21/05/2021
በደቡብ ክልል በከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ተጠቃሚ ከተሞች የ2012 በጀት ዓመት ስራ አፈጻጸም ግምገማ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡
ከተሞቹ በተናጥል ያገኙት ውጤትም በዝርዝር ቀርቧል፡፡
በክልሉ 20 ከተሞች በከተሞች የተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡
ፕሮግራሙም በህዝቡ የሚጠየቁ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችና ማስፋፊያዎች ላይ ምላሽ በመስጠት ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ይገኛል፡፡
በከተሞች የዲች ግንባታ፣ የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ፣ የመብራት ዝርጋታና መሰል ተግባራትን በሰፊው ከማከናወኑም በላይ ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን እያበረከተ መሁኑ ይታወቃል፡፡
ከተሞቹ ተቋማትን ለመገንባትና መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት የሚያውሉትን ገንዘብ በየዓመቱ የሚያገኙት ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር ቢሆንም የብድር መጠኑ የሚወሰነው ከተሞቹ በሚያስመዘግቡት የተቋማት አፈጻጸም ውጤት መሰረት ነው፡፡
የኢፌድሪ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በመደበው ገለልተኛ አማካሪ በክልሉ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ የሆኑ ሁሉም ከተሞች አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል ማለቱን ከደቡብ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በደቡብ ክልል የከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ዳታ እንደተናገሩት ከተሞቹ ያስመዘገቡትን ውጤት ማስቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
በክልሉ የ20 ከተሞች አማካይ ውጤት 95.26 በመቶ መሆኑን የተናገሩት አቶ ዳምጤ ክልሉም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረጉና ከተሞቹ ባደረጉት ጠንካራ ስራ ነው ብለዋል፡፡
ከተሞች በ2013 በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ በ2014 በጀት ዓመት የተሻለ የገንዘብ ብድር ለማገኘት ከወዲሁ አስበው ሊሰሩ ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
SNNPRS Urban Development & Construction Bureau,
UIIDP 3rd APA Summary Results (EFY 2012 performance)
1 Arbaminch ------ 95.84
2 Dilla YES ---------90.38
3 Wolayta S**o -----97.77
4 Areka ------ 96.69
5 Butajira ------ 96.53
6 Hosaena ------- 97.54
7 Mizanaman ------ 95.59
8 Bodite ------- 90.51
9 Bonga ------- 93.10
10 Durame ------- 98.45
11 Hadero -------- 97.53
12 Alaba Kulito ---- 95.41
13 Jinka ------- 96.93
14 Sawula ------ 93.80
15 ShinShicho ----- 91.66
16 Shone ------ 98.25
17 Tepi ----- 91.56
18 Welkite ------ 96.38
19 Worabe ------ 96.20
20 Yirga Chefe -------- 94.98
Average Score of 20 ULGs 95.26
Source:SNNPRS Urban Development & Construction Bureau