ፈጣን መረጃ : Fast Mereja

  • Home
  • ፈጣን መረጃ : Fast Mereja

ፈጣን መረጃ : Fast Mereja Ethiopian daily hot news alert.

26/10/2024

እስራኤል በኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች

እስራኤል ከእኩለ ለሊት ጀምሮ በኢራን ወታደራዊ ተቋማት ላይ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።

ኢራንም በበኩሏ ንጋት ላይ እንዳስታወቀችው በዋና ከተማዋ ቴህራን፣ ኹዜስታን እና ኢላም በተባሉ ግዛቶቿ ውስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ሰፈሮች የእስራኤል ጥቃት እንደተፈጸመባቸው አስታውቃለች።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል ጥቃቱን የፈጸመው ኢራን እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ አጋሮቿ የሆኑ ታጣቂ ቡድኖች ለፈጸሙት “ለወራት የዘለቀ ጥቃት" ምላሽ መሆኑን አስታውቋል።

የእስራሌል መከላከያ ኃይል ጥቃቱን የፈጸመው “በተመረጡ ወታደራዊ ዒላማዎች” ላይ መሆኑን አስታውቆ፣ ኢራን ካለፈው ዓመት መስከረም 23/2016 ዓ.ም. ጀምሮ “ያለማቋረጥ እስራኤል ላይ ጥቃት ስትፈጽም ቆይታለች” ሲል ወንጅሏታል።

ከመከላከያ ኃይሉ መግለጫ ቀደም ብሎ የኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን በዋና ከተማዋ ቴህራን እና አካባቢው በርካታ ፍንዳታዎች መድረሳቸውን አስታውቆ ነበር።

የእስራኤል የቅርብ አጋር የሆነችው አሜሪካ በበኩሏ ጥቃቱን “ራስን የመከላከል ተግባር” መሆኑን ገልጻለች ሲል ቢቢሲ ነው ያስነበበው

06/10/2024

መሬት መንቀጥቀጥ ይሆን እንዴ?

ፌደራል ፖሊስ የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል ባላቸው 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን ተገለጸ።ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የ...
25/08/2024

ፌደራል ፖሊስ የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል ባላቸው 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን ተገለጸ።

ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ተጠርጣሪዎቹ ተብለው ከተቀመጡት መካከል
👉 ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣
👉አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣
👉ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣
👉ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣
👉ይዲድያ ነጻነት አበበ እና
👉 እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው ተብሏል።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ ናቸው በሚል በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።

በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸው ንብረት የሆነውን አየር መንገድ ማንቋሸሻቸው አሳዛኝ ተግባር ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መግለጹ ተመላክቷል።

በመሆኑም እነዚህ በቁጥጥር ስር የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎችን ቢሮው በተላለፉት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አሰራር ጥሰት ብሎም በሽብር ወንጀሎች የምርመራ መዝገብ ነገ ነሀሴ 20 ቀን 2016 ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው ለማወቅ ተችሏል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።

የአዲስ አበባ ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት “በከተማዋ መግቢያ” ቦታዎች ሊከናውን ነው   | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛውን ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እንደ ኮዬ አደባባይ፣ ጎሮ ...
21/08/2024

የአዲስ አበባ ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት “በከተማዋ መግቢያ” ቦታዎች ሊከናውን ነው

| የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛውን ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እንደ ኮዬ አደባባይ፣ ጎሮ እና ሰሚት ባሉ “የከተማዋ መግቢያ” እና “ማስፋፊያ ላይ በሚገኙ” አካባቢዎች ሊያከናውን ነው።

43 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ፤ ከሸገር ከተማ የኮሪደር ልማት ጋር “በማስተሳሰር” እንደሚከናወን ታቅዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የኮሪደር ልማት” ሲል የጠራውን ዋና ዋና መንገዶችን የማስዋብ፣ የእግረኛ መንገድን የማስፋት፣ መዝናኛ ቦታዎችን የመገንባት እንዲሁም የመንገድ ዳር መብራት እና ቴሌኮሚዩኒኬሽን መስመሮችን በዘመናዊ መንገድ የመዘርጋት ሥራ የጀመረው በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ ነበር።

የከተማዋን ታዋቂ እና ነባር አከባቢዎችን የሸፈነው የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት፤ አምስት መስመሮችን የያዘ ነው። በመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ፒያሳ፣ አራት ኪሎ፣ ቦሌ፣ መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ሲኤምሲ ይገኙበታል።

የኮሪደር ልማቱ ሲከናወን ተለይም በፒያሳ አካባቢው ጥንታዊ ኪነ ሕንጻዎችን ጨምሮ በርካታ ቤቶች የፈረሱ ሲሆን፣ በዚሁ ግንባታ ምክንያት 11 ሺህ ገደማ ነዋሪዎች ከአካባቢው መነሳታቸውን ከንቲባዋ አስታውቀው ነበር።

የከተማ አስተዳደሩ፤ በድምሩ 48 ኪሎ ሜትር ለሚሸፍነው ለመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት፤ 33 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉንም መግለጻቸውም ይታወሳል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግምማ እየተደረገበት የተካሄደው ይህ የኮሪደር ልማት፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማዋ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መስመሮችን ተከፋፍለው ሥራውን መርተውታል።

ከኮሪደር ልማቱ መስመሮች ውስጥ ቀድሞ የተመረቀረው በከንቲባዋ ክትትል ስር የነበረው ከአራት ኪሎ ፒያሳ የሚደርሰው መንድ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ሰኞ የተመረቀውን ከመገናኛ ሲኤምሲ የተዘረጋውን ልማት ጨምሮ ሌሎቹ መስመሮች በተለያዩ ጊዜያት ክፍት ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ በመጀመሪያው ምዕራፍ የገነባቸውን እነዚህን “መሃል ከተማ” ውስጥ የሚገኙ መስመሮች፤ “የከተማዋ መግቢያ ተብለው የተለዩ ቦታዎች እና በማስፋፊያ ከሚገኙ አካባቢዎች ጋር ለማስተሳሰር” ማቀዱን ቢቢሲ ከከተማ አስተዳደሩ ጥናት ተመልክቷል።

በምዕራፍ ሁለት የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ላይ የተደረገው ይህ ጥናት በከተማዋ የፕላን እና ልማት ቢሮ የተዘጋጀ ነው። በአጠቃላይ 43 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚኖረው የምዕራፍ ሁለት የኮሪደር ልማት፤ ቦሌ፣ ለሚ ኩራ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞችን እንደሚያካትት የጥናት ሰነዱ ያሳያል።

ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ በአምስት መስመሮች ላይ የሚከናወን ነው። ከእነዚህ መስመሮች ውስጥ ከፍተኛ ዝርመት ያለው “ከአንበሳ ጋራዥ - መብራት ኃይል - ጎሮ - ኮዬ አደባባይ” የሚደርሰው መንገድ ነው። ይህ መስመር 14.8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው።

“ከቦሌ ካርጎ - ቡልቡላ - ኮዬ አደባባይ” የሚደርሰው ሁለተኛው ረጅም መስመር ደግሞ 12.8 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ውስጥ የተካተተው ሌላኛው መስመር “ከቦሌ ድልድይ” ተነስቶ “በቦሌ ሆምስ - በአየር መንገድ ቪአይፒ መግቢያ” አድርጎ መዳረሻው “ጎሮ” አካባቢ ነው።

“ከጎሮ አደባባይ” የሚነሳው አራተኛው መስመር አምስት ኪሎ ሜትር ርዝመት እንደሚኖረው በጥናት ሰነዱ ላይ ሰፍሯል። ይህ መስመር “ከጎሮ አደባባይ - በሰባ ሁለት አካባቢ - ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ አካባቢ - ፍየል ቤት - ሲ ኤም ሲ አደባባይ” አካባቢዎችን ይሸፍናል።

“ከፍየል ቤት - ፊጋ - ሰሃሊተ ምህረት አደባባይ - ጃክሮስ” የሚደርሰው አምስተኛው መስመር ደግሞ 5.9 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው።

በከተማዋ የአስተዳደር ወሰን ማብቂያ አካባቢ የሚገኙ አካባቢዎችን ያካተተው ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ፤ “በትግበራ ላይ ከሚገኙ የሸገር [ከተማ] ልማት ኮሪደሮች ጋር በማስተሳሰር የሚከናወን” እንደሆነ የጥናት ሰነዱ ያመለክታል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ አምስት ከተሞችን በአንድ የከተማ አስተዳደር ስር በማድረግ ባለፈው ዓመት የተመሠረተው የሸገር ከተማ፤ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ “ዘጠኝ የልማት ኮሪደሮችን” በመለየት ወደ ሥራ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቆ ነበር።

የአዲስ አበባ ከተማ ፕላን እና ልማት ቢሮ ያዘጋጀው የጥናት ሰነድ፤ ከኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ጋር በሚዋሰኑ አካባቢዎች የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ከአጎራባቹ ከተማ ጋር “ወጥ የሆነ ዲዛይን ተዘጋጅቶላቸው በጋራ የሚለሙበትን ማዕቀፍ መፍጠር” እንደሚያስፈልግ አስፍሯል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ውስጥ የተካተቱ አካባቢዎች ላይ የሚከናወነው የኮሪደር ልማት እንደ መጀመሪያው ምዕራፍ ሁሉ የእግረኛ መንገድን የማስፋት ውጥን ያለው ነው። በዋና መንገድ (አስፓልት) ጠርዝ የሚገኙ አካባቢዎች የአስር ሜትር ስፋት እንዲኖራቸው እንደታሰበ በጥናቱ ላይ ሰፍሯል።

አምስት ሜትሩ የሚውለው ለእግረኛ መንገድ ሲሆን፤ የሳይክል መስመር ደግሞ ሦስት ሜትር ስፋት ይኖረዋል። በአስፓልቱ በኩል የሚኖረው ቀሪው ሁለት ሜትር የአረንጓዴ ልማት ቦታ እንደሚኖረው ጥናቱ ያስረዳunication

የምስሉ መግለጫ,ቦሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ግንባታ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ሰኞ ዕለት መጎብኘታቸውን የክፍለ ከተማው ኮሚዩኒኬሽን ዘግቦ ነበር

በአምስቱ መስመሮች የሚገነባው የኮሪደር ልማት በሌሎች አካባቢዎች እንደተሠራው ሁሉ፤ የታክሲ ማቆሚያ ቦታዎችን፣ የሕዝብ መፀዳጃ፣ የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሁም በከተማ፣ ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ደረጃ የሚገነቡ ፓርኮችን እንደሚያካትት ጥናቱ ገልጿል።

የመኖሪያ ቤቶች ግንባታም የዕቅዱ አካል እንደሆነ የሚያመለክተው ጥናቱ፤ “ከቦሌ ሆምስ - አንበሳ ጋራዥ -አይሲቲ ፓርክ” ባለው አካባቢ ውስጥ “የማስፈሪያ ቦታ” (relocation site) ይኖራል። በዚህ ስፍራ ላይ “ቅይጥ የመኖሪያ ቤቶች” (mixed residence) ይገነባሉ ተብሏል።

በኮሪደር ልማቱ ምክንያት “ሙሉ በሙሉ የሚነሱ” ቦታዎች ጉዳይ በሰነዱ ላይ “ውሳኔ” እንዲሰጥባቸው ከተዘረዘሩ ነጥቦች መካከል ነው። ነባር ግንባታዎች “በልማቱ ውስጥ የሚካተቱበት መንገድ” መፈጠር እንዳለበት የሚያስገነዝበው ሰነዱ፤ ኮሪደር ልማቱ በሚከናወንባቸው መስመሮች ላይ ለሚገኙ ሕንጻዎች ሁለት አማራጮችን አካትቷል።

“ከሁለት ወለል በላይ” ላላቸው ሕንጻዎቸ የተቀመጠው አማራጭ “ታዛ (Arcade) እንዲያካትቱ ማድረግ” የሚል ነው። ይህ ዓይነቱ አማራጭ በመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ላይ በሚገኙ ሕንጻዎች ላይ የተተገበረ ሲሆን፣ ሕንጻዎች የምድር ወለላቸውን የፊት ለፊት ገጽታ በማፍረስ ለእግረኛ ክፍት አድርገዋል።

ከሁለት ወለል በታች ላሉ ግንባታዎች የተቀመጠው አማራጭ “በጥናቱ መሠረት ወደ ልማት ውስጥ ማስገባት” የሚል ነው። በምዕራፍ ሁለት በተካተቱ ቦታዎች ለሚገኙ “ይዞታዎችን የመለየት፣ የመተንተን፣ ግምት እና የምትክ አገልግሎቶችን የመለየት ሥራ” እየተከናወነ መሆኑን ጥናቱ ይጠቅሳል።

በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ውስጥ ከተካተቱት መስመሮች ውስጥ በቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኙት ሦስት ግንባታዎች “በቅርቡ” እንደተጀመሩ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ለቢቢሲ አረጋግጧል።

በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ የሚገኙት መስመሮች ላይ ደግሞ ሥራውን ለማስጀመር “ከሕብረተሰቡ ጋር ውይይት እየተደረገ” መሆኑን የክፍለ ከተማው የኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

BBC

ህወሓት ምርጫ አካሂዷልዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ሆነው በድጋሚ ተመረጡ። -አቶ አማኑኤል አሰፋ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የፓርቲው ...
19/08/2024

ህወሓት ምርጫ አካሂዷል

ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ሆነው በድጋሚ ተመረጡ።

-አቶ አማኑኤል አሰፋ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

ህወሓት ሁለቱን የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ምርጫ ያደረገው ላለፉት ስድስት ቀናት በመቐለ ከተማ ሲያደርገው የነበረውን አወዛጋቢ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ሲያጠናቅቅ ነው። በዛሬው የጉባኤ ውሎ፤ ዘጠኝ አባላት ያሉበት የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫም ተከናውኗል።

ፓርቲው ከስድስት ዓመት በፊት ባከናወነው ጉባኤ ከመረጣቸው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ውስጥ በአሁኑ ምርጫ የተካተቱት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚያብሔር እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ብቻ ናቸው። ከጠቅላላ ጉባኤው ራሳቸውን ያገለሉት አቶ ጌታቸው ረዳ እና አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ 6 የፖሊት ቢሮ አባላት በአዲስ ተመራጮች ተተክተዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

  በህፃን ሄቨን ላይ በተፈፀመው ወንጀል በተሰጠው ውሳኔ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር  እንደሚሰራ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ!!በህፃን ሄቨን ላይ በተፈፀመው ዘግናኝ የሆ...
17/08/2024

በህፃን ሄቨን ላይ በተፈፀመው ወንጀል በተሰጠው ውሳኔ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰራ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ!!

በህፃን ሄቨን ላይ በተፈፀመው ዘግናኝ የሆነ ኢ ሰብአዊ ወንጀል የተሰጠው ዉሳኔ አስመልክቶ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚኬድበት አግባብ ባለመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰራ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የህፃናትን መብት በማስጠበቅ ረገድ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ተግባራትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በህፃናት መብት ጥበቃ ላይ በተለየ መልኩ የፖሊሲ አቅጣጫዎች እንዲቀመጡና የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የሚፈፀሙ ጥቃቶች የሚመዘገቡበትና ተገቢ የሆነ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት እንዲያገኙ የህፃናት የመረጃ አያያዝ ሰርዓት እንዲዘረጋ እና የቅንጅት ስራዎች እንዲጠናከሩ እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለችውን ህፃን ሄቨን በተመለከተም በደረሰው ዘግናኝ የሆነ ኢ-ሰብአዊ ወንጀል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰማውን ሀዘን ገልፆ ይህንን አይነት የህፃናት ጥቃት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በፅኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡

በተፈፀመው ወንጀል ዙሪያም የተሰጠውን ዉሳኔ አስመልክቶ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚኬድበት አግባብ ባለመሆኑ ከፍትህ አካላት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ እና እንደሚከታተል አረጋግጧል፡፡

"የእኔ ስልጣን መልቀቅ አይታሰብም!"  ዶ/ር አሸብር “ እንደ ኃይሌ ገ/ስላሴ ሰልፍ ሳይ አሮጥም “ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ  የ ኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የፓሪስ ቆይታውን አስመልክቶ እየ...
16/08/2024

"የእኔ ስልጣን መልቀቅ አይታሰብም!" ዶ/ር አሸብር

“ እንደ ኃይሌ ገ/ስላሴ ሰልፍ ሳይ አሮጥም “ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ

የ ኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የፓሪስ ቆይታውን አስመልክቶ እየተሰጠ የሚገኘው መግለጫ ቀጥሏል።

ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ምን አሉ ?

“ ከሀላፊነት በመውረድ እና በመውጣት የሚመጣ ለውጥ የለም እግር ኳሱን ምሩ ብዬ ጥዬ ወጥቼ የመጣ ለውጥ የለም።

- ጉዳፍ ፀጋይን ለማግባባት ሞክረን ነበር ፣ ነገር ግን አቋሟ ጥሩ ስለነበር በሶስቱም ርቀቶች እወዳደራለሁ ስላለች ትተናታል።"

- እኔ ከሀላፊነት ብለቅ እንኳ ኃይሌ ገብረ ስላሴ የሚገባበት መንገድ የለም።

- ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠብቅሀል ተብዬ ነበር ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው ፣ እንደ ኃይሌ ሰልፍ ሳይ አሮጥም።

- የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከማንም በላይ ጉልበት አለው ፣ ጉባኤው ጠንካራ ነው።

- ህግ ላይ አጥብቀን ስለምንሰራ ብዙ ጊዜ አልሸነፍም “ ብለዋል።

በተጨማሪም “ በህዝቡ ከሀላፊነት እንዲለቁ እየተጠየቁ ነው ፣ በባንዲራው ስም ይልቀቁ ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር አሸብር “ ከሀላፊነት አለቅም “ ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

" ይህ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም " - አቶ ጌታቸው ረዳየህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥተዋል።ጉባኤ...
13/08/2024

" ይህ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥተዋል።

ጉባኤው " በችኮላና የጋራ መግባባት ሳይደረስበት ፤ በማደናገርና በአቋም አልባነት አሰባስበናቸዋል በሚሉት ኔትወርክ ' ይቃወሙናል ' የሚሉዋቸው የተወሰኑ አመራሮች ለማስወገድ በማለም የሚካሄድ ጉባኤ ነው " ብለውታል።

" ይህ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም " ሲሉ ገልጸዋል።

ምክትል ሊቀመንበሩ ፤ " የተሻሻለው የፓለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ ህወሓት እንደ አዲስ እንደሚዘገብ የሚያደርግ ፣ ወርቃዊው የትግራይ ህዝብ ትግል የሚያጎድፍ በቀጣይ ቅርቃር ውስጥ የሚከት መሆኑን በመገንዘብ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ በማእከላዊ ኮሚቴ አባላት መግባባት ተደርሶ ነበር " ብለዋል።

" ይሁን እንጂ የተደረሰው መግባባትና መተማመን ወደ ጎን በመተው ' ከፌደራል መንግስት ተማምነናል ' በሚል ማደናገሪያ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመነጋገር ከማእከላዊ ኮሚቴ እና ካድሬ በመደበቅ የተሄዴበት ሂደት ወዳልተፈለገ ወጥመድ እንድንገባ ተደርገናል " ብለዋል።

" በዚህ ምክንያት የሚፈጠር ማንኛውም ጥፋት ተጠያቂው ለጠባብ ቡድናዊ ፍላጎቱ ብቻ የሚንቀሳቀሰው ቡድን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው " የህዝቡ ሰላም እንዳይደፈርስና እንዳይረበሽ ከህዝባችንና ከመላ አባላችን በመሆን እንታገላለን " ብለዋል።

" ሁሉም የትግራይ አቅሞች በማቀናጀት በተደራጀ ትግል ከፍተኛ ፓለቲካዊ ድርድር በማካሄድ የህወሓት ህጋዊነት በመመለስ ካጠላብን ዙርያ መለስ ፈተና በመውጣት የትግራይ የተሟላ ደህንነትና እድገት እንደሚረጋገጥ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ " ብለዋል።

  : ህወሓት የጉባኤ መክፈቻ እያደረገ ይገኛል።ድርጅቱ " 14ኛው ጉባኤ መክፈቻ እየተካሄደ ነው " ብሏል።በሊቀመንበሩ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ቡድን ነው ጉባኤውን በመቐለ ...
13/08/2024

: ህወሓት የጉባኤ መክፈቻ እያደረገ ይገኛል።

ድርጅቱ " 14ኛው ጉባኤ መክፈቻ እየተካሄደ ነው " ብሏል።

በሊቀመንበሩ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ቡድን ነው ጉባኤውን በመቐለ በሰማእታት የሓወልቲ አዳራሽ " ጉባኤ ድሕነት ! / የመዳን ጉባኤ ! " በሚል መሪ ቃል የጀመረው።

እንደወጣው መርሀ ግብር ጉባኤው ከነሀሴ 7 - 12/2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ነው የተነገረው።

የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞና በሌሎችም ምክንያቶች አይሳተፉም።

የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና ነፍገዋል።

በተለይ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉና ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ በሚደረግ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና የማይሰጥ መሆኑን ለህወሓት በጻፈው ደብዳቤ ቀድሞ አሳውቋል።

  ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ፤ " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ " ሲል ውድቅ አድርጎታል።ህወሓት ባወጣው መግለጫ ፥ " የስራ ኃላፊዎቼ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግ...
11/08/2024



ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ፤ " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ " ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ህወሓት ባወጣው መግለጫ ፥ " የስራ ኃላፊዎቼ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማካሄድ ሕጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል።

" በአፍሪካ ህብረት ፓናል ውይይትም ይህ ጉዳይ ተነስቶ ህጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት ስምምነት ተደርሶበታል " ሲል ገልጿል።

ይህን ተከትሎ " ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰውነታችን ወደነበረበት እንዲመለስልን ብቻ በሀምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጥያቄ አቅርበናል " ብሏል።

ሆኖም " ቦርዱ የፕሪቶሪያውን ስምምነት፣ ከዚህ በፊት በሌሎች የፌደራል ተቋማት የተሰጡትን ውሳኔዎች፣ ሌሎች ህጎችና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረሱ መግባባቶች ወደጎን በመተው ጥያቄውን ' በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ' መልሷል " ሲል ገልጿል።

ይህን ተከትሎ ህወሓት " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ ሆኗል " በማለት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበልም " ሲል አሳውቋል።

" በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ የተካተቱት ዝርዝር ይዘቶች አዲስ በወጣው ማሻሻያ ህግ መሰረት የተቀመጡና ካቀረብነው ጥያቄ ጋር የማይገናኙ ናቸው " ሲልም አክሏል።

" የቦርዱ ውሳኔ ህጋዊ ሰውነቴን ወደነበረበት እንዲመለስ የቀረበውን ጥያቄ የማይመልስ ፤ የነበሩ ውይይቶችን የሚቃረኑ ዝርዝር ይዘቶች የሚጭንብን በመሆኑ አልተቀበልኩትም " ያለው ህወሓት " ጥያቄያችን እስኪመለስ ድረስ የፓርቲው ሕገ ደንብ በሚፈቅድልን መልኩ ተያያዥ ስራዎችን እናከናውናለን " ብሏል።

የፌደራል መንግስቱም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመከሩበት ወቅት ፦

- TPLF እና መሰል ፓርቲዎች በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ሕጋዊ ፓርቲ እንዲሆኑ አዋጅ መሻሻሉ፤
- አቃቤ ህግ ለምርጫ ቦርድ መጻፍ የነበረበትን ማለትም ስራውን ሰርቶ የሚያጣራውን አጣርቶ በሕጋዊ መንገድ እንዲፈቅድላቸው፤
- የአስፈጻሚውን ስራ 100% መሰራቱን፤
- ፓርቲ ለፓርቲ ፤ የመንግሥት ለመንግሥት ውይይቶች ላይ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ እንደተሰጠ፤
- TPLF ምርጫ ቦርድ ሄዶ የሚጠበቅበትን ዶክመንት አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ጉባኤ ማድረግ እንዳለበት ፤ ይህን ባያደርግ ምርጫ ቦርድም ካልተቀበለው፤ TPLFን ሕጋዊ ፓርቲ ካላለው ፦
➡ በምርጫ ሊሳተፍ እንደማይችል ፤
➡ መንግሥትም ሊሆን እንደማይችል ይህ ደግሞ ተመልሶ ጦርነት ውስጥ የሚያስገባ እንደሆነ፤
- ተመልሶ ጦርነት ውስጥ ከመግባት በተበጀው ሕግ ፤ በተደረሰው ስምምነት ህወሓት የቀረውን ጉዳይ አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ጉባኤ አካሂዶ ፓርቲውን መልሶ ወደ ፖለቲካ ስርዓት መመለስ እንዳለበት መግለጻቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎን ወርቅ አገኘች !ሀገራችን በኦሎምፒኩ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ በማራቶን በጀግናው አትሌትላችን ታምራት ቶላ አማካኝነት አግኝታለች።ምንም እንኳን በፓሪስ እየተመዘገበ ያ...
10/08/2024

ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎን ወርቅ አገኘች !

ሀገራችን በኦሎምፒኩ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ በማራቶን በጀግናው አትሌትላችን ታምራት ቶላ አማካኝነት አግኝታለች።

ምንም እንኳን በፓሪስ እየተመዘገበ ያለው ውጤት አንገት የሚያስደፋ ቢሆንም ዛሬ በወንዶች ማራቶን የተገኘው ውጤት የሚያኮራ ነው።

አትሌት ታምራት እጅግ በሚደንቅ ብቃት ነው ወርቁን ወደ ኢትዮጵያ እጅ ያስገባው።

አትሌት ታምራት ተጠባባቂ የነበረ ሲሆን የአትሌት ሲሳይ ለማን መጎዳት ተከትሎ ነው በውድድሩ ሊሳተፍ የቻለው።

በብራዚል በአውሮፕላን አደጋ የ62 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ   በብራዚል ሳኦ ፓውሎ ግዛት 58 መንገደኞችን እና አራት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ የነበረ አውሮፕላን ተከስክሶ በህይወት የተረ...
09/08/2024

በብራዚል በአውሮፕላን አደጋ የ62 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

በብራዚል ሳኦ ፓውሎ ግዛት 58 መንገደኞችን እና አራት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ የነበረ አውሮፕላን ተከስክሶ በህይወት የተረፈ ሰው አለመኖሩ ተገለጸ።

ባለ መንታ ሞተር ቱርቦፕሮፕ አውሮፕላን በደቡብ ብራዚል ፓራና ከምትገኘው ካስካቬል ወደ ሳኦ ፖሎ ዋና አውሮፕላን ማረፊያ በመብረር ላይ ሳለ ቪንሄዶ ከተማ ሲደርስ ቁልቁል መውረዱን የቮፓስ አየር መንገድ ተናግሯል።

ስለ አደጋው መንስኤ ለጊዜው የታወቀ ነገር ባይኖርም በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩ በሙሉ ህይወታቸው ማለፉን ነው ቢቢሲ የዘገበው።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፈጣን መረጃ : Fast Mereja posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share