ስብሰባ በከፍተኛ ሕዝብ ተቃውሞ መቋረጡ ተዘግቧል፡፡

እንደሚታወቀው በዶር ደብረጺሆን ገ/ሚካኤል እና በአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን መካከል በተፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት፤ አቶ ጌታቸው ረዳ በሰሜን ትግራይ አከባቢዎች ማለትም ሽሬ፤አክሱም፤ አድዋ፤ አዲግራት፤ አቢአዲ እና የመሳሰሉት ቦታዎች ላይ ተቀባይነት በማጣቱ በሕዝቡ ጋር ውይይት ማድረግ አልቻለም።
Share
Share

04/09/2024

#ሶማሊያ ኢትዮጵያን የነካ የለውም በረካ

ትችላለህ 👌🙏
10/08/2024

ትችላለህ 👌🙏

03/08/2024

በባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ደረሰ?

የኢትዮጵያ ንግድ ባንድ 1 ዶላር በ95.69 ብር እየገዛ በ101.43 ብር እየሸጠ ነው።
ሸመጠጠው አለ🤔

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰበር ዜና ኢትዮጵያ Ethiopian Breaking News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share