12/12/2024
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ላይ ደረሱ
የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መሪዎች በሁለቱ ሀገራት መካከል
ለአንድ ዓመት ያህል መካረር ውስጥ የቆየውን አለመግባባት ለማቆም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ተናግረዋል።
ኤርዶጋን ማምሻውን በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በአንካራ ለሰዓታት የቆየ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ተከትሎ፤
በሀገራቸው አደራዳሪነት "ከ8 ወራት በፊት የተጀመረ የአንካራ ሂደት ዛሬ
ትላንት አመሻሽ ላይ ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሷል" ብለዋል።
"አንዳንድ ቅሬታዎችን እና አለመግባባቶችን በጋራ በመፍታት
በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ሰላም እና ትብብር ላይ የተመሰረተ
አዲስ ጅምር ለመጀመር የመጀመሪያውን እርምጃ ወስደናል ሲሉም ተናግረዋል።
"የሁለቱን ሀገራት ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነትን ለማረጋገጥ ያለመ
በመርህ ላይ የተመሰረተ ስምምነት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል።
ኢትዮጽያ እና ሶማሊያ የተስማሙበት የጋራ የስምምነት ሰነድ መዘጋጀቱን የገለጹት ኤርዶጋን፤
ይህ የጋራ ሰነድ የሚያተኩረው የበፊቱ ላይ ሳይሆን
በቀጣይ ሁለቱ ወዳጃዊ አገሮች በሚገነቡት መርሆች ላይ ነው ብለዋል።
ትላንት ማምሻውን የተደረሰው የጋራ ስምምነት በመጪዎቹ ጊዜያት በመከባበር ላይ የተመሰረተ ትብብር፣
ኢኮኖሚያዊ ልማት እና ብልፅግናን ለማስፈን
ጠንካራ መሰረት ይጥላል ብዬ አምናለሁ ሲሉም አክለዋል።
በመጨረሻም "ውድ ወንድሞቼ በታላቅ ቁርጠኝነት ለዚህ ታሪካዊ ስምምነት ላይ በመድረሳችሁ
ከልብ አመሰግናቸዋለሁ ሲሉ ለሁለቱ ሀገራት መሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጋራ መግለጫው ላይ፤
የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ከህልውናዋ ጋር የተያያዘ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤
የዛሬው ውይይት ወደ ጓደኝነት መልሶናል ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም የኢትዮጵያ የሶማሊያ ሕዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና
በደም የተሳሰሩ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ለጋራ ሰላምና ልማት
ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አስታውቀዋል፡፡
የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በበኩላቸው፤
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት መካከል የነበረውን ልዩነት ያስቆመ ነው" ብለዋል።
መንግሥታቸውና ሕዝባቸው “ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ጋር ለመስራት
ከመቼም ግዜ በበለጠ አሁን ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ጦር በሶማልያ ለዓመታት የከፈለውን መስዋዕትነት ያነሱት ፕሬዝደንቱ፤
ሱማሊያ የኢትዮጵያ "እውነተኛ ጓደኛ" ሆና ትቀጥላለች ሲሉም አስታውቀዋል።
ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ ለወታደራዊ እና ለባሕር ንግድ አገልግሎት የሚውል
የባህር በር ማግኘት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊላንድ ጋር ስለመፈራረሟ
ታሕሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ማስታወቋ ይታወሳል።
ለዚህም ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና ለመስጠት መስማማቷ መግለጿን ተከትሎ፤
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አንድ ዓመት ያክል የከረረ ውዝግብ ውስጥ ገብተው ቆይተዋል።
ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ አለመግባባቶችን የፈጠረ ሲሆን፤
ሶማሊያ "ስምምነቱ ሉዓላዊነቴን የጣሰ ነው" ስትል ከሳለች።
በዚህም የተነሳ "የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ዳግም ግጭት ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት
በብዙዎች ዘንድ ፈጥሮ ቆይቷል።
ቱርክ ከፈረንጆቹ ሀምሌ ወር ጀምሮ ሁለቱን ወገኖች በማደራደር
ልዩነቶቻቸውን ለመፍታት ያለመ ውይይቶችን እየመራች ቢሆንም፣
በአንካራ ቀደም ብለው የተካሄዱት ሁለት ድርድሮች ግን
ምንም አይነት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ሳይችሉ መቅረታቸው ተገልጿል።
ነገር ግን በዚህ ሦስተኛ ዙር ድርድር ሁለቱ ሀገራት መካከል ከስምምነት መደረሱ የተገለጸ ሲሆን፤
ይህንንም ስምምነት ለማስፈጸም ይረዳ ዘንድ የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቷል።
በዚህ ሰነድ ላይም ኢትዮጵያ በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና
ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት አማራጭ ላይ
የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር ሁለቱ ሀገራት መስማማታቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና እና
ቀጣይነት ያለው የባህር በር መዳረሻ ተጠቃሚነት እንዲኖራት ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን፤
ይህም በሶማሊያ መንግሥት ስልጣን ሥር የሚተገበር መሆኑ ተገልጿል።
ለዚህም የሚሆን የኮንትራንትና የሊዝ ውልን ጨምሮ
ሌሎች ሞዳሊቲዎች ላይ በቀጣይ በቅርበት አብረው ለመስራትና ለማጠናቀቅ መስማማታቸው ተመላክቷል።
ይህንን ስምምነት ለማስፈጸምም ከመጋቢት ወር 2017 በፊት
የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ የማመቻቸት ሥራ ይሰራል የተባለ ሲሆን፤
በ4 ወራት ውስጥ ደግሞ ሂደቱ ተጠናቆ ስምምነት እንደሚፈራረም ተገልጿል።
።።።።።
ሳውዲ አረቢያ የ2034 የአለም ዋንጫ አስተናጋጅ ሆነች!
ሳውዲ አረቢያ የ 2034ቱን አለም ዋንጫ ውድድር ለማዘጋጀት
በብቸኝነት ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ በትላንትናው ዕለት ይፋ ተደርጓል።
ዛሬ በነበረ የፊፋ ጉባኤ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ሳውዲ አረቢያ ማሸነፏን አረጋግጠዋል።
ለብዙዎች የሳዑዲ ዓለማቀፍ ዋንጫ ማፅደቁ
ሀገሪቱ አሁን በስፖርታዊ ጨዋነት የምትጠቀምበት ኃያልነት
የመጨረሻ መግለጫ እና ከዚ ጋር ተያይዞ የመጣው ዕድል፣ መቋረጥ እና ውዝግብ ይሆናል።
እ.ኤ.አ. ከ2021 ጀምሮ
መንግሥቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ ኢንቨስት አድርጓል።
መንግሥቱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ፎርሙላ 1ን፣ የእግር ኳስ የስፓኒሽ እና
የጣሊያን ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታዎችን፣ የዓለም ክለቦች ዋንጫን እና
ከፍተኛ ደረጃ ቦክስን፣ ጎልፍን፣ የፈረስ እሽቅድምድም እና ቴኒስን አስተናግዷል።
የሀገሪቱ የህዝብ ኢንቬስትመንት ፈንድ የተለየውን ።
አራት የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ክለቦችን ተቆጣጥሮ ኒውካስል ዩናይትድን ገዝቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ የዴንማርክ ድርጅት ፕሌይ ዘ ጨዋታ ባወጣው ዘገባ
ሳዑዲ አረቢያ ከ900 በላይ የስፖንሰርሺፕ ስምምነቶችን መፈራረሟን ገልጿል፣
ውጪያዊ እና በደርዘን የሚቆጠሩ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖችን
በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ተጽእኖዋን እያሰፋች ትገኛለች።
በግንቦት እና በሴፕቴምበር መካከል፣ አማካኝ የየቀኑ የሙቀት መጠን
ከ27C እስከ 43C በውስጥ አካባቢ፣ እና
በባህር ዳርቻዎች ከ27C እስከ 38C መካከል ይደርሳል።
የሳውዲ ስፖርት ሚኒስትር ልዑል አብዱልአዚዝ ለቢቢሲ እንደተናገሩት
አዘጋጆቹ በበጋው ዝግጅት ይቻል እንደሆነ በእርግጠኝነት እያጠኑ ነው።
በበጋው ወቅት ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለምን አትታይም?
በበጋም ሆነ በክረምት ለኛ ምንም ለውጥ አያመጣም,
እንደዚህ አይነት ክስተት ለማስተናገድ
ትክክለኛውን ከባቢ አየር እንደሰጠን እስካረጋገጥን ድረስ." በማለት ተናግሯል።
የአለም ዋንጫው እየተስፋፋ ሲሆን ከ2026 ጀምሮ 48 ቡድኖች ይሳተፋሉ።
ይህም በኳታር ከተወዳደሩት 32 ጭማሪዎች ነው ተብሏል።
።።።።።።።።