23/03/2023
Yihune Belay/fan follow, like share
ድምጻዊት የዝና ነጋሽ
ከተወለደችበት ጎንደር ዳባት ጥዋ ጊዮርጊስ በ1979 ነበር አባትዋ እርስዋን እና ወንድሟን መሳፍንት ነጋሽን ወደ አዲስ አበባ ይዘው የሄዱት።ያኔ የ10 ዓመት ልጅ ነበረች። አባታቸው አዲስ አበባ የወሰዷቸው እንዲማሩ ነበርና ትምሕርት ቤት አስገቧቸው። ግን በትምህርቱ ብዙም አልገፉበትም። የዝናና ወንድሟ በምሽት ክበብ መዝፈን ጀመሩ።
በተለያዩ አልበሞቿ ደጋግማ የዘፈነችው ሰቆጣ መለያዋ ነው።በዚህና በሌሎችም ተወዳጅ የባህል ዘፈኖቿ የምትታወቀው ድምጻዊት የዝና ነጋሽ ኑሮዋን ለንደን ካደረገች 20 ዓመት ሆኗታል። ትዳር መሥርታ የልጆች እናት ከሆነች ወዲህ ሙዚቃውን እንደ ፍላጎቷ ማስኬድ ባትችልም ሁኔታዎች ሲመቻቹላት ነጠላ ዜማም ይሁን አልበም ታወጣለች።ከመካከላቸው በዚህ ዓመት ለህዝብ ያቀረበችው አንድ ነጠላ ዜማ ይገኝበታል።በቅርቡም አንድ አዲስ አልበም ለማውጣት ዝግጅቷን አጠናቃለችት።የዝና ከብዙ ዓመታት በኋላ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ለህዝብ ያቀረበችው ያዳመጣችሁት እናመስግናቸው የራስዋ ድርሰት ነው።ከቀደሙት ዘፈኖቿ ለየት ያለውን ይህን ዘፈን የደረስኩበት ምክንያት አለኝ ትላለች።የዝና የሙዚቃውን ዓለም የተቀላቀለችው በልጀነቷ ነው።ከተወለደችበት ጎንደር ዳባት ጥዋ ጊዮርጊስ በ1979 ነበር አባትዋ የዝና ነጋሽን እና ወንድሟን መሳፍንት ነጋሽን ወደ አዲስ አበባ ይዘው የሄዱት። ያኔ የዝና የ10 ዓመት ልጅ ነበረች። አባታቸው አዲስ አበባ የወሰዷቸው እንዲማሩ ነበርና ትምሕርት ቤት አስገቧቸው። ግን በትምህርቱ ብዙም አልገፉበትም። የዝናና ወንድሟ በምሽት ክበብ መዝፈን ጀመሩ።እንዲህ እንዲህ እያለች የዝና የመጀመሪያ ካሴትዋን በ16 ዓመቷ ለማውጣት በቃች። ከመጀመሪያው ካሴት በኋላ ቦለሎች በሚል ስም ከጓደኞችዋና ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር በከፈተችው የምሽት ክበብ የርስዋና የቡድኑ አባላት ዝና እየናኘ ሄደ።በወቅቱ ቦለሎች በህብረት ያወጡት ካሴት ታዋቂነትን አትርፎላቸዋል።ከዚያ በኋላም የዝና ዘፈኖች በሀገር ውስጥ በውጭም ለመታተም በቅተዋል። ከዚህ አጋጣሚ በኋላ ቦለሎች በተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት እየተዘዋወሩ ሥራዎቻቸውን ቢያቀርቡም የጋራ ጉዞአቸው ግን ቀስ በቀስ እየከሰመ ሄደ።የዝናም ከጥቂት ዓመታት በኋላ ኑሮዋን ለንደን አደረገች።ትዳር መስርታ ልጆችም ከወለደች በኋላ እንደበፊቱ በዘፈኑ ብዙም መግፋት ባትችልም ጭርሱን ግን አልተወችውም።የዝና ከልጅነት አነስቶ በተሰማራችበት በዘፈኑ ዓለም በተለያዩ መድረኮች ከአድናቂዎቿ ልዩ ልዩ ስጦታዎች ተበርክተውላታል።ከመካከላቸው ለሁለቱ ልዩ ቦታ ትሰጣለች።
Yihune Belay/fan
music