Walta Tv ዋልታ ቲቪ

Walta Tv ዋልታ ቲቪ This is official page of WALTA TV MULTIMEDIA

በዩኒቨርሲቲው ስር የሚገኘው የካንሰር ማዕከል በአርቲስት አሊ ቢራ ስም ተሰየመመስከረም 30/2016 (አዲስ ዋልታ) በሀረር ከተማ የሚገኘው የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ሆስፒ...
11/10/2023

በዩኒቨርሲቲው ስር የሚገኘው የካንሰር ማዕከል በአርቲስት አሊ ቢራ ስም ተሰየመ

መስከረም 30/2016 (አዲስ ዋልታ) በሀረር ከተማ የሚገኘው የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሰር ማዕከል በአርቲስት አሊ ቢራ ስም ተሰየመ።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ አርቲስት አሊ ቢራ ህይወቱ አስኪያልፍ ድረስ ስለሰው ልጆች መብትና ፍቅር የኖረና የደግነት ምልክት ነው ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም ያለውን ሲያካፍል የኖረ አርቲስት መሆኑን አስታውሰው አብሮነትና ወንድማማችነት እንዲጠናከር የራሱን አስተዋጽኦ ያደረገ ለሌሎችም በአርዓያነት የሚጠቀስ ስለመሆኑ አንስተዋል።

የካንሰር ማዕከሉ የአርቲስቱን ጥንካሬ በሚመጥን መልኩ አገልግሎት መስጠት ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል ዩሱፍ (ዶ/ር) አርቲስት አሊ ቢራ ለኦሮሞ ህዝብ እና ለመላው ብሔር ብሔረሰቦችና የኖረ የጥበብ ሰው መሆኑን አስታውሰዋል።

ማዕከሉ በአርቲስቱ ስም መሰየሙም ከካንሰር ህመም ጋር በተያያዘ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለውን የአመለካከት ክፍተት ለመቅረፍ ያግዛል ብለዋል።

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር ቅርንጫፍ)

ከ450 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ሥር ዋለመስከረም 16/2016 (አዲስ ዋልታ) ከ450 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት ዋጋ ያለው የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ሥር ዋለ።...
27/09/2023

ከ450 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ሥር ዋለ

መስከረም 16/2016 (አዲስ ዋልታ) ከ450 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት ዋጋ ያለው የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ሥር ዋለ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ከ450 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት ዋጋ ያላቸውን የኮንትሮባንድ ልባሽ ጨርቆችን እና በጉዳዩ የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦችን ከሁለት ተሽከርካሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ሊያዙ ያቻሉት መነሻቸውን ሻሸመኔ ከተማ በማድረግ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር ባደረጉት ክትትል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዚህም የሰሌዳ ቁጥራቸው አ.አ ኮድ 3- A84787 እና A31581 በሆኑ ሁለት የጭነት ተሽከርካሪዎች በርካታ ልባሽ ጨርቆችን በድንች ስር ደብቀው በመጫን ሲጓዙ ጦር ኃይሎች አካባቢ እንደደረሱ በተደረገባቸው ድንገተኛ ፍተሻ ከነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል::

የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች አስመረቀመስከረም 12/2016 (አዲስ ዋልታ) የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰል...
23/09/2023

የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች አስመረቀ

መስከረም 12/2016 (አዲስ ዋልታ) የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች አስስመረቋል።

በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪ እና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል አለምሸት ደግፌ የሰላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አዛዥ ኮሎኔል ደመቀ መንግስቱ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ወታደራዊ መኮንኖችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

ከተመራቂ ወታደራዊ መኮንኖች መካከል ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የሶስት ጎረቤት አገራት ከፍተኛ የጦር መኮንኖችም ይገኙበታል።

ተመራቂዎቹ የስታፍ መኮንንነት የወታደራዊ ታዛቢነት፣ በግጭት ወቅት ሲቪሎችን መከላከል የሲቪል ሚሊተሪ ትስስር የሚሽን ሚዲያ የሎጅስቲክስ የትምህርት አይነቶችን ጨምሮ ሌሎች የሰላም እና ግጭት አፈታት ትምህርቶችን መከታተላቸውን ከኢዜአ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጳጉሜን 1 - የአገልጋይነት ቀን       “ኢትዮጵያን እናገልግል”
06/09/2023

ጳጉሜን 1 - የአገልጋይነት ቀን
“ኢትዮጵያን እናገልግል”

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በደቡብ አፍሪካ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነውነሐሴ 30/2015 (አዲስ ዋልታ) የኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በደቡብ ...
05/09/2023

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በደቡብ አፍሪካ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው

ነሐሴ 30/2015 (አዲስ ዋልታ) የኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በደቡብ አፍሪካ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ጄነራል ሩድዛኒ ማፕህዋንያ ባቀረቡላቸው ግብዣ መሠረት ነው በሀገሪቱ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በደቡብ አፍሪካ መከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ በወታደራዊ ትርዒት የታጀበ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ለክብራቸውም 13 ጊዜ መድፍ መተኮሱን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

በዚሁ ወቅት ከደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ውይይት በሁለቱ ሀገራት እና ሕዝቦች መካከል ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረው ታሪካዊ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ ለመጣው ወታደራዊ ትብብር ጠንካራ መሰረት የጣለ መሆኑን አንስተዋል።

በቀጣይ የትብብሮቹን አድማስ ለማስፋትና ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል ።

በተጨማሪም የደቡብ አፍሪካ የመከላከያ ልዩ ልዩ የአቅም ግንባታ ተቋማትን በተመለከተ ገለጻዎች የተደረጉ ሲሆን፥የወታደራዊ ትዕይንቶችም ቀርበዋል።

የፅንፈኞች እንቅስቃሴ ስጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ደርሷል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላነሐሴ 26/2015 (አዲስ ዋልታ) በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ያለው የፅንፈኞች እንቅስቃሴ ስጋት ወደ ማ...
01/09/2023

የፅንፈኞች እንቅስቃሴ ስጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ደርሷል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ነሐሴ 26/2015 (አዲስ ዋልታ) በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ያለው የፅንፈኞች እንቅስቃሴ ስጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ላይ መድረሱን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከመከላከያ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች አሁን ላይ ስጋት ወደማይሆኑበት ደረጃ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊቱ ጥበብ በታከለበት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከስተው የነበሩ የፀጥታ ችግሮችን እየቀረፈ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በአማራ ክልል የህዝቡን የመብት ጥያቄ ካባ በማድረግ ፍላጎቱን በኃይል ለማሳካት የተንቀሳቀሰው ኃይል ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ አመርቂ ውጤት መመዝገቡንም ገልጸዋል።

የተከበረውን የፋኖ ስም መጠቀሚያ በማድረግ የክልሉን ፀጥታ ሲያውኩ የነበሩ ኃይሎችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያም ፋኖ ከጥንት ጀምሮ ሀገር ተወረረች ሲባል ጦርና ጋሻ ይዞ ለኢትዮጵያ ነፃነት የሚሰለፍ እንጂ መልሶ የሀገሩ ሰራዊት ላይ ጦር የሚመዝ አይደለም ብለዋል።

አሁን ላይ በፋኖ ስም እየተንቀሳቀሰ ያለው ኃይል በዘረፋ ተግባር ላይ የተሰማራና መንገዶችን በመዝጋት የህዝቡን ሰላም የሚያወክ ነው ማለታቸውም ተመላክቷል።

ህዝቡን ሰላም ሲነሳ የነበረው ኃይልም የሰራው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ መልሶ እርቃኑን እንዲቀር እንዳደረገና አሁን ከህዝቡ እየተነጠለ ያለውን ይህን ኃይል አቅሙን በማዳከም ስጋት ከማይሆንበት ደረጃ ማድረስ ተችሏልም ሲሉ ገልፀዋል።

አገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ሆነው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚነዙ ኃይሎች ለሀገርና ለህዝብ ሲል ውድ ህይወቱን እየከፈለ ሰላም የሚያረጋግጠውን ሰራዊት ስነ-ልቦና ያልተረዱ ናቸው ብለዋል።

ኢታማዦር ሹሙ አክለውም ሰራዊቱ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮውን በአስተማማኝ እየተወጣ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የፅንፈኞች የሀሰት ፕሮፖጋንዳን የተገነዘበው ህዝባችን ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመሆን ለሰላሙ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሀሰተኞች ሴራ ተታለው ከፅንፈኞች ጋር የተሰለፉ ወጣቶች በሰላማዊ መንገድ ወደ ህዝቡ እንዲመለሱም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

  🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ 3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ ለሀገራችን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል።...
22/08/2023

🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹

በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ 3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ ለሀገራችን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ታሪክ በአትሌት ለሜቻ ግርማ አማካኝነት አማካኝነት 101ኛ ሜዳልያዋን ማስመዝገብ ችላለች።

ውድድሩን ሞሯኳዊው አትሌት ኤል ባካሊ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ኬንያዊው ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ሁለት የብር ሜዳልያዎች ማስመዝገቧን ተከትሎ በውድድሩ ያላትን የሜዳልያ ቁጥር ወደ ስድስት ከፍ ማድረግ ችላለች።

🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ 1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ለሀገራችን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችላለች።ሀገራችን ኢ...
22/08/2023

🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹

በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ 1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ለሀገራችን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችላለች።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ታሪክ በአትሌት አማካኝነት 100ኛ ሜዳልያዋን ማስመዝገብ ችላለች።

ኢትዮጵያ በታሪኳ በአለም አትሌቲክስ ውድድር በ1500 ሜትር የመጀመሪያውን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችላለች።

ኢትዮጵያ በዘንድሮው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አምስተኛ ሜዳልያዋን ማሳካት ችላለች።

ውድድሩን ኬንያዊቷ አትሌት በበላይነት ስታጠናቅቅ ሲፋን ሀሰን ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።

የ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ዛሬ ይደረጋልነሐሴ 14/2015 (አዲስ ዋልታ) 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሁለተኛ ቀን ውሎ አትሌቶቻችን ተጠባቂ ውድድራቸውን በቡዳፔስት የአትሌቲክ ...
20/08/2023

የ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ዛሬ ይደረጋል

ነሐሴ 14/2015 (አዲስ ዋልታ) 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሁለተኛ ቀን ውሎ አትሌቶቻችን ተጠባቂ ውድድራቸውን በቡዳፔስት የአትሌቲክ ሴንተር ያደርጋሉ።

ኢትዮጵያ ሜዳሊያ ታገኝበታለች ተብለው ከሚጠበቁ ርቀቶች መካከል የሆነው የ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ዛሬ ምሽት 1:25 ይደረጋል::

በውድድሩ በሪሁ አረጋዊ ሰለሞን ባረጋ እና ይስማው ድሉ ይሳተፋሉ፡፡

ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ወርቅ ያገኘችው 2011 ላይ በዴጉ የዓለም ሻምፒዮና በኢብራሂም ጄይላን አማካኝነት ነበር።

በሌሎች መርሀግብሮች 12:05 ላይ የ1 ሺህ 500ሜ ሴቶች የግማሽ ፍፃሜ ሲደረግ ኢትዮጵያ በ ሂሩት መሸሻ ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ሀየሎም ትወከላለች::

Budapest 🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹🥇ጉዳፍ ፀጋዬ 🇪🇹🇪🇹🥈ለተሰንበት ግደይ 🇪🇹🇪🇹🥉እጅጋየሁ ታዬ 🇪🇹🇪🇹
19/08/2023

Budapest 🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹

🥇ጉዳፍ ፀጋዬ 🇪🇹🇪🇹
🥈ለተሰንበት ግደይ 🇪🇹🇪🇹
🥉እጅጋየሁ ታዬ 🇪🇹🇪🇹

ፋጤ ስርሞሎ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል በአዲስ በተመሰረተው ክልል አፈጉባኤ ሆነው ተሾሙነሐሴ 14/2015 (አዲስ ዋልታ) ፋጤ ስርሞሎ በአዲስ በተመሠረተው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና አፈ ጉ...
19/08/2023

ፋጤ ስርሞሎ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል በአዲስ በተመሰረተው ክልል አፈጉባኤ ሆነው ተሾሙ

ነሐሴ 14/2015 (አዲስ ዋልታ) ፋጤ ስርሞሎ በአዲስ በተመሠረተው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው ተሾሙ፡፡

ነባሩ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የ"ማዕከላዊ ኢትዮጵያ" በሚል በአዲስ ስያሜ ምስረታ ጉባኤ ላይ ለክልሉ የዋና አፈ ጉባኤ ዕጩ ቀርቦ አባላት ድምፅ ሰጥተውበት ፀድቋል።

በዚህም መሰረት ፋጤ ስርሞሎ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ በመሆን በ2 ተቃውሞ በ4 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ሹመታቸው ፀድቋል።

በተጨማሪም ወ/ሮ መነቴ ሙንዲኑ ለምክትል አፈጉባኤነት በእጩነት ቀርበው በ3 ድምፀ ተአቅቦ በአብለጫ ድምፅ ሹመታቸው የፀደቀ ሲሆን የተሰጣቸውን ሀላፊነት ለመወጣትና ህዝባቸውን በቅንነት ለማገልገል ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።

በትግስት ዘላለም

የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ጨዋታ ዛሬ ይደረጋልነሐሴ 10/2015(አዲስ ዋልታ) የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዛሬ ምሸት 4 ሰዓት ላይ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ እና በአው...
16/08/2023

የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል

ነሐሴ 10/2015(አዲስ ዋልታ) የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዛሬ ምሸት 4 ሰዓት ላይ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ እና በአውሮፓ ሊግ አሸናፊው የስፔኑ ሴቪያ መካከል ይደረጋል፡፡

የፍፃሜው ጨዋታ በግሪኩ ኦሎምፒያኮስ ጊዮርጊዮስ ካሪስካኪስ ስታዲዮም የሚደረግ ይሆናል፡፡

“ዛሬ ጠዋት የኢትዮጵያ ትልቁ ኤሊት ኃይል የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በመገኘቴ ክብር ይሰማኛል። ይህ ኃይል ሁለት ዓላማዎች አሉት:- 1)ውጊያ ማስቀረት እና 2)ገፍቶ ከመጣ ደግሞ ውጊያን የመጨ...
12/08/2023

“ዛሬ ጠዋት የኢትዮጵያ ትልቁ ኤሊት ኃይል የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በመገኘቴ ክብር ይሰማኛል። ይህ ኃይል ሁለት ዓላማዎች አሉት:- 1)ውጊያ ማስቀረት እና 2)ገፍቶ ከመጣ ደግሞ ውጊያን የመጨረስ ተልዕኮ ያለው ነው:: እንዲህ ያለው ኃይል ይህቺን ትልቅ ሀገር አጽንቶ ለትውልድ ያሻግራል።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

11/08/2023
በአማራ ክልል በተፈጠረው አለመረጋጋት  ዜጎች ለሰብዓዊ ችግሮች ተጋልጠዋል - የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርነሐሴ 4/2015 (አዲስ ዋልታ) በአማራ ክልል በተፈጠረው አለመረጋጋት ዜጎች ለሰብ...
10/08/2023

በአማራ ክልል በተፈጠረው አለመረጋጋት ዜጎች ለሰብዓዊ ችግሮች ተጋልጠዋል - የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር

ነሐሴ 4/2015 (አዲስ ዋልታ) በአማራ ክልል በተፈጠረው አለመረጋጋት ዜጎች ለሰብዓዊ ችግሮች መጋለጣቸውን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ገለፀ፡፡

ማህበሩ በአማራ ክልል ጉዳት የደረሠባቸውን አካባቢዎች ድጋፍ ማድረግን በተመለከተ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሐን ጋዜጣዊ መግለጫ ሠጥቷል።

በዚህም በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በርካታ ሴቶች፣ ህጻናት እንዲሁም አረጋውያንና አቅመደካሞች ለተለያዩ ሰብአዊ ችግሮች ተጋልጠዋል ብሏል፡፡

በተከሠተው ግጭት የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ሰብዓዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ በቅርቡ እርዳታ ለማሰባሰብ የተለያዩ ድጋፍ ሰጪ ኮሜቴዎችን በማዋቀር ወደ ስራ መገባቱንም አስታውቋል።

በመሆኑም በግጭቱ ምክንያት ዜጎች የከፋ አደጋ እንዳይደርስባቸው ሁሉም አካል ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ የተጠየቀ ሲሆን አገር አቀፍ ድርጅቶች፣ አለምአቀፍ ተቋማት፣ ባለሀብቶች እና ሁሉም ዜጋ በምግብ፣ በመድሃኒት፣ በቁሳቁስና በገንዘብ እርዳታ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ቀይ መሥቀል ማህበር ጥሪ አቅርቧል።

በቤዛዊት አበበ

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

| አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።ለረዥም ጊዜ በህመም ላይ የቆየው አርቲስት አብነት በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ አርቲስት አብነት በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊ...
09/08/2023

| አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ለረዥም ጊዜ በህመም ላይ የቆየው አርቲስት አብነት በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት አብነት በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈ ነበር።

ከዚህ ውስጥ አሉላ አባነጋ፣ የቼዝ ዓለም፣ ዳኛው፣ እስረኛው ንጉስ እና ነቅዕ ቴአትሮች ላይ ተውኗል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አያስቅም፣ አንድ እድል፣ ላምባዲና፣ ሰበበኛ፣ ባንቺ የመጣ፣ ቁልፉን ስጭኝ፣ የነገርኩሽ እለት፣ ፍቅር እስከ መቃብር እና አትሸኟትም ወይ በተሰኙ ፊልሞች ላይ በመተወን አድናቆትን አግኝቷል።

ስንቅ ፣መለከት፣ ትርታ እና ለወደዱት ደግሞ የተሳተፈባቸው ቲቪ ድራማዎች ሲሆኑ፥ በግሉም የቅብብሎሽ ድራማን ደርሷል።

የሥነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደነሐሴ 3/2015 (አዲስ ዋልታ) ከተገልጋዮች በቀረበ ጥቆማ መሰረት ተጣርቶ በማስረጃ ጥፋተ...
09/08/2023

የሥነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ነሐሴ 3/2015 (አዲስ ዋልታ) ከተገልጋዮች በቀረበ ጥቆማ መሰረት ተጣርቶ በማስረጃ ጥፋተኛ መሆናቸው የተረጋገጡ 112 ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መወሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

ተቋሙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተጠያቂነት ሥርዓትን ለማስፈን ከተገልጋዮች በቀረበ ጥቆማ መሰረት 133 ጥቆማዎችን ተቀብሎ በ112 አመራርና ሰራተኞች ላይ ከጹሑፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ስንብት የሚደርስ አስተዳደርዊ እርምጃ መውሰዱንም አመላክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የዲሲፕሊን ችግር በታየባቸው 1 ሺሕ 60 ሠራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን የወሰደ ሲሆን በ288 ሠራተኞች ላይ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ በ719 ሠራተኞች ላይ የደመወዝ/ገንዘብ ቅጣት፣ በ39 ሠራተኞች ላይ ስንብት፣ በ9 ሠራተኞች ላይ ከቦታ ማንሳት እና በ11 ሠራተኞች ላይ ባደረገው ማጣራት ነጻ ብሏቸዋል፡፡

ተቋሙ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችና ጥቆማዎችን ለመቀበል ከተዘረጉ የ905 እና 904 ነጻ የጥሪ ማዕከላት በተጨማሪ ደንበኞች ቅሬታቸውን ቀላልና ምቹ በሆነ መንገድ ማቅረብ የሚችሉበት ዘመናዊ የሙስና ጥቆማ መቀበያ ሥርዓት ለመዘርጋት በሂደት ላይ መሆኑን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣነሐሴ 2/2015 (አዲስ ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሶስት ህፃናት ላይ የግብረ ሰዶም ወንጀል...
08/08/2023

የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

ነሐሴ 2/2015 (አዲስ ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሶስት ህፃናት ላይ የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡

የ43 ዓመት ዕድሜ ያለው ተከሳሹ ወንጀሉን የፈፀመው በክፍለ ከተማው ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ማር ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ግለሰቡ የጎረቤቱ ልጆች የሆኑ የ5፣ የ6 እና የ10 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃናትን በተለያዩ ቀናት ከረሜላ እየገዛ በማታለል መኖሪያ ቤቱ ውስጥ አስገብቶ ወንጀሉን ፈፅሞባቸዋል ነው የተባለው፡፡

ወንጀሉ ከተፈፀመባቸው ህፃናት መካከል የ6 ዓመቱ ህፃን ስለሁኔታው ለወላጅ እናቱ በመናገሩ ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

በ ቴለግራም መረጃዎችን በትኩስ ያገኙ             👎👎)👎
08/08/2023

በ ቴለግራም መረጃዎችን በትኩስ ያገኙ
👎👎)👎

ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫሰላም እስተንፋስ ላለው ፍጡር ሁሉ የህልውናው ማረጋገጫ ነው። ሰላም ለአፍሪካችን፣ ሰላም ለኢትዮጵያችን፣ ሰላም...
07/08/2023

ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

ሰላም እስተንፋስ ላለው ፍጡር ሁሉ የህልውናው ማረጋገጫ ነው። ሰላም ለአፍሪካችን፣ ሰላም ለኢትዮጵያችን፣ ሰላም ለህዝባችን የማንደራደርበት የህዝባችን ህልውና ነው! ወጥቶ መግባት የምናረጋግጥበት መሠረታዊ ፍላጎት ነው!! ሰላም ለህብረተሰባችን ቅንጦት ሳይሆን እለት እለት የምንሰራበት ጉዳይ ነው!!

የኢትዮዽያ መንግስት ሰላምን የማስከበር ጉዳይ ለህዝቦቿ የልማት መረጋገጫ ዋነኛው መንገድ ነው ብሎ በፅኑ ያምናል! ለሰላም መከበር እና መረጋገጥ የሚከፈለውን ማንኛውም መስዋትነት እየከፈለ ይገኛል::

ለዚህም ቁርጠኛ አቋሙን ሁሉ በሚያደርጋቸው ውሳኔዎች አረጋግጧል::

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሞኑን ባጋጠመው የፀጥታ መደፍረስ እና የሰላም እጦት ምክንያት በክልሉ ህዝብ ላይ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል።

የክልሉን ጥሩ የሰላም ንፋስ በክሎ፣ ለማንኛውም ሰላማዊ የንግግር መንገዶች በሩን ዘግቶ፣ በድንፋታ ፣ በህገ ወጥነት እና በኢ-ሰብአዊነት ነፍጥ አንግቦ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማፍረስና ስልጣን በኃይል ለመቆጣጠር በግልፅ እየተናገረ ያለው የዘራፊና ወንበዴ ስብስብ እንዲሁም ህገ -ወጥ አደረጃጀት በክልሉ ህዝብና መንግስት ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት አድርሷል፣ በማድረስም ላይ ይገኛል።

ሙሉውን ለማንበብ ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://shorturl.at/DHJST

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

አዲስ ዋልታ በመዝናኛው ኢንዱትሪ ከተሰማሩ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመሐምሌ 30/2015 (ዋልታ) አዲስ ዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን በመዝናኛው ዘርፍ በትኩረት ለመስራት ከተለያዩ በመ...
06/08/2023

አዲስ ዋልታ በመዝናኛው ኢንዱትሪ ከተሰማሩ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ

ሐምሌ 30/2015 (ዋልታ) አዲስ ዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን በመዝናኛው ዘርፍ በትኩረት ለመስራት ከተለያዩ በመዝናኛው ኢንዱትሪ ከተሰማሩ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡፡

አዲስ ዋልታ ይዘቶችን በማሻሻል ተመልካቾችን በሚመጥን መልኩ ከሰኞ እስከ ሰኞ የመዝናኛ መርኃ ግብሮችን ለማድረስ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

በዚህም ተከታታይ ድራማዎችን ከሚያቀርቡ የመዝናኛ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ የተፈጸመው እየተካሄደ ባለው የአዲስ ዋልታ አዲስ መንገድ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ ነው፡፡

ድርጅቱ ትላንት ከ15 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ከጅቡቲ ወደብ ማጓጓዙን አስታወቀሐምሌ 30/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ድርጅት በትላንትናው...
06/08/2023

ድርጅቱ ትላንት ከ15 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ከጅቡቲ ወደብ ማጓጓዙን አስታወቀ

ሐምሌ 30/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ድርጅት በትላንትናው ዕለት ከ15 ሺሕ 279 ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ከጅቡቲ ወደብ ማጓጓዙን አስታወቀ፡፡

348 ከባድ የጭነት መኪና ተሽከርካሪዎች እና በኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አማካይነት 1 ዋገን ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በትናንትናው ዕለት ብቻ 15 ሺሕ 279 ነጥብ 1 ሜትሪክ ቶን ጭነት የገባ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ ጭነት የማጓጓዝ ሥራውንም ከዕለታዊ ግብ አንጻር ሲቃኝ 122 ነጥብ 24 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታውቋል።

በፆመ-ፍልሰታ ምዕመናን ስለ ሰላምና ፍቅር እንዲማፀኑ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጥሪ አቀረቡሐምሌ 29/2015 (ዋልታ) በፆመ-ፍልሰታ ምዕመናን በተመስጦና በንስሐ ሕይወት ስለ ሰላምና ፍቅር...
05/08/2023

በፆመ-ፍልሰታ ምዕመናን ስለ ሰላምና ፍቅር እንዲማፀኑ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጥሪ አቀረቡ

ሐምሌ 29/2015 (ዋልታ) በፆመ-ፍልሰታ ምዕመናን በተመስጦና በንስሐ ሕይወት ስለ ሰላምና ፍቅር እንዲማፀኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጠየቁ።

አቡነ ማቲያስ የፆመ-ፍልሰታ መግቢያን አስመልክተው ለምዕመናን ባስተላለፉት መልዕክት ፆመ-ፍልሰታ በፍቅር ለፍቅር የተፈጸመ ነው።

"የቅዱስ ወንጌል አስተምህሮ መሠረትና ጣሪያ ወለልና ግድግዳ በፍቅርና በፍቅር ብቻ የተገነባ ነው ፍቅር እግዚአብሔር ዓለምን ያዳነበት መድኃኒት ነው" ብለዋል።

"ፍቅር የጥላቻና የመለያየት ግንብን ንዶ ይቅርታንና አንድነትን የሚገነባ ጠንካራ ዓለት ነው፤ ፍቅር መጽናናትንና ደስታን የሚያፈራ ጣፋጭ ተክል ነው፤ በፍቅር ለፍቅር የሚደረግ ሁሉ ፍስሐን እንጂ ጸጸትን አያስከትልም " ሲሉም ተናግረዋል።

በመሆኑም ሕዝበ-ክርስቲያኑ በፆመ-ፍልሰታ በተመስጦና በንስሐ ሕይወት ስለ ሰላምና ፍቅር እንዲማፀኑ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በፆሙ ወቅት ምዕመናን ስለ ሰላምና ፍቅር እየተማፀኑ ካላቸው በረከት ለተራቡትና ለተፈናቀሉት እንዲለግሱም አቡነ ማቲያስ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል የሚፈጠሩ ችግሮች በርካታ ጥፋቶችን የሚያስከትሉ መሆኑን ገልጸው ችግሮች ሲፈጠሩ በሥርዓትና በእርቅ መፍታት እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀሐምሌ 28/2015 (ዋልታ) የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የትምህርት ሚ...
04/08/2023

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

ሐምሌ 28/2015 (ዋልታ) የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ::

ፈተናው ከሐምሌ 19 እስከ 21 በማህበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 25 እስከ 28/2015 በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተሰጥቷል።

ፈተናውን ለመፈተን በአጠቃላይ 868 ሺህ 74 ተማሪዎች መመዝገባቸውንና ከዚህ ውስጥ 840 ሺህ 859 ፈተናውን መውሰዳቸውን የገለፁት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የፈተና ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን አስቀድሞ በማዘጋጀትና በመከለስ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር በማድረግ በጥብቅ ዲሲፕሊን የተተገበረ ነው ብለዋል::

ነገር ግን በአንዳንድ መፈተኛ ጣቢያዎች የተወሰነ የስነ ምግባር ጉድለቶች መስተዋላቸው የተነሳ ሲሆን ካጋጠሙት ችግሮች መካከልም ለፈተና ያልተፈቀዱ ነገሮችን ወደ ዩኒቨርሲቲ ይዞ ለመግባት መሞከር አንዱ መሆኑን በአብነት ተጠቅሷል::

ጋምቤላ ላይ የተወሰኑ ተማሪዎች ባጋጠማቸው ሕመም 38 ተማሪዎች ፈተና እንዳልወሰዱም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ብሄራዊ ፈተናው በዝግጅቱ፣ በስርጭቱ እና አሰጣጡ ስኬታማ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ለቀጣይ መሰረት የጣለ ነው ብለዋል::

በህግ ጥላ ስር ላሉ ተፈታኞች፣ በኢትዮጵያ ስርአተ ትምህርት ለሚማሩ እንዲሁም በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ተፈታኞች ከነሃሴ 23 እስከ 26/2015 ዓ.ም ድረስ ብሄራዊ ፈተናው እንደሚሰጣቸው ተመላክቷል::

በሄብሮን ዋልታው
ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎች እና የተከለከሉ ተግባራት ይፋ ሆኑሐምሌ 28/2015 (ዋልታ) በአማራ ክልል የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባወጣ...
04/08/2023

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎች እና የተከለከሉ ተግባራት ይፋ ሆኑ

ሐምሌ 28/2015 (ዋልታ) በአማራ ክልል የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባወጣው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎች እና የተከለከሉ ተግባራት ይፋ ሆኑ።

ዝርዝሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

ለሽልማቱ ተዘጋጅተዋል? ለቀልጣፍ ግብይት hulu payን ይጠቀሙ  ስቀላቀሉ ብቻ የ25ብር 🎁 BONES ይሰጣል አንድ ሰው በጋበዛችው ቁጥር 3 በር በሽልማት መልክ ይሰጣል አሁኑኑ ይጀምሩ መል...
02/08/2023

ለሽልማቱ ተዘጋጅተዋል? ለቀልጣፍ ግብይት hulu payን ይጠቀሙ ስቀላቀሉ ብቻ የ25ብር 🎁 BONES ይሰጣል አንድ ሰው በጋበዛችው ቁጥር 3 በር በሽልማት መልክ ይሰጣል አሁኑኑ ይጀምሩ መልካም ዕድል
👎👎👎👎https://t.me/hulepay_official_bot?start=r0757733165

በበጀት ዓመቱ ከ7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ደርሷል - የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣንሐምሌ 25/2015 (ዋልታ) በ2015 በጀት ዓመት በ...
01/08/2023

በበጀት ዓመቱ ከ7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ደርሷል - የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

ሐምሌ 25/2015 (ዋልታ) በ2015 በጀት ዓመት በተሸከርካሪዎች ግጭት ምክንያት 7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ባለው የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።

በበጀት ዓመቱ በቀለበት መንገድ ላይ 135፣ ከቀለበት መንገድ ውጪ ደግሞ 199፣ በድምሩ 334 የግጭት አደጋዎችም ደርሰዋል ተብሏል፡፡

በተሽከርካሪዎች ግጭት በአብዛኛው ጉዳት እየደረሰባቸው የሚገኙት የመንገድ መብራት ምሶሶዎች፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የአቅጣጫና ርቀት አመላካች ሰሌዳዎች፣ የእግረኛ መከላከያ አጥሮች፣ የመንገድ አካፋይ ከርቭስቶን እና የማንሆል ክዳኖች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በተሽከርካሪ ግጭት ሳቢያ እየደረሰ ላለው የመንገድ ሀብት ጉዳት መንስኤ ከሆኑት መካከል ጠጥቶ ማሽከርከር፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ መንዳት እና ያለ መንጃ ፈቃድ ማሽከርከር ተጠቃሽ ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ካደረሱ አሸከርካሪዎች ተገቢውን የካሣ ክፍያ ከመሰብሰብ ጎን ለጎን ጉዳት የደረሰባቸውን የመንገድ ሀብቶች በመጠገን ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን መረጃ ያመለክታል።

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

ሚኒስትሩ በአማሮ ልዩ ወረዳ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የመቄሬዲ አጸደ ህጻናት ት/ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ ሐምሌ 25/2015 (ዋልታ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስ...
01/08/2023

ሚኒስትሩ በአማሮ ልዩ ወረዳ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የመቄሬዲ አጸደ ህጻናት ት/ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

ሐምሌ 25/2015 (ዋልታ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የመቄሬዲ አጸደ ህጻናት ት/ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) የደቡብ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በአማሮ ልዩ ወረዳ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ አስጀምረዋል።

ሚኒስትሩ በልዩ ወረዳው ከሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን የመቄሬዲ አጸደ ህጻናት ት/ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

የአረጋውያን ቤት እድሳት የችግኝ ተከላ እና ሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች የማከናወን መርሐ ግብር መካሄዱን የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ሲጓዙ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር  ዋሉሐምሌ 24/2015 (ዋልታ) ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ሲጓዙ የነበሩ አራት...
31/07/2023

ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ሲጓዙ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ሐምሌ 24/2015 (ዋልታ) ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ሲጓዙ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎችን ከነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ገለፀ።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት መነሻቸውን ከአዋሽ አድርገው በመንግሥት መኪና ሁለት ስናይፐር ጠመንጃ፣ አንድ ላውንቸር፣ አምስት የላውንቸር ተተኳሽ ቁንቡላ፣ 28 የስናይፐር ካርታ ከመሰል ጥይት ጋር፣ ሁለት ሙሉ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም ልብስ፣ ሦስት ሙሉ የአፋር ልዩ ኃይል ዩኒፎርም ልብስ እና ሸሚዝ ጭነው ለሸኔ የሽብር ቡድን ለማድረስ ሲጓዙ ሰበታ ከተማ እንደደረሱ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይሉ ባደረገው ጠንካራ ክትትል መሆኑ ታውቋል።

ኅብረተሰቡም እነዚህ ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎች በሸኔ የሽብር ቡድን እጅ ቢገቡ ኖሮ በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ከፍተኛ ጉዳት ተገንዝቦ መሰል የወንጀል ተግባራትን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ጥሪ ማቅረቡን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

ከ454 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉሐምሌ 24/2015 (ዋልታ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከሐምሌ 14 እስከ 20 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 194 ሚሊዮን...
31/07/2023

ከ454 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሐምሌ 24/2015 (ዋልታ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከሐምሌ 14 እስከ 20 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 194 ሚሊዮን የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና ከ260 ሚሊዮን ብር በላይ የወጭ፤ በድምሩ ከ454 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዙን አስታወቀ፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር የላቀ አፈጻጸም የተመዘገበ ሲሆን በዚህም ኤርፖርት ፣ ጅግጅጋ እና ድሬድዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በቅደም ተከተላቸው 183 ሚሊዮን፣ 44 ሚሊዮን እና 28 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ 11 ግለሰቦች እና 4 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኮሚሽኑ የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የምርምር ማዕከል በጋራ ለማቋቋም ተስማሙሐምሌ 19/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የባዮሎጂካል ሳይንስ የጥናትና ምርምር ማዕከል በጋራ ለማቋቋም የሚያስችላቸውን ስም...
27/07/2023

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የምርምር ማዕከል በጋራ ለማቋቋም ተስማሙ

ሐምሌ 19/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የባዮሎጂካል ሳይንስ የጥናትና ምርምር ማዕከል በጋራ ለማቋቋም የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከሩሲያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ቫለሪ ፋልኮቭ ጋር ተፈራርመዋል።

የሩሲያ ተመራማሪዎች በኢትዮጵያ ከ35 አመታት በላይ በስነ ህይወት ዙሪያ ጥናትና ምርምር ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል።

የአሁኑ ስምምነት ከዚህ በፊት ሩሲያውያን ተመራማሪዎች ሲያካሂዱ የቆዩትን ጥናት አድማስ ለማስፋትና ምርምሮቹም ተቋማዊ ባለቤትነት ኖሯቸው ኢትዮጵያም ከዘርፉ የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ የሚያስችል ስምምነት መሆኑን የኢኖብቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ማእከሉን ሁለቱ ሀገራት በጋራ አቋቁመው ወደ ተግባር ሲገቡ በዘርፉ ያለውን የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ያስፋፋል ተብሏል።

የሁለቱ ሀገራት የዘርፉ ባለሙያዎችና የስራ ሃላፊዎች በጉዳዩ ዙሪያ በተያዘው አመት ለስምምነት የሚያበቃቸውን ውይይትና ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው ዛሬ የስምምነት ፊርማ ያካሄዱት።

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

 ተሽከርካሪ ነዳጅ የሚበላባቸው (የነዳጅ ፍጆታ የሚጨምርባቸው) ምክንያቶችና መፍትሄዎች! (ክፍል 2)በሳሙኤል አማረሐምሌ 18/2015 (ዋልታ) የነዳጅ ፍጆታ እንዲጨምር የሚያደርጉ የአሽከርካሪ...
25/07/2023



ተሽከርካሪ ነዳጅ የሚበላባቸው (የነዳጅ ፍጆታ የሚጨምርባቸው) ምክንያቶችና መፍትሄዎች! (ክፍል 2)
በሳሙኤል አማረ

ሐምሌ 18/2015 (ዋልታ) የነዳጅ ፍጆታ እንዲጨምር የሚያደርጉ የአሽከርካሪ ስህተቶችና የአነዳድ ሁኔታዎች:-

1ኛ, የጀሪካን ነዳጅ መጠቀም (በብላክ ማርኬት ነዳጅ መቅዳት) - በብላክ ከጀሪካን የሚቀዳ ነዳጅ ከቆሻሻ ጋር የመቀላቀል እድሉ በጣም ከፍተኛ ነው፤ በተለይም ደግሞ ናፍጣ ቆሻሻን የመሳብና የመሸከም ባህሪ ስላለው እንዲሁም ለብዙ ተሽከርካሪዎች በተመሳሳይ እቃ የሚቀዳ በመሆኑ ቆሻሻ ከነዳጅ ጋር ተቀላቅሎ ይገባል፡፡ ይህም የነዳጅ ማጣሪያ፣ ኢንጀክሽን ፓምፕና ኢንጀክተር ኖዝል በቆሻሻ እንዲደፈኑ በማድረግ በክፍል አንድ ያየናቸው ችግሮች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፡፡

👉መፍትሄ:- ከህጋዊ ነዳጅ ማደያዎች ውጭ በብላክ ማርኬት የጀሪካን ነዳጅ አለመቅዳት

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

ችግኝ በመትከል ዘመን ተሻጋሪ አሻራችንን እናኑር!
14/07/2023

ችግኝ በመትከል ዘመን ተሻጋሪ አሻራችንን እናኑር!

አየር መንገዱ ከእንግሊዙ የአውሮፕላን ሞተር አምራች ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመሐምሌ 2/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእንግሊዙ ሮልስ ሮይስ የአውሮፕላን ሞተር አምራች ኩባን...
09/07/2023

አየር መንገዱ ከእንግሊዙ የአውሮፕላን ሞተር አምራች ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

ሐምሌ 2/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእንግሊዙ ሮልስ ሮይስ የአውሮፕላን ሞተር አምራች ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱ አየር መንገዱ በቀጣይ ለሚረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ሞዴል ሞተሮች አጠቃላይ የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ኮንትራቱ የተፈረመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ኃላፊዎች በእንግሊዝ ደርቢ የሚገኘውን የሮልስ ሮይስ የአውሮፕላን ሞተር አምራች ኩባንያ ዋና መሥሪያ ቤት በጎበኙበት ወቅት መሆኑም ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ግንኙነት ልዩ ትርጉም ያለው ነው - ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ሰኔ 30/2015(ዋልታ) የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ሁለንተናዊ ግንኙነት ጥብቅ እና ልዩ ትርጉም ያለው መሆኑን...
07/07/2023

የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ግንኙነት ልዩ ትርጉም ያለው ነው - ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ

ሰኔ 30/2015(ዋልታ) የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ሁለንተናዊ ግንኙነት ጥብቅ እና ልዩ ትርጉም ያለው መሆኑን የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የጅቡቲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ዘመናዊ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ባልነበረበት ጊዜም የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩ ጠንካራ እንደነበር ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ አስታውሰዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ የኢትዮጵያ ጉብኝት ስትራቴጂካዊ ግንኙነቱን የበለጠ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።

የጅቡቲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ መሪና የአገር ውስጥ ሚኒስትር ዴኤታ ሲራጅ ኦማር በበኩላቸው የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩ በንግድ መስክም እንዲጠናከር ሁኔታዎችን ማመቻቸት ያስፈልጋል ብለዋል።

የጅቡቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ በኢትዮጵያ ቆይታው በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እና በውይይት መድረኮች ሲሳተፍ መቆየቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

የ2016 ዓ.ም ጠቅላላ በጀትለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉhttps://t.me/waltatv100
06/07/2023

የ2016 ዓ.ም ጠቅላላ በጀት

ለበለጠ መረጃ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/waltatv100

💥ይሳተፉ ይሸለሙ !የኳታር የዓለም ዋንጫ ከሁለት ቀናት እረፍት በኋላ ነገ ምሽት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ይካሄዳል፡፡በነገው እለት ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ አርጄንቲና ከክሮሺያ የሚያደርጉት የግማ...
12/12/2022

💥ይሳተፉ ይሸለሙ !

የኳታር የዓለም ዋንጫ ከሁለት ቀናት እረፍት በኋላ ነገ ምሽት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ይካሄዳል፡፡

በነገው እለት ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ አርጄንቲና ከክሮሺያ የሚያደርጉት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

ይህንን ወሳኝ ጫወታ ማን ያሸንፋል? ግምትዎን ያስቀምጡ!

በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መቀበያችን 8970 ላይ WS በማስቀደም ግምታችሁን ላኩልን!

የቴሌግራም ቻናላችንን መቀላቀል አለባችው👉https://t.me/waltatvnews

💥ይሳተፉ ይሸለሙ !በኳታሩ የዓለም  ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ  ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ ሞሮኮ ከፖርቹጋል የሚያደርጉት ጫወታ ተጠባቂ ነው፡፡ይህንን ወሳኝ ጫወታ ማን ያሸንፋል ?  ግምትዎን ያስቀምጡ...
10/12/2022

💥ይሳተፉ ይሸለሙ !

በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ ሞሮኮ ከፖርቹጋል የሚያደርጉት ጫወታ ተጠባቂ ነው፡፡

ይህንን ወሳኝ ጫወታ ማን ያሸንፋል ? ግምትዎን ያስቀምጡ!

በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መቀበያችን 8970 ላይ WS በማስቀደም ግምታችሁን ላኩልን!

የትላንትና ብቸኛ ተሸላሚ አህመዲን አብዱርአማን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

telegram
👎👎👎👎
https://t.me/waltatvnews

Address

Bole
Addis Ababa
64446

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Walta Tv ዋልታ ቲቪ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category