ሙዚቃዊያን Muzikawiyan

ሙዚቃዊያን Muzikawiyan Here we talk about music and musicians

14/04/2024
ሙሉቀን መለሰ ነብስህ በሰላም ትረፍ
09/04/2024

ሙሉቀን መለሰ ነብስህ በሰላም ትረፍ

Let’s vote Adchalew Feteneውድድሩ ዛሬ ማታ ይጠናቀቃል እና ሁለት ደቂቃ ብቻ ወስደን እንምረጠው አብረን እናሸንፍ አሞላሉ ቀላል ነው ሙሉ አሞላሉ በፎቶ ታግዞ ከላይ ፖስቱ ላይ ...
31/03/2024

Let’s vote Adchalew Fetene

ውድድሩ ዛሬ ማታ ይጠናቀቃል እና ሁለት ደቂቃ ብቻ ወስደን እንምረጠው አብረን እናሸንፍ አሞላሉ ቀላል ነው ሙሉ አሞላሉ በፎቶ ታግዞ ከላይ ፖስቱ ላይ አለ ።
ሊንኩ ይሄው 👇👇👇

https://www.koraawards.com/top20/best-artistgroup-traditional-music-top-20

እፀገነት ትባላለች ጊታርስት ናት (የሙዚቀኛ ክብሮም ሚስት)አዲስ አልበም ጨርሰዋልእኔ በበኩሌ የsynth machine effects ብዙ ጠብቃለው የ guitar effects እንደነበሩGood L...
22/03/2024

እፀገነት ትባላለች ጊታርስት ናት (የሙዚቀኛ ክብሮም ሚስት)
አዲስ አልበም ጨርሰዋል
እኔ በበኩሌ የsynth machine effects ብዙ ጠብቃለው የ guitar effects እንደነበሩ
Good Luck ወገኖች

Congratulations Alexo ዮቶር ቁ-2 ወቷል:: አሌክሶ  ከዜማና ግጥም ድርሰት የሙዚቃ እውቀቱ ባለፈ በጥልቅ ሀሳቦች Such as General knowledge,philosophy,Rel...
12/03/2024

Congratulations Alexo ዮቶር ቁ-2 ወቷል:: አሌክሶ ከዜማና ግጥም ድርሰት የሙዚቃ እውቀቱ ባለፈ በጥልቅ ሀሳቦች Such as General knowledge,philosophy,Religious,Astronomy,journalism, Sports ,Music ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ያፈራችው ድንቅ ባለሞያ ነው :: Maximum Respect ወንድሜ Alemayehu Demeke

Musician Smiz Mayle

Aschalew Fetene ትዝታ ዘ-ቻግኒ
09/03/2024

Aschalew Fetene ትዝታ ዘ-ቻግኒ

የክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዲ አፍሮ ወቅታዊ መልዕክት አስተላለፈ"ባለፉት 5 አመታት ያለጥፋታቸው ህይወታቸው እንደ ቅጠል የረገፈው ወገኖቻችንን እናስብ"ለአንፀባራቂውና የጋራ አንድነታችን ውጤት ...
29/02/2024

የክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዲ አፍሮ ወቅታዊ መልዕክት አስተላለፈ

"ባለፉት 5 አመታት ያለጥፋታቸው ህይወታቸው እንደ ቅጠል የረገፈው ወገኖቻችንን እናስብ"

ለአንፀባራቂውና የጋራ አንድነታችን ውጤት ለሆነው፣ ከሀገር አልፎም ለመላው የአፍሪካ ሕዝብ ኩራት ሆኖ በታሪክ ሲዘከር ለሚኖረው ለ128ኛው የዐድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ የሚል መልእኬቴን እያስተላለፍኩ፤

የዘንድሮውን 128ኛው የዐድዋ ድል በዓል ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ በገጠማት ፖለቲካዊ ቀውስ ሳቢያ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ያለማቋረጥ አለጥፋታቸው በማንነታቸው ብቻ ተለይተው በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ ሕይወታቸው እንደ ቅጠል እየረገፈ ያሉ ንፁሓን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን በሙሉ በሕሊና ጸሎት እያሰብን ሊሆን ይገባል።

ይህንንም ከሰው ልጅ የሞራል ሕግ ያፈነገጠ እጅግ ዘግናኝና ኢሰብዐዊ ተግባር ሲፈፀም አለማውገዝና ከዳር ሆኖ በዝምታ ማየት እንደ አንድ ሀገር ተወላጅ ዜጋ ነገ ማናችንንም ከታሪክ ተወቃሽነት እና ተጠያቂነት እንደማያድነን ከግንዛቤ ውስጥ ልናስገባ ግድ ይለናል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ፍቅር ያሸንፋል!

ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

የድምፅ መስጫው ቀን እስከ ሐሙስ ነው !ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ በኮራ ሽልማት እየመራ ነው!በእናትዋ ጎንደር እና ካሲናው ጎጃም ባህላዊ ጣዕመ ሙዚቃዎችና በቅርቡ በተለቀቀው "አስቻለ" አልበም ...
26/02/2024

የድምፅ መስጫው ቀን እስከ ሐሙስ ነው !

ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ በኮራ ሽልማት እየመራ ነው!

በእናትዋ ጎንደር እና ካሲናው ጎጃም ባህላዊ ጣዕመ ሙዚቃዎችና በቅርቡ በተለቀቀው "አስቻለ" አልበም ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ በኮራ አዋርድ "በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ዘርፍ" እጩ መሆኑ ይታወሳል።

ከደቂቃዎች በፊት ኮራ አዋርድ በማህበራዊ ትስስር ገፆቸው በይፋ ባደረጉት መሰረት ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ከ40 እጩዎች ውስጥ በ20.67 በመቶ በራሱ ምድብ እየመራ ይገኛል።

አሸናፊው የሚወሰነው እኛ በምንሰጠው ድምጽ ስለሆነና

የድምፅ መስጫው ቀንም እስከ ሀሙስ ስለሆነ ለድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ድምፃችሁን ለመስጠት የሚከተሉትን ሊንኮች ተጠቀሙ ተብላችኋል:-

1) በመጀመሪያ በአስተያየት መስጫው ላይ የተቀመጠውን ሊንክ ይክፈቱት ፣
https://www.koraawards.com/top40

2) ቀጥሎም በሚከፈተው ገፅ ወደ ግርጌ በመውረድ በምስል 1 ላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ በመንካት የድምፅ መስጫውን ያግኙ፣

3) በመቀጠል ከሚመጣው የእጩዎች ዝርዝር ውስጥ በምስል 2 የተመለከተውን ይክፈቱት፣

4) በመጨረሻም በምስል 3 ላይ የተመለከተው የኢትዮጵያ እጩውን ምስል ያለበትን ያገኛሉ ፤ እሱን በመክፈት ድምፅ መስጠትዎን ያረጋግጡ ።

በመጨረሻም ይህንን ፅሁፍ ኮፒ በማድረግ ከነምስሎቹ በገፅዎ ላይ በማስፈር ለበርካቶች ተደራሽ ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

https://www.koraawards.com/top40

https://www.koraawards.com/top40

ድምጻዊ አዲስ ፍቃዱ ሙላት
25/02/2024

ድምጻዊ አዲስ ፍቃዱ ሙላት

ዲሽታ ጊና
25/02/2024

ዲሽታ ጊና

የወላይትኛ ድምጻዊ ዲዲ ጋጋ
25/02/2024

የወላይትኛ ድምጻዊ ዲዲ ጋጋ

🎉 ኢትዮጵያ እየመራች ነው! 🌍🔝እንዴት እንደሚመረጥ፡-▶ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።▶ የአርቲስቶችን ዝርዝር ያስሱ እና ምድብ ይምረጡ።▶ ለእነሱ ድምጽ በመስጠት ተወዳጆችዎን ይምረጡ። በእያን...
25/02/2024

🎉 ኢትዮጵያ እየመራች ነው! 🌍🔝

እንዴት እንደሚመረጥ፡-

▶ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
▶ የአርቲስቶችን ዝርዝር ያስሱ እና ምድብ ይምረጡ።
▶ ለእነሱ ድምጽ በመስጠት ተወዳጆችዎን ይምረጡ። በእያንዳንዱ ምድብ 3 ድምጽ እንደተፈቀደልዎ ያስታውሱ።

🔗 እዚህ ድምጽ ይስጡ፡ https://www.koraawards.com/top40

ይህንን አስደሳች ዜና ለጓደኞችዎ ያካፍሉ እና ከሁሉም በላይ አርቲስቶችዎ እንዲያሸንፉ ለመርዳት ድምጾቹን በቅርበት ለመከታተል መመዝገብዎን አይርሱ።

አሁን_ድምጽ_ይስጡ

KORA Awards

__________________________________

በሙዚቃው የተለያዩ ትውልዶችን ያስተሳሰረው ጌታቸው ካሳ አረፈ‘አገሬን አትንኳት’፣ ‘አዲስ አበባ’ እና ‘ትዝታ’ በተሰኙ ሙዚቃዎቹ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው አንጋፋው ሙዚቀኛ ጌታቸው ካሳ ...
21/02/2024

በሙዚቃው የተለያዩ ትውልዶችን ያስተሳሰረው ጌታቸው ካሳ አረፈ

‘አገሬን አትንኳት’፣ ‘አዲስ አበባ’ እና ‘ትዝታ’ በተሰኙ ሙዚቃዎቹ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው አንጋፋው ሙዚቀኛ ጌታቸው ካሳ ከዚህ ዓለም ማረፉ ተሰማ።
ሙዚቀኛው ባደረበት ህመም በየካቲት 12 ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ የካቲት 12/ 2016 ዓ.ም ሌሊት ሕይወቱ አልፏል።
በሙዚቃው የተለያዩ ትውልዶችን ማስተሳሰር የቻለው ጌታቸው ካሳ በኢትዮጵያ ሙዚቃ በነገሰበት የአምስት አስርት ዓመታት ቆይታውም አይረሴ የሚባሉ ሙዚቃዎችን አበርክቷል።
‘እወድሻለሁ’፣ ‘ትዝ ባለኝ ጊዜ’፣ ‘የከረመ ፍቅር’፣ ‘ውበትም ይረግፋል’፣‘አትጥፊ ከጎኔ’ እና ሌሎችን ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃዎችን የተጫወተው ጌታቸው ምን ያህል ዘፈኖችን እንደሰራም በትክክል ቁጥሩን እንደማያውቀው በአንድ ወቅት ተናግሮ ነበር።
ጌታቸው ለየት ባለ ድምጹ እና ቅላጼው፣ በመድረክ ውዝዋዜው፣ የአዘፋፈን ስልቱ የራሱን አሻራ በኢትዮጵያ የሙዚቃ መድረክ መፍጠር የቻለ አርቲስት እንደሆነ ይነገርለታል።
ወርቃማ ተብሎ በሚጠራውም የኢትዮጵያ የሙዚቃና የሥነ ጥበብ ታሪክ ላይ አስተዋጽኦ ማድረጉንም ይመሰክሩለታል።
በዓለማችን ውስጥ ስመ ጥር ከሆኑ እና ታላላቆቹ የሙዚቃ ጸሐፊ ከሚባሉት ውስጥ የሆነው አንዱ ቦብ ዲለንም ምርጥ ካላቸውም የሙዚቃ ስራዎች አንዱ የጌታቸው ካሳ ‘ትዝታ’ የሚለው ሙዚቃ እንደሆነ የሰፈረ ሲሆን ራሱ ጌታቸውም ስለዚህ ጉዳይ ተናግሮ ነበር።
ሙዚቀኛው ለ28 ዓመታት ገደማ ኑሮውን በአሜሪካ አድርጎ የነበረ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያም የተመለሰው ከአስር ዓመት በፊት ነበር።
ወደ ኢትዮጵያም ከተመለሰ በኋላ በተለያዩ መድረኮች ስራውን ያቀርብ ነበር።
በአዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ ተወልዶ ያደገው ጌታቸው ሙዚቃን መጫወት የጀመረው ገና በልጅነቱ ነበር።
በወቅቱ ታዋቂ የነበሩትን የጃዝ እና የሶል ሙዚቀኞች የነበሩትን የነ ሃሪ ቤላፎንቴ፣ ስቲቪ ወንደር እና የመሳሰሉ አፍሪካ አሜሪካውያን ዘፈኖችን አስመስሎ በመጫወትም ነበር ወደ ሙዚቃ ሕይወት የገባው።
የሙዚቃ ሕይወቱ በአባቱ ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቱና እና አባቱም በእሳቸው ስም [በጸጋዬ] እንዲጠራ ባለመፈለጋቸው ጌታቸው የአባቱን ስም ለመለወጥ ተገዶ ነበር።
በአንድ ወቅት ፍቅረኛው የነበረችውን እና ዘፋኝ የነበረችውን አሰገደች ካሳ አባት ስምም በመውሰድ መጠሪያውን ጌታቸው ካሳ በሚል ቀየረ።
በኋላም ሂልተን ሆቴል ከዋልያስ ባንድ ጋር እየተጫወተ በነበረበት፣ በአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ ወቅት አባትየውን እንደጋበዛቸውና ተጸጽተው እንደተቀበሉትም ተናግሯል።
ከዚያም በኋላ በደረሰበት የሙዚቃ ስኬቱ አባቱ ይኮሩበት እንደነበር አስረድቷል።
ጌታቸው በፓትሪስ ሉምምባ ክለብ ውስጥ እየሰራ በነበረበት ወቅት ነው ታዋቂውን እና የመጀመሪያ የሆነውን ዘፈኑን ‘እመኛለሁ’ን ያወጣው።
ከዚያም በኋላ ያወጣቸው ‘የከረመ ፍቅር’ ‘ ትዝታ’ እና ሌሎችም ዘፈኖቹ ታዋቂነትን አስገኝተውለታል።

ከዘፈን በተጨማሪ በቬነስ፣ ዋሊያስ እና ኢትዮ ስታር ባንዶችም ቆይታውም ከበሮ ይጫወት ነበር።
አሜሪካም በአውሮፓውያኑ 1981 ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ለስድስት ዓመታት ያህል ‘ እወድሻለሁ’ እና ‘ አዲስ አበባ’ የሚሉ ዘፈኖቹንም እየሰራ ነበር።
ኢትዮጵያም ተመልሶ ከመጣ በኋላም እነዚህ ተወዳጅ የሆኑት ሙዚቃዎቹ ወጡ።
ተመልሶም ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ለሁለት አስርት ዓመታት በኖረባት አሜሪካ በታዋቂዎቹ ኢትዮጵያውያን ሬስቶራንቶች ብሉ ናይል፣ አዲስ አበባ፣ ዱከም፣ እቴቴ፣ ኩዊን ሼባ ሬስቶራንቶች ይጫወት ነበር።
ለሙዚቃው ባደረገውም አስተዋጽኦ በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን የሕይወት ዘመን ሽልማት አበርክተውለታል።
‘ትዝታ’ የሚለው ሙዚቃው ‘ጎልደን ይርስ ኦፍ ሞደርን ሚዪዚክ’ በሚል ስብስብ ውስጥ በቡዳ ሬከርድስ አሳታሚነት፣ በፍራንሲስ ፋልሴቶ አማካኝነት ኢትዮፒክስ በሚለው አልበም ተካትቶ ሙዚቃው በመላው ዓለም ተሰሚነት እንዲኖረው አድርጎታል።
ነገር ግን ‘ያለኔ ፈቃድ ነው’ ሙዚቃዬ የወጣው በሚልም ክስ እንደመሰረተ ጌታቸው በቅርቡ ከኢቢኤስ ጋር ባደረገው ቆይታ ተናግሮ ነበር።
ትዝታ (እኔስ አልከፋ ) የሚል መጠሪያ ያለው ሙዚቃው መጀመሪያ የታተመው ጌታቸው ከዋልያስ ባንድ ጋር እየተጫወተ በነበረበት ወቅት ነው። የሙዚቃውም አሳታሚ የአምሐ ሬከርድስ ባለቤት አምሐ እሸቴ ነበር።
አንጋፋው ሙዚቀኛ ጌታቸው የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነው።

✍️ BBC Amharic

እንገር ወሎ- የአፍታ የግጥም ዳሰሳውብአረገ አድምጥከሳምንታት በፊት አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) “አስቻለ” የሚል መጠሪያ ያለውን የመጀመሪያ አልበሙን ለአድማጭ እንካችሁ ብሏል። ሙዚቃው በአድማጭ...
21/02/2024

እንገር ወሎ- የአፍታ የግጥም ዳሰሳ

ውብአረገ አድምጥ

ከሳምንታት በፊት አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) “አስቻለ” የሚል መጠሪያ ያለውን የመጀመሪያ አልበሙን ለአድማጭ እንካችሁ ብሏል። ሙዚቃው በአድማጭ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝቷል። በተለይ “እንገር ወሎ” የሚለውና ስለወሎ ታሪካዊና ማህበራዊ ውቅር ብሎም ውበት የሚያትተው ዘፈኑ ብዙዎችን ማስደነቁን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚንሸራሸሩ ጽሑፎች ምስክር ናቸው።

ከዜማና ከቅንብሩ ባለፈ የግጥሙ ሃሳብና ጥራት ለሙዚቃዊ እሴቱ ትልቅ ዋጋ ሰጥቶታል። በተለይ በዘመናችን የግጥም ነገር ችላ እየተባለ ነው የሚል ወቀሳ ይበዛ ነበር። ወቀሳው እውነትም አለው። ይሄ ሙዚቃ ግን እንደ አንድ አብዮት የሚታይ ነው ማለት ይቻላል።

ይሄን “እንገር ወሎ” በሚል ርዕስ በ 6:34 ደቂቃ የተቀነበበውን ዘፈን ግጥሙን ብቻ ለአፍታ ለመዳሰስ ተሞክሯል። ይሄ አተያይም የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ የግል ምልከታ መሆኑ ይታወቅ ዘንድ አሳስባለሁ። አብረን እንዝለቅ።

እንገር ወሎ

ድምጻዊ- አስቻለው ፈጠነ (አርዲ)
ዜማ- አስቻለው ፈጠነ (አርዲ)
ሙዚቃ ቅንብር ሚክስ እና ማስተር- ቢንአንዴ (ዜማ አዘዝ)
ግጥም- ኃይለኢየሱስ ደርብ (Hader)፥ አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) እና ለመምቴ ሞገዱ
===
ከመቃብር በላይ፥ ስም ይቀራል ብሎ
ፍቅርና ጀግንነት፥ ያውቅበታል ወሎ
የቀድሞው “ቤተ አምሐራና አንጎት” የአሁኑ ወሎ የባህል፥ የታሪክ፥ የቋንቋ እንዲሁም የማህበራዊ ክዋኔዎች ሁሉ ማሰሮ (Melting pot) ነው ይሉታል። አማራው፣ ትግሬው፣ አፋሩ፣ ኦሮሞው፣ አርጎባው እንዲሁም ሌሎች ህዝቦች ተገምደው የፈጠሩት ልዩ ማንነት ነው። የእስልምና፣ የክርስትና እንዲሁም የዋቂ ፈናው ሽምን ውጤት ነው።

ታዲያ ወሎ ብዝሃነትን የሚያውቅ፣ ስለፍቅርና ስለጀግንነትም ለምስክር የሚጠሩት ህዝብ ነው። ሙዚቀኛው አስቻለው፡ ወሎ ይሄን ፍቅርንና ጀግንነትን አሳምሮ የሚያውቅበት ገፊ ምክንያት “ሰው ቢያልፍም ስም ከመቃብር በላይ ቀሪ ነው ብሎ ስለሚያምን ነው” ይለናል። አባቶቻችንስ ሲተርቱ “ከስብ ስም ይሸታል” አይደል የሚሉት? ወሎም ሰው አላፊ ጠፊ፣ ህይወት ጊዜያዊ፣ ስምና ማንነት ግን ህያው ነው ብሎ የሚያምን አበ ፍቅር ወ ጀግንነት ነው ይለናል።

ወሎ ልቡ ሰፊ፥ መተኛ ድንኳን
አበጋር ይፈራል፥ እንኳን አምላኩን

ልብ የሚለው ቃል “ለበወ” ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ነው። ለበወ ማለትም ልብ አደረገ፣ አስተዋለ ማለት ነው ይላሉ ሊቃውንቶቻችን።

የወሎ ልብም እንኳን ለማረፊያነት ይቅርና ለመተኛነትም የሚያገለግል እንደ ድንኳን የሰፋ ነው ይለዋል። ለዚህ የልብ ስፋቱ አስረጂ ብዙም መሄድ አይጠበቅብንም፤ እንኳን አምላክን ይቅርና አበጋርንም ይፈራል ይለናል። ለመሆኑ አበጋር ምንድን ነው?
ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ በ2006 ዓመተ ምህረት ለ”ፋክት” መጽሔት ካዘጋጀው ቃለመጠይቅ እንዲህ የሚል ጽሑፍ እናገኛለን።
“እንባ የሚደርቀው በፍርድ ሳይሆን በፍቅር ነው” ይላል ቃለ መጠይቁ የተደረገለት በአምባሰል ወረዳ ውስጥ በምትገኝ ጎጥ አበጋር የነበረው አበጋር ይማም እርጋታው።

አበጋር ምን ማለት ነው? የሚል ጥያቄ የቀረበለት አበጋር ይማም እንዲህ ነበር የመለሰው።

“ሽማግሌ ነዋ። የተጣላ ያስታርቃል። ክፉ እንዳይሰራ ተው ይላል። ጅል ነገሩን ዱዓ አድርጎ ያባርራል። እንቅፋት የተባለን ሁላ ያስገልላል። ሰውን አብሮ እንዲበላና እንዲጠጣ ያደርጋል። ይሄ ነው አበጋር ማለት። ያገር ራስ አይነታ ማለት ነው። መሪ ማለት ነው አስታራቂ።”

ከላይ እንዳየነው አበጋር ማለት በሰው ልጆች ዘንድ ሰላማዊ ኑሮ ይሰፍን ዘንድ ከዘሩ በተቀበለው፣ በስብዕናው ባስመሰከረው እውነት ላይ ተመስርቶ ሃይማኖት፥ ባህል ሳይገድበው ለሰው ልጆች ሁሉ የሚኖር ልባም ነው። ከፍርድ ይልቅ ፍትሕንና ፍቅርን የሚያሰፍን ነው። ለዚህ ነው ድምጻዊ አስቻለው አበጋርን ይፈራል እንኳን አምላኩን እያለ የሚመሰክርለት።

የራስ አሊ ሀገር፥ የሴሩ ጓንጉል
ይሾማል ይቀባል፥ አቡን ይመስል

በአስራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሀገራችንን መልክ የቀየሩ ሁለት አበይት ክስተቶች እንደነበሩ ታሪክ ያስረዳል። እነሱም የግራኝ አህመድ ወረራና የኦሮሞ ህዝብ መስፋፋት ናቸው። በዚህ ምክንያት የቀድሞዋ ቤተ አምሐራ ወደ ወሎ ተቀይራ ቀደምት ኃያልነቷ ተቀዛቅዞ ነበር። ነገር ግን በቀደምት የታሪክ ማዕከልነቷና፥ በዘመነ መሳፍንት ገፊ ምክንያትነት በወሎ አዲስ ስርወ መንግስታት ተመሰረቱ። በዋናነትም የማመዶች ስርወ መንግስትና የወረሴሆች (የየጁዎች) ስርወ መንግስት ናቸው።

አባ ሴሩ ጓንጉልም የየጁ ስርዎ መንግስት ሲመሰረት አካባቢውን ያስተዳድሩ ዘንድ በሽማግሌዎች እንደተመረጡ ታሪክ ይዘግባል። ነገር ግን የየጁ ስርወ መንግስት ከፍተኛ ጉልበት ያገኘው በልጃቸው በአሊ ጓንጉል ነው። “ታላቁ ራስ አሊ” በመባልም ይታወቃሉ። በጠንካራ የጦር አደረጃጀታቸው ቀድመው ይጠራሉ።
አሊ ጓንጉል ብዙ ቦታዎችን ከግዛታቸው በማካተት የጁን ጠንካራ መሰረት ላይ ማቆም ችለዋል። በዘመነ መሳፍንት ከነበሩ አካባቢያዊ መንግስታት ጠንካራውና ተጽእኖ ፈጣሪው እሳቸው ነበሩ።

ብዙ ጦርነቶች ላይ ከመሳተፍ ባሻገር ማዕከላዊ መንግስት ላይ ተጽእኖ ማሳደር ችለዋል። ንጉሰ ነገስቱን አጼ ተክለ ጊዮርጊስን (1779-1784) ሳይቀር ከስልጣኑ በማውረድ አምባሰል ውስጥ በግዞት አኑረዋቸው ነበር። ሳልሳዊ ኢያሱንም ያነገሷቸው እሳቸው መሆናቸውን ታሪክ ዘግቧል።

ወደ አስቻለው ስንመጣ ወሎዬው የጓንጉል ልጅ ራስ አሊ በጉልበታቸው ንጉስን መሻርና መሾም የሚያስችል ብቃት ነበራቸው። ይሄንን ያፈራችም የወሎ ምድር ናት። ስለዚህ የአቡኑን ግብር ሳይቀር መጋራት የቻሉ የሀገራችን ጀግኖች መፍለቂያ ወሎን ታሪኳን እየመዘዘ ይተርክልናል።

ሐሊማ ብላችሁ፥ እስኪ ስሟን ጥሩ
መነን አይደለም ወይ፥ የጁ ስልጣን ክብሩ

እቴጌ መነን በዘመነ መሳፍንት አድራጊ ፈጣሪ የሚያስብል ጉልበት ነበራቸው። እቴጌ መነን ከማመዶች ባላባት ከነበሩት ከሊበን አመዴ ተወለዱ። የመጀመሪያ ስማቸው ሐሊማ ነበር። ክርስትና ተነስተው መነን ተባሉ። ከመጀመሪያ ባላቸው ከየጁው አሉላ ጉግሳ፡ ራሲ አሊን ወለዱ። ትንሹ ራስ አሊን። ትንሹ ራስ አሊም በ13 ዓመታቸው ስልጣን ተረከቡ። ራስ ዓሊም ተዋበችን ወለዱ። እንግዲህ ተዋበች የመይሳው ካሳ (አጼ ቴዎድሮስ) ሚስት ናቸው። የዘመነ መሳፍንት ማክተሚያ የሆኑት “ካሳ ኃይሉ” እቴጌ መነንንና ራስ አሊን አሸንፈው የየጁዎችንና የማምውዶችን ዘመን እንዲያከትም አደረጉ። ራስ አሊን አይሻል ላይ እንደረታቸው ልብ ይሏል።

ለዚህ ነው አስቻለው የቀድሞ ስማቸውን ሳይረሳ እስኪ ለየጁ ስልጣን “ክብር” የነበሩትን እኒያን ገናና እናት እቴጌ መነንን ሐሊማ እያላችሁ ጥሩልኝ የሚለው። ምንም ቢሆን የመይሳውን የልብ ንግስት ተዋበችን በእሳቸው በኩል አላገኘንምን? መይሳውስ ቢሆኑ ተዋበችን የመሰሉ የሴት ልክ ባያገኙ ከህልማቸው ይደርሱ ነበርን? ከተራ ሽፍታነት የተሻገረ ሚና ይኖራቸው ነበርን? ስለዚህም የዚህን ሁሉ ምንጭ ሐሊማን ጥሩልኝ ይላል የዘመናችን አንጎራጓሪ አስቻለው ፈጠነ።

አጀብ
እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ፥ የምወድሻዋ
እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ፥ መገን አንገትዋ

እዚህ ላይ አንጀት በሚያባባ ዜማ እንዴት ነሽ እያለ ወደ አሁን የሚወረወር ቃል ይልካል። የምወድሽዋ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እያለ ለዚህች የታሪክ ሙዳይ ይንገበገባል። መገን አንገትዋ እንደምን ነሽልኝ ይላል። ለምን አንገት ቢሉ ሚስጥሩ ቢረቅብን እንጂ አይርቅብንምና ነው።

አንገት እኮ ሃይማኖት ነው። አንገት እኮ አዙሮ ማየት የሚያስችል የልብ አካል ነው። አንገት እኮ የቃል መጽኛ የደስታም የመከፋትም ምልክት ነው። አንገት እኮ የድሪው፥ የጌጡ ማረፊያ የንቅሳቱ ማረፊያ ጸዳል ነው። አንገት እኮ የእስትንፋስ ማዕከል ነው። አንገት እኮ ሚስጥር ነው እያለን አይደለም ወይ?

የሀገር ዋርካ ልኩ፥ ሀገረ መንግስት
ጠቅልል ሰውነቱ፥ አማራ ሳይንት

ሰውነት የሚጠቀለልበት ጥላው ለሚያሳርፍ ሀገር ልኩ ወሎ አይደለም ወይ? ሰውነትን የሚጠቀልል፣ መተናነስን ሳይሆን እኩልነትን ባሪያና ገባርነትን፡ አለቃና ምንዝርነትን ሳይሆን የፍቅር ልጅነትን የሚሰብክ፡ ሰውነትን እንደ አርማ ከፍ የሚያስደርግ የሀገር ካስማ ወሎ ነው ይለናል።

አንድም የ”አባ ጠቅል” የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የሰውነት አካል፥ የአካላቸው ክፋይ የእቴጌ መነን አስፋው እትብታቸው የተቀበረበትን የወሎዋ አምባሰልን እየጠቀሰልን ነው ብለን ብንደመም ማን ይከለክለናል? ማንም!

አንኮበር ወንዝ ላይ፥ አንዲት ፀሐይ ወጥታ
መቄት ታየች አሉ፥ ብልህ መሪ መርጣ

እናታቸው ከመቄት የምሚመዘዙት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ትልቅ ታሪክ ያላቸው ብልህ መሪ ናቸው። በሁሉም ዘንድ እንደ እናት የሚታዩት ምኒልክ “እምዬ” የሚል ስምም ወጥቶላቸዋል። በዓለም መድረክ ላይ ስላላቸው የዲፕሎማሲ ብቃትም እንደ ሬይመንድ ጆናስ (Raymond Jonas) ያሉ የታሪክ ባለሙያዎች brilliant strategist ሲሉ ያደንቋቸዋል።

ነገረ ውልደታቸውንም ጳውሎስ ኞኞ እንዲህ ይተርክልናል።
“ምኒልክ በ1836 ዓ.ም ነሐሴ 12 ቀን ቅዳሜ ዕለት ተወለዱ። አባታቸው ኃይለ መለኮት ሣህለሥላሴ ሲሆኑ እናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አዲያሞ ይባላሉ።

የምኒልክ እናት ወይዘሮ እጅጋየሁ የንጉስ ሣህለሥላሴ ሚስት የወይዘሮ በዛብሽ ገረድና የልጆች ሞግዚት ነበሩ። እጅጋየሁ የግርድና ሥራ የጀመሩት በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ቤት አልነበረም። ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ቤት ከመቀጠራቸው በፊት የአንኮበር ቤተ ክርስቲያን አለቃ የነበሩት የመምህር ምላት ገረድ ነበሩ። በአለቃ ምላት ቤት ግርድና ተቀጥረው ሳለ አንድ ቀን ጧት ለጓደኞቻቸው “….ዛሬ ማታ በሕልሜ ከብልቴ ፀሐይ ስትወጣ አየሁ….” ብለው ተናገሩ። ሥራ ቤቶች የሰሙት ወሬ መዛመቱ አይቀርምና ወሬው ከጌትዮው ከአለቃ ምላት ዘንድ ደረሰ። አለቃ ምላትም “እንግዲያው ይህ ከሆነ ወደላይ ቤት ትሂድ” አሉ። የላይ ቤት የሚባለው የአንኮበሩ የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ቤተ መንግሥት ከኮረብታ ላይ በመሆኑ አገሬው በተለምዶ “ላይ ቤት” ይለዋል።

እጅጋየሁ እንደተመከሩት ከንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ቤት ሔዴው ተቀጠሩ። የእጅጋየሁ የሕልም ወሬ ተዛምቶ ንጉስ ሣህለ ሥላሴም ቤት ገብቶ ስለነበረ የንጉስ ሣህለ ሥላሴ ባለቤት ወይዘሮ በዛብሽ ያ በሕልም የታየው ፀሐይ ከልጃቸው እንዲወለድ ፈለጉ። ወይዘሮ በዛብሽ ከልቻቸው ሁሉ አብልጠው ሰይፉ ሣህለ ሥላሴን ይወዱታል። ስለዚህ ሰይፉ ከእጅጋየሁ ልጅ እንዲወልድ ማታ እጅጋየሁን ወደሰይፉ መኝታ ቤት ልከው ያን ጐረምሳ እንድትጠብቅ አድረጉ።

የልጅ ሰይፉ አሽከሮች የእጅጋየሁን መላክ እንዳወቁ ለጌታቸው ለልጅ ሰይፉ ተናገሩ። ሰይፉ የሚወዳት ሌላ ሴት አለችው የአዲሲቱን የእጅጋየሁን መምጣት እንደሰማ ተናዶ እንዲያባራትም እናቱን ፈርቶ ከወንድሙ ከኃይለ መለኮት ዘንድ ሔዶ “እባክህ ሌላ ሴት ከፈልህ እሜቴ የላኳትን ያቺን ገረድ ውሰድልኝ” አለ። ኃይለመለኮትም እሺ ብሎ ከእጅጋየሁ ጋር ባደረጉት ግንኙነት ልጅ ተፀነሰ”።

የአጼ ምኒልክ እናት ዘራቸው ከመቄት እንደሚመዘዝም አለቃ ለማ ኃይሉ በትዝታ መጽሐፋቸው እንዲህ ይላሉ።
«ያጤ ምኒልክ እናት አባት የላስታ የመቄት ተወላጅ ናቸው አድያሞ ይባላሉ፤ ደጃች አድያሞ።. . . ከዚያ ሸዋ መጣ። እዚህ ሎሌነት ገባ ለሣህለ ሥላሴ አያት። ሲኖር አድያሞ ለማ ከመንዝ ሴት ወልዷት ያጤ ምኒልክን እናት፤. . . እንግዲህ የምኒልክ እናት ባባቷ መቄት ናት።»

በእርግጥ ሌሎች የታሪክ መዛግብት የወይዘሮ እጅጋየሁን ሀገር የተለያየ ቦታ ሲያደርጉት ይስተዋላል። ጳውሎስ ኞኞ አጤ ምኒልክ በሚለው መጽሐፋቸው ወይዘሮዋ ከጉራጌ ሀገር የተማረኩ ባሪያ ናቸው የሚሉ እንዳሉ አስፍረዋል። የሚሉ አሉ አሉ እንጂ በማስረጃ የተደገፈ ነገር የለም። በዚያው በአጼ ምኒልክ ዘመን ከተጻፉ የታሪክ ማስረጃዎች ውስጥ የአለቃ ተክለኢየሱስ ዋቅጅራ የታሪክ መዝገብ ወይዘሮ እጅጋየሁን ጎጃም ውስጥ የጎዛምን ወረዳ ተወላጅ ያደርጋቸዋል። ዞሮ ዞሮ ራሳቸው ጳውሎስ ኞኞ እንደሚሉት “ዋናው ቁም ነገር ታሪክ መስራት እንጂ ትውልድ አይደለምና” ወይዘሮ እጅጋየሁ በአንኮበር ሰማይ ላይ ፀሐይ እንድትንጎገቦግ አድርገዋል።

ያቺ አንኮበር አናት ላይ በእጅጋየው አፈ ማህጸን በኩል የወጣች ፀሐይ ማረፊያዋ ከባዶ ላይ አልነበረም ይለናል አስቻለው። ከመሪም መሪ መርጣ ከብልሁ ላይ አረፈች እንጂ። ይሄው ከአገልጋይ ደጅ የተገኘች ፀሐይ ከሀገረ ኢትዮጵያ አልፋ ለዓለም ጥቁር ህዝቦች ችቦ ሆነች። ለተገፉት መጽናናትን ይዛ ከተፍ አለች። የገረዲቷ የውድቅት ህልምም ተራ ቅዠት አልነበረም። ለሰው ልጆች እኩልነት የሚያበራውን እምዬን ይዞ ከተፍ አለ እንጂ ይለናል።

አገር ክተት ብለው፥ አዋጅ ሲማማሉ
ከቶ ከቶ አደረ፥ ጃማ ወረኢሉ

መጋቢት 5 ቀን 1887 ዓ/ም ንጉስ ምኒልክ አዋጅ አስነገሩ። ከአዋጁ መጨረሻ አካባቢም እንዲህ ይላል።

“ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፣ ለምሽትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሃዘን እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ። አልተውህም። ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም። ዘመቻዬ በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ።” አሉ እምዬ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነት ተመመ። መሰብሰቢያውንም የወሎዋ ታሪካዊ ቦታ ወረኢሉ እንድትሆን ተወሰነ። እንደሚታወቀው ለአድዋ ጦርነት መነሻ የሆነው የውጫሌ ውልም የመዋዋያ ቦታው ወሎ ውስጥ ነው። አድዋ የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካውያንና የዓለም ጭቁን ህዝቦች እጣ ፋንታ የተወሰነበት የዓለም ክስተት ነው። ለዚህ ሽርጉድ መሰብሰቢያ ዳስ ወሎ ናት። አቤት መመረጥ!
ታዲያ በወረኢሉ ጥቅምት 18 ቀን 1888 ከሀገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰበው ጦር ምክሩንና ስምሪቱን ጨርሶ ከወረኢሉ እስከወጣበት ቀን እስከ ህዳር 2 ድረስ እንግዳ ተቀባዩ የወሎ ህዝብ አብሮ ከመዝመት ባሻገር ምግብ በማሰናዳትና በማቅረብ ሀገራዊ ግዴታውን በክብር ተወጥቷል። የህዝቡ አጋርነትም በገሃድ ታይቷል። ወደ መቶ ሺህ የሚጠጋ ሰራዊት ከወረኢሉ እስከ አድዋ ድረስ በወሎ ውስጥ ሲያልፍ ደጀንነቱ አልተለየውም። ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ስላሴ ለሰንጋው፣ ለበጉ፣ ለጠጁ ልክና መጠን የሌለው ሲሉ የገለጽጹት ከህዳር 8 እስከ 14 በደሴ ለዘማቹ የተደረገውን ከፍተኛ መስተንግዶ ነበር።

ለዚህ ነው የሀገርንና የሰው ልጅን ነጻነት ለማብሰር ቀደምት አባት እናቶቻችን ሲማማሉ የወሎ ምድር የታዘበቸው። በድል ሲመለሱም የቦረቀችው። ይሄን ታሪክ እቅፍ አድርጋ ለያዘች ወሎ ነው ድምጻዊው ከአንቺ ከተው አደሩ ፣ የረሳሁት እንዳይመስልሽ አበባዬ እያለ የሚያሞካሻት። አጃይብ ነው።

ከልጅ እግሩ ሁሉ፥ የአባ ጤና ባሰ
ሌባ ሻዩን ሁሉ ወርዶ እየመለሰ

“አባ ጤና” የልጅ ኢያሱ የፈረስ ስም ነው። የአድዋው መሪ፣ የአሁኗ ኢትዮጵያ ቅርጽ ሰሪ እምዬ ምኒልክ በጠና ሲታመሙ ግንቦት 10 ቀን 1901 ዓ/ም ልጅ እያሱን አልጋወራሽ አድርገው መሾማቸውን በአዋጅ አስነገሩ። ራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደውንም እንደራሴ አድርገው ሾሟቸው። ምክንያቱም ልጅ ኢያሱ እድሜአቸው ትንሽ ነበርና ነው። ንጉስ ምኒልክ ወራሽ የሚሆን ወንድ ልጅ አልነበራቸውም። ልጅ እያሱ ከልጃቸው ከወይዘሮ ሸዋረጋ ምኒልክና ከወሎው ንጉስ ሚካኤል ጥር 27 ቀን 1889 ዓ/ም ወሎ ውስጥ መወለዳቸው ይነገራል።

ታዲያ ከሁለት ዓመት በኋላ ሚያዝያ 3 1903 ዓ/ም ራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ድንገት አረፉ። ልጅ እያሱም በ14 ዓመታቸው ለብቻቸው ስልጣኑን ያዙት። እስከ ቀይ ባህር ድረስ ታሪካዊ ድንበራችንን ማስመለስ ፍላጎት እንዳላቸውና የዳር ሀገር ህዝቦችንም ለማቀፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበራቸው ታሪካቸው ይናገራል።

የመንግስቱን ስልጣን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠሩ በኋላ ከደነገጓቸው አምስት ህጎች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ የተጠቀሰው የሌባ ሻይ ጉዳይ ነው።

ህጉም ቃል በቃል እንዲህ ተጠቅሷል።

"ሌባ ሻይ ሲጠጣ በአንዱ ቤት ገብቶ ቢተኛ ባለቤቱ የጠፋውን እቃ ከፍሎ እንደገና እሱው ዋና ሆኖ ሌባ ሻይ ያጠጣና ከሁለተኛው ሰው ቤት ሲተኛ የከፈለውን ያህል ተቀብሎ ሲሄድ፤ ደግሞ ይህ ሁለተኛ ያጠጣና ከሶስተኛው ይቀበል ነበር። በዚሁ አኳኋን እየተከታተለ ሌባ ሻይ እየጠጣ ህዝቡ ያልበላውን እዳ እየከፈለ ተቸግሮ እንግዳም እንዳይቀበል ሌባ ሻይ እፈራለሁ እያለ ከጽድቅ ተነሳስቶ ይኖር ነበር።

ስለዚህም እቃ ጠፋብኝ የሚል ሰው ሌባው እስኪያዝለት ድረስ በሰው ቤትም ቢተኛ በወንዝም ቢታጠብ፣ በራሱ ኪሳራ ሌባ ሻዩን እየጠጣ እደረሰበት ደርሶ ገንዘቡን ይፈልግ እንጂ የባለጸጋ ቤት እያየ ሌባ ሻይ እያሰተኛ ገንዘቡን መክፈሉ የማይገባ ሥርዓት ነውና ከዛሬ ጀምሮ እንዲቀር ወስኛለሁ ብለው አስታወቀ።” ይላል።
በእርግጥ የልጅ እያሱ ዘመን ብዙም ያልተባለለት ነው። በብዛት መጥፎ ገጽታው ይነገራል። በሌላ በኩል ብዙ ለሀገር የሚበጁ ተግባሮች ነበሩት የሚሉም አሉ። ለጊዜው የተነሳንበት ጉዳያችን ስላልሆነ በዚሁ እንለፈው።

ከላይ ድምጻዊው አባጤና ኢያሱን ምን ልጅ ቢሆኑ እንኳን ያንን የሌባ ሻይ አጉል ስርዓት አስወግደዋልና የወሎ ማህጸን ያፈራቸውው እንደመሆኑ መጠን እንደ አምላክ መልካሙን ስራቸውን እያየ ያነሳሳቸዋል።

እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ፣ የምወድሻዋ
እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ፡የእኔ ሰለውላዋ
አጀብ
መጣች ሰለውላዋ
አንቺሆዬው ለእኔ ብለሽ ከመጣሽ
በትዝታ አምባሰል ባቲን ቃኝተሽ።

ያቺን የወሎ ፍልቅልቅ የእኔ ሰለውላዋ እያለ ያሞጋግሳታል። ወሎ ታሪኳ ተነግሮ አያልቅም። የዘመናት ሂደቷን እንደ ታሪክ ነጋሪ አለፍ አለፍ እያለ የሚያወሳሳት ሰው የዜማ ምንጭ መሆኗንም አይቶ ሊያልፍ አልፈለገም። አራቱ ቅኝቶችን ከልቦናዋ ዲብ ያፈለቀች ውብ ደብር ናት ወሎ። ባቲና አምባሰል ብላ ደግሞ ከአፈሯ ላይ የቅኝቶቿን ስም ያተመች ሽቅርቅር እኮ ናት፣

ከንፈሯ ሲቀላ፥ እንደ ዶሮ ክንታት
ልክ እንደ ቆቅ አውራ፥ ሂጄ ልመግምጋት

ልክ የቅኝቷን ነገር እያሰበ ያ ህብር ውበቷ ከፊቱ ላይ ድቅን ይልበታል። የሚርበተበተው ውብ ከንፈሯ የዶሮ ክንታት መስሎ ሲቀላ በዓይነ ህሊናው ይሳላል። ሌላ ምንም አያስብም። ልቀኝ ቢል ቅኔ ከወሎ ወዲያ። ላዚም ቢል ዜማ ከወሎ ወዲያ። ነፍስያውን ተከትሎ እንደ ብልጡ የቆቅ አውራ ዘሎ መመግመግ ነው ያማረው። እዚህ ጋር ደረቅ ታሪክ እየነገርኋችሁ ሳይሆን ወሎን በሰው አምሳል ነው ያቀረብሁላችሁ ይለናል።

ከሰዋዊ ስሜቱና ከውበት ምርኮኛነቱ የተሰደደ ማንነት የለውማ ከያኒው። ከእነዚህ ስሜቶች ቢፋታማ ምኑም ከያኒ ሆነው? ምኑን እንስፍስፍ ልብ ታደለው? ምኑን ተመረጠው?

ባለረጅም ሲዋክ፥ ሱናዋን ያሟላች
ጡሐራ ሳዱላ፥ ተገማሽራ አለፈች

በዓይነ ህሊናችን ገምሻራ ልጃገረድ እንድንስል ያደርጋል። መስል ከሳችነቱ ከአንጀት ነው። ገላጭ (descriptive poetry) እንለው ዘንድ ያስገዳድል። ድርጊታዊም ነው። በእንቅስቃሴ ውስጥ ሆኖ ጥርሷን በረጅሙ እየፋቀች እምነቷ የሚያዛትን ቅዱስ ትዕዛዝ አሟልታ፣ በነፍስም በስጋም ውብ ሆና የምታልፍ ገምሻራ ወሎዬ ከች ትላለች።

የሼኾቹ ልጅ ናት፥ የራስ ሚካኤልዋ
እንደበተሐ ጠጅ፥ የተጣለችዋ

ወሎ የሼሆች ማጽጸን ናት ሲባል እንዲሁ ለወጉ አይደለም። እውነት አስገድዶን እንጂ። እንደ አምላክ የከበዱ ሼሆች መፍለቂያ። ስንቱን እናውሳው? የጀማ ንጉሱ መስጂድ መስራች ምሁሩ ሀጂ መሐመድ ሻፊ እንዴት ይረሳሉ? ከ500 መጻሕፍት በላይ በእጃቸው እንደጻፉ የሚነገርላቸው የገታ መስጂድ መስራች ሀጂ ቡሽራ የወሎ ምልክት አይደሉም ወይ? በወረባቦ ወረዳ የሚገኘውን የእስልምና ትምህርት ማዕከል እንደሆነ የሚነገርለትን የጎጃም መስጂድን መስራች፣ ጉልህ አሰላሳይ፣ አንባቢና ደራሲ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሼህ ጎጃም እንዴት ይዘነጋሉ? ሌላም ሌላም ብዙ።

ታዲያ እንደ በተሐ ጠጅ የተጣለችዋ ውብ ልጃገረድ የሼሆቹ ብቻ ሳትሆን የራስ ሚካኤልም ልጅ ናት። ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስም “በተሐ ጠጅ እንደ ተሞላና ሊቀደድ እንደ ቀረበ አቁማዳ፥ ሊፈነዳ እንደማይችል እንደ ወይን ጠጅ አቁማዳ፥ እነሆ፥ አንጀቴ ሆነ” እያለ የሚመሰክረው የለጋ ጠጅን ጣዕምና ጉልበት ቢገነዘብ አይደለምን?

ራስ ሜካኤል የመጀመሪያ ስማቸው መሐመድ አሊ ይባል ነበር። አባታቸው የማመዶች ስርወ መንግስት የወረሒመኖ ባላባትና ገዢ አሊ አባ ቡላ ናቸው። ህጋዊ ሚስታቸውም ንግስት ወርቂት ናቸው። ከህጋዊ ሚስታቸውም አንድ ወንድ ልጅ እሱም አመዴ አሊን ብቻ ወለዱ። በቤታቸውም ከወደ ግንደበረት የመጣች ጌይቲ ገባቤ የምትባል አገልጋይ ነበረች።

አሊ አባ ቡላ ከሚስታቸው ተጨማሪ ልጅ ባለማግኘታቸው እሱን ችግር ለመቅረፍ የወዳጃ ስነ ስርዓት ተደረገ። ንግስት ወርቂቱም በወዳጃው እንግዶችን ከመንከባከብ ይልቅ ሲተኙ አገልጋይ ጌይቲ ሌሊቱን በሙሉ ቡና ስታቀራርብ ስትካድም አደረች።
በነጋም ጊዜ ወዳጃውን የመሩት ሼህ እንዲህ ብለው ጌይቲን መረቋት ይባላል።

ልጅንስ አየን ከገረድ
ስሙንም አልነው ማመድ
የነቢይን ዲን የሚንድ።

አሊ አባ ቡላም ከአገልጋያቸው ከጌይቲ በድብቅ መሐመድ አሊን ወለዱ። የነቢይን ዲን የሚንድ ማለታቸው የንጉስ ሚካኤልን ከእስልምና ወደ ክርስትና መለወጥ በራዕያቸው አይተው ነው ይባላል።

ግንቦት 21 ቀን 1870 ዓ/ም ቦሩሜዳ ሥላሴ ንጉሰ ነገስት አጼ ዮሐንስ ጉባኤ ጠርተው የሃይማኖት ክርክር ተደርጎ ሌሎች ሃይማኖቶች በግድ የኦርቶዶክስ ክርስትናን እንዲቀበሉ አወጁ። ሰኔ 12 ቀን 1870 ኢማም መሐመድ አሊ ሃይማኖታቸውን ወደ ክርስትና ቀይረው በጎቦ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተጠመቁ። ስማቸውን ሚካኢል አሏቸው። አጼ ዮሐንስም የራስነት ማዕረግ ሰጧቸው።

ቆይቶ በልጃቸው በልጅ እያሱ ዘመንም ንጉስ ሚካኤል “ንጉሰ ወሎ ወትግሬ” የሚል ማዕረግ ተሰጣቸው። በሸዋና በወሎ ሹማምንት መካከል በተፈጠረው ሽኩቻ ልጃቸውን ልጅ እያሱን ለማገዝ ጦርነት ገጥመው በእነ ፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ (ሃብቴ አባ መላ) በሚመራው የሸዋ ጦር እስከተማረኩበት ድረስ ለወሎም ሆነ ለሀገራችን ብዙ ስራ ሰርተዋል።

ይሄንን ውለታቸውን እያነሳሳ ነው ከሼሆች እኩል ለዚያች ውብ እንስት አባት አድርጎ የሚሰጣት። ይህቺ በውብ ቀዘባ እንስት የምትጠቀሰው የሰው ልክ ራሷ ወሎ አይደለችምን እንድንል ያደርጋል።

ሀገር ሙሉ ሳቋን፥ አቃምሳው ሸጋዋ
እሷ ጋር ያወራ፥ ሐቲማ ነው ፍቅሯ
አደስ ተቀባብታ፥ የእኔ ሰለውላዋ
የተነደፈ ጥጥ፥ እንገር ነው ገላዋ
መገን አንገትዋ፥ የምወድሽዋ
አርሒቡ በይኛ፥ የእኔ ሰለውላዋ
ያቺ እንክብክብ የወሎ ሸጋ ስትስቅ የተመለከተ በፍቅሯ ይወድቅ ዘንድ ግድ አለበት ይላል አንጎራጓሪው። የወሎ ሸንተረር ባበቀለው አደስ የሚዘናፈል ገላዋን ነክራ ሰለውለው ስትል ለሚመለከት የውበት ምርኮኛ፤ “አርሒቡ” ብላ ከፍቅር ጎጆዋ ትጋብዘው ዘንድ አለመመኘት እንደምን ይቻላል? ሰው መሆንና መኖርስ ከዚህ ወዲያ ምንድን ነው? የወሎን ምድር ረግጦስ ከዚህ የውበት ምትሃት ማምለጥ ቀላል ነው ወይ የሚል ድምጸት አለው።

እንገር ወሎ እንገር ወሎ
አርሂቡ መጋሎ
ላይቆርጥልኝ መመለሴ (2)
ባቲና ከሚሴ
ይህቺን የውበትና ሰው የመሆን ድርሳንም እንገር እያለ ይጠራታል። ገጸ ውበቷን ከተነደፈ ጥጥ ጋር አወዳድሮ በእንገር ይመስላታል። ለምን የተነደፈ ጥጥ ቢሉ ኑንጉሩ ተነቅሶ ልስላሴው እንደ ደመና ገላ ነውና እንላለን። እንገር በነጭና በቢጫ መንፈስ ላይ የሚመላለስ ክቡድ የተፈጥሮ መልክ ነው። እንገር ህይወት ነው። እንገር የመጀመሪያ ቅምሻ ነው። እንገር መንገድ ከፋች ነው። እንገር ጣዕሙ ከወተቶች ሁሉ ቁንጮ ነው። አንድም እንገር “የመሆን” መጀመሪያ ነው። የሀገር፥ ሰው የመሆን፥ የአንድነት፥ የቤቴ አምሐራ እሸት፣ የወሎዬነት ውበት ነው።

ይህቺን ቀዘባ የሰው ቁመና ሰጥቶ በእንገር ቢመስላት ቃልን አከበረ እንጂ ገደፈ አንለውም። የነፍስያውን ምህዋር ተከትሎ ከእንገር ቢደርስ እልል እንላለን። ድምጻዊው በዚህ አያቆምም ባቲና ከሚሴን እያሰበ መመለሱ ሊቆርጥለት አይችልም። ወሎ የገባ ወደ ነፍስ ቡጥ ደረሰ ማለት አንችልምን? ከከፍታ አጽናፍ ላይ ቂብ አለ ብንልስ የከያኒው ግጥም አይፈቅድልንም ወይ? ታዲያ ከዚህ መመለስ እንደምን ይቻላል?

እህህ የቦርከናን፥ ውሃ ወልይ የመረቀው
እህህ አንቺን አንቺን አለኝ፥ ቀድቼ ብጠጣው
ከወሎ ኩታበር ማህጸን የሚፈልቀው ቦረከና ደሴና ኮምቦልቻን እየገረመመ ወደ ወንድሙ አዋሽ የሚተምም ወንዝ ነው። እንኳን አንቺን ይቅርና ቦርከናን ብቀምሰው ጣዕሙ አንቺን አንቺን አለኝ ይላል። ከወንዙ ጋር አንድና አቻ ናችሁ እያላት ነው። ድሮስ የወሎ ሊቅ የወሎ ወልይ የመረቀው ውኃ ጣዕሙ ከአንቺ ቢተካከል ትፈርጂብኛለሽ ወይ? እያለ የሚሞግትም ይመስላል።

ፈረንጅ ገባ ደሴ፥ ቁንጂናሽን አይቶ
ላብሽን አንቆርቁሮ፥ ሊያሰራው ነው ሽቶ
እዚህ ላይ ገጣሚው እንዲህ መቀኘቱ ውበትን ለማጉላት ብቻ አስቦ አይመስልም። ይልቅስ ታሪካዊ ዳራ ስላለው እንጂ። እንደሚታወቀው በሀገራችን በ19ኛው ሁለተኛ አጋማሽ ከተመሰረቱ ጥቂት ከተሞች ውስጥ አዲስ አበባን ጨምሮ አንደኛዋ ደሴ ናት። ስለምስረታዋ የተለያዩ መላ ምቶች ቢኖሩም በ1875 በንጉስ ሚካኤል ተመሰረተች የሚለው ሚዛን ይደፋል።

ደሴ ከተመሰረተች በኋላ የአካባቢው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጠቅሜታ በፍጥነት አደገ። አጼ ምኒልክን ጨምሮ የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ጎቢኚዎች ደሴን እየተመላለሱ ጎብኝተዋታል። አንዳንድ በዓላትንም በደሴ ማክበር እየተለመደ መጣ።

ቀስ በቀስ በርካታ ቤቶችና አብያተ ክርስቲያናት መገንባት ጀመሩ።ከአርመን ከግሪክና ከተለያዩ የአረብ ሀገራት የመጡ የዘመናዊ ህንጻ ባለሙያዎች የንጉሱ ሚካኤልን ቤተመንግስትና ሌሎችንም ግንባታዎችን መስራት ጀመሩ።

ከአዲስ አበባ አስመራ በተዘረጋው የመጀመሪያው የስልክ መስመር ከሰባቱ ጣቢያዎች ውስጥ አንደኛዋ ደሴ ነበረች። በ1905 የመጀመሪያው የውሃ ቧንቧ በደሴ ተዘረጋ።
ለዚህ ነው በላብ የተገነባ ውበትሽን ሲያይ ፈረንጅ ወደ አንቺ መትመም ጀመረ የሚለው። ከውበትሽ ላይ የሚፈሰውን ወዝም እየጨለፈ እኒያን የሚያማምሩ ግንባታዎችን መስራቱን ተያያዘው ይለናል። ውበት ከገጽ ቅብ ባሻገር በትጋትም እኮ ይገለጻል።

በጥረት ውስጥ በሚንቆረቆር ላብ የውበት መዓት አለ ብንል ማን ቃልን ገደፋችሁ ይለናል?
ኮለምላማ (4)
የራያ ከራማ
አይጠየፍ ሆኖ፥ ይታያል አንገትሽ
ለዳናው ተስዬ፥ እጅሽን ልሳምሽ

አሸዋና ድንጋይ ከቦርከናና ከገራዶ ወንዞች፥ ኖራ ደግሞ ከአምባሰል እየተጋዘ የተሰራ ውብ አዳራሻ። በ2131 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የአምባ ላይ ውበት። 45 ሜትር በ27 ሜትር ስፋት እንዳለውና አንድ አንድ ሜትር ውፍረት ባላቸው ሰባ ምሰሶዎች እንደተዋቀረ ይነገራል። በ1905 ተጀምሮ በ1907 ዓመተምህረት ተጠናቀቀ። የውጭም ዜጎች በግንባታው ላይ ተሳትፈዋል። ታላቁ የንጉስ ሚካኤል አዳራሽም “አይጠየፍ” የሚል ስም ተሰጠው። አይጠየፍ ማለት ዘር፣ ብሄር፣ ቀለም ሳይለይና የመደብ ልዩነት ሳይደረግ ጌታ ከአሽከሩ፥ እመቤት ከአገልጋይዋ፥ ጋር በአንድነት የሚስተናገዱበት አዳራሽ ማለት ነው።

ለዚያ ነው ከፍታና ዝቅታ ሳይገድበን፥ ከዳና መስጅድ ተስዬ እጅሽን ልሳምሽ፤ አንገትሽን፣ የሰውነት የሃይማኖት፣ የማንነት መልክሽን ከአይጠየፍ ሆኖ አይቼዋለሁና ይላታል። ሰውን በሰውነቱ ብቻ ከሚመለከተው የአይጠየፍ አዳራሽ የሰው ልክ አንገታም አለች እያለን ነው።

ጡቷ የራያ ቀንድ፥ ዓይኗ ኮለምላማ
በሌላ አይምጡ፥ እንጂ በይህ በይህማ
ሌላኛ ነው መልኳ፥ ጤነኛ ሚሰብር
የምሬን ወድጃት፥ ሐዋን እስከ እጇ አምባር
ሳልደርስ አላማጣ፥ ሳልረግጠው ደጅሽን
ከወንዙ ጠጥቼ ፥አወቅሁት ጣዕምሽን
መገን ራያዋ(2)
የወሎን ገመገም በሃሳብ ፈረስ ከሰገረበት በኋላ ወደ ራያ ይምዘገዘጋል። ቀንዳቸው ተጀንኖ ያቆበቆቡ የራያ በሬዎችን ምስል በንቁ አእምሮው ያመላልሰዋል። እንደ ክዋክብት የሚያበሩ ዓይኖቿንና የተወደሩ ጡቶቿን በሃሳቡ እያመነዠከ የእሷስ ውበት ሌላ ነው ማለት ያምረዋል። ከዚህ በፊት በሚያውቀው የውበት ቀመር ሊፈታው አልቻለምና። የሐዋ ውበት እንኳን በሽተኛውን ይቅርና ጤነኛውን ሳይቀር እንደ ጓያ ይሰባብራል ይላል። መሰበርን በፍቅር ስንመለከተው እንደምን ያምራል? የራያ ሜዳዎችን እየተነሰነስሁባቸው አላማጣ ካለው ደጅሽ ሳልደርስ ጠረንና ውበትሽን ይዞት ከተሰደደው ወዝሽ ቀምሼ አዎቅሁት እያለ ምስክርነቱን ይሰጣታል። መገን የቆቦ ሰው!
አይይ
አውጉሪሩ(4)
ህምረን አውጉሪሩ
የከያኒው መጻተኛ የውበት ነፍስ በራያ በኩል ወደ ዋግኸምራ ትሻገራለች። መቼስ የወሎ ልብ ሰፊ ነው። የገላዋ ስፋቱም በገመገሙ የተዘረጋ ነው። ከደሴ አላማጣ አልፎ ወደ ዋግ ሲጠጋ ህምረን አውጉሪሩ ማለት ይጀምራል። አንቺ የአገው ኮረዳ ደህና ነሽ ወይ ከቶ? እያለ እንደማትከለክለው እያወቀ ስሟን ያነሳሳል። እንዲህ ነው በውበት የሚጎተት ሰጋሪ መንፈስ አካሄዱ። አንሳውማ አስቻለ

ሐገርን በፍቅር፥ እንዲህ ሲገልጸው
በጦቢያ ታረቁ፥ ጓንጉልና አፄው

እዚህ ላይ ከያኒው ቆም ይልና ከታሪክ ሰበዝ ህያው እውነት መምዘዝ ይጀምራል። እነዚህ ስንኞች ሀገር የሚለውን የወል ስም ለማንጠሪያነት ይጠቅማሉ። ለየትኛውም ሀገር የትርክትን ክቡርነት ማንጸር የስልጣኔ ከፍታ መሆኑን ያበስራሉ። ጓንጉል በዘመኑ ኃያል ነበር። በአመዛኙ ማዕከላዊ መንግስት ደግሞ በጎንደር በከተማው ሳይቀር ጉልበት የቸገረው ተልካሻ ነበር። ከትግሬ፣ ከጎጃም፣ ከሸዋ፣ እንዲሁም ከጎንደር መሳፍንት በተሻለ ወሎዬዎች በዋናነት የጁዎች ወታደራዊ ሃቅም ነበራቸው። የማይመቻቸውን ንጉስ አንስተው የሚመቻቸውን መሾም የሚያስችል ጉልበት ነበራቸው። እሱንም በተደጋጋሚ አድርገው አሳይተዋል።

በሃይማኖት የተለዩ ቢሆኑም እንኳ ከሰለሞን ይመዘዛል የሚለውን የዘመናት ትርክት ለመናድ አልፈለጉም። ከሁሉም ነገር ይቅል ሀገር እንደምትቀድም ገብቷቸዋል። ሀገር ደግሞ ያለ ትርክት በእግሮቿ ለመቆም እንደማትችልም ተረድተዋል። ለዚያም ነው ህዝብን የሚያስማማውን የሰለሞን ዘር ትርክት እያስቀጠሉ በአንድ ሀገር ልጅነት መኖርን የመረጡት።

ታዲያ ከዚህ በላይ ምን ሰው መሆን አለ? ከዚህ በላይ ሀገርን ማስቀደም ከየት ይመጣል? ዛሬ የጠፋብንን ሀገራዊ አረዳድ ከእነሱ እንማር ዘንድ አይደለም ወይ ከያኒው ለሀገር ሲሉ ግን ታረ’ቁ የሚለን?

ለሀገር ሲባል ጉልበትና ስልጣን መረን አይለቅም። ለሀገር ሲባል ስርዓትና ትርክት አይደመሰስም። ለሀገር ፍቅር ሲባል የግል ዝናና ሃብት ልኩን አያልፍም።

ዋግም ሹም አይጣ፥ የመክሊቱ ሞገስ
ዳና ኸሚስ ታድሮ፥ ሮሐ ይቀደስ

ዋግ ሹም የማዕረግ ስም ነው። በዋናነት ለአገው ተወላጆች ማለትም ለዋግና ለላስታ የመሳፍንት ዝርያዎች ብቻ ይሰጠ የነበረ ማዕረግ ነው። አንዳንዴ ግን በማዕከላዊ መንግስት ጫና የዋግና የላስታ ተወላጅ ላልሆኑትም ይሰጥ ነበር። የትግራዩን ዋግሹ ሰባጋዲስን፣ የሸዋውን ዋግሹም አባተ ቧ ያለውን እንዲሁም የወሎውን ዋግሹም ገብረህይወትን መጥቀስ ይቻላል። እኒህ ከላስታና ከዋግ ውጪ ለሆኑት የሚሰጠውን ማዕረግ ግን ህዝቡ አይቀበለውም ነበር።

በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው ከሆነ ዋግሹምነት የተጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው ይባላል። የዳዊት ልጅ፥ የይትረሃም ልጅ አዲል የተባለው የአገዎችች መሪ አገው የሚል ስያሚ ካገኘ በኋላ ነው የሚሉ አሉ።

በሌላ በኩል በ14ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጅር ወሰን በሚባለው የዋግ ተወላጅ ባላባት ዋግሹምነት እንደተጀመረ ይገልጻሉ። የሆነው ሆኖ ዋግሹምነት ከተጀመረበት አንስቶ ከ45 በላይ ቁጥር ያላቸው መሳፍንት በዋግሹነት ማዕረግ እንደተሾሙ ይነገራል።

ለአብነት ያህልም ዋግሹ ጅር ወሰን ፣ ዋግሹም ርቱዕ አምላክ፣ ዋግሹም ጊጋር፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ፣ ዋግሹም ጎበዜ፣ ዋግሹም ከበደ ተፈሪ እያልን መዘርዘር እንችላለን።

ዛሬ የወሎ አካል የሆነው ዋግኸምራም የዋግነቱን መክሊት ሳያጣ በሞገሱ ይቀጥል እያለን ነው። የሁለቱን የወሎ ክፍሎች አንድነት ለማሳየትም በዳና መስጂድ ታድሮ በሮሐ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ይቀደስ ይላል።

ዳና መስጂድ በሰሜኑ የወሎ ክፍል በሐብሩ አካባቢ ይገኛል። መስራቹም ስመ ጥሩ የእስልምና አስተምህሮ ሊቅ ሼህ አህመድ አደም ናቸው። ምዕመኑን ለሼሁ ያለውን ፍቅር ሲገልጽ “ጌታው ሼህዬ” ይላቸዋል። ሼህ አህመድም በወሎ ከነበሩ ስመጥር ኡላማዎች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ የእስልምና አስተምህሮን ለማስፋፋት ጉልህ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ይህ የሱፊ እስልምና የትምህርት ማዕከል የሆነው ዳና መስጂድ እንደ ሼህ ዒሳ ሃምዛ፣ የአብሬቱ ሼህ ቡሽራ፥ የወለኔው ሼህ ዑመርና ሌሎችንም ሊቃውንት አፍልቋል።

በሌላ በኩል ሮሐ ወይም ላሊበላ ከአስራ አንዱ ከዛጉዌ ነገስታት ውስጥ አንዱ በሆኑት በንጉስ ላሊበላ (ቅዱስ) (1157-1197) አማካኝነት ከአንድ ወጥ ዓለት የተፈለፈሉ የ11 አብያተ ክርስቲያናት መገኛ ነው።

በአስደናቂነታቸው ዓለም የመሰከረላቸውን ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት ገንብቶ ለመጨረስ 23 ዓመታትን እንደፈጀባቸው ገድላቸው ይናገራል። ለግንባታ የሚሆነውን መሬትም “ቀይት” ከምትባል ባላባት በወርቅ ገዝተው እንደሆነም ያትታል።

አብያተ ክርስቲያናቱ በአስደናቂነታቸው ይታወቃሉ። ቅዱስ ላሊበላን ጎብኝተው ከጻፉ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ጸሐፍት እንደምሳሌ ለመጥቀስ ያህል በ1512 ቅዱስ ላሊበላን በመጎብኘት የመጀመሪያው አውሮፓዊ ነው የሚባለው የፖርቱጋል ተወላጅ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ እንዲህ ብሏል።

“It wearied me to write more of these works. because it seems to me that they will not believe me if I write more and because as to what I have already written the truth, the may accuse me of untruth. therefore, I swear by God in whose power that I am all that I have written is the truth... the like of which and so many, cannot as it appear to me, be found in the world. *(F Alvearies the Prester John of indies Vol 1 page 315)
ስማቸው ያልተጠቀሰ ኢትዮጲያዊ ባለቅኔም ስለ ላሊበላ እንዲህ ተቀኝተዋል።

ሞት ሕንጻ ላሊበላ ኩለሄ እንግዳ
ሞትና ህንጻ ላሊበላ ሁልጊዜ አዲስ ናቸው። ማለት ነው።

ታዲያ አስቻለው በዘመናችን ወሎን በገመደበት ስንኞቹ ከዳና መስጂድ አድረን ከሮሐ ብናስቀድስ ሁሉም የእኛ ነውና ይበል ያሰኛል እንጂ መቼም አያስነቅፍ እያለን ነው።
በዚያውም የወሎን የሃይማኖት ህብረት ይፈክራል። እስልምናና ክርስትና አንዱ አንዱን ሳይገፋው በአቻነት እኮ እየሰሙና እየተሰሙ የሚገኙበት የስልጡን ህዝቦች ሀገር ነው እያለን ነው። ይበል እንጂ ምን ይባላል?

ላኮመልዛም ብሔድ፥ አልደርስም ሰቆጣ
የራስ ኃይሉን አንገት፥ ከሮም ሳላመጣ

ሮሐም አስቀደሰን ዳናም ተለማምነን፣ በቱፍታውና በውዳጃውም አደርን ከላኮመንዛ (ደሴ) አልፈን፥ የአላማጣዋን ባለ ጉብጉባ ኮረዳ ተሳልመን ወደ ሰቆጣ ለመሄድ ግን አንድ የታሪክ አደራ አለብን ይላል። እኔ እያለ መቀኘቱ በእሱ ውስጥ እኛም እንዳለን ቢያምን አይደለምን? እሱም የዋግሹም ከበደ ልጅ የሆኑትን የራስ ኃይሉ ከበደን አንገት ከሮም ማምጣት አለብኝ እያለን ነው። ለመሆኑ አንገታቸው ከሮም የደረሰው ራስ ኃይሉ ማናቸው?
ደጃዝማች (በኋላ ሌተናል ጄኔራል) ኃይሉ ከበደ የዋግሹም ከበደ ተፈሪና የየጁ መስፍን የራስ አሊጋዝ የልጅ ልጅ የወይዘሮ ኂሩት ንጉስ ልጅ ናቸው። ፋሽስት ጣሊያን ሀገራችንን ለሁለተኛ ጊዜ በወረረ ወቅት የዋግን ህዝብ አስተባብረው ከእነ ራስ ካሳ ኃይሉ ጋር ተባብረው ወራሪውን ያስጨነቁ አርበኛ ናቸው።

በአምባላጌ፣ በአክሱም፣ በተንቤን እንዲህም በማይጨው ተዋግተዋል። ንጉሰ ነገስቱ ማይጨው ላይ ተሸንፈው የኢትዮጵያ ጦር ሲፈታ በዋግ ገጠር ገብተው አርበኝነታቸውን ጀመሩ። በሲልዳ፣ በአምደወርቅ፣ እንዲሁም ድግርሻና ሌሎችም ቦታዎች ላይ ጣሊያንንና ባንዳን ረትተዋል። የመርዝ ጋዙንና የአውሮፕላን ድብደባውን ተቋቁመው ተዋድቀዋል። በመጨረሻም በ1930 ዓ/ም ከሰቆጣ 10 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ወለህ ሜዳ ላይ በተደረገው ከባድ ጦርነት ቆስለው ወዲያው ህይወታቸው አልፏል። በዚህ ጦርነት ታላላቅ የጦር መኮንኖና አርበኞች ለእናት ሀገር ክብር ወድቀዋል።

ራስ ኃይሉ በጣሊያኖች ዘንድ ይፈ’ሩ ስለነበር መሞታቸው ሲሰማ ጣሊያኖች አስከሬናቸውን ወደ ሰቆጣ ወሰዱት። አንገታቸውን ቆርጠውም በእንጨት ላይ ሰቀሉት። ለሶስት ቀንም ሰቆጣና ኮረም ላይ አንጠልጥለው አቆዩት። በእናት ምድራቸው እንዳይቀበሩ አስከሬናቸውን ለአውሬና ለአሞራ ቀለብ ይሁን ብለው ክቡሩን የአርበኛ ገላ ወደ ገደል ጣሉት። በመጨረሻም የቆረጡትን አንገቱን ወደ ሮም ላኩት። ለዚህ ተጋድሏቸውም ከተገጠሙላቸው ግጥሞች ውስጥ ጥቂቱን ልጥቀስ።

“አባ መረብ ኃይሉ፥ ኃይሉ አባ ይባስ
አንገቱን የሰጠው፥ እንደ ዮሐንስ
ሥጋ አማረኝ አለች፥ የአባ መረብ ሚስቱ
ወለህ አትሄድም ወይ፥ ከታረደበቱ?
አንቺ ወለህ ማርያም፥ ሲቃጠል ቤትሽ
ዓርብ ተሰቀለ፥ ኃይሉ እንደ ልጅሽ
እሺ ላለው ስጠው፥ እምቢ ላለው ንሳ
አባ መረብ ኃይሉ፥ የተከዜው ነበር፥ የወለሁ አንበሳ”።
ሙዚቀኛው ይሄንን መስዋዕትነት ነው ሊያስታውሰን የፈለገው። የአባ መረብ ኃይሉ አንገት እንዲሁ አንገት ብቻ አይደለም። የማንነታችን ውል ነው እንጂ። የትናንትናችን መልክ፣ የአባቶቻችን ተጋድሎ፣ የተከፈለውን ዋጋ ማንጸሪያም ነው። አንገቱ፣ እምነቱ፣ ጀግንነቱ፣ ሰውነቱ እስካልመጣ ድረስ ወደዚያች ቅዱስ ደብር አልሄድም እያለ ነው። አምባና ገመገሙን ሲያይ ጆቢራ የመነተፈው የአባ መረብ ስጋ ቢሸተው አይደለምን? የተንዠቀዠቀው ደም ሲረግጠው ቢያሳቅቀው አይደለምን? አሁንም እናት ምድሩ የልጇን አንገት መቀበል፣ ማቀፍ፣ መሳም ትፈልጋለች እኮ።

አውጉሪሩ
ህምረን አውጉሪሩ
መገን ቅኔ፥ መገን ዜማ
ጃኖና መንዙማ
በመጨረሻም ታሪክ ነገራና ኩርኮራውን ሲጨርስ አበይት ጉዳዮች አንስቶ ነው። መገን ቅኔ ብሎ ሰፊ ጉዳይ አንስቶ ያቀብለናል። በቅኔ ይሸኘናል። ለመሆኑ ለወሎ ዘፈን ስለቅኔ ማንሳት ምን ይሉታል? ለምንስ አነሳው ብሎ መጠየቅ የአባት ነው። ምክንያቱም ገጣሚ የቃላትን ረቂቅ ጉልበት ጠንቅቆ ያውቃል። እውቁ አሜሪዊ ገጣሚና ድንቅ መምህር ሪቻርድ ሁጎ (Richard Hugo) Triggering town የሚታትን የነፍስ ቡጥ አይስትምና። ለወሎም ቅኔን ሸልሞት እብስ ይላል።

በእርግጥ ቅኔ በኑሮ ይገለጣል ማለት መብታችን ነው። ሚስጥር ባያደላድም ወሎዬነት ቅኔ ነው። እንዲያው ለመሆኑ ከቅኔ ጋር በተያያዘ ስለ ወሎ ምን ይባላል?
ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሺፈራው ስለ ቅኔ እንዲህ ይሉናል። ቅኔ ማለት ቀነየ፡ ገዛ ከሚለው ግስ የተገኘ ጥሬ ዘር ነው። ወይም ቀነየ ፣ ገዛ የሚለውን አንቀጽ ያስገኘ ጥሬ ዘር ነው። ፍቺውም መገዛት ማለት ነው ይላሉ።

ስለቅኔ ሲነሳ የመጀመሪያው ጥያቄ ቅኔን በሀገራችን ማን ጀመረው የሚል ነው። ስለጀማሪው የተለያዩ ታሪኮች አሉ። አንደኛው ቅዱስ ያሬድ ጀመረው ይላል። ሌላው ዮሐንስ ዘገብሎን (ገብላዊ) የተባለ የዋድላ ተወላጅ ነው ይላል። እንዲሁም ቅኔን የጀመረው ተዋነይ ነው የሚሉ አሉ። ደቀ እስጢፋ የሚባል የጎጃም ተወላጅ ነው የሚሉም አሉ።

ለዚህም ነው የዋድላ አገባብ የጎጃም አገባብ፣ የዋድላ ቅኔ የጎጃም ቅኔ እየተባለ እስካሁን የዘለቀው። ድድቅ ወልደማርያምና ሌሎች ስድስት ድድቅ በመባል የሚጠሩ ሊቃውንት በዳውንት የጨረቃ በምትባል ቦታ እየተቀባበሉ ቅኔን አስተምረዋልም አስቀጥለዋልም ይባላል ። ድድቅ ማለት ጀግና ማለት ነው። እውነትም ጀግና። በቅኔ የመዋደቅ ልበ ሙሉነት።

ለዚህ ነው ከላይ መገን ቅኔ ሲል መቀኘቱ።
የዜማውን ጉዳይም ከላይ እንዳየነው ነው። ወሎ ለኢትዮጵያ የዜማ ቅኝቶች ማህጸን ናት። ስለዚህ ወሎ የቅኔም የዜማም መፍለቂያ ናት ይለናል።

የእነ ጃኖ መንዙማም ከዜማና ከግጥም ወገን ነውና ልብ ብለን እናየው ዘንድ በአንክሮ ነግሮናል።

ሲጠቀለል
አስቻለው እንገር ወሎ ሲል ለአድማጭ ያቀረበው ሙዚቃ ከዚህ በላይ መታየት ይችላል ብዬ አምናለሁ። ግጥሞቹ ታሪክን፣ ባህልን፣ ማንነትን፣ ከአሁናዊ መልክና ውበት ጋር የሚፈክሩ ናቸው። በግልብ የምንመለከተውን ጉዳይ አጽንኦት ሰጥተን እናየው ዘንድ እንዲህ ነው እያለ ይነግረናል። ከጥልቅ ንባብ የተገኙ ስንኞቹ ለመረዳት በደንብ መመርመርን የሚጠይቁ ናቸው።

ግጥም ጠጠር ሲል አድማጪን ያርቃል የሚለውን ብሂል የሻረ ሙዚቃም ነው ለማለት ያስደፍራል። በሀገራችን የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የሆነ መልክ ይዞ እንደመጣ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በጽኑ ያምናል።

ወደፊትም መሰል ስራዎችን ያቀርብለን ዘንድ እየተመኘሁ በዚሁ ልሰናበት።

ከያኒዎቻችንን ያብዛልን።

Aschalew Fetene Ardi

የድምፃዊት ኢየሩሳሌም አስፋው(ጄሪ) 3ኛ አልበም ለአድማጭ ቀረበ።     የ1990 ዎቹ ድምፃውያን ተብለው ከሚጠቀሱት መሃል አንዷ የሆነችውና "ሃሎ አዲስ አበባ" በተሰኘው የበኩር አልበሟ ከህ...
16/02/2024

የድምፃዊት ኢየሩሳሌም አስፋው(ጄሪ) 3ኛ አልበም ለአድማጭ ቀረበ።

የ1990 ዎቹ ድምፃውያን ተብለው ከሚጠቀሱት መሃል አንዷ የሆነችውና "ሃሎ አዲስ አበባ" በተሰኘው የበኩር አልበሟ ከህዝብ ጋር የተዋወቀችው ድምፃዊት ኢየሩሳሌም አስፋው(ጄሪ) "የማነህ?" የተሰኘውን 3ኛ አልበሟን ወደ አድማጭ እንደቀረበ ይፋ አድርጋለች።አልበሙ ለአድማጭ መቅረቡ ይፋ ሊሆን የነበረው ከሁለት ወር በፊት ቢሆንም በገና በዓል እንዲሁም በተወዳጁ የመዝናኛ ዝግጅት አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ ህልፈት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ ነበር።

ሰርቶ ለማጠናቀቅ 10 አመታትን የወሰደው ይሄው "የማነህ?" የተሰኘዉ የሙዚቃ አልበም 16 ሙዚቃዎችን ያካተተ ሲሆን ብስራት ጋረደው፣ ምስክር አወል፣ ምዕራፍ አሰፋ፣ ቢኒያምር አምዱ፣ አብርሃም ኪዳኔ እንዲሁም ሌሎች አንጋፋ እና ወጣት የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን እስካሁን ሁለት የሙዚቃ ቪዲዮዎች ይፋ ተደርገዋል።አልበሙ ይፋ የሆነው በአውታር መተግበሪያ በኩል ነው።በተለይም ድምፃዊቷን በስፋት ከአድማጩ ጋር ያስተዋወቃት "ሃሎ አዲስ አበባ" የተሰኘው ዜማ በአዲስ መልክ ተሰርቶ በአልበሙ ውስጥ መካተቱን ለማወቅ ተችሏል።አልበሙን በሲዲ ወደህዝብ የማሰራጨትና የአልበም ምርቃት ስነስርዓት ለማሰናዳት ዕቅድ ተይዟል።

ድምፃዊቷ አልበሙ 10 አመታትን የወሰደው ዜማና ግጥም በመሰብሰብና ከስቱዲዮ ጋር በተያያዙ ሂደቶች መሆኑን ገልጻ የአድማጩን ፍላጎት ለማርካት የተሰራ ስራ ነው ስለሆነም ውጤቱ የባለሙያዎቹና አስተያየቱን በመስጠት እዚህ ያደረሰኝ አድማጭ ነው ስትል ገልጻለች።

ደግ ሠው እና ጎበዝ ከያኒ አይጥፋ/ አትጥፋ   | እስቲ በህይወታችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ያያችሁትን የጉሙዝ ሠው አስታውሱ።ስሙ ማ ይባላል? (ከታች ብትጽፋት ደስ ይለኛል)።የእኔው ግራ...
15/02/2024

ደግ ሠው እና ጎበዝ ከያኒ አይጥፋ/ አትጥፋ

| እስቲ በህይወታችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ያያችሁትን የጉሙዝ ሠው አስታውሱ።ስሙ ማ ይባላል? (ከታች ብትጽፋት ደስ ይለኛል)።የእኔው ግራኝ ጉደታ ይባላል።ያው እንደምታዩት ከስሙ ጉሙዝ መሆኑ ማወቅ የሚቻል አይደለም።ለነገሩ ይሄ የጉሙዝኛ ስም/ቃል ነው ብዬ የማስታውሰው አንድም ነገር ጭንቅላቴ ውስጥ የለም፤ይህን ስል ከእፍረት ጋ ነው፡፡

ጋሽ ግራኝን ያገኘሁት የድሮ ቢሮዬ (ቦርዷ ዘንድ) የፓርቲ ጉዳይ ኖሮት ነው፡፡ይህ የሆነው ስራ በጀመርኩ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ነበር።ታዲያ ይኼ ሠውዬ እንደ አንዳንዶቻችን የእስር ቤት ደምበኛ ነው ነበር ማለት ይቻላል።እንደ ጫማ ክር ሲፈቱት ሲያስሩት የኖረ....:)ለመጀመሪያ ጊዜ ሳገኘው የነገረኝ ይህንኑ ነው፤ያው እንደለመደው ልቤን ሀዘን ወረረው:: በነገራችን ላይ ሰውየው አማርኛውን ይራቀቅበታል ነው የሚባለው::

በጣም ደናቂው ነገር ግን እስከ አሁን ያወራሁት አይደለም።ዝንተዐለም በፖለቲካ ሲንገላታ እና ሲታሠር የምናውቀው ስጋ ለባሽ ሠው(ለሁለቱም ጾታ ያገለግላል) ነው አይደል) በእነ ጋሽ ጉደታ ጉዳይ ግን እነሱ በለውጥ የመጀመሪያ ቀናት ተፈተው፣ ሠው ሰራሽ ህልውና ባለው ፓርቲያቸው ላይ በፍ/ቤት የተሸጎረው የብረት መወርወሪያ ተከርችሞ ቀረ።ድርጅቱ የጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ጉ.ህ.ዴ.ን) በወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ እንዲዘጋ ተወስኖበት ነበር፡፡

ፓርቲ ሲማር(ምህረት ሲደረግለት) ታውቃላችሁ? በህግም በልምድም የሚባል ነገር የለም።እና ባይኖርሳ ያለጥፋቱ ከስሞ ሊቀር ብዬ ለብርሀኑ ጸጋዬ ስልክ መታሁ፤ያኔ የፍትህ ሚኒስትሩ እሱ ነበር።ቀጥታ ወደ ጥያቄዬ- እባክህ ይህን ፓርቲ በምታረገው ነገር አድርገህ በፕሬዝዳንቷ አስምረው ።ከነገሩ ሁሉ ብርሀኑ የመሠለውን ነገር እዳር ለማድረስ እጅግ ቀና፣ ተባባሪ እና ደፋር ሠው ነው።ከፍትህ መ/ቤቶች መንደር ያን አይነት ሠው ያለሱም አላየሁ።ካልመሠለው ደሞ እሱን ለማሳመን መሞከር ማገዶ ጨራሽ ተግባር ይባላል።እግዜር ይስጠው በቀናት ውስጥ ለጉ.ህ.ዴ.ን ይቅርታ እንደተደረገ የሚገልጽ ደብዳቤ ደረሰን፤ ፓርቲውም እንደገና ህልው ሆነ።

ለማስታወስ ያህል ከአንድም ሁለት የይቅርታ ደብዳቤ አለኝ ያለኝ ሰው ነኝበሌላ አባባል ሁለቴ ለወንጀሌ ይቅርታ ጠይቔአለሁ። ሰውየው(የሴትዮዋ ተቃራኒ ነው መሠል) ዝም ብለው ለፉ አይደል?!ጋሽ ግርማ ወ/ጊዮርጊስን ማለቴ ነው፤ መፈረም ራሱ አሠልቺ ነገር ነው።ነፍስ ይማር!!

ለማንኛውም የአቶ ግራኝ እና የጉ.ህ.ዴ.ን ታሪክ ማብቂያ የለውም።የምርጫውም ህግ ወጣና ቦርዱም ተሟላና ፓርቲዎች ሠነድ አሟሉ ፣ፊርማ ጨምሩ ፣ጉባዔ አርጉ ወዘተ መባል መጣ።ደብዳቤ በደብዳቤ ላይ ፣እንደገና ሌላ ደብዳቤ ጋሽ፤ ግራኝ እና ፓርቲው ግን ምንም አልመለሱም።ጉ.ህ.ዴ.ን እንደገና ተጠረቀመች።

ይህ ከሆነ ከአንድ ዐመት በኋላ በኋላ ደርጉ(ስሙ ሁሌ ይገርመኛል) የሚባል የዛው ፓርቲ ወጣት ደውሎ ሁሉን ነገር ነገረኝ-አረዳኝ ብል ይሻላል።ለካ የክልሉ መንግስት ለወሬ ነገሬ ሳያስቀር ሠብስቦ እስር ቤት አጉሮአቸዋል።የቤኒሻንጉል ክልላዊ መንግስት በዚህ በዚህ በጣም ደፋር መንግስት ነው፡፡አመንቴ የሚባለውን የቦሮ(ቦሮ የሺናሻ ማህበረሰብ ሌላ ስም ነው) ፓርቲ መሪ፣ መሳሪያ አንስቷል በሚል ጀምሮ ፓርቲውን ከመቀላቀሉ በፊት ዐ/ህግ ሆኖ ሲሰራ ሞስሷል በሚል ለወራት ያከረመው ነገር የስንት ባለስልጣን ፊት አሳይቶኛል፡፡ተመስገን ነው መቼስ፤ዛሬ አመንቴ የክልሉ የኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ነው፡፡የነጋሽ ጉደታ ነገር ግን በደብዳቤም በደጅ ጥናትም አልተሳካልኝም ነበር፡፡
መቼስ በክልሉ የታየው መከራ ከእኔ የመዘከር ችሎታ በላይ ነው፡፡ጉድ እኮ ነው-የግድቡ እናት ወረዳ የሆነችው ጉባ እራሷ ለስንት ዐመት ደም ፈሰሰባት፡፡በስተመጨረሻ ከፍያለው አምዴ የሚባል እውነተኛ ወታደር (ጄኔራል ነው) የቤ/ሻንጉልን የመከራ ቀናት አሳጠረላት፡፡እውነቴን ነው የምላችሁ የዚህን ሰው ስራ ፈልፍላችሁ ብታውቁ ትህትና እና ተስፋ ይቀርቡዋችኋል፡፡(It is just recommendation)እኔ የማውቀውን ያህል በአጭሩ ልንግራችሁ፡፡ካጎደልኩ ካሳሳትኩ ማነው ማነች ሳይል ሁሌም እውነቱን የሚናገረው የቦሮ ፓርቲ ልጅ ዮሀንስ ተሰማ ያርመኛል፡፡
https://www.facebook.com/profile.php?id=100018155504434&mibextid=JRoKGi

ወንድሜ ከፍያለው (ከጄኔራልነት ወንድምነት ይበልጣል ብዬ ነው) የኮማንድ ፖስቱ ሀላፊ ሆኖ እንደተመደበ የክልሉን መንግስት ጎትጉቶ ጋሽ ጉደታ እና ሌሎች በርካታ እስረኞችን አስፈታ፡፡ከዛ እንግዲህ አብረው ያልዋሉበት ቀበሌ ያልሰበሰቡት ስብሰባ የለም፡፡ የተስፋ ምክንያት ሁኚ ሲላት መሰለኝ፣ ቤኒሻንጉል የ Chronic Violence ( የማይድን አመጻ) ተምሳሌት እንዳልተባለች ዛሬ ጉምዝ ከጫካ ወደ ሰው መኖሪያ ሠፈሩ ተመልሷል(ያልታጠቁትን ማለቴ ነው)፡፡ታጣቂዎቹም ካምፕ ገቡ፤ በአሶሳ ዞንም ለቤ.ህ.ነ.ን እና ለበርታ ማህበረሰብ ተመሳሳዩ ተደረገ፡፡ አማራ ፣ሺናሻ፣አገው፣ከምባታ እና የሌሎችም ማሀህበረሰቦች አባላት በመሆናቸው በጉሙዝ ታጣቂዎች ተፈናቅለው ቻግኒ፣ ቡለን፣ ድባጤ ፣ፓዊ እና ግልገል በለስ የተባሉ የወረዳ ከተሞች ላይ ተጠልለው ከነበሩት ብዙዎቹ ወደመንደራቸው ተመልሰዋል፡፡የህዝብ ትራንስፖርትም ከተቋረጠ በስንት አመቱ ጀመረ፡፡
ጋሽ ከፍያለው ንግግር አዋቂ የሚሉት አይነት አይደለም፡፡ፊትለፊት ተገናኝተን ሰለማናውቅ አጭር ይሁን ረጅም አላውቅም፡፡በስልክ ግን ለሰዓታት አውርተናል፤አዳምጬዋለሁ ብል ይቀላል፡፡እኔ እራሴን እንደ ታጋሽ አልቆጥርም፡፡በተለይ BS( Bullsh*ting)ከቁጥጥሬ ውጭ ያስወጣኛል፤እንዲያ ያለውን ወሬ አሳምሬ አቋርጣለሁ፡፡ገራገሩ እና እውነተኛውን ጋሽ ከፈፍያለውን ግን ያለመታከት አዳምደጫለሁ፡፡የሚያወራው ነገር ሁሌም ይነሽጠኛል፤ያስተምረኛል(ውትድርና፣ ቅንነት፣ ግጭት አፈታት……..ወዘተ) ፡፡ከ30 ደቂቃ በታች አውርተን አናውቅም፤ሊያውም በቀጥታ ስልክ፡፡ለምን ብለን ዋትስአፕ) ስለሁሉም አይነት ፖለቲከኞች እውነት እውነቱን ይናገራል፡፡ሁለታችንም ዮሀንስን እና በቤኒሻንጉል የተሻለ ቀን ለማየት ደፋ ቀን የሚሉትን ሰዎች እናደንቃለን፡፡በ 2013 መጀመሪያ አካባቢ ዮሀንስን እዚሁ አዲስ አበባ፣ የቤኒሻንጉል ፖሊሶች ሲያሳድዱት እንዳያስሩት በመኪናዬ ሸሽጌ ወደሚሄድበት ይዤው ሄጄ አውቃለሁ፡፡ጋሽ ከፍያለው ግን ከሞት ሳይከለልለው አይቀርም፡፡
የዮሀነስ እና መሰሎቹን ታሪክ ለሌላ ቀን ላቆየው እና ዛሬ ወደ ቤኒሻንጉል ዥንጉርጉር ትዝታዎቼ ወዳመጣኝ ሰው ልምጣ- አስቻለው ፈጠነ፡፡በቃላት እና ዜማ ስለሚጠበብ ሰው፣ ደስታን ብቻ ሳይሆን የጋራ እንጉርጉሮን(collective lamentation) ምን የመሰለ ውበት አድርጎ ስላቀረበ ሰው መናገርን የመሰለ አወላካፊ ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡

የአሰቻለውን ዘፈኖች በጆሮዬ ሳሆን በሆዴ የምሰማው ነው የሚመስለኝ.፤ ደግሜ ደግሜ ያልሰማሁት ዘፈኑ ባይኖርም ከመጠሪያ ስሙ ግፋ ሲልም ታጣቂዎቹ ስለፈጠሩት ግጭት ከሚወራው በስተቀር ትንሽ በሚታወቅለት የጉሙዝን ቋንቋ ከአገውኛ እና አማርኛ ጋር ቀላቅሎ ስለ አዲስ አበባ እንደዘፈነበት «ዊያ ዊያ ´ የወደድኩት የለም፡፡

https://video.search.yahoo.com/search/video?fr=mcafee&p=aschalew&type=E210US91105G0 =view&id=14&vid=59e6e8e0b1c42a6b50fe9ee197fcc29b
በዘፈኑ ውስጥ አፍቃሪው ጽጌረዳን ልውሰድሽ ኳስ ሜዳ ይላታል፡፡ የሼህ ሆጀሌ ጥንታዊ ቤተመንግስት ለሚገኝበት ጉለሌ ቅርብ ወደ ሆነው ሜዳ መሰለኝ፡፡ወይም እኔ ቅርሱ የሚገኝበትን ስላለበት ሁኔታ ለመናገር ፈለጌ አጠጋጋሁት፡፡ይሄ ማህል እና ዳር አገናኝ የሆነን ቅርስ አርጅቶ የንጉስ ሆጀሌ ቤተሰቦች ብቻ ሊያስጠግኑት ከላይ ታች ሲሉ በማየቴ በጣም አዝኛለሁ ፡፡
አስቻለው ከአመታት በፊት ስለሰራው የጉምዝኛ ስራ ቪዲዮ ግን በስድ ንባብ ከምፅፍ በተገጣጠሙ ቃላት አስቻለውን ልጠይቀው ወደድኩ፤

https://youtu.be/5PU_0Alq2mg?si=ARcGx8KrfbiWtZ_n

እስቲ ንገረኝ አስቻለ
እንዴት ወዴት ሆነኸው ነው
ወዝህ ወዛቸውን የነሳው፡፡?

ከውስጥ ያወጡትን ቱም ቱምታ
የጅማታቸውን ትርትርታ
የረገጣቸውን ሆታ
የዜማቸውን ፈለግ
የኑሯቸውን ቆንጅዬ ወግ
እንዴት ብለህ ተጣባኸው፡፡?

በየት በኩል እንዴት ሆነህ
ምኑን ቀምሰህ ምኑን ምሠህ
ያንን ግርሻን ተጣላኸው፡፡?

እስኪ አሳየኝ
እንዴት አርገህ
ወንድምህን ለብሰህ ሆንከው!?

ጉባ፣ማንዱራ፣ፓዌ፣ድባጤ፣አሶሳ፣ካማሺ፣ቻግኒ፣ቡለን ኮንሰርትህን አቅርበህ እዛው መገኘት -ለራሴ የተመኘሁት ምኞት!!

ብርቱኳን ሚደቅሳ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሙዚቃዊያን Muzikawiyan posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሙዚቃዊያን Muzikawiyan:

Videos

Share

Category


Other Record Labels in Addis Ababa

Show All