Mereja Daily24

Mereja Daily24 This is official Page of Mereja Daily
Ethiopia's Information & Entertainment
Website.

" የተፈጠረውን የፖለቲካ ልዩነት በማጥበብ የትግራይን ህዝብ ቀጣይ እጣ ፈንታ ማቃናት ይገባል " - ጄነራል ታደሰ ወረደ ➡️ " ጊዜያዊ አስተዳደሩ ነፃነቱን ጠብቆ ስራውን አንዲሰራ የበኩሌን ...
11/04/2025

" የተፈጠረውን የፖለቲካ ልዩነት በማጥበብ የትግራይን ህዝብ ቀጣይ እጣ ፈንታ ማቃናት ይገባል " - ጄነራል ታደሰ ወረደ

➡️ " ጊዜያዊ አስተዳደሩ ነፃነቱን ጠብቆ ስራውን አንዲሰራ የበኩሌን አስተዋፅኦ እወጣለሁ " - ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ፤ " የጊዜያዊ አስተዳደሩ ተቋማዊ ነፃነቱን ጠብቆ ስራውን አንዲሰራ የበኩሌን አስተዋፅኦ እወጣለሁ " አለ።

የአዲሱ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በይፋ ስራቸውን የጀመሩ ሲሆን ከነባሩ ካቢኔና ከደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ጋር ተገናኝተዋል።

ካቤኔያቸው መልሰው እንደሚያደራጁ የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ጎን ለጎን የሦስት ወር እቅድ እንዲዘጋጅ አዘዋል።

የስራቸው ዋና ማጠንጠኛ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ መተግበር መሆኑ ገልጸዋል።

- የህዝብ ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝነት መጠበቅ
- የክልሉ ኢኮኖሚ ማነቃቃት
- የአስተዳደር መዋቅሩን ማስተካከል የትኩረት አቅጣዎች መሆናቸው ተናግረዋል።

የተፈጠረውን የፓለቲካ ልዩነት በማጥበብ የትግራይ ህዝብ ቀጣይ እጣ ፈንታ ማቃናት እንደሚገባ ያሳሰቡት ጄነራል ታደሰ " አሸናፊና ተሸናፊ ከሚል መገፋፋት በመውጣት በአብሮነት በመደጋገፍ በጋራ መስራት አለብን " ብለዋል።

" ህወሓትና ጊዚያዊ አስተዳደር " የሚል ልዩነት የሚያሰፋ አጀንዳ እንዲፈታና እንዲዘጋ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በቅርብ ጊዜ የህዝብ ኮንፈረንስ በማካሄድ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት እንዳቀዱና እቅዳቸው እውን እንዲሆን የሁሉም ፓለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ እንደሚሹ ጠይቀዋል።

በተያያዘ ፕሬዜዳንቱ ትላንት ማምሻውን ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት በፅህፈት ቤቱ ይፋዊ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ለፕሬዜዳንቱ ያላቸው መልካም ምኞት በማስቀደም ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ተልእኮዎቹ ለመፈፀም በሚያደርገው ጥረትና እንቅስቃሴ የህወሓት ድጋፍ አይለየውም ብለዋል።

" የክልሉና የህዝቡ ችግሮች መፍታት የጋራ አጀንዳ ነው " ያሉት ጄነራል ታደሰ የፓርቲው አመራሮች ላደረጉላቸው አቀባበልና ለገለፁላቸው መልካም ምኞች አመስግነዋል።

" የትግራይና ህዝቡን መልካም ገፅታ ለመመለስ በጋራ ከመስራት ውጪ ሌላ አማራጭ የለም " ሲሉም ተናግረዋል።

መረጃው ከክልሉ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት እና ከህወሓት የማህበራዊ የትስስር ገፅ የተወሰደ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

ፎቶ፦ TPLF

አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አ...
11/04/2025

አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ጌታቸው ረዳን የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትራቸው አድርገው ሾመዋል።

ሶፍት የሚያጎርሱ ፓስተሮች‼️በቤተክርስቲያን ዉስጥ ለምዕመናን ላብ የተጠረገበት ሶፍት በሚያበሉ አካላት ላይ እርምጃ ተወስዷል ተባለ‼️የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በ...
02/04/2025

ሶፍት የሚያጎርሱ ፓስተሮች‼️

በቤተክርስቲያን ዉስጥ ለምዕመናን ላብ የተጠረገበት ሶፍት በሚያበሉ አካላት ላይ እርምጃ ተወስዷል ተባለ‼️
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በስሩ አባል ለሆኑ በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ዉጪ የሆኑ አጃሄዶች እና ልምምዶችን በሚመለከት ከድርጊቶቹ እንዲቆጠቡ መክሯል።

ዳጉ ጆርናል ከተመለከተዉ እና የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረት ለካዉንስሉ የላከው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ፤ አባላት በቤተክርስቲያን ዉስጥ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከሆኑ ተግባራት እንዲቆጠቡ የሚያሳስብ ነዉ።

ለአብነትም ዘይት ፣ ዉሃ ፣ ጨርቃጨርቅ የሚሸጡ እንዲሁም ላባቸዉን የጠረጉበትን ሶፍት ለምዕመናን የሚሰጡ መኖራቸዉን አመላክቷል። ካዉንስሉ አባላት ቤተክርስቲያኖች ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠቡ በጥብቅ አስጠንቅቋል መባሉንም ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረት ካዉንስሉ ያወጣዉን መመሪያ እንደምትተገብር አሳዉቃ መሰል ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምዶችን እንደምትጸየፍ ገልጻለች።

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ከነብይ እዩ ጩፋ ጋር ዉጥረት ዉስጥ መግባታቸዉ የሚታወስ ሲሆን ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምዶችን በሚተግብሩ አካላት ላይም እርምጃ እየወሰደ ነዉ።

ነብይ እዩ ጩፋ በጸጥታ አካላት ሀዋሳ ከተማ ላይ እጀባ የተደረገላቸዉ መሆኑ ፤ ካዉንስሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ዉጪ ነዉ ብሎ የነበረ ቢሆንም ነብይ እዩ ጩፋ ግን የካዉንስሉን መግለጫ አጣጥለዉ ነበር። በዚህም የተነሳ በነብዩ የሚመራዉ የክራይስት አርሚ ቸርች በካዉንስሉ እገዳ ተጥሎበታል።
አዩዘሀበሻ

7 አመት ደፈኑ‼️ ሀሳብ ስጡበት ‼️ክቡር ጠ/ር ዐብይ አህመድ መጋቢት 24 ,2010 ከዛሬ 7 አመታት በፊት ነበር ወደ ስልጣን የመጡት። ያለፉት ሰባት አመታት ለናንተ እንዴት ነበር⁉️
02/04/2025

7 አመት ደፈኑ‼️

ሀሳብ ስጡበት ‼️

ክቡር ጠ/ር ዐብይ አህመድ መጋቢት 24 ,2010 ከዛሬ 7 አመታት በፊት ነበር ወደ ስልጣን የመጡት።

ያለፉት ሰባት አመታት ለናንተ እንዴት ነበር⁉️

ኢትዮጵያ 15 ሚሊዮን ዶላር ለሱዳን ሰብዓዊ ድጋፍ ለገሰች‼️ኢትዮጵያ በጦርነት ለምትታመሰው ሱዳን የ15 ሚሊዮን ዶላር (1.8 ቢሊዮን ብር) ለሰብዓዊ ድጋፍ መለገሷን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ...
14/02/2025

ኢትዮጵያ 15 ሚሊዮን ዶላር ለሱዳን ሰብዓዊ ድጋፍ ለገሰች‼️
ኢትዮጵያ በጦርነት ለምትታመሰው ሱዳን የ15 ሚሊዮን ዶላር (1.8 ቢሊዮን ብር) ለሰብዓዊ ድጋፍ መለገሷን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለጎረበት አገር ሱዳን እርዳታ እንምታደርግ ይፋ ተደረገው በሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ላይ የሚመክር የመሪዎች ጉባኤ ላይ ነው፡፡ ጉባኤው በኢትዮጵያ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ በአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄ ይገኛል፡፡

በጉዳባኤው ላይ ተገኝተው ንግግር ያድጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያ ለሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ 15 ሚሊየን ዶላር ለግሳለች ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለሱዳን ህዝብ ሰላምና መረጋጋት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሱዳኑ ጦርነት እጇ አለበት የምትባለው የኢትዮጵያ መንግሥት አጋር የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በበኩሏ 200 ሚሊዮን ዶላር ለግሳለች፡፡ የኢትዮጵያ እና ዱባይ የገሱት ድጋፍ በሱዳን ጦርነት ለተገዱ ሰዎች የሰብዓዊ አቅርቦት የሚውል ነው ተብሏል፡፡

💥 vacation time 🇪🇹 💥💘💘💘
14/02/2025

💥 vacation time 🇪🇹 💥
💘💘💘




  ❤
14/02/2025


በ ምያንማር የወንጀል ካምፖች ተይዘው የነበሩ "138 ኢትዮጵያውያን" ተለቀቁ‼️በምያንማር በሚገኙ የሳይበር ወንጀል ካምፖች በግዳጅ ሠራተኝነት ተይዘው የነበሩ "138 ኢትዮጵያውያን" ተለቀው ...
14/02/2025

በ ምያንማር የወንጀል ካምፖች ተይዘው የነበሩ "138 ኢትዮጵያውያን" ተለቀቁ‼️

በምያንማር በሚገኙ የሳይበር ወንጀል ካምፖች በግዳጅ ሠራተኝነት ተይዘው የነበሩ "138 ኢትዮጵያውያን" ተለቀው በትናንትናው ዕለት ወደ ታይላንድ መግባታቸውን በሀገሪቱ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል። ኢትዮጵያውያኑ ዜግነታቸውን የማጣራት እና ሌሎች ሂደቶችን ካለፉ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል። በደቡብ ምሥራቅ እስያዋ ምያንማር ውስጥ የሚገኙ ቢያንስ 154 ግቢዎች ውስጥ የሚፈጸሙት የማጭበርበር ወንጀሎች በአብዛኛው የሚከናወኑት "የሥራ ዕድል ታገኛላችሁ" በሚል ተታልለው በግዳጅ ለዚህ ድርጊት በተዳረጉ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ነው። ኢትዮጵያውያኑ መደብደብ እና በኤሌክትሪክ ሾክ መደረግን ጨምሮ የተለያዩ የማሰቃየት ቅጣቶች ይፈጸሙባቸዋል ተብሏል።
አሁንም በርካታ ኢትዮጵያዊያን ያልተለቀቁ ሲሆን ባልተለቀቁት ላይ የበቀል እርምጃ እንዳይወሰድ መንግሥቱ ትኩረት ሰጥትቶ እንዲሰራ ተጠይቋል።
70 ኢትዮጵያዊያን በአጥር ዘለው ለማምጣት የሞከሩ ቢሆንም እንደገና ተይዘዋል።
አዩዘሀበሻ

ደቡብ አፍሪካ አሜሪካ ላይ እግድ ለመጣል አቅዳለች‼️ደቡብ አፍሪካ አሜሪካ ማንኛውንም የንግድ ስራ በአገሯ እንዳታደርግ እገዳ ልትጥል እንደምትችል እየዘገበ ይገኛል።ከደቡብ አፍሪካ ወደ አሜሪካ...
14/02/2025

ደቡብ አፍሪካ አሜሪካ ላይ እግድ ለመጣል አቅዳለች‼️
ደቡብ አፍሪካ አሜሪካ ማንኛውንም የንግድ ስራ በአገሯ እንዳታደርግ እገዳ ልትጥል እንደምትችል እየዘገበ ይገኛል።
ከደቡብ አፍሪካ ወደ አሜሪካ የሚላኩ ጥሬ እቃዎች ላይ እገዳ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የሀገሪቱ ማዕድን ሚኒስቴር ተናግረዋል።
ደቡብ አፍሪካ ይህን ለማድረግ እያጤነች ያለችው አሜሪካ ለደቡብ አፍሪካ የምትሰጠውን እርዳታ እንዳቆመች ከወሰነች በኋላ ነው።

የደቡብ አፍሪካ ማዕድን ሚኒስቴር ለትራምፕ አስተዳደር " አሜሪካን ያለ አፍሪካ ጥሬ እቃ የትም መድረስ እንደማትችልና ትራምፕ አፍሪካን ምንም የማታመጠና እንደ ለማኝ አድርጎ የሚቆጥር ከሆነ ከአፍሪካ የሚያገኘውን ውድ ጥሬ እቃዎችንና ማእድን ሌላ ቦታ ሄዶ ይፈልግ" በማለት ገልጿል።
ደቡብ አፍሪካ በአሜሪካ ላይ እግድ ለመጣል ያቀደች የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ሀገር ሳትሆን አትቀርም።
አዩዘሀበሻ

10/02/2025

What alook 👁️👀

  🙏በዱባይ በተደረገው የፖሊስ SWAT ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 101ኛ መውጣቱ ታወቀ‼️ላለፉት ጥቂት ቀናት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ዱባይ ከተማ በተካሄደው እና የ103 ሀገ...
10/02/2025

🙏
በዱባይ በተደረገው የፖሊስ SWAT ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 101ኛ መውጣቱ ታወቀ‼️
ላለፉት ጥቂት ቀናት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ዱባይ ከተማ በተካሄደው እና የ103 ሀገራት የSWAT ፖሊስ ቡድን አባላት በተሳተፉበት ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 101ኛ መውጣቱ ታውቋል።

ይህ Special Weapons And Tactics (የልዩ መሳርያዎች እና ታክቲኮች) የቡድን ውድድር ላይ የቻይና B ቡድን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ፣ የካዛክስታኑ ሱንካር ፖሊስ ሁለተኛ እንዲሁም የቻይና C ቡድን ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል (ሊንክ: https://uaeswatchallenge.com/?page_id=11727)

በ SWAT ውድድሩ ላይ ሲወዳደር የቆየው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ቡድን ከሁለት ቀን በፊት በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ስትራቴጂክ አመራሮች አቀባበል ተደርጎለታል።

በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤ እንደ ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ የፖሊስ ተቋም በተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች SWAT ውድድር ላይ መሳተፉ ለሀገራችን ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ ከማስገኘቱም ባሻገር ዓለም አቀፍ የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነትን ለማዳበር ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የፖሊስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ውድድር ላይ መሳተፍ መቻላችን ልምድና ተሞክሮ እንድናገኝ ያስቻለን ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም እ.ኤ.አ 2026 በሚካሄደው ውድድር ላይ አስፈላጊውን ስልጠና በመውሰድ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትጋት እንሠራለን ሲሉም ገልፀዋል።
#መሰረትሚዲያ

10/02/2025

መቼም በአጥር ሾልካ ገብታ ወይም በፓራሹት ወርዳ አይሆንም፣

ይህ እንደ አንድ ተራ ክስተት ብቻ ሊወሰድ አይገባም፣ አመራሩ ሳያውቅ እንዲህ አይነት ድርጊት በሀላል የሚፈፀም ከሆነ የኤርፖርቱ ግቢ ደህንነት ምን ያህል አስተማማኝ ነው የሚል ጥያቄንም ያጭራል።

Address

Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mereja Daily24 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mereja Daily24:

Share