Tasik Tadese የ21

Tasik Tadese የ21 ሰው አይናቅም !

እወዳችኋለሁ ❤🙏

06/11/2023
 ኪዳነ ምህረት ማለት ምን ማለት ነው  #ኪዳን ፦ በግእዙ '  ተካየደ  '  ትርጉሙም ተማማለ፣ ቃልኪዳን ተጋባ ማለት ስሆን እግዚአብሔር አምላክም ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ጋር የገባው ውል ' ቃል...
27/10/2023



ኪዳነ ምህረት ማለት ምን ማለት ነው
#ኪዳን ፦ በግእዙ ' ተካየደ ' ትርጉሙም ተማማለ፣ ቃልኪዳን ተጋባ ማለት ስሆን እግዚአብሔር አምላክም ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ጋር የገባው ውል ' ቃል ኪዳን '

 አርሴማ ማለት ምን ማለት ነው ?አርሴማ ማለት በወርቅ ልብሶች የተጎናጸፈች መልከ መልካም፣ ውብ ማለት ነው ።አርሴማ ማን ናት ?እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሌን ተሸክሞ ይከ...
16/09/2023



አርሴማ ማለት ምን ማለት ነው ?

አርሴማ ማለት በወርቅ ልብሶች የተጎናጸፈች መልከ መልካም፣ ውብ ማለት ነው ።

አርሴማ ማን ናት ?

እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ፣ ሰው አለሙን ሁሉ ቢገዛ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል? ተብሎ የተነገረውን የክርስቶስ ወንጌል ተከትላ ዘመድ አዝማዶቿን ትታ ጌታን የተከተለች፣ በሮምና በአርማንያ ድርጣደስን፣ በሀይማኖቷ ጸንታ ድል ያደረገች፣ የሮም ወታደሮች የሚያደርሱባት መከራና ግፍ፣ እስራትና ግርፋት ያልበገራት መላ ህይወታቸውን ለእሳትና ለስለት ከሰጡት ከ27ቱ ቅዱሳት ደናግል አንዷ ሰማዕት ናት ።

የቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን። 🙏🙏❤❤

 አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በረከታቸው ይደርብን  🙏❤
16/09/2023



አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በረከታቸው ይደርብን 🙏❤

  👆👆
11/09/2023

👆👆

Follow and share
25/06/2023

Follow and share

በመከራም ሆነ በደስታ ጊዜ አመስጋኝ ሁን✔️

#ተወዳጅ ሆይ እግዚአብሔር ላደረገልህ ብቻ የምታመሰግን ከሆነ አንተ የምትወደው እግዚአብሔርን ሳይሆን የተደረገልህን ነገር ነው ልብ ብለህ አስተውል አንድ ስው ሥጦታ ሲሰጥህ ከዛ ሰው በላይ ሥጦታውን አታስበልጥ አላማህ ለመቀበል ብቻ አይሁን። እግዚአብሔርን ለምነኸው የከለከለህ ነገር ካለ እመነኝ ያ ነገር አይጠቅምህም ስለዚህም #ስላላደረገልህ ነገር አመስግነው መከራም ሲደርስብህ "ከዚህ በላይ ስቃይ እንዳላይ አላደረክምና አመሰግንሀለው " በለው መሰረትህ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ እንጅ በሥጦታ ላይ አታድርግ ለምነህ ተሰጠህም ላልተሰጠህም አመስግን በማንኛውም ጊዜ እና አጋጣሚ ምሥጋናህን አታቋርጥ።

ሰለሥቱ ደቂቅ ፣ህፃኑ ቂርቆስ እና እናቱ እየሉጣ በእቶን እሳት ውስጥ ሆነው ፣ነብዩ ዳንኤል በተራቡ አናብስት ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ፣ጳውሎስ እና ሲላስ በእሥር ቤት ውስጥ ፣እዮብም በዛ መከራ ውስጥ ሆኖ ለምሥጋርና አንደበታቸውን ከፈቱ ተመልከት እነሱ በመከራ ውስጥ እንኳን ሆነው አላማረሩም አንተ ደግሞ እንደነሱ የፀና ችግር ውስጥ ሳትሆን ፣እግዚአብሔር የሚያስፈልግህን መልካም ነገር እየሰጠህም "እኔ ያልኩት ካልሆነ "ብለህ ችክ አትበል !
ማን ያውቃል የለመንከው ነገር መጥፊያህ ሊሆንም ይችላል ምን አልባትም ያጠፋኸው ፣የሳትከው ነገር ሊኖር ስለሚችል እራስህን ፈትሽ ዙሪያህን ቃኝ።

መከራ ሲደርስብህ አትዘን የክርስቲያን መገለጫው አንዱ መንገድ ነውና ችግር ውስጥ ስትሆን አብዝተህ ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለህ ያ ጸሎትህ ደግሞ ከአምላክህ ጋር ይበልጥ እንድትቀራረብ እና እንድትተሳሰር ያደርግሀል አስተዋልክ ? ፈተና የሚያመጣው መልካም ነገርም እንዳለ ከተረዳህ እና ለበጎ መሆኑ ከገባህ "ተመስገን "ማለትን አትረሳም
እናም አመስግን አሁንም ነገም ሁል ጊዜም አመስጋኝ ሁኑ የማማረር ቃል ፍጽም ከአንደበትህ አይውጣ።

ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን አሜን!!!
💕መልካም ምሽት የነገ ሰው ይበለን 💕

Please follow and share this page
25/06/2023

Please follow and share this page

ጉባዔ አቅሌሲያ ከመናንያን ገዳማውያን ጋር

በጎንደር ሃገረ ስብከት ስር በሚገኘው ሐሙሲት ገነተ ማርያም ቤተክርስቲያን ታላቅ ጉባኤ በሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል ገዳም እና ማህበር ቁስቋም አዘጋጅነት ገናና ምስጉን የሆነውን እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ከገዳሙ መናንያን ቡራኬ የምናገኝበት የነፍስ ማረፊያ የሆነ ቃለ ወንጌልን የምንማርበት ኦርቶዶክሳዊ ጉባኤ ሰኔ 18 ተዘጋጅቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይም ከአዲስ አበባ በመምጣት

ቃለ ወንጌልን በመመገብ መምህር ኤርሚያስ ክፍሌ
መምህር የማርያምወርቅ ተሻገር
አጥንት በሚያለመልም ዝማሬ
ዘማሪ እስጢፋኖስ ሳህሌ (ቄሴ)
ዘማሪት አዜብ ከበደ
ከመሳሪያ ተጫዋች ሱራፌል ተክሌ ጋር ነፍሳችን ያሳርፏታል።

እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የኪነጥበብ ባለሙያ አርቲስቶች በመርሃግብሩ ላይ ይሳተፋሉ።

ሰርክ ስለ ሃገራችን ስለ ነፍሳችን ከሚተጉት ገዳማውያን ጋር በመሆን የልጅነት ፍቅራችንን እየሰጠናቸው ከጉባኤው ተሳተፈን በረከትን እናትርፍ።

ኑ! በእግዚአብሔር ደስ ይበለን

ጉባኤ አቅሌሲያ

አዘጋጅ:-ማህበር ቁስቋም

follow and share
25/06/2023

follow and share

follow and share
25/06/2023

follow and share

Follow and share this page እወዳችኋለሁ ❤❤
25/06/2023

Follow and share this page
እወዳችኋለሁ ❤❤

#አመስጋኝ 🙏

እዮብ- በጤናው አመስጋኝ ነበር።
እዮብ- በበሽታውም አመስጋኝ ነበር።
እዮብ- ሀብት እና ንብረት ሞልቶት አመስጋኝ ነበር።
እዮብ- ልጆቹ አልቀውበት አመስጋኝ ነበር።
እዮብ- ሚስቱ ከድታው አመስጋኝ ነበር።
እዮብ- ዘመዶቹ ፊት ነስተውት አመስጋኝ ነበር።
እዮብ- ቀን እና ሌሊቱ ተፈራርቀውበት ሲነጋ መች ነው የሚመሸው ሲመሽ መች ነው የሚነጋው እያለ ሰውነቱን ትል እያፈላ አመስጋኝ ነበር።
እዮብ- እንዴት አደርክ ሲሉት እግዚአብሔር ይመስገን ነው የሚለው።

ታጋሽ እንደ እዮብ እንድንሆን ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን በማግኘት እና በማጣትም አመስጋኞች እንድንሆን ዘንድ አምላክ ማስተዋሉን ያድለን።
አሜን አሜን አሜን!

25/06/2023

በትክክል መምህሬ 🙏🙏🙏
follow and share this page ❤

Please  -Share this page
25/06/2023

Please -Share this page

Please follow this page
25/06/2023

Please follow this page

ሰንበት ክብር ናት 🙏ሰንበቴ ክርስቲያን ( እሑድ )እሑድ ማለት ፦አሐደ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ስሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው ። ይህቺ ዕለት በበመጽሐፍ ቅዱስ ፣ከሳምንት በፊተኛው ...
18/06/2023

ሰንበት ክብር ናት 🙏
ሰንበቴ ክርስቲያን ( እሑድ )

እሑድ ማለት ፦አሐደ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ስሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው ። ይህቺ ዕለት በበመጽሐፍ ቅዱስ ፣ከሳምንት በፊተኛው ቀን በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ የጌታ ቀን ያላት ናት ( ራእይ 1 ፥ 10 )።ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ዕለተ እግዚአብሔር የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፦

👉 እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት የሥነፍጥረት መጀመሪያ ዕለተ ( ጥንተ ዕለት ) ናትና
👉 ዕለተ ሥጋዌ ናት። ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት የፈሰሐ ቀን።
👉 ዕለተ ትንሳኤ ናት ። ጌታ ከሙታን የተነሳበት ዕለት
👉 የቤ/ክ የልደት ቀን ናት። መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደባትኃይልና ፅናትን ያገኑባት ዕለት
👉 በጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም ቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣበት ታላቅ የፍርድ ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አግልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት ናት ( 1ኛ ቆሮ 16፥1 )
👉 የሐዋርያት ዘመንም በጠሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን ይሰበሰቡ ነበር ( የሐዋ 20፥7 በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስትያኖች ሰንበት ናት በማለት ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር

ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ክዳን መከበር የጀመረ ብሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት ሰንበት ( የቀዳሚት ) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀረቡበት ቀን ነበር። ( ራዕ 1፥10 )

በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራ ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን ( በሰንበተ ክርስቲያን ) በጌታችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የሚናሰብበት ነው። ( ዕብ 4፥1-10 )

ከሰንበት ረድኤት በረከት ያካፍለን
ሌሎች እህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❤❤🙏🙏

Please follow and share me ❤

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tasik Tadese የ21 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share