Kambaati Harde qu'mita

Kambaati Harde qu'mita struggle for Kambata

02/09/2024

#ይውጠልህ!!
#ባዱ #ገሻንቹ ቤቱ መገኑ #ኣሶሄ ከምባታ!!

02/09/2024

አቅማችንን ስላወቁ ልያሳንሱን ልበትኑን ወደዋል አይሁዳውያንም በህትሌር ተጣልተው ነበር ነገር ግን እስከሁን በአለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ ናቸዉ ።እኛንም ስለፈሩ ነው የትኩረት አቅጣጫቸው አድርገዋል ለከምባታ እግዚአብሔር አለ እናሸንፋለን ድሉየኛ ይሆናል ። አሁን ቦሓላ አንድነታችን አጠናክረን ውስጣዊ ነገሮቻችንን አስቀምጠን የተጋረጠብንን ጠላት ጠላት ለመመከት በጋራ መቆም ያስፈልጋል ።

ከምባታነቴ ማንነቴ ኩራቴ ነው!! ሌላ ብሔር የለኝም... ሕዝቤን እወዳለሁ እታገላለሁ ለፍትህ እቆማለሁ!!!
31/08/2024

ከምባታነቴ ማንነቴ ኩራቴ ነው!! ሌላ ብሔር የለኝም... ሕዝቤን እወዳለሁ እታገላለሁ ለፍትህ እቆማለሁ!!!

Justice For Kembata
29/08/2024

Justice For Kembata

ለጠቅላላ እውቀት ፨፨   ፨፨ሼር♨የእርግዝና የጊዜ ቆይታ ~ 280 ቀናቶች♨ የአጥንታችን ብዛት ~ 206♨አማካይ የደም መጠን ~ ከ 4-5 ሊትር♨ የጡንቻዎቻችን ብዛት ~ 639♨የኩላሊቶቻችን ...
28/08/2024

ለጠቅላላ እውቀት ፨፨ ፨፨ሼር

♨የእርግዝና የጊዜ ቆይታ ~ 280 ቀናቶች
♨ የአጥንታችን ብዛት ~ 206
♨አማካይ የደም መጠን ~ ከ 4-5 ሊትር
♨ የጡንቻዎቻችን ብዛት ~ 639
♨የኩላሊቶቻችን ብዛት ~ 2
♨የወተት ጥርሶቻችን ብዛት ~ 20
♨ የጐን አጥንቶቻችን ብዛት ~ 24 (12 ጥንዶች)
♨ የልባችን ውስጥ ክፍሎች ብዛት ~ 4

※ ትልቁ ደም ቅዳ ~ አኦርታ
※ ጤናማ አማካይ የደም ግፊት መጠን ~ 120/80
※ የደም ፒ ኤች (PH) መጠን ~ 7.4
※ አዲስ የተወለደ ህፃን የአጥንት ብዛት ~ 300
※ በጀርባ ላይ የሚገኙ የአከርካሪዎች ብዛት ~ 30
※ በአንገት ላይ የሚገኙ የአከርካሪዎች ብዛት ~ 7
※ በፊት ላይ የሚገኝ የአጥንት ብዛት ~ 14
※ በጭንቅላት ላይ የሚገኝ የአጥንት ብዛት ~ 22
※ በደረት ላይ የሚገኝ የአጥንት ብዛት ~ 25
※ በክንድ ላይ የሚገኙ የአጥንት ብዛት ~ 6
※ በሰው እግር ላይ የሚገኙ የአጥንቶች ብዛት ~ 33
※ በእያንዳንድ የእጅ አንጓ (wrist) ላይ የሚገኙ የአጥንቶች ብዛት ~ 8
※ በእጅ ላይ የሚገኙ የአጥንቶች ብዛት ~ 27
※ በእያንዳንድ ጆሮአችን ላይ የሚገኙ የአጥንቶች ብዛት ~ 3
※ በክንድ ላይ የሚገኙ የጡንቻዎች ብዛት ~ 72
※ ትልቁ ኦርጋን ~ ቆዳ
※ ትልቁ ዕጢ ~ ጉበት
※ ትንሹ ሴል ~ የደም ሴል
※ ትልቁ ሴል ~ የዕንቁላል ሴል
※ ትንሹ አጥንት ~ ሰታፕስ (stapes)
※ የመጀመሪያው ንቅለ ተከላ የተደረገው የሰውነት ክፍል ~ ልብ
※ አማካይ የትንሹ አንጀት ቁመት ~ 7 ሜትር
※ አማካት የትልቁ አንጀት ቁመት ~ 1.5 ሜትር
※ አዲስ የተወለደ ህፃን አማካይ ክብደት ~ 2.6 ኪሎ ግራም
※ የልብ ምት በአንድ ደቂቃ ውስጥ ~ 72 ጊዜ
※ የሰውነት ሙቀት ~ 36.9 ዲግሪ ሴንቲግሬድ (98.4 ዲግሪ ፋራናይት)

※ ቀይ የደም ሴል በህይወት የሚቆዮበት ጊዜ ~ 120 ቀናቶች

※ ትልቁ የኢንዶክራይን ዕጢ ~ ታይሮይድ
※ ትልቁ የሊምፋቲክ (lymphatic) ዕጢ ~ ጣፊያ
※ ግዙፉ ሴል ~ ነርቭ ሴል
※ ትልቁ የአእምሮ ክፍል ~ ሰርብረም
※ ትልቁና ጠንካራው አጥንት ~ ፌሙር (Femur)
※ ትንሹ ጡንቻ ~ ስታፒደስ (Stapedius) (የመካከለኛው ጆሮ)
※ በሴል ውስጥ ያለ የክሮሞዞም ብዛት ~ 44 (23 ጥንዶች)
※ ትልቁ ጡንቻ ~ መቀመጫ (ቂጥ)

ምንጭ⚂ Anatomy -75/109 for firaw
ለተጨማሪ መርጃ ⚂ፔጁን ሼር፣፣ላይክ ያድርጉ

ካነበቡ በኋላ ለጓደኛወ ሸር ✔

28/08/2024

የ2017 ዓ.ም የመሳላ አዋርድ ተሸላሚዎችን ጥቆማ ይስጡ!
********
ከነሐሴ 22- 27 ድረስ ብቻ!

ማሳሰቢያ የ2016 ዓ.ም የመሳላ አዋርድ ተሸላሚዎች በዘንድሮ የመሳላ አዋርድ ተሸላሚዎች ጥቆማ ውስጥ አይካተቱም። እዚህ ይመልከቱ።(https://www.facebook.com/share/p/E6BdM87EK91PWvNK/?)

የቪዚት ከምባታ አስጎብኚ እና ኢቨንትስ ድርጅት ካዘጋጃቸው "የመሳላ ሳምንት" ዝግጅቶች አንዱ የመሳላ አዋርድ ሲሆን የእውቅና ዝግጅቱ በተመረጡ 14 ዘርፎች ለከምባታ ብሄረሰብ ብሎም ለሀገር ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሰዎች ዕውቅና የሚሰጥበት ታላቅ ዝግጅት ነው። የተመረጡ 13ቱ ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው! በቅደም ተከተላቸው መሰረት ጥቆማ ይስጡ።

1. በትምህርት ዘርፍ
2. በጤና ዘርፍ
3. በህይወት ዘመን አገልግሎት ዘርፍ
4. በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ
5. በማስታወቂያ እና የመድረክ ስራዎች ዘርፍ
6. በበጎ አድራጎት ማህበራት ዘርፍ
7. በበጎ አድራጊ ግለሰቦች ዝርፍ
8. በቱሪዝም ዘርፍ
9. በስፖርት ዘርፍ (በወንድ እና በሴት)
10. በኢንቨስትመንት እና የስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ
11. ምርጥ የከምባታ ባህላዊ ሙዚቃ
12. ምርጥ ዘጋቢ ጋዜጠኛ (ስለ ብሄረሰቡ የተሰራ ዶክመንተሪ)
13. ልዩ የመሳላ አዋርድ ተሸላሚ

⚪የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሰዎችን ስም የትምህርት ሁኔታ ምን ምን እንዳበረከቱ ኮሜንት በማድረግ ጥቆማ ይስጡን።

🔵መልካም የሰሩ ሰዎችን በማክበርና በማጀገን ገድላቸውን ለሚቀጥለው ትውልድ እናሸጋግራለን!

🔴ጥቆማ መስጠት የሚቻለው በቪዚት ከምባታ የፌስቡክ ድህረገጽ ብቻ ነው!

ሁለተኛው የመሳላ አዋርድ!

28/08/2024

ከግብርና ቢሮ የአደጋ ስጋት ቁጥጥር እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ከዱራሜ ለመውሰድ የምደረገው እንቅስቃሴ እንቃወማለን!

25/08/2024

ግብርና ቢሮ ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ ተጠሪ ተቋማትን የማይሆን ምክንያት እየጠቀሱ ከዞናችን ለመንጠቅ የምደረግ ጥረት ሕዝብን ያስቆጣል ይቁም!!

ሜጦማን አብናም ከምባታ!!በማእከላዊ ኢትዮጵያ  #በቢሮ ድልድል ግዜ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለው የሕዝብ ልጅ  #ገዝሽ እና የከምባታ ልማት ጉዳይ የሚያንገሸግሻት በሁሉም ዘርፍ ወጣቶችን በማንቃት በ...
25/08/2024

ሜጦማን አብናም ከምባታ!!
በማእከላዊ ኢትዮጵያ #በቢሮ ድልድል ግዜ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለው የሕዝብ ልጅ #ገዝሽ እና የከምባታ ልማት ጉዳይ የሚያንገሸግሻት በሁሉም ዘርፍ ወጣቶችን በማንቃት በማስተባበር #ገጽታችን የሆነች #ጸጋ በደቡብ አፍሪካ

ሆላ መሳል ወጋ!
25/08/2024

ሆላ መሳል ወጋ!

25/08/2024
25/08/2024
የከምባታ ሴት ዶ/ር ቦጋለች ከተወለደችበት ምድር የወጠች ብርቱ የከምባታ ገጽታ ገንቢ ፣ታጋይ ከምባታ በህሉን ፣ወጉን በሰው ሀገር ለራሷ ሳይጎልባት እየኖረች የሕዝብ ድምፅ ሆናለች ። ልማት አ...
21/08/2024

የከምባታ ሴት ዶ/ር ቦጋለች ከተወለደችበት ምድር የወጠች ብርቱ የከምባታ ገጽታ ገንቢ ፣ታጋይ ከምባታ በህሉን ፣ወጉን በሰው ሀገር ለራሷ ሳይጎልባት እየኖረች የሕዝብ ድምፅ ሆናለች ። ልማት አንድነት እንደ ህዝብ በአገርና በአለም ዙርያ ከፍ ብለን እንድንታይ የራሷ አስተዋጽኦ እየተወጠች ነው። ዶ/ር Tsega!

21/05/2021

በደቡብ ክልል በከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ተጠቃሚ ከተሞች የ2012 በጀት ዓመት ስራ አፈጻጸም ግምገማ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡

ከተሞቹ በተናጥል ያገኙት ውጤትም በዝርዝር ቀርቧል፡፡

በክልሉ 20 ከተሞች በከተሞች የተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

ፕሮግራሙም በህዝቡ የሚጠየቁ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችና ማስፋፊያዎች ላይ ምላሽ በመስጠት ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ይገኛል፡፡

በከተሞች የዲች ግንባታ፣ የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ፣ የመብራት ዝርጋታና መሰል ተግባራትን በሰፊው ከማከናወኑም በላይ ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን እያበረከተ መሁኑ ይታወቃል፡፡

ከተሞቹ ተቋማትን ለመገንባትና መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት የሚያውሉትን ገንዘብ በየዓመቱ የሚያገኙት ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር ቢሆንም የብድር መጠኑ የሚወሰነው ከተሞቹ በሚያስመዘግቡት የተቋማት አፈጻጸም ውጤት መሰረት ነው፡፡

የኢፌድሪ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በመደበው ገለልተኛ አማካሪ በክልሉ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ የሆኑ ሁሉም ከተሞች አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል ማለቱን ከደቡብ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በደቡብ ክልል የከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ዳታ እንደተናገሩት ከተሞቹ ያስመዘገቡትን ውጤት ማስቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

በክልሉ የ20 ከተሞች አማካይ ውጤት 95.26 በመቶ መሆኑን የተናገሩት አቶ ዳምጤ ክልሉም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረጉና ከተሞቹ ባደረጉት ጠንካራ ስራ ነው ብለዋል፡፡

ከተሞች በ2013 በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ በ2014 በጀት ዓመት የተሻለ የገንዘብ ብድር ለማገኘት ከወዲሁ አስበው ሊሰሩ ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

SNNPRS Urban Development & Construction Bureau,
UIIDP 3rd APA Summary Results (EFY 2012 performance)


1 Arbaminch ------ 95.84
2 Dilla YES ---------90.38
3 Wolayta S**o -----97.77
4 Areka ------ 96.69
5 Butajira ------ 96.53
6 Hosaena ------- 97.54
7 Mizanaman ------ 95.59
8 Bodite ------- 90.51
9 Bonga ------- 93.10
10 Durame ------- 98.45
11 Hadero -------- 97.53
12 Alaba Kulito ---- 95.41
13 Jinka ------- 96.93
14 Sawula ------ 93.80
15 ShinShicho ----- 91.66
16 Shone ------ 98.25
17 Tepi ----- 91.56
18 Welkite ------ 96.38
19 Worabe ------ 96.20
20 Yirga Chefe -------- 94.98
Average Score of 20 ULGs 95.26
Source:SNNPRS Urban Development & Construction Bureau

21/05/2021

የዱራሜ ከተማ ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው 2ኛ ዙር 8ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ አሰቸኳይ ጉባኤ አቶ አሸናፊ ሀይሉን ተጠባባቂ ዋና ከንቲባ አድርጎ መሾሙ የሚታወስ ሲሆን ተጠባባቂ ዋና ከንቲባው በምክር ቤቱ ለተገኙት የህዝብ ተወካዮችም ንግግር አድርገዋል፡፡

በተለይም "መሪነት ባላደራነት ነው የህዝብ ሃላፊነት ለእኔ ይገባል ከማለት ይልቅ ለህዝቤ ይገባል ማለት ነው፡፡ ልጠቀመውን ሳይሆን ልጥቀመውን ማሰብ ከራስ ምቾት ይልቅ የህዝብ ምቾት ማስቀደም ነው" በማለት ነው ንግግራቸውን የጀመሩት፡፡

"ማህበረሰባችን ልከኛና ትዕግስተኛ እንደመሆኑ መጠን በርካታ የሚጎረብቱ ችግሮች እያሉትም ከትላንት ዛሬ ከዛሬ ነጌ እንደሚሻል በማመን ሁሉንም መሪ አቅፎ ደግፎ ጊዜ ስጥቶ በተስፋ የሚጠባበቅ ንቁ ማህበረሰብ ነው ብለዋል፡፡ ጥሩ የስራውን ሁሉንም ወገኔ ብሎ ከሚደግፍ ያጠፋውን ገስጾ ከሚያቀና ማህበረሰብ አብራክ የወጣው እንደመሆኔ መጠን ኩራት ይሰማኛል" ብለዋል፡፡

በማስከተልም "ትላንት ከተማችንን ሲመሩ ከነበሩ መሪዎች ጠንካራ ጎናቸውን ታታሪነታቸውን በማድነቅ ከደካማ ጎናቸው ደግሞ ትምህርት በመውሰድ በቀጣይ ለማህበረሰባችን ለውጥ እንዲመጣ አበክረን እንስራለን በማለት በቀጣይም ትኩረት ሰጥተው በሚስሩዋቸው ጉዳዮች ላይም ሰፊ ማብራሪያ ስጥተዋል፦

፩. የመሬት ወረራን በማስቀረትና በህጋዊ መንገድ መሬትን ለተለያዩ አገልግሎቶች በስፋት በማቅረብ ፣ ኘላን የማውረድ ሥራ እንደሚሰራ ፣ የፀጥታ ችግርን በተመለከተ ከማህበረሰቡ ፣ ከፀጥታ አካላትና ከፍትህ አካላት ጋር በመቀናጀት የፀጥታ ችግሮችን ከምንጩ ለማድረቅ እንደሚሰራ፡፡

፪. በሲቪል ሰርቪስ ፣ በተቋማት አስራር ውስጥ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ከሙስና የፀዳ አስራር እንደሚፈጠር ፣ የፋይናንስ አስተዳደር ግልፀኝነት እንደሚፈጠር ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ መንግስት ሠራተኞችና ፣ መምህራንና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በህጋዊ መንገድ የቤት መስሪያ ቦታ በልዩ ውሳኔ እንደሚሰጥ፡፡

፫. ስራ አጥነትን ለመቅረፍ ፣ ከተማው ለኢንቨስተሮች ሳቢ እንዲሆን በማስቻል ረገድ ፣ ከተማውን ፅዱና ውብ የማድረግ ሥራ ፣ የዓለም ባንክ ኘሮጄክቶች በጥራትና በፍጥነት እንዲሰሩ ልዩ ትኩረት ተስጥቶ ክትትል እንደሚደረግ ፣ በአምስቱም የዕድገት ዘርፎች ከሌሎች አቻ የዞን ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ እንድትሆን ውጤታማ ስራ እንደሚሰራ ፣ የከተማ ግብርናን የማሳደግ ፣ የፍጆታ ዕቃና ሸቀጦች ላይ አላግባብ ዋጋ በሚጨምሩ ስግብግብ አካላትን የመቆጣጠር ስራዎች እንደሚሰሩ፡፡

፬. ከተማዋ የኢንዱስትሪ ከተማ እንድትሆን የኢንዱስትሪ መስሪያ ቦታዎችን የማዘጋጀት ፣ የከተማውን የኢኮኖሚ አቅም ባገናዘበና ፍትሐዊ አካሄዱን በጠበቀ መልኩ የግብርና ታክስ ስርዓት እንደሚሰራ ፣ የትምህርትና የጤና ጥራትና ተደራሽነትን የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰራ አዲሱ ተጠባባቂ ከንቲባ አቶ አሸናፊ ሀይሉ በምክር ቤቱ ቀርበው ገልፀዋል፡፡

በመጨራሻም ከንቲባው ባስተላለፉት መልዕክት "ገና ስንፈጠር ጀምሮ መልካችንና አሻራችን የተለያየ ቢሆንም ከሚከፋፍሉን አጀንዳዎች ርቀን ሰውን በሰውነቱ አክብረን ዘር ፣ ጎሳና ሃይማኖት ሳንል ሁሉን በእኩልና በታማኝነት ለማገልገል ቃል እገባለው" ብለዋል፡፡
የዱራሜ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት
ዱራሜ
ሚያዚያ 30 2013

18/05/2021
14/05/2021

በየትኛውም ሁኔታ ስራ ማግኘት ፈተና የሆነብን ወጣቶች የሚጠብቀን ነገር ብዙ መሆኑ ፈተና ሆኖብናል ፡፡በዚህ ዙርያ የዱራሜ ከተማ ከuniversity ተመርቀው በተለያዩ የአስተዳደር ችግር የተነሳ ወጣቶች ከምማሩበት ት/ት ቤት ይዘው የወጡትን የአዕመሮ ሀብት ከመጠቀም ይልቅ እርስ በራሳቸው በያንዳንዱ ስራ ዘርፍ አስተዳደር ቦታዎችን ሸፋፍነው መጠቀምን እንደ አማራጭ እየተጠቀሙ እንደ ሆና የተለያዩ የመረጃ ምንጮች እያሳዩን ነው ፡፡ በሀገሪቱ የተንሰራፋውን ስራ አጥነት መቅረፍ መንግስት አዳዲስ አስተሳሰቦችን ስራ ላይ ለማዋል የፖሊሲ ማሻሻዎችን ጭምር ለማድረግ ስሞክር ይታያል። እንደ እኛ ዞንና ከተማ ግን እየተካሄደ ያለው ነገር ስራ አጥነትን ከመቀነስ ይልቅ በብዛት እያመረተ የለ የአስተዳዳር ችግሮች እየታዩ ቆይቷል እሄ አካሄድ ነገሮችን ወደ መይፈለጉ አቅጣጫ ይመራል ።
ዘመናዊ አሰራር መተግበርን ጨምሮ አዳዲስ እሳቤዎችን ተጠቅሞ ሰራ ላይ በማዋል ለውጥ ለማምጣት አሁን ያለ የብልጽግና አመራር በትኩረት ከልሰራ አስቸጋሪ ይሆናል ፡፡ መንግስት በየጊዜው ከመናገር በዘለል የሚፈለገውን እና ወቅቱ የሚጠይቀውን ያክል ውጤት አላመጣበትም።

13/05/2021

የስራ አጥ ምሩቃን ድምጽ እንሁን

VOTE Abiy
18/04/2021

VOTE Abiy

11/12/2019

#የሰሞኑ ጉዳይ
(ለእውቀትም ለመተባበርም)

#ትኩረት #ይደረግ።
ከሰሞኑ በከምባታ ጠምባሮ ዞን እየሆነ ስላለው፣ ስለሚታሰበውና ጥንቃቄ ስለሚሹ ጉዳዮች ያጠናቀርናቸውን የሚከተሉትን መረጃዎች እነሆ።

1) #የከምባታ ብሔራዊ ክልል

ይህ ጉዳይ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም። ከምባቶች በተፈጥሮ ከማንም ጋር አብሮ በመኖርና የኢትዮጵያን አንድነት ከማንም በላይ እንደግፋለን፣ ይህ እውነት ነው። አሁን ባለው የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በደቡብ ክልል ለተወሰኑት በራሳቸው እንዲተዳደሩ እየተፈቀደ ሲሆን፣ የከምባታ ጉዳይ ግን ባሉን ደካማ ተመራጮች የተነሳ ተቀባይነቱ እየቀነሰ ነው። ይህም የሆነው ለህዝቡ ጥቅም ሳይሆን ለራሳቸው ሆድና ስልጣን በሚጨነቁ የገዢው ፓርቲ አባላት የተነሳ ነው።

"ከምባታ የራሱ የሆነ ያደገ ከተማ ስለሌለው ራሱን ማስተዳደር አይችልም።" የሚል ማስተባበያ ከሰሞኑ በህዝቡ መሀል ለማሰራጨት እነዚሁ ደካማ ካድሬዎች እየተዘጋጁበት ነው። የከምባታ ከተሞች ያላደጉት በፖለቲከኞች ደካማነት ሆኖ እያለ በዚህ ሰው ሰራሽ ደካማ ሰበብ አሁንም የበይ ተመልካች ሊያስደርጉን ነው። አካባቢው አድጎ ራሱን በማስተዳደር እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ብሄረሰብ እኩል በፖለቲካ ለመሳተፍ ከምባታ ጠምባሮ ህዝብ ምን ይጎድለዋል?

ራስን በማስናቅና ለሚጣልላቸው ፍርፋሪ ተብሎ የህዝቡን ጥቅም የዞኑ ፖለቲከኞች አሳልፈው እየሰጡ ስለሆነ ህዝቡ አንድ ሊላቸው ይገባል። ወላይታና ከፋ በቅርቡ የራሳቸውን ክልል እንደሚመሰርቱ ከሁኔታዎች መረዳት ይቻላል። ከምባታን በነዚህ ሆዳም ካድሬዎች ምክንያት የአንዱ ተለጣፊ በማድረግ አሁንም በየሄደበት እንዲገፋ፣ እንዲንከራተትና የራሱን ሳይሆን ሌሎች ከተሞችን እያሳደገእስከመቼ ይኖራል? አሁን ካልተባበርንና ካልተንቀሳቀስን ግን ይህ ተፈርዶበታል። ይህ እንዲሆን መፍቀድ የለብንም። ፖለቲከኞች የህዝቡ ተወካዮች ከሆኑ ህዝቡ ይህን ሲጠይቅና ለመብቱ ሲከራከር ማሳፈን የለባቸውም።

2) #የሰሞኑ ድለላዎች

ከሰሞኑ ከከምባታ አካባቢ የወቅቱን የፖለቲካ አመራሮች ሴራ ለማጋለጥ ወደ ክልል የተንቀሳቀሱ ሰዎች እንደነበሩ ከክልሉ የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ። እነዚህ ሰዎች ሊደመጡና የአካባቢያቸውን ጉዳይ በተመለከተ በውሳኔዎች ሁሉ ተሳታፊ መሆን ስላለባቸው ክልሉ ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል እንላለን። በአንፃሩ ተከሳሾቹ (ዞኑን የሚያምሱት ፖለቲከኞች)፣ በአንዳንድ ካድሬዎች ሰሞኑን ባፃፉት ፅሁፍ ህዝቡን ለማሳሳት ጥረት ማድረጋቸውን ታዝበናል። "ውሻ በበላበት እንደሚጮህ" የዘራፊዎቹ የዞን ባለስልጣናት ደጋፊዎች ከመንጫጫት አልፈው ከሰሞኑ ህዝቡን ለማሳሳት ጥረት ሲያደርጉ ታይቷል። ሁለት ነገሮችን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።

ምሳሌ 1) "የህንድ ኢንቨስተሮች ወደ ዱራሜ መጡ" የሚል የመሬት ሽያጭ ለማካሄድ የተሰራ ሴራ አንዱ ነው። ሺንሺቾ ለውሃ ቁፋሮ ያሸነፈው የህንድ ኩባንያ የቀን ሰራተኞችን ልብ ቀይሮ ኢንቨስተሮች አስመስሎ ማስወራት አላማው ግልፅ ነው። ይኸውም ከሰሞኑ የተቀጣጠለውን የህዝቡን ግፊት ለማብረድ "ኢንቨስተር አመጣን" ለማለት የተሰራ ቀልድ መሆኑ ነው። ከዚያ በእነርሱ ስም መሬት ወስዶ ለመቸብቸብና ሲባረሩ ለመጦሪያ መሆኑ ነው። ከምባታ ግን ስንቴ ነው የሚሸወደው? ያሳዝናል።

2) #አምባሳደርሺፕ => ይኸ ሀሳብ የዞኑን ትምህርት ለማጠናከር አዲስአበባ በሚገኙ የዞኑ ምሁራን በቀናነት ሲካሄድ እንደነበረ ይታወቃል። የዚህ ፕሮግራም አላማና አደራረግ ከፖለቲካ ነፃ በሆኑ ሰዎች ስለነበረ የሚደገፍ ነው። አሁን ግን "ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል" እንዲሉ፣ ስሙን በመጠቀሚያነት ሽፋን የከምባታን ህዝብ ጥያቄ ለማዳፈን፣ ነገ አርብ የፖለቲካ ስታ ሊሰራበት መታሰቡን ከደረሱን መረጃዎች ተረድተናል። በእርግጥ ከዚህ ፅሁፍ በኋላ ሲነቃባቸው ተደናግጠው የሚያስተካክሉትና የሚያስተባብሉት ነገር ይኖራል። ይኸን እውነት ግን አይክዱም።

#ሲጠቃለል፣
የከምባታ ጠምባሮ ህዝብ ህገመንግስቱ የሚፈቅድለትን ራሱን የማስተዳደር ጥያቄ እስካላቀረበ ወደፊት በሚደረገው አከላለል እንደሚዋጥ ግልፅ ነው። ይህ ሲሆን ደግሞ ቢያንስ በአካባቢው የስራ እድልን ለመፍጠር፣ በራሱ ተመራጮች አካባቢውን ለማስተዳደር፣ በክልል ደረጃ የሚቋቋሙ ፕሮጀክቶች እንዳያገኝና የመሰረተልማት ለማስፋፋትም አይችልም። ይህ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ክልሎችም ሆነ ከሀገር ውጭ ራሱን የቻለ ግንኙነት ኖሮት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሚሆንባቸውን ፕሮጀክቶች ለመዘርጋት አይችልም። ስለዚህ አሁን የተከፈተው በር ሳይዘጋና በደቡብ ክልል የተሰጠው ትኩረት ሳይቀዘቅዝ ሊፈቀድላቸው ካሉ ብሄረሰቦች እኩል ከምባታ ጥያቄውን ማስደመጥ አለበት።

ህዝቡ ይህን ጉዳይ ችላ ቢለው ነገ ውሎ አድሮ ፀፀቱ ምንም ሊለውጥለት እንደማይችል ሊረዳ ይገባል። ጊዜው አሁን ነው። እስካሁን የበይ ተመልካች የተሆነው በታጨቅንበት ቅርጫት ተሰሚነት ስላልነበረን ነው። ይህ እንዲቀጥል መፍቀድ ስህተት ነው። ኢትዮጵያ የሁላችንም ስለሆነች ሁሉም ተጋግዞ የሚያሳድጋት ሀገር ልትሆን ይገባል።

ፍትህ ለከምባታ!

ቸር እንሁን።
መንቾ ከም (ታህሳስ 1/2012 ዓ•ም)

02/12/2019

Bihirawi kililaw mangis

Address

Durame@tati. Yom. Mail
Addis Ababa

Telephone

+14422012371

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kambaati Harde qu'mita posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share