Yetay Media ይታይ ሚዲያ

Yetay Media ይታይ ሚዲያ ፖለቲካዊ ማሃበራዊ መረጃዎች የሚቀርብበት

22/12/2024

የአሜሪካ የጦር ጄት በስህተት ተመትታ ወደቀች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በልምምድ ላይ የነበረች የአሜሪካ ኤፍ/ኤ-18 ሆርኔት የጦር ጄት በቀይ ባህር አካባቢ በአሜሪካ ጦር ተመትታ መውደቋ ተነገረ፡፡

በጦር ጄቱ ውስጥ የነበሩ ሁለት አብራሪዎች የከፋ ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፋቸው የተነገረ ሲሆን÷ አንደኛው አብራሪ ላይ አነስተኛ ጉዳት መከሰቱ ተነግሯል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ የተነገረ ሲሆን÷ አሜሪካ ክስተቱ የተፈጠረው በልምምድ ላይ በነበሩ ጦሯ መካከል መሆኑን አስታውቃለች፡፡

የአሜሪካ ጦር በቀይ ባህር አካባቢ በየመን መቀመጫውን ያደረገውን የሁቲ አማጺ ቡድን ኢላማ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ክስተቱ አስደንጋጭ ነው ተብሎለታል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ አዘዥ ኤፍ/ኤ-18 ሆርኔት የጦር ጄት መብረር ከጀመር ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መውደቁን አስታውቋል፡፡

ምንም እንኳ አሜሪካ አደጋው የተፈጠረው በልምምድ ላይ ባለ ጦሯ መካከል መሆኑን ብትገልጽም ከሁቲ አማጺ ቡድን የተተኮሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና የጸረ- መርከብ ክሩዝ ሚሳኤልን ለመመከት የተወነጨፈ አንደሆነ ተነግሯል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ አዘዥ ቀደም ሲል በርካታ የሁቲ አማጺ ቡድንን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና የጸረ- መርከብ ክሩዝ ሚሳኤሎችን መትቶ መጣሉን ይፋ ማድረጉን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡

14/12/2024

በአዲስ አበባ ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ 42 ሆቴሎች አገልግሎት እንዲሰጡ ተለዩ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሆቴልና አገልግሎት ሰጪ ዘርፍ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ሊገነባ በሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ታሪኩ ደምሴ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ለጉባኤው የሚመጡ እንግዶች በኢትዮጵያ የሚኖራቸው ቆይታ የተሳካ እንዲሆን በሆቴልና አገልግሎት ሰጪ ዘርፍ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጀምሯል፡፡

ከባለሶስት ኮከብ እስከ አምስት ኮከብ ደረጃ ያላቸው 42 ሆቴሎች አገልግሎት እንዲሰጡ መለየታቸውን ገልጸዋል፡፡

በሆቴሎች ከአቀባበል ጀምሮ ባህላዊ አለባበስና ስርአትን በተከተለ መልኩ እንዲካሄድ፣ አግባብነት የሌለው የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር፣ የክፍሎች ጥራትና ደህንነት ማረጋገጥ፣ የምግብ ጥራትና የመስተንግዶ ሰራተኞች የቋንቋ ብቃትን ጨምሮ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

እንግዶች ሲመጡ በጉባኤው ከመሳተፍ ባለፍ ለቱሪዝሙ ዘርፍ መነቃቃትን የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፤ ከእንግዳ አቀባበል ጀምሮ ደረጃውን የጠበቀና ተወዳዳሪ አገልግሎት በመስጠት የአትዮጵያን ገጽታ ለመገንባታ የዝግጅት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የተለዩት ሆቴሎች በቂ ዝግጅት እንዲያረጉ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጋር የድጋፍና የክትትል ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በማህሌት ብዙነህ

ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ቴሌግራም https://t.me/ethpress
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/...
ድረ ገጽ https://www.press.et

24/01/2024

ዐይን‼️

🇪🇹 መረጃ ከብልፅግና ፓርቲ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘ
የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እያካሄደ ነው

የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሀገራዊ፣ቀጠናዊ እና አለምአቀፋዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደያስቀምጥ ፓርቲው አስታውቋል። ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ አንድምታ ያላቸው ይዘቶች በመርሀግብሩ ላይ በአግባቡ የሚመከርባቸው ሲሆን እንደ ሀገር በብሔራዊነት ትርክት የተጀመረውን ጉዞ ማጠናከር የሚችሉ ግብአቶች እንደሚገኙበት ይጠበቃል ተብሏል።

🇪🇹 መረጃ ከኢፕድ የተገኘ
በመዲናዋ የሚገኙ ከ30 ሺህ በላይ ግንባታዎች ላይ የጥራትና ቁጥጥር ሥራ እየተሠራ ነው

በመዲናዋ በሂደት ላይ የሚገኙ ከ30ሺህ በላይ ግንባታዎች ላይ የጥራት ደረጃና የደህንነት ቁጥጥር እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ። በየመንገዱ የተሰቀሉ ከ45ሺህ በላይ ሕገወጥ ማስታወቂያዎች ተነስተው ወደዲጂታል ሥርዓት እንዲገቡ አቅጣጫ ተቀምጧል።
https://press.et/?p=118874

🇪🇹 መረጃ ከኢፕድ ተገኘ
የባህር በር ስምምነቱ በዓለም መድረክ የመደራደርና የኃይል ሚዛንን የማስጠበቅ አቅምን ያሳድጋል

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችው የባህር በር ስምምነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመደራደርና የኃይል ሚዛንን ለማስጠበቅ አቅም እንደሚያሳድግላት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽንና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ መምህርና ተመራማሪ ደመላሽ መንግስቱ (ዶ/ር) አስታወቁ።https://press.et/?p=118850

🇪🇹 መረጃ ከኢፕድ የተገኘ
ለውጭ ገበያ ከተላኩ የሆርቲካልቸር ምርቶች ከ298 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ለውጭ ገበያ ከተላኩ የሆርቲካልቸር ምርቶች ከ298 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።https://press.et/?p=118852

🇪🇹 መረጃ ከኢፕድ የተገኘ
በመዲናዋ የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ የሚያራዝሙ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል

በመዲናዋ የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ማራዘም የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ። በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ማስፋፋት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን አይናቸው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ቱሪስቶች የመዲናዋን የቱሪዝም መስህቦችና መዳረሻዎች እንዲጎበኙ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል።https://press.et/?p=118870

🇪🇹 መረጃ ከኢፕድ የተገኘ
የግብርና ተኪ ምርቶች ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታ

በግብርና ውስጥ በመሠረተ ልማት፣ በምርምርና በቴክኖሎጂ ኢንቨስት በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የግብርና ምርቶችን ሊተኩ የሚችሉ የሰብል ምርቶችን ማሳደግ እንደሚገባ ይነገራል። በግብርና ተኪ ምርቶች ላይ ትኩረት ማድረግ በምጣኔ ሀብት ዘርፍ ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ እንዳለውም ምሁራን ይናገራሉ።https://press.et/?p=118851

🇪🇹መረጃ ከኢፕድ የተገኘ
የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተመራቂዎችን ከአሰሪዎች ጋር የሚያገናኝ አውደርእይ ተከፈተ

በአዲስ አበባ ካቶሊካዊ ገዳማት ኮንሰርቲም ፕሮጀክት "ክህሎትን እና እድሎችን ማገናኘት " በሚል መሪ ቃል በቴክኒክና ሙያ ትምህርት የሰለጠኑ ወጣቶችን ከአሰሪዎች ጋር የሚያገናኝ አውደርእይ በዛሬው እለት ተከፈተ። አውደርእዩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የቴክኒክና ሙና ትምህርት ስልጠና ተመራቂዎችን ከአሰሪዎች ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ነው።
https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/694746646182127

🇪🇹 መረጃ ከኢፕድ ተገኘ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሪክስ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ዓመታዊ ሽልማትን አሸነፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በህንድ ዴልሂ ከተማ የተካሄደውንና የ2024 የብሪክስ ምክር ቤት ንግድና ኢንዱስትሪ ዓመታዊ እውቅና ሽልማት አሸናፊ ሆኗል፡፡ ሽልማቱ ዘላቂነት ላለው ተቋማዊ ስኬት የሚሰጥ ሲሆን አየር መንገዱም በዚህ ስኬቱ ይህንኑ እውቅና አግኝቷል። የብሪክስ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት በአባል አገራቱ መካከል ንግድ እና ኢንዱስትሪ ትብብር እንዲጎለብት የሚያበረታታ ነው።
https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/694792129510912

🇪🇹 መረጃ ከሚኒስቴሩ የተገኘ
በትግራይ ክልል በሴፍትኔት ፕሮጀክት ለታቀፉ ከተሞች ድገፍ ተደረገ

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረገው የሴፍቲኔት ፕሮጀክት በትግራይ ክልል ለሚገኙ በፕሮጀክቱ ለታቀፉ ከተሞች ድጋፍ አደረገ፡፡በትግራይ ክልል ለሚገኙ በከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ለሚደገፉ አምስት የፕሮጀክት ተግባሪ ከተሞች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ተጓዳኝ መሣሪያዎች እንዲሁም የቢሮ ዕቃዎች ርክክብ ተደርጓል፡፡

🇪🇹 መረጃ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ
ከ 630 ሜትሪክ ቶን በላይ ገቢ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታገደ

በበጀት ዓመቱ መጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከ 630 ሜትሪክ ቶን በላይ ገቢ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ማገዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ5ሺ 713 አስመጪዎችን ጥያቄ በመቀበል ከአንድ ሚሊየን 868 ሺ በላይ ሜትሪክ ቶን የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ የወጣላቸው የገቢ ዕቃዎች ላይ የጥራት ቁጥጥር ሥራ ማከናወኑን አመላክቷል፡፡

🇪🇹 መረጃ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘ
በአዲስ አበባ አንዲት ግለሰብን ገድሎ ራሱን ያጠፋውን ግለሰብ በተመለከተ የተሰራጨው መረጃ የተዛባ ነው

በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ አንዲት ግለሰብን ገድሎ ራሱን ያጠፋውን ግለሰብ በተመለከተ "የሪፐብሊካን ጋርድ አባል ነው “ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተዛባ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ። ጥር 7 ቀን 2016 ዓ/ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው 82 አፓርትመንት አካባቢ አንድ ግለሰብ ወ/ሮ ሃይማኖት ተአረ የተባለች የቤት እመቤትን በመግደል ራሱን ማጥፋቱ ይታወቃል፡፡

ጥር 15 ቀን 2016 ዓ.ም

የቡና ግንድ አድርቅ በሽታ መከላከያ መድኃኒት መገኘቱ ተነገረ........................... አበባ ዩኒቨርሲቲ የቡና ግንድ አድርቅ በሽታን መከላከል የሚያስችል መድኃኒት በምርምር ...
07/12/2023

የቡና ግንድ አድርቅ በሽታ መከላከያ መድኃኒት መገኘቱ ተነገረ...........................
አበባ ዩኒቨርሲቲ የቡና ግንድ አድርቅ በሽታን መከላከል የሚያስችል መድኃኒት በምርምር ማግኘቱን አስታወቀ።

የቡና ግንድ አድርቅ በሽታ መድኃኒት የሌለው ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ የቡና ምርታማነት ላይ ጉዳት እያደረሰ የሚገኝ ነው፡፡

ወደ ኢትዮጵያ የገባው ከመካከለኛው አፍሪካ አገራት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ በስፋት የሚከሰት፤ በፈንገስ አማካኝነት የሚተላለፍ በሽታ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እንዳሉት፤ ቡና ለምስራቅ አፍሪካ አገራት ካለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንጻር ምርታማነትን ለማሳደግ የተለያዩ የምርምር ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ በቡና ምርታማነት ላይ ጉዳት እያደረሱ ከሚገኙት በሽታዎች መካከል የቡና ግንድ አድርቅ በሽታን ለመከላከል የተሰራው የምርምር ሥራ ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ዶክተር ተስፋዬ አለሙ ባለፉት 18 ዓመታት ባካሄዱት ምርምር የቡና ግንድ አድርቅ በሽታን መከላከል የሚያስችል ''ትራያስፐር ባዮፈንጊሳይድ'' የሚል ስያሜ የተሰጠው ሥነ-ህይወታዊ መድኃኒት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡

መድኃኒቱ 70 በመቶ በፈንገስ የሚተላለፍ የቡና ግንድ አድርቅ በሽታን መከላከል የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

እንደዚሁም በቡና ግንድ አድርቅ የሚደርስን የምርት ጉዳት ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚያስቀር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በምርምር የተገኘው መድኃኒትም በምስራቅ አፍሪካ በስፋት ጉዳት እያደረሰ ያለው የቡና አድርቅ በሽታን ለመከላከል ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

መድኃኒቱን ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በኬንያና በዩጋንዳ ተደራሽ ለማድረግ ከአጋር አካላት ጋር እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

1 ኪሎ ግራም የቡና ግንድ አድርቅ መከላከያ መድኃኒት ''ትራያስፐር ባዮፈንጊሳይድ'' ለ2 ሺህ የቡና እግር የሚያገለግል ሲሆን፤ በውህድ መልክ አፈር ውስጥ በማድረግ ወይም በቅርንጫፍ ላይ በመርጨት መጠቀም የሚቻል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

መድኃኒቱ በአካባቢ ላይም ሆነ በቡና ጥራት ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ የማይፈጥር መሆኑን በተለያዩ አገራት ተመራማሪዎች ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
ምንጭ ኢትዮ ራዲዮ

 #18ኛው ብሄር ብሄርሰቦች ቀንየብሄር ብሄርሰቦች መቻቻል ፣ አንድነት እና እኩልነት ድምር ዉጤት ኢትዮጵያን ከፍ ያደርጋታል ::
30/11/2023

#18ኛው ብሄር ብሄርሰቦች ቀን
የብሄር ብሄርሰቦች መቻቻል ፣ አንድነት እና እኩልነት ድምር ዉጤት ኢትዮጵያን ከፍ ያደርጋታል ::

22/11/2023

የእሥራኤልና ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነት

በአሜሪካ፣ በአውሮጳ ኅብረት፣ በጀርመን እና በሌሎች «አሸባሪ ድርጅት» በሚል የተሰየመው ሐማስ እና እስራኤል ለአራት ቀናት የሚቆይ የተኩስ ፋታ ስምምነት ዛሬ ማድረጋቸው ተገልጿል ። የተኩስ ፋታው ማድረግ ታጋቾችን ማስለቀቅ ፡ መድሃኒት ወደጋዛ እንዲገባ ማድረግ ከዛሬ ይጀምራል ተብሏል ።

21/11/2023
 #ሼኔ v  ብልጽግና በመንግስት እና በሸኔ መካከል በሁለተኛ ዙር ሲኪያሄድ የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት መጠናቀቁን የመንግሥት ኮምኒኬሽን አገልገሎት ገልጿል::
21/11/2023

#ሼኔ v ብልጽግና

በመንግስት እና በሸኔ መካከል በሁለተኛ ዙር ሲኪያሄድ የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት መጠናቀቁን የመንግሥት ኮምኒኬሽን አገልገሎት ገልጿል::

ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ ተቋሙን በሀላፊነት እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በፓስፖርት አሰጣጥ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋ...
17/11/2023

ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ ተቋሙን በሀላፊነት እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በፓስፖርት አሰጣጥ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ሀላፊው በዚህ ጊዜ እንዳሉት በኢትዮጵያ የፓስፖርት ፈላጊዎች ቁጥር 300 ሺህ እንደነበር ገልጸው 110 ሺህ ዜጎች ፓስፖርት አግኝተዋል ብለዋል።

አሁን ላይ ፓስፖርት እንዲያገኙ ለኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ያመለከቱት ዜጎች ቁጥር 190 ሺህ እንደሆኑም ተገልጿል።

ተቋሙ ባለፉት ሶስት ወራት በሰራቸው ስራዎች ከ531 ሺህ በላይ ፓስፖርት ታትሞ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል ያሉት ሀላፊዋ 43 ሺህ 366 ለሚሆኑ በአዲስ አበባ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ፓስፖርት ተሰጥቷልም ብለዋል።

እንዲሁም 15 ሺህ 793 ለሆኑ ዜጎች ደግሞ ለአስቸኳይ ፓስፖርት ፈላጊዎች ሲሰጥ 8 ሺህ 500 ለሚሆኑ በክልሎች ለሚኖሩ ዜጎችም ፓስፖርት እንደተሰጡ ተገልጿል።

ይሁንና ፓስፖርት እንዲሰጣቸው ካመለከቱ ሰዎች ውስጥ 15 ሺህ 924 ሰዎች ፓስፖርታቸውን መጥተው እንዲወስዱ የጽሁፍ መልዕክት ቢላክላቸውም አልወሰዱም ተብሏል።

ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አክለውም ከፓስፖርት አሰጣጥ ጋር በተያያዝ የስነ ምግባር ጥሰት ፈጽመዋል የተባሉ 38 የተቋሙ ሰራተኞችም በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጋቸውንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የመዳረሻ ቪዛን ወይም ቪዛ ኦን አራይቫል አገልግሎትን ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ጀምሮም በመስጠት ላይ መሆኗን ወይዘሮ ሰላማዊት በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል።

"የመዳረሻ ቪዛ ከ120 ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ጎብኚዎች በመስጠት ላይ እንገኛለን" ሲሉ የተናገሩት ሀላፊው በአገልግሎቱ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ቀስ በቀስ እየፈተን እንሄዳለንም ብለዋል።

creadit alain

ነገረ አህያሰሞኑ የአህያ ስጋ በየሉካንዳቤቱ ተቀላቅሎ እየተሸጠ እንደሆነ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ከሞሉት ወሬዎች ዋነኛው ሆኖ እያነጋገረ ነው። በተለይም በአዲስ አበባና በአንዳድ የክልል ...
17/11/2023

ነገረ አህያ
ሰሞኑ የአህያ ስጋ በየሉካንዳቤቱ ተቀላቅሎ እየተሸጠ እንደሆነ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ከሞሉት ወሬዎች ዋነኛው ሆኖ እያነጋገረ ነው። በተለይም በአዲስ አበባና በአንዳድ የክልል ከተሞች ከከብት ሥጋ ጋር ተቀላቅሎ እየተሸጠ እንደሚገኝ እየተነገረ ነው። የአህያ ሥጋ ከሃይማኖትና ባሕል አንጻር ጽዩፍ በሆነበት ሁኔታ እንዲህ አይነት ተግባር መፈጸም የሚያስኮንን ነው በማለት መንግስት አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ አጥፊዎችን ለሕግ እንዲያቀርብ ብዙዎች እየወተወቱ ነው።

09/11/2023

ኢስራኤል የፓላስታይንን (የጋዛን) የጦር ሃይል መቆጣጠሯን ገለፀች::

09/11/2023

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛውን የቦይንግ የጭነት አውሮፕላን አስገባ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛውን የቦይንግ (Boeing 777-200LR) የጭነት አውሮፕላን ማስገባቱን አስታወቀ።

አውሮፕላኑ ዘመናዊ ባለሁለት ሞተር መሆኑንና ከመቶ ቶን በላይ ጭነት የመሸከም አቅም እንዳለው ተጠቅሷል።

እስከ አሁን ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች የምዝገባ ኮድ በA የሚጀምር የነበረ ሲሆን የዚህ አዲስ አውሮፕላን ምዝገባ ኮድ ግን በB በመጀመር ET-BAA የሚል ስያሜን በመያዝ አዲስ የአውሮፕላን ምዝገባ ምእራፍ መክፈቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ያመላክታል።

የዋጋ ግሽፈቱ እዲባባስ እዲህ አይነቱ ወጀል ከፍተኛ ሚና ስላለው መፍትሄ ያሻዋልሀሰተኛ ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች ተያዙ***********ሀሰተኛ የውጪ ሀገራትና የኢትዮጵያን...
09/11/2023

የዋጋ ግሽፈቱ እዲባባስ እዲህ አይነቱ ወጀል ከፍተኛ ሚና ስላለው መፍትሄ ያሻዋል

ሀሰተኛ ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች ተያዙ
***********

ሀሰተኛ የውጪ ሀገራትና የኢትዮጵያን ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሀሰተኛ ገንዘብ በማዘጋጀት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የተያዙት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ቦሌ አዲስ ትምህርት ቤት አካባቢ ነው።

የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው ሦስት ግለሰቦች ሙሉ ግቢ የመኖሪያ ቤት በመከራየት ሀሰተኛ ብር እና የውጭ ሀገር ገንዘቦችን በማተም እንደሚያሰራጩ እና የከበሩ ማዕድናትን በህገ-ወጥ መንገድ እንደሚያዘዋውሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ባሰባሰበው ማስረጃ አረጋገጧል ፡፡

ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በተደረገ ብርበራ ተጠርጣሪዎቹ ሀሰተኛ ገንዘቦችን ለማዘጋጀት የሚገለገሉባቸውን መሳሪያዎች ፣ ልዩ ልዩ ኬሚካሎችን ፣ በሀሰተኛ መንገድ የታተሙ ገንዘቦች ፣ በገንዘብ ልክ ተቆራርጠው የተዘጋጁ ወረቀቶችን እንዲሁም የዘንዶ ቆዳዎችን በኤግዚቢትነት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሀሰተኛ ገንዘብ ከማዘጋጀት በተጨማሪ የፀና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖራቸው እየኖሩ ያሉና በህገ-ወጥ መንገድ የከበሩ ማእድናትን እንደሚዘዋውሩ በምርመራ ማረጋገጡ ተጠቅሷል፡፡

ፖሊስ የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ መመስረቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ በተለያዩ ክ/ከተሞች ውስጥ በተመሳሳይ መንገድ ሀሰተኛ ገንዘቦችን ሲያትሙ የተገኙ ግለሰቦች እንደተያዙ ፖሊስ አስታውሶ መሰል የወንጀል ድርጊቶች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ በመሆኑ ወንጀሉን በመከላከል እና ህገ-ወጦችን ተጠያቂ የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

28/10/2023

በእስራኤል ድንበር የምትገኘው የግብጿ ከተማ በሚሳይል ተመታች

እየተካሄደ ባለው የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት ምክንያት የተተኮሰው ሚሳይል ከጋዛ ሰርጥ 220 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የግብጿን የመዝናኛ ከተማ መምታቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

ሚሳይሉ በታባ የጤና ማዕከል ላይ ማረፉን እና ስድስት ሰዎችን ማቁሰሉን ዘገባው ጠቅሷል።

ታባ ግብጽን ከቀይ ባህሯ የእስራኤል ወደብ ኢላት የምታገናኝ ቦታ ነች።

የእስራኤል ጦር ከድንበር ውጭ ስለተፈጠረው የጸጥታ ችግር መረጃ እንዳለው ገልጿል።

ሀማስ በበኩሉ ባለፈው ሮብዕ እለት እንደገለጸው የእስራኤሏን ኢላት ኢላማ አድርጎ እንደነበር የገለጸ ቢሆንም የእስራኤል ጦር ከኢላት ወጣ ቦታ ማረፉን አስታውቋል።

የእስራኤል-ሀማስ ግጭት ከተቀሰቀሰበት ባለፈው ጥቅምት ወዲህ ይህ የመጀመሪያው የረጅም ርቀት የፍልስጤም ጥቃት ነው ተብሏል።
https://am.al-ain.com/article/missile-struck-egypt-red-sea-town

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yetay Media ይታይ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yetay Media ይታይ ሚዲያ:

Share