Daily Media

Daily Media Home of balanced and Timely News and Programs!

Ityoophiyaan bara 2030'tti lafa manca’ee hektaara miiliyoona 22 dabalataan deebistee bosonoomsuuf karoorfatteetti-MM Abi...
10/11/2022

Ityoophiyaan bara 2030'tti lafa manca’ee hektaara miiliyoona 22 dabalataan deebistee bosonoomsuuf karoorfatteetti-MM Abiy Ahimad

Finfinnee, Sadaasa 1, 2015 (Daily Media)–Ityoophiyaan hanga bara 2030'tti lafa manca’e hektaara miiliyoona 22 dabalataan deebistee bosonaan uwwisuuf karoorfattee hojjechaa jiraachuu Muummeen Ministiraa FDRI Abiy Ahimad ibsan.

Muummeen Ministiraa Abiy Ahimad Yaa’ii Jijjiirama Qabeenya Qilleensaa Dhaabbata Mootummoota Gamtoomanii Ijiptitti gaggeeffamaa jirurratti sagantaa Ashaaraa Magariisaa Ityoophiyaa ilaalchisuun ibsa taasisaniiru.

Ibsa isaaniin muuxannoo gama inisheetivii Ashaaraa Magariisaan jiruu fi hojiilee hojjetamaaniin bu’aalee argaman kaasaniiru.
Kanaanis Ityoophiyaan hanga bara 2030'tti lafa manca’e hektaara miiliyoona 22 dabalataan deebistee bosonaan uwwisuuf karoorfattee hojjechaa jiraachuu dubbatan.

Gumaachi Ityoophiyaan jijjiirama qabeenya qilleensaa ittisuu keessatti qabdus sadarkaa kamiinuu kan dinqisiifamuudha jedhan.

በኦሮሚያብህብረተሰቡን ከቱሪዝም ኢንዱስትሪው ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው***************ጥቅምት 30,2015(ዴይሊ ሚዲያ)የኦሮሚያ ክልል በዓለም ለ43ኛ በክልሉ ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ ...
09/11/2022

በኦሮሚያብህብረተሰቡን ከቱሪዝም ኢንዱስትሪው ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው
***************
ጥቅምት 30,2015(ዴይሊ ሚዲያ)
የኦሮሚያ ክልል በዓለም ለ43ኛ በክልሉ ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረውን የቱሪዝም ቀን "አዲስ እሳቤ ለቱሪዝም" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ፕሮግራሞች ከጥቅምት 27 ጀምሮ በምስራቅ ሐረርጌ እያከበረ ይገኛል።

በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ እንደገለጹት፤ ህብረተሰቡ ከቱሪዝም ኢንዱስትሪ ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስት በትኩረት በመስራት ላይ ይገኛል።

ህብረተሰቡ ለቱሪዝም ያለውን አስተሳሳብ በማሳደግ በክልሉ የሚገኙ ቱሪዝም መስህቦች ለዓለም በማስተዋወቅ እየተስተዋለ ያለውን ስራአጥነት በማቀነስ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በዓሉ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ሁሴን ፈይሶ በበኩላቸው ቱሪዝም ከሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዘርፍ ማሳደጊያ ዘርፎች ውስጥ አንዱ መሆኑን አብራርተዋል።

ህብረተሰቡ ያለውን የሚታዩና የማይታዩ ቱሪስት መስህቦችን በመንከብከብና በማልማት ለማህባራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ሊያውል ይገባል ብለዋል።

የምስራቅ ሀረርጌ ዞን አስተዳደር ወይዘሮ ሚስኪ መሐመድ በዓሉ ህብረተሰቡ ያለው ቱሪዝም ሀብት በማልማት ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል ግንዛቤ በመፍጠር የቱሪዝም ሀብቱን እንዲከባከብ ያደርጋል ብለዋል።

በምስራቅ ሀረርጌ በባቢሌ ወረዳ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎች ፣ ከመቶ በላይ የዱር እንስሳ ዝሪያ የሚገኙበት ደን፣ የትክል ድንጋዮች፣ ከሃያ ሰባት በላይ ማዕድናት፣ አንድ ሺ 416 ዓመት ያስቆጠረ መስጊድና መሰል የቱሪዝም መስህቦች ተጎብኝቷል።

ህብረተሰቡ ያለውን የቱሪዝም ሀብት ማልማት፣ በዞኑ የሚገኘውንና ዝሪያው በታንዛንያ ብቻ የሚገኘውን የዝሆን ዝሪያ መጠበቅ ከቻለ የዓለምን ትኩረት መሳብ ስለሚያስችል ፋይዳው የጎላ በመሆኑ መንግስት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በዓሉ በፓናል ውይይት፣ ቱሪዝም መስህብ ቦታዎች በመጎብኘት እየተካሄደ ነው።

የአንጋፋው አርቲስት ዓሊ ቢራ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የአንጋፋው የጥበብ ሰው አርቲስት ዓሊ ቢራ የቀብር ሥነ ስርዓት በድሬዳዋ ከተማ ተፈፀመ፡...
08/11/2022

የአንጋፋው አርቲስት ዓሊ ቢራ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የአንጋፋው የጥበብ ሰው አርቲስት ዓሊ ቢራ የቀብር ሥነ ስርዓት በድሬዳዋ ከተማ ተፈፀመ፡፡

አርቲስት ዓሊ ቢራ ከአባቱ አቶ መሐመድ ሙሣ እና ከእናቱ ወይዘሮ ፋጡማ ዓሊ በ1940 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ገንደ ቆሬ እንደተወለደ የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡

ባለፉት 60 ዓመታትም ለሙያው ታምኖ የኖረው ዓሊ÷ ከድሬዳዋ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ተበርክቶለታል፡፡

አርቲስቱ ባጋጠመው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በተወለደ በ75 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ዛሬ ጠዋት የአርቲስቱ አስክሬን ቢሾፍቱ ከሚገኘው መኖሪያ ቤት ሽኝት የተደረገለት ሲሆን÷ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይም የጀግና የክብር ሽኝት ተደርጎለታል፡፡

እንዲሁም በድሬዳዋ ስታዲየም የሽኝት መርሐ ግብር ከተካሄደ በኋላ የቀብር ሥነ ስርዓቱ በለገሀሬ የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡

አርቲስት ዓሊ ቢራ ከወይዘሮ ሊሊ ማርቆስ ጋር ትዳር መስርቶ ይኖር ነበር፡፡

የአርቲስት አሊ ቢራ አስክሬን የትውልድ ቦታ በሆነች ድሬዳዋ ከተማ ደርሷል******************(ዴይሊ ሚዲያ)የክቡር ዶክተር አርቲስ አሊ ቢራ አስከሬን በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ...
08/11/2022

የአርቲስት አሊ ቢራ አስክሬን የትውልድ ቦታ በሆነች ድሬዳዋ ከተማ ደርሷል
******************
(ዴይሊ ሚዲያ)

የክቡር ዶክተር አርቲስ አሊ ቢራ አስከሬን በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ የእምነት አባቶች፣ የአርት ባለሙያዎች፣ የአርቲስቱ አድናቂዎች በተገኙበት ሽኝት ከተደረገለት በኋላ ድሬደዋ ገብቷል።

በአሁኑ ጊዜ አስክሬኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የደረሰ ሲሆን የድሬዳዋ ህዝብ፣ የእምነት አባቶች ለአርቲስቱን አስክሬን የክብር አቀባበል አድርገዋል።

ከደቂቃዎች በኋላ የክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ የቀብር ስነስርአት የሚፈጸም ይሆናል።

ዝነኛው አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2015 የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡ከ50 ዓመታት በላይ በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ...
06/11/2022

ዝነኛው አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2015 የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡

ከ50 ዓመታት በላይ በሙዚቃው ኢንዱስትሪ የቆየው ድምጻዊ አሊ ቢራ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

አርቲስት አሊ ቢራ በ1940 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ገንደ ቆሬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የተወለደው፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በድሬዳዋ ከተማ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በአዲስ አበባ ካቴድራል ትምህርት ቤት ተከታትሏል። አሜሪካ አገር በሚገኘው የሳንታ ሞኒካ ኮሌጅም የሙዚቃ ትምህርት ስለመማሩም ነው የሚነገረው፡፡

ድምጻዊ ዓሊ ቢራ በ1954 ዓ.ም በ13 ዓመቱ የኦሮሞን ሙዚቃ ለማስተዋወቅ ዓላማ አድርጎ የተቋቋመውን ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን “ አፍረን ቀሎ ”ን በመቀላቀል ነው የሙዚቃ ስራውን አንድ ብሎ የጀመረው።

በኢትዮጵያ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ታሪክ ውስጥ ከ60 ዓመታት በላይ በጽናት የዘለቀ የሙዚቃ ንጉስ አሊ ቢራ ከ267 ሙዚቃዎችን መጫወቱም ይነገራል፡፡

በአፋን ኦሮሞ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው የሆነውን አልበሙን በ1971 ከሰራው በተጨማሪ ለገበያ የቀረቡ 13 አልበሞችን ስርቷል፡፡

ድምጻዊ አሊ ከአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በተጨማሪ፣ በሱማሊኛ፣ በአፋርኛ፡ በሐረሪ፣ በአማርኛና በሱዳን ቋንቋዎች በርካታ ዘፈኖችን መጫወት ችሏል።

ከሙዚቃ ስራዎቹ መካከልም ……..

"BIRRAA DHAA BARIHE" የመጀመሪያ ስራው

" Waa Malli nu dhibe "

" Jaalaluma teeti "

" Barnootaa "

" Ushuruururuu "

"Karaan Mana Abbaa Gadaa "
"Nin deema "

" Dabaala Keessan " የሰርግ ሙዚቃ

" AMALELE " ከብዙዎቹ መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ድምጻዊ ዓሊ ቢራ “Birra Children’s Education Fund” የተባለ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ከባለቤቱ ጋር አቋቁሞ ለሕፃናት ትምህርት ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አርቲስት አሊ ቢራ ከድሬዳዋ እና ከጅማ ዩኒቨርስቲዎች የክብር ዶክትሬትን የተቀበለ ሲሆን በህይወት ዘመኑ ሌሎች በርካታ ሽልማትን እና እውቅናዎችን አግኝቷል፡፡

በዛሬው ዕለትም አርቲስቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷ፡፡

ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሩሲያ ድሮን ማቅረቧን አመነች*******************ጥቅምት 26,2015 (ዴይሊ ሚዲያ)የኢራኑ የውጭ ጉዳይ  መ/ቤት ሚንስትር ሆሲን አሚር አብዱልአሂያን ዛሬ ለ...
05/11/2022

ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሩሲያ ድሮን ማቅረቧን አመነች
*******************
ጥቅምት 26,2015 (ዴይሊ ሚዲያ)
የኢራኑ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ሚንስትር ሆሲን አሚር አብዱልአሂያን ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢራን ሠራሽ የሆኑ ሰዉ አልባ ድሮኖች ለሩስያ ማቅረቧን ገልፀው ነገርግን ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ወደ ጦርነት ከመግባቷ በፊት የተላለፈ መሆኑን አፅእኖት ሰጥተው ገልፀዋል።

ይሄ በኢራን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተሰጠው አስተያየት የመጣው ለወራት ስለ ጉዳዩ አወዛጋቢ መረጃ ስትሰጥ ከቆየች በኋላ ነው። የአለም የመገናኛ ብዙሃን፣ የአሜሪካና የአውሮፖ ሃገራት በተደጋጋሚ የዩክሬን የሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ የድሮን ጥቃቶች በኢራን ሰራሽ ድሮኖች መፈፀማቸው በተደጋጋሚ ቢገልፁም፣ ኢራን ጉዳዩን እያስተባበለች ቆይታለች።

በቴሄራን የተደረገ ስብሰባ መዝጊያን ተከትሎ ለሪፖርተሮች መግለጫ የሰጡት ሚኒስትሩ " የተወሰኑ ድሮኖችን ጦርነቱ ከመጀመሩ ወራቶች በፊት ነው ለሞስኮ ያቀረብነው" ብለዋል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የኢራን የተባበሩት መንግስታት አምባሳደር አሚር ሰኢድ ክሱ መሰረተ ቢስ እንደሆነ ገልፀው ሃገራቸው በጦርቱ የያዘችውን ገለልተኛና ሚዛናዊ አቋም የሚፃረር መሆኑን ገልፀው ነበር።

አሜሪካና የምራብ ሃገሮች ለተባበሩት መንግስታት ድርጀት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዬ ጉቴሬዝ ባቀረቡት ጥሪ የኢራን ድሮኖች በዩክሬን እየደረሰ ባለው ጥቃት ጥቅም ላይ መዋል አለመዋላቸውንና ያደረሱትን ጉዳት እንዲጣራ ጥያቄ አቅርበው ነበር።

የኢራን ህዝብ ተወካዬች ም/ቤት አብዬታዊ ዘብ ለአለም ቀዳማይ ሃያል ለሆኑ ሃገሮች የድሮን አቅርቦት እንዲጨምር የወሰነ ሲሆን ተያይዞም የሃገሪቱ ላዕላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካህሚኒ የሃገራቸውን የድሮን ብቃት አድንቀው በምራባውያኑ ስጋት የሹፈት አስተያየት ሰጥተዋል።

በትላንትናው እለት እኤአ 1979 በኢራን የተካሄደውን የኢራን አብዬት ለመዘከር አደባባይ ለህዝበ ትእይንት የወጡት ኢራናውያን የድሮን ቴክኖሎጂው የሃገር ኩራት ብለውታል።(ABC News)

የግብርና መካናይዜሽን መስፋፋት ለምርታማነት መጨመር ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ነው**************************ጥቅምት 26/2015 (ዴይሊ ሚዲያ)የግብርና መካናይዜሽንን ለማስፋት የ...
05/11/2022

የግብርና መካናይዜሽን መስፋፋት ለምርታማነት መጨመር ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ነው
**************************
ጥቅምት 26/2015 (ዴይሊ ሚዲያ)የግብርና መካናይዜሽንን ለማስፋት የተከናወኑ ስራዎች ለዘርፉ ምርታማነት መሻሻል ከፍተኛ ሚና እያበረከቱ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ሶሰት ዓመታት ለስንዴ ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ሲሆን፤ በዚህም የስንዴ ምርትን ከአገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በሚቻልበት ሽግግር ላይ ትገኛለች፡፡

ለዚህ ደግሞ በበጋ መስኖ ብቻ በአገር አቀፍ ደረጃ 52 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማግኘት እቅድ ተይዞ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፤ እቅዱን እውን ለማድረግ ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶች ስርጭት ቀደም ብሎ መከናወኑ ተገልጿል፡፡

ባለፉት ሶስት ዓመታት በተከናወኑ ስራዎች የስንዴ ምርታማነት በእጅጉ እየተሻሻለ መሆኑን ነው ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ የሚጠቁመው፡፡

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል ብቻ ባለፉት ሶስት ዓመታት የመኸር ስንዴ ልማትን በእጥፍ መጨመር መቻሉን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡

ከሶስት ዓመት በፊት በክልሉ በመኸር ወቅት በስንዴ የሚለማው መሬት ከ800 ሺህ ሄክታር እንደማይበልጥ ጠቅሰው፤ አሁን ላይ ቁጥሩ ወደ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር ማደጉን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት በአንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ለማከናወን እቅድ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰዋል፡፡

ለምርትና ምርታማነት መጨመር ደግሞ የግብርና መካናይዜሽን ለማስፋት የተከናወኑ ስራዎች ትልቅ ፋይዳ ማበርከታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም አርሶ አደሮች ትራክተርን ጨምሮ ሌሎች የግብርና ማሽነሪዎችን በብድር እንኳ ማግኘት የማይችሉበት አሰራር እንደነበር ጠቅሰው፤አሁን ላይ ችግሩ መቀረፉን ጠቅሰዋል፡፡

አርሶ አደሩ የግብርና ማሽነሪዎችን በብድር ከቀረጥ ነጻ እንዲያገኝ መንግስት ከፍተኛ ስራ ማከናወኑን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ይህም በአጭር ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት ወደ አዲስ ምእራፍ እያሸጋገረው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ውጤት አመራሩ ትኩረት ሰጥቶና ህብረተሰብን አስተባብሮ መስራት ከቻለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያን መለወጥ እንደሚቻል አመላካች ነው ብለዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የገጠሟትን አስቸጋሪ ፈተናዎች ተቋቁማ ሰፋፊ የልማት ስራዎችን እያከናወነች መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

ይህም ኢትዮጵያ እየተከተለች ያለው የኢኮኖሚ አቅጣጫ ትክክለኛ መሆኑን ያመላከተ ነው ያሉት፡፡

በቀጣይም ኢትዮጵያን የሚለውጡ በርካታ የልማት ስራዎች እንደሚከናወኑ በመጥቀስ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ የስንዴ ምርት አሰባሰብ ሂደትን ጎበኙ *********************** ጥቅምት 26,2015(ዴይሊ ሚዲያ)በጠቅላይ ...
05/11/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ የስንዴ ምርት አሰባሰብ ሂደትን ጎበኙ
***********************
ጥቅምት 26,2015(ዴይሊ ሚዲያ)
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ ልዑክ በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ የስንዴ ምርት አሰባሰብ ሂደትን ጎብኝቷል።

ልዑኩ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም ሚኒስትሮችን እና የዲፕሎማቲክ አባላትን ያካተተ ነው።

''በ አፍሪካ ቀንድ በሁሉም ረገድ ተወዳዳሪ የሆነች ከተማን እየገነባን ነዉ'' ከንቲባ ሀይሉ ጀልዴዴይሊ ሚዲያ ፣ አዳማ (ጥቅምት 25/2015)የአዳማ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የስማርት ሲ...
03/11/2022

''በ አፍሪካ ቀንድ በሁሉም ረገድ ተወዳዳሪ የሆነች ከተማን እየገነባን ነዉ'' ከንቲባ ሀይሉ ጀልዴ
ዴይሊ ሚዲያ ፣ አዳማ (ጥቅምት 25/2015)
የአዳማ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ስኬት የሚረዳዉን ስምምት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ተፈራርሟል።
በትላንትናው ዕለት ኢትዮ ቴሌኮም በ አዳማ ከተማ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ የ5 G የኢንተርኔት አገልግሎት ያስጀመረ ሲሆን አገልግሎቱ የከተማ አስተዳደሩ እየሰራ ለሚገኘው የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት መሳካት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል ።
ከኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር በመሆን የስራ ስምምነቱን የፈረሙት የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሀይሉ ጀልዴ '' እንደ አፍሪካ ቀንድ ተወዳዳሪ የሆነች ከተማን እየገነባን ነዉ '' በማለት ለዚህ ስኬትም እንደ ኢትዮ ቴሌኮም፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል ።
በከተማዋ የሚሰሩት ስራዎች ጠንካራ አስተዳደር ለመገንባት ፣ ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመዘርጋት እና ጠንካራና ተደራሽ የጤና ስርዓት ለመገንባት ትኩረት የሰጠ መሆኑን ያብራሩት አቶ ሀይሉ በዚህ አመት በከተማዋ ሁሉም ሴክተሮች የሚከናወኑ ስራዎችን ዲጂታል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አክለዋል ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ ከተሞች በቴክኖሎጂ ትስስር በመፍጠር መዘመን እንዳለባቸዉ በመግለፅ፣ ኢትዮ ቴሌኮም የአዳማ ከተማ አስተዳደር እየሰራ ለሚገኘው የዲጂታላይዜሽን ስራ አስፈላጊዉን ትብብር እንደሚያደርግም ገልፀዋል ።

ለሰሜኑ ግጭት ሰላማዊ እልባት ለመስጠት  ሲደረግ የነበረው ንግግር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቀቀጥቅምት 23፣ 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) ለሰሜን ...
02/11/2022

ለሰሜኑ ግጭት ሰላማዊ እልባት ለመስጠት ሲደረግ የነበረው ንግግር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቀቀ

ጥቅምት 23፣ 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሰላማዊ እልባት ለመስጠት ሲደረግ የነበረው ንግግር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቀቀ።

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ሲቋጭ የተደረገው ስምምነት ግጭትን በዘላቂነት ማቆምን ያካተተ ነው።

በትግራይ ክልል ህገመንግስታዊ ስርዓት እንዲመለስም ከስምምነት ተደርሷል።

ስምምነቱ በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የታጠቀ ሀይል ሊኖር እንደማይችል የጠቀሰ ሲሆን፥ በዚህም መሰረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱ ይሆናል።

በትግራይ ክልልም መሰረታዊ አገልግሎት እንዲጀመርም እንደዚሁ ከስምምነት ተደርሷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአራዳ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መርቀው ከፈቱ**********************ጥቅምት 17,2015(ዴይሊ ሚዲያ)ጠቅላይ ሚኒስትር ...
27/10/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአራዳ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መርቀው ከፈቱ
**********************
ጥቅምት 17,2015(ዴይሊ ሚዲያ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመዲናዋ አራዳ ክፍለ ከተማ በአዲስ መልክ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መርቀው ከፍተዋል።

በተለምዶ "15 ሜዳ" ተብሎ የሚጠራው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ከዚህ ቀደም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ምቹ አልነበረም።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አነሳሽነት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በአዲስ መልክ ተገንብቶ በመጠናቀቁ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

የስፖርት ማዘውተሪያው አሁን ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ በሚያመች መልኩ የተገነባ በመሆኑ የቀደመ አግልግሎቶቹን ይሰጣል።

የስፖርት ማዘውተሪያው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመርቆ ሲከፈት ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።

የስፓርት ማዘውተሪያ ስፍራው ግንባታ የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮጀክት አካል መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

23/10/2022

Sayo Mokonin On Stage. New Year Celebration at Adama.Sayo #2022 #

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቡራዩ ከተማ የተገነባው የልዩ ተሰጥአ ማበልፅጊያ ኢንስቲትዩት መርቀው ከፈቱ******************* ጥቅምት 10,2015 (ዴይሊ ሚዲያ)የኢፌዲሪ ጠቅላይ...
20/10/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቡራዩ ከተማ የተገነባው የልዩ ተሰጥአ ማበልፅጊያ ኢንስቲትዩት መርቀው ከፈቱ
*******************
ጥቅምት 10,2015 (ዴይሊ ሚዲያ)
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቡራዮ ከተማ ከ708 ሚሊዮን 693 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባውን የልዩ የተሰጥኦ ማበልጸጊያ ኢንስቲትዩት መርቀው ከፍተዋል።
ይህ ኢንስቲትዩት እስከ አንድ ሺህ ባለተሰጥኦዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ አቅም አለው።
ጠቅላላ ፕሮጀክቱ በ10 ሄክታር ያረፈ ሲሆን፤ ዛሬ የተመረቀው በአምስት ነጥበ አራት ሄክታር ላይ ያረፈው ፕሮጀከት ነው።

ይህ ኢንስቲትዩት ወደፊትም የማስፋፊያ ስራ ይኖረዋል ተብሏል።

ኢንስቲትይቱ የባለተሰጥኦዎች ማደሪያ፣ የመገገቢያ አዳራሽ፣ የአስተዳደር ህንጻዎች፣ የህክምና ማዕከል፣ መማሪያ ክፍሎችና ቤተ ሙከራዎችን አካቶ መያዙን ተገልጿል ።

የልዩ የተሰጥኦ ማበልጸጊያ ኢንስቲትይቱ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አስፈላጊ ቁሳቁሶች የተሟላለት ሲሆን መጸሐፍ ፥ኮምፒውተሮች፥ የቤተ ሙከራ ዕቃዎችንና ሌሎች አስፈላጊ ዕቃዎች የተሟሉለት መሆኑ ተጠቅሷል ።

የተሰጥኦ ማበልጸጊያ ኢንስቲትዩቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አነሳሽነትና ክትትል ለፍጻሜ መድረሱ ተነግሯል።

ኢትዮጵያ የብሩህ ዓቅሞችና ተሰጥዖዎች ምድር በመሆኗ ይህ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አስዋጸኦ ይኖረዋል ተብሏል ።

አዲስ አበባ የበካይ ጋዝን በሚያስቀር የዘመናዊ ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት በመዘርጋት ባከናወነችው መልካም ሥራ ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈች ************************ጥቅምት ...
20/10/2022

አዲስ አበባ የበካይ ጋዝን በሚያስቀር የዘመናዊ ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት በመዘርጋት ባከናወነችው መልካም ሥራ ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈች
************************
ጥቅምት 10,2015 (ዴይሊ ሚዲያ)

አዲስ አበባ የበካይ ጋዝን በሚያስቀር የዘመናዊ ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት በመዘርጋት ባከናወነችው መልካም ሥራ በC40 የከንቲባዎች ፎረም ዓለም አቀፍ ውድድር አሸናፊ ሆነች።

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በአካል ተገኝተው ሽልማቱን መቀበላቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት አስታውቋል።

አዲስ አበባ ከተማ እ.ኤ.አ ከጥቅምት 19 - 21 ቀን 2022 በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ ከተማ እየተካሄደ ባለው የC40 የዓለም ከንቲባዎች ፎረም ላይ የአየር ንብረትን የሚከላከል ተስማሚ እና መልሶ የመጠቀም አሠራርን የያዘ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት በመዘርጋት (decentralized composting and recycling) ለአረንጓዴ እና ጤናማ የከተማ ግንባታ ሂደት እና ቆሻሻን ወደ ኮምፖስት በመቀየር ለገቢ ማስገኛ ሥራ በማዋልዋ ጉልህ ድርሻ በማበርከት በመልካም ተሞክሮ ተሸላሚ መሆን ችላለች።

የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም የነበረውን ለበካይነት የተጋለጠ አሠራር በማስቀረት በቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት የብዙዎችን ሕይወት ሊታደግ የሚችል እና በካይ (fossil) ፎሲል ጋዝ ልቀትን ያስቀረ፣ ተመልሶ በከተማ እየተከናወነ ላለው የጓሮ አትክልት ልማት ሥራ ማዳበርያ ማቅረብ ያስቻለ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት መዘርጋቱ ለእውቅና እንዳበቃው ተጠቅሷል።

በዚህም ሥራ የበርካታ ወጣቶችን ገቢያቸውን በከፍተኛ ደረጃ ከማሳደጉም በተጨማሪ ተፈጥሮን የሚያክም ቆሻሻን ወደ ሀብትነት የቀየረ በመሆኑ ከብዙ ትላልቅ የዓለማችን ከተሞች ከቀረቡ ተሞክሮዎች ጋር በመወዳደር አሸናፊ በመሆኗ ሽልማቱን ማግኘት ችላለች።

የC40 የዓለም ከንቲባዎች ፎረም ከተሞች የአየር ንብረት ከካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት እና ለዓለም ከተሞች የሙቀት መጨመር ምክንያት ሆነው ግሪንሃውስ ጋዝ ተፅእኖ በጋራ ለመከላከል የተመሠረተ የዓለም ሀገሮች 100 ዋና ከተሞች ጥምረት የተመሠረተ ነው።

አዲስ አበባ ከቀናት በፊት በተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ የእውቅና ሽልማት ማግኘቷ አይዘነጋም።

ይህ ጅምር ድሉ በሁሉም መስክ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የከንቲባ ጽ/ቤት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና በአለም አቀፉ ኤግዚቢሽን ላይ ቀረበጥቅምት 09 ቀን 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የኢትዮጵያ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና በጃፓን በተካሄደው አለም አቀፉ የባለ ልዩ ጣዕም ቡ...
19/10/2022

የኢትዮጵያ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና በአለም አቀፉ ኤግዚቢሽን ላይ ቀረበ

ጥቅምት 09 ቀን 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የኢትዮጵያ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና በጃፓን በተካሄደው አለም አቀፉ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ ቀርቧል።

በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ለጉባኤውና ኤግዚቢሽኑ የተዘጋጀውን ዝግጅት ከሌሎች ቡና ላኪ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ከፍተዋል።

በዝግጅቱ ላይ ከኢትዮጵያ የተውጣጡ ከ40 በላይ የቡና ላኪዎች፣ የቡና ላኪዎች ማህበር እንዲሁም የዘርፍና ንግድ ማህበራት ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የቡና ላኪዎቹ የኢትዮጵያን ባለ ልዩ ጣዕም ቡና፣የተለያዩ የቡና ዝርያዎችን፣ ባህላዊ የቡና አፈላል ስነስርዓት ለጎብኚዎች የቀረቡ ሲሆን በጃፓን የኢትዮጵያን ቡና ከሚገዙ ባለሀብቶች ጋር የአንድ ለአንድ የንግድ ውይይቶች ማድረጋቸው ተመላክቷል።

በጃፓን በመካሄድ ላይ የሚገኘው ጉባኤና ኤግዚቢሽን በእስያ ትልቁ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ኤግዚቢሽን መሆኑንና ከተለያዩ ሀገራት የቡና አምራቾች፣ላኪዎች እንዲሁም አቀናባሪዎች ምርታቸውንና አገልግሎታቸውን ለእይታ የሚያቀርቡበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

Guyyaan Alaabaa Akka Biyyaatti yeroo 15ffaaf guutuu Biyyaatti sirnoota gara garaatin kabajamee Oolera.
17/10/2022

Guyyaan Alaabaa Akka Biyyaatti yeroo 15ffaaf guutuu Biyyaatti sirnoota gara garaatin kabajamee Oolera.

Bulchiinsi Magaalaa Adaamaa Waliigaltee dhaabbilee Investimantii 21 adda kutuu beeksise.(Daily Media, Onkololeessa/ 6 /2...
16/10/2022

Bulchiinsi Magaalaa Adaamaa Waliigaltee dhaabbilee Investimantii 21 adda kutuu beeksise.
(Daily Media, Onkololeessa/ 6 /2015)
Bulchiinsi magaalichaa Dhaabbilee Maqaa Inveestimantiin lafa fudhatanii yoo xiqqaate Waggoota 14 darban oliif lafa fudhatan akkaataa Waliigaltee qabaniitin misoomsaa hin jirre irratti Tarkaanfi fudhachuu eegalu beeksise.

Akka Bulchiinsa Magaalaatti Piroojektoonni Investimantii 1198 Investimantiif Bulchiinsa Magaalichaarra lafa fudhachuu kan Ibsan, Itti gaafatamaan Waajjira Inveestimantii fi Industirii Magaalaa Adaamaa Obbo Turaa Gizaaw kanneen keessaa Pirojektoonni 800 akkatuma waliigaltee isaanitin hojiirra jiraachuu ibsuun piroojektoonni 200 ta'an Ijaarsarra jiraachuu himan.
Gama biraatin piroojektoonni hafan Waliigaltee galan diiguun lafa hojii Inveestimantiif fudhatan kaayyoo biraatif oolchaa jiraachuu ibsuun isaan kanarrattis akkaata qajeelfama Investimantii Naannichaan tarkaanfii irratti fudhacha jiraachuu ibsan.
Kantiibaan Magaalaa Adaamaa Obbo Hayiluu Jaldee Bulchiinsi Magaalaa dhaabilee fi Abbootiin qabeenyaa Lafa Inveestimantii Agroo Industirii fi Maanufakchariingiif fudhatanii mana kuusaa itti ijaaruun waggoota 15 olif kireeffachaa turan, diinagdee biyyaa miidhaa turu ibsuun dhaabbilee hojii wal fakkaataa akkasii irratti bobba'an 24 keessa 21 waliigaltee isaanii adda kutuun 3 f akeekkachiisni xummuraa kennamu eeran.
Obbo Hayiluun Bulchiinsi Magaalaa Dhaabbilee Lafa magaalaa Investimantiif fudhatan akkaata waliigalteetin itti hojjechaa hin jirre biroorrattis sadarkaa sadarkaan tarkaanfii fudhachuu itti fufa jedhaniiru.

የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል አል ቡርሃን ለጣና ፎረም ባህር ዳር ገቡጥቅምት 5፣ 2015፣ ( ዴይሊ ሚዲያ) የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል ...
15/10/2022

የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል አል ቡርሃን ለጣና ፎረም ባህር ዳር ገቡ

ጥቅምት 5፣ 2015፣ ( ዴይሊ ሚዲያ) የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ለጣና ፎረም ባህር ዳር ገቡ።

ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ባህር ዳር ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሲሆን፥ ከጥቅምት 4 እስከ 6 ቀን 2015 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል፡፡

ፎረሙ ትናንት የቀድሞውን የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ኬኔት ካውንዳን በማሰብ በቅድመ ጉባኤ ደረጃ ተካሂዷል።

በፎረሙ ላይ ለመካፈል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የአሁን እና የቀድሞ የሀገራት መሪዎች፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ክፍል የመጡ ተመራማሪዎች እና ፖለቲከኞች ባህር ዳር ገብተዋል።

13/10/2022

Elsa Nigusie On Stage. New Year Celebration at Adama.Elsa music #2022 #

11/10/2022

Getachew Hailemariam On Stage. New Year Celebration at Adama.Getachew #2022 #

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን የመኪና ሽልማት ተረከበ**************ጥቅምት 01/2015 (ዴይሊ ሚዲያ) በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በ10 ሺሕ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው አት...
11/10/2022

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን የመኪና ሽልማት ተረከበ
**************
ጥቅምት 01/2015 (ዴይሊ ሚዲያ)
በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በ10 ሺሕ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን መኪና ዛሬ ተረክቧል።

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ ብቸኛው የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቱን ተከትሎ ከመንግስት የመኪና ሽልማት እንደተበረከተለት ይታወሳል።

ሽልማቱ በተለያየ ምክንያት ለሰለሞን እንዳልተሰጠው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን የመኪና ሽልማቱን ተረክቧል።

Magaalaa Adaamaatti Sagantaan Nyaata Barattoota Manneen Barnootaa Magaalicha hunduma keessatti eegalameera.
11/10/2022

Magaalaa Adaamaatti Sagantaan Nyaata Barattoota Manneen Barnootaa Magaalicha hunduma keessatti eegalameera.

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መሰጠት ጀመረመስከረም 30፣ 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መሰጠት ጀመረ።የፈተናውን ደህንነት በጠበቀ መልኩ ያለምንም የፈተና ስርቆ...
10/10/2022

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መሰጠት ጀመረ

መስከረም 30፣ 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መሰጠት ጀመረ።

የፈተናውን ደህንነት በጠበቀ መልኩ ያለምንም የፈተና ስርቆትና ኩረጃ ለመስጠት እንዲቻል ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ዩኒቨርስቲ በመግባት ነው ፈተናውን መውሰድ የጀመሩት።

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 976 ሺህ 18 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዘንድሮ ተፈታኞቾ ባስተላለፉት መልዕክት፥ "የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ" ብለዋል።

የሀገራችን የነገ ተስፋዎች ያሏቸው ተፈታኞቹን፥ "ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት" ብለዋል።
"እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል" ነው ያሉት።

"ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነውም" ብለዋል።

"የተሰጣችሁን መመሪያ አክብሩ፤ ተረጋግታችሁ ፈተናችሁን ሥሩ፤ በምንም አትሸበሩ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ" ሲሉም አሳስበዋል።

Mekdes Girma best music
09/10/2022

Mekdes Girma best music

Mekdes Girma Fana Lamrot Winners While Performing on stage for New Year Holidayመቅደስ ግርማ ለ2015 አዲስ አመት በዓል በመድረክ የሰራችው

08/10/2022

የ2015 አዲስ አመት በዓልን(እንቁጣጣሽ ) አከባበር በአዳማ ከተማ ዴይሊ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር በአዳማ ከተማ የተዘጋጀ ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራም Ethiopian 2015 New Ye...

የሆረ አምቦ ኢሬቻ በዓል ከ150 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከበረመስከረም 28 ፣ 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የሆረ አምቦ ኢሬቻ በዓል ከ150 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው ዕለት በ...
08/10/2022

የሆረ አምቦ ኢሬቻ በዓል ከ150 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከበረ

መስከረም 28 ፣ 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የሆረ አምቦ ኢሬቻ በዓል ከ150 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው ዕለት በአምቦ ከተማ ተከብሯል፡፡

በአከባበር ስነ ስርዓቱ የቱለማ አባ ገዳ እና የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ጉባኤ ጸሃፊ አባ ገዳ ጎበና ሆላን ጨምሮ ሌሎች አባ ገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎች ተሳትፈዋል፡፡

የበዓሉ ተሳታፊዎች÷ የኢሬቻ ሆረ አምቦ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዳግም መከበር መጀመሩ እንዳስደሰታቸው መግለጻቸውን የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በጅግጅጋ ማካሄድ ጀመረስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይገኛል።ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተወያይቶ የተለያዩ ...
07/10/2022

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በጅግጅጋ ማካሄድ ጀመረ

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይገኛል።

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተወያይቶ የተለያዩ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

"አፍሪካ ሳይንስን የዕቅዷ ማዕከል ማድረግ አለባት"፦ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ********************** መስከረም 26/2015 (ዴይሊ ሚዲያ)የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ "አፍ...
06/10/2022

"አፍሪካ ሳይንስን የዕቅዷ ማዕከል ማድረግ አለባት"፦ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ
**********************

መስከረም 26/2015 (ዴይሊ ሚዲያ)የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ "አፍሪካ ሳይንስን የዕቅዷ ማዕከል ማድረግ አለባት" ሲሉ ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ ይህን የገለጹት የኢትዮጵያ የሳይንስ ሙዚየምን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ከጎበኙ በኋላ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ነው።

አፍሪካ ለጥናት እና ምርምር ሥራዎች የገንዘብ ድጋፍ ማሳደግ እና ከሳይንቲስቶች ጋር በመተባበር መሥራት አለባት ያሉት ፕሬዚዳቱ፣ ይህን ማድረግ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማፋጠን የሚረዱ ፖሊሲዎችን በማውጣት ረገድ አዳዲስ መረጃዎችን እና ሐሳቦችን ለማመንጨት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

Fulbaana 26, 2015 (Daily Media) Pireezidaantin Bulchiinsa Mootummaa Naannoo Oromiyaa Obbo Shimallis Abdiisaa barataa kut...
06/10/2022

Fulbaana 26, 2015 (Daily Media) Pireezidaantin Bulchiinsa Mootummaa Naannoo Oromiyaa Obbo Shimallis Abdiisaa barataa kutaa 8ffaa ibsaa kalaquun hawaasa naannoo isaa fayyadamaa taasiseef beekkamtii fi badhaasa qarshii kuma 200 kennan.

Godina Booranaa Aanaa Waacilee Ganda Weebitti kan dhalateefi barataa kutaa 8ffaa kan ta'e Aadan Huseen Diidaa rakkoo uummata naannoo isaa hubachuun waantota naannoo isaatti argaman kanneen akka dhoqqee Loonii, Ashaboo, shiboo elektirikaa, pilaastika fi sibiilota caccabaa walitti qabuun ibsaa hojjateera.

Barataan umuriin isaa ganna 15 ta'e Aadan kalaqa isaa kanaan bakka dhaloota isaa kan taate Ganda Weebiif ibsaa gumaachuun abbootiin warraa 28 tajaajila ibsaa sa’aa 24 akka argatan taasisee jira.

Pirezidaantiin Bulchiinsa Mootummaa Naannoo Oromiyaa Obbo Shimallis Abdiisaa haasaa taasisaniin "namoonni akkanaa yoo baay'atan guddinna biyyaa keessatti gahee olaanaa qaba jechuun kalaqaan cinattis barnoota idileenis cimuun murteessaa ta'uu himaniiru.

Gara fuulduraattis Mootummaan Naannoo Oromiyaa namoota dandeettii kalaqaa akkanaa qaban cinaa dhaabbachuun kan jajjabeessu ta'uu dubbataniiru.
Barataa Aadan Huseen mana barumsaa sadarkaa 2ffaa Araddaa Yaa’aa fi mana baruumsa sadarkaa 1ffaa Weeb tajaajila ibsaa akka argatan taasiseera.

Barataan Aadan Huseen kalaqa argate kanaan mana namoota dhuunfaatti ibsaa galchuun galii argataa kan jiru yoo ta'u ji'aan giddu galeessaan hanga qarshii kuma 7 argataa jira.

Aadan kalaqoota rakkoo hawaasa isaa furuu danda’an kalaquuf fedhii fi kaka’umsa guddaa kan qabu yoo ta’u mul’ata isaa kana galmaan ga’uufis deeggarsi dabalataa qorannoon deeggarame akka isaaf taasifamu gaafateera.
Abbaan kalaqaa barataa Aadan Huseen pireezidaantii Bulchiinsa Mootummaa Naannoo Oromiyaa obbo Shimallis Abdiisaatiif kennaa uffata aadaa kenneera.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን ሳይንስ ሙዚየም መርቀው  ከፈቱ **************መስከረም 24/2015 (ዴይሊ ሚዲያ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የመ...
04/10/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን ሳይንስ ሙዚየም መርቀው ከፈቱ
**************
መስከረም 24/2015 (ዴይሊ ሚዲያ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውና ዘመናዊ የሳይንስ ሙዚየም መርቀው ከፍተዋል።

የሳይንስ ሙዚየሙ ትልቁና በቀለበት ቅርፀ የተገነባው ህንፃ ከ15 ሺህ ሜትር ካሬ በሚበልጥ መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ አጠቃላይ ርዝመቱ 132 ሜትር ያህል ነው፡፡

ሙዚየሙ አዳዲስ ተሞክሮዎችና ዕውቀቶች የሚቀሰሙበት መድረክም ነው ተብሏል።

የሥነ ጥበብና የሳይንስ ሙዚየም ትላንት፣ ዛሬንና ነገን በአንድ ላይ አያይዞ ሳይንስን ጥበባዊ በሆነ መንገድ፣ ጥበብ በሳይንሳዊ መንገድ የያዘ መሆኑ ተገልጿል ፡፡

ግቢውም በሰባት ሺህ ሄክታር ያህል ስፋት አለው ተብሏል። ሙዚየሙ እጅግ ዘመናዊና የስነ ህንፃ ውበቱም በጣም ማራኪ ነው፡፡

በአይነቱ አዲስ የሆነው የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም በዛሬው እለት ይመረቃል ************መስከረም 24/2015 (ዴይሊ ሚዲያ) በመዲናችን አዲስ አበባ አስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ያለው ...
04/10/2022

በአይነቱ አዲስ የሆነው የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም በዛሬው እለት ይመረቃል
************
መስከረም 24/2015 (ዴይሊ ሚዲያ) በመዲናችን አዲስ አበባ አስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ያለው ህንጻ እና ማራኪ የጉልላት ቅርጽ ያለው ተደርጎ የተገነባው ማዕከል በአይነቱ አዲስ የሆነው የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም በዛሬው እለት ይመረቃል ::

ሙዚየሙ በ7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በኪነ-ህንጻ ንድፍ ውስጥ ያካተተው ክብ ቅርጽም በማያቋርጥ እድገት ውስጥ ያለን እድገትና የሰው ልጆችን ጥበብ የሚያመለክት ነው።

በተጓዳኝም ኢትዮጵያ በአስገራሚ ፍጥነት በማደግ ላይ ካለው ቴክኖሎጂ ጋር ለመጣመር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይም ነው።

የስነ ጥበብና የሳይንስ ሙዚየሙን አስደናቂ የሚያደርገው ምንድነው ?

👉 ሁለት ግዙፍ ህንጻዎችን በተንጣለለ ስፍራ ላይ ቢያሳርፍም 80 በመቶ የሚሆነው ክፍሉ ከ4ሺህ በላይ በሆኑ ሀገር በቀል ዛፎች፣ እጽዋትና ባሸበረቁ አበቦች የተሸፈነ ስፍራ በመሆኑ አረንጓዴነቱ ጎልቶ ይታያል።

👉 ሙዚየሙ በጥንቃቄ የተዘጋጁ የመኪና ማቆሚያዎች በተጨማሪ በዙሪያው ካሉ የከተማችን ፓርኮች ጋር የሚያገናኘው ውብ የእግረኛ መንገዶች ያሉት ነው።

👉 የአትክልት ስፍራዎቹ ጎብኚዎች አረፍ ብለው ንፋስ የሚቀበሉባቸው ምቹ መቀመጫዎችን እንዲሁም በጥበብ ስራዎች የሚዝናኑባቸውን የስነ ጥበብና የመዝናኛ ቦታዎችን የያዙ ናቸው።

👉 ትልቁ ህንጻ ከ15ሺህ ሜትር ካሬ በሚበልጥ መሬት ላይ ያረፍ ሲሆን አጠቃላይ ስፋቱ 132 ሜትር ያህል ነው።

👉 ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ በሆነ መንገድ ሃይል ከሚያመነጩ የውሃ ግድቦቻችን እንዲሁም በጣሪያው ላይ ከተገጠሙ የጸሀይ ብርሃን ሰብሳቢ መሣሪያዎች የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ አቅርቦት የሚያገኘው ይህ ሙዚየም ተፈጥሮአዊ የሃይል ማስተላለፊያዎችንና ሃይል ቆጣቢ የተፈጥሮ ብርሃንን የሚጠቀም ነው።

ይህ የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም ትላንታችንን፣ ዛሬያችንን እና ነገአችንን በአንድ ላይ አሰናስኖ ሳይንስን ጥበባዊ በሆነ መንገድ፤ ጥበብን ደግሞ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያስቃኝ በመሆኑ አስደማሚ ተሞክሮዎችና አዳዲስ እውቀቶች የሚቀሰሙበት ነው።

ህዝባዊ በዓላቱ ስኬተማ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቁ አስተዋጽኦ ለነበራቸው የፀጥታ አካላት፣ የሀይማኖት ተቋማተና አባ ገዳዎች እወቅና ተሰጠመስከረም 23/2015(ዴይሊ ሚዲያ) የአዲስ አበባ ከተማ...
03/10/2022

ህዝባዊ በዓላቱ ስኬተማ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቁ አስተዋጽኦ ለነበራቸው የፀጥታ አካላት፣ የሀይማኖት ተቋማተና አባ ገዳዎች እወቅና ተሰጠ

መስከረም 23/2015(ዴይሊ ሚዲያ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰሞኑ የተካሄዱትን ህዝባዊ በዓላት ኢትዮጲያዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ እንዲከበሩ ሚናቸው ከፍተኛ ለነበሩት የፀጥታ አካላት፣ የሀይማኖት ተቋማተና አባ ገዳዎች እወቅናና ምስጋና ተሰጥተዋል።

በእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብሩ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጰያ ህዝብ ሰላም ወዳድነት የአደባባይ ህዝባዊ በዓላት በአስቸጋሪ ወቅትም ላይ ሆነን ስኬተማ በሆነ በደመቀና ከምንም ጊዜ በላይ ውጤታማ በሆነ መልኩ ማክበር መቻሉን ገልፀዋል።

ህዝባዊ በዓላቱ ያለ ምንም ልዩነት የጋራ በዓሎቻችን ናቸው በማለት ሁሉም በያለበት የበኩሉን አስተዋጽዖ በማድረግ የኢትዮጵያን ገፅታ ከፍ ባለ መልኩ ማክበር ችለናል ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች ተቀራርበንና ተደጋግፈን በመስራት በመተባበር በሌሎች ሥራዎቻችን ለይም ውጤታማ መሆን እንደምንችል የታየባቸው ህዝባዊ በዓላት ነበሩም ብለዋል ::

በክረምቱ ሃገራችን ከነበረችበት አጠቃላይ ሁኔታ ህዝባዊ በዓላት በአደባባይ ወጥቶ ለማክበር ምቹ ባልሆነበት በሰላም ወዳዱ ኢትዮጲያዊያን ፥ በፀጥታ አካላት፡ የሃይማኖት አባቶች : አባገዳዎች ፥ በየደረጃው በሚገኝ አመራር ትልቅ መተበበር ስለነበረ የህዝባዊ በዓላቱ ስኬተማ ሆነው መጠናቀቅ ችለዋል ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሁሉም ደረጃ ህዝባዊ በዓላቱ እጅግ ስኬታማ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በከተማ አስተዳደሩ ሥም አመስግነዋል ሲል የከንቲባ ጽሕፈት ቤት አሰታውቋል።

አትሌቱ ከማንኛውም ውድድር ለ5 ዓመት ከ4 ወር ታገደ መስከረም 23/2015 (ዴይሊ ሚዲያ) አትሌት ታዬ ግርማ የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም በመጠቀሙ ለ5 ዓመት ከ4 ወር ከማንኛውም የ...
03/10/2022

አትሌቱ ከማንኛውም ውድድር ለ5 ዓመት ከ4 ወር ታገደ

መስከረም 23/2015 (ዴይሊ ሚዲያ) አትሌት ታዬ ግርማ የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም በመጠቀሙ ለ5 ዓመት ከ4 ወር ከማንኛውም የስፖርት ውድድር መታገዱን የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አስታወቀ።

ከመጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ አትሌቱ ያስመዘገባቸው ውጤቶች እንዲሰረዙና በውድድሮቹ ያገኛቸው ሽልማቶች ተመላሽ እንዲሆኑ ውሳኔ ማስተላለፉን ባለስልጣኑ አመላክቷል።

መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 50ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ እንዲሁም ሰኔ 13 ቀን 2013 ዓ.ም በጣሊያን ቴሌሴ ቴርሜ ከተማ በተከናወነው የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ በተደረገው የአበረታች ቅመሞች ምርመራ አትሌት ታዬ ግርማ ‘Erythropoietin’ የተሰኘ የተከለከለ አበረታች ቅመም ሁለት ጊዜ መጠቀሙን የሚያመላክት ውጤት ማግኘት መቻሉን አመላክቷል።

ባለስልጣኑ ውጤቱን ተመርኩዞ በአትሌት ታዬ ላይ ጊዜያዊ እገዳ በመጣል ባካሄደው ምርምራ አትሌቱ ጥፋተኛ ሆኖ አግኝቶታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም አትሌት ታዬ ከመጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያስመዘገባቸው ውጤቶች እንዲሰረዙ እና በውድድሮቹ ያገኛቸው ሽልማቶች ተመላሽ እንዲሆኑ የቅጣት ውሳኔ እንደተላለፈበት ነው ባለስልጣኑ የጠቆመው።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ የሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አርሰዲ እሬቻ በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ መጠናቀቁን ገለጹ መስከረም 22 ቀን 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የሆራ ፊንፊኔ እና ሆ...
02/10/2022

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ የሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አርሰዲ እሬቻ በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ መጠናቀቁን ገለጹ

መስከረም 22 ቀን 2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አርሰዲ እሬቻ በዓል ባህልና ወጉን በጠበቀ መልኩ በሰላምና በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ መጠናቀቁን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

የዘንድሮው የእሬቻ በዓል በሰላምና በደመቀ ሁኔታ መከበሩን አስመልክተው ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ የምስጋና መግለጫ ሰጥተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት እሬቻ ባህልና ወጉን በጠበቀ እና እሴቱን ባጎላ መልኩ ደምቆ እንዲከበር ለረዳን ፈጣሪ ምስጋና በማቅረብ፤ በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ጉልህ ሚና ለተጫወቱት አካላትም ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት ሽመልስ የኦሮሞ እና መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በበዓሉ ደምቃችሁ አድምቀችሁናልና ለዚህ ታላቅ ሁነት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና በራሴ ስም ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ቤት ያፈራውን ይዛችሁ በየመንገዱና በየአዳባበዮቹ የበዓሉ ታዳሚ ወንድሞቻችሁን በታላቅ ክብር ተቀብላችሁ በማስተናገድ ላሳያችሁት ታላቅ ፍቅር ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

የቢሾፍቱ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎችም ደምቆ ለተመመው የበዓሉ ታዳሚ በደማቁ አስተናግዳችኋልና አመሰግናለሁ ነው ያሉት አቶ ሽመልስ።

እሬቻ ለሁለቱ ከተሞች በኢኮኖሚውም ሆነ በባህሉ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም ጠቁመዋል።

ውቡን ባህሎቻችንን ላልተፈለገ ዓላማ ለማዋል ሁሌም የሚተጉ ጠላቶች ምኞታቸው ከሽፏል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የጸጥታ መዋቅሩ ሌት ተቀን ሳይዘናጋ በዓሉ እንዲደምቅ እና የጠላት ምኞት እንዲከሽፍ በማድረጋችሁ የስራችሁ ሁጤት ደምቋልና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

እሬቻ ሳይበረዝና ሳይደበዝዝ ወጉና እሴቱን ጠብቆ ከትውልድ ትውልድ እንዲሸጋገር ላደረጋችሁ፣ ዛሬም በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር ረጅም መንገድ ተጉዛችሁ ለታደማችሁ ህዝባችን፣ አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች 'ገለቶማ' ልላችሁ እወዳለሁ በማለት ምስጋና አቅርበዋል።

የእሬቻ በዓል አከባበር መስህብ ይሆን ዘንድ የዓለም ማህበረሰብ እንዲያውቀው ላደረጋችሁ እና አይተኬ ሚና ለተጫወታችሁ የሀገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ የሚዲያ ተቋማት በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

Fulb. 21, 2015 (Daily Media)Walitti qabaa Gamtaa Abbootii Gadaafi Abbaan Gadaa Tuulamaa Goobanaa Hoolaa,Ayyaana irreecha...
01/10/2022

Fulb. 21, 2015 (Daily Media)Walitti qabaa Gamtaa Abbootii Gadaafi Abbaan Gadaa Tuulamaa Goobanaa Hoolaa,Ayyaana irreecha bara 2015 ilaalchisuun ibsa kennaniiru.

Hoogganaan Biiroo Aadaaf Tuurizimii Oromiyaa Huseen Fayyisoo, duudhaa Sirna Gadaafi Irreechaa dhugoomsuun tasgabbiin ayyaana Irreecha Hora Finfinnee xumuruu keessaniif ulfaadhaa jedhan.

Ayyaana Hora Harsadiis akkasuma nagaan irreeffattanii diina qaaneesitanii akka galtan abdiin qabaas jedhan.

Kantiibaan Magaalaa Bishooftuu Obbo Alamaayyoo Asaffaa, gama isaaniitiin giddu gala Irreechaa Hora Harsadiitti baga nagaan dhuftan jedhan.

እናመሰግናለን!!በከተማችን አዲስ አበባ "የሆራ ፊንፊኔ " የኢሬቻ በአል ባማረና በደመቀ ባህላዊ እሴቱንና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ በሰላም ተጠናቋል፡፡ከለዉጡ ወዲህ ለ4ኛ ጊዜ በከተማች...
01/10/2022

እናመሰግናለን!!

በከተማችን አዲስ አበባ "የሆራ ፊንፊኔ " የኢሬቻ በአል ባማረና በደመቀ ባህላዊ እሴቱንና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ በሰላም ተጠናቋል፡፡
ከለዉጡ ወዲህ ለ4ኛ ጊዜ በከተማችን አዲስ አበባ የተከበረውና በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ የተሳተፈበት የዘንድሮው የሆራ ፊንፊኔ በዓል ገና ከዋዜማው ጀምሮ ባማረ ድባብ፣ በከፍተኛ ድምቀትና ውበት፣ በእንግዳ ተቀባይነት ስሜት ባህላዊ እሴቱንና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ከመቼውም ጊዜ በላይ በጋራ ያከበርነው፣ ትብብራችን ጎልቶ የወጣበት፣ ኢትዮጵያዊ አብሮነትንና ህብረብሄራዊነት ደምቆና ፈክቶ ድንቅ የበዓል አከባበር የታየበት ነው፡፡

አሸባሪ ቡድኖች በቀቢፀ ተስፋ በጦር ሜዳ የደረሰባቸውን ኪሳራ ለማካካስ በከተማችን የተከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የሁከት ማእከል ለማድረግ በተጨባጭ ቢንቀሳቀሱም፣ በሰላም ወዳዱ ህዝብ፣ በፀጥታ ሃይሎችና ህዝባዊ ሰራዊታችን እንዲሁም በአመራሩ ቅንጅትና ትብብር የጥፋት ህልማቸውን በማክሸፍ ሰላማዊና የተረጋጋ በዓል ማክበር ተችሏል።ለዚህም እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ!!
ይህ በዓል ስኬታማ እና ያማረ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ዋናውንና የማይተካ ሚና የተጫወተው የአዲስ አበባ ህዝብ ትልቅ ምስጋና ይገባዋል፡፡ከተማዋን ከማስዋብ እና አካባቢን ከማፅዳት ጀምሮ እንግዶቹን በየአካባቢው ባማረ መስተንግዶ በመቀበል፣በዓሉ ሰላማዊ ድባቡን ይዞ እንዲጠናቀቅ መንደሩንና አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ፣ የፀረ ሰላም ሃይሎችን በያሉበት አጋልጦ በመስጠት ላበረከተው አስተዋፅኦ ከልብ እናመሰግናለን!!
አባገዳዎች፣ ሀደሲንቄዎች፣ ቄሮዎች፣ ቀሬዎች እና ፎሌዎች ይህ በዓል እሴቱንና ስርዓቱን ጠብቆ በከፍተኛ ድምቀትና ሰላማዊነት እንዲከበር ስላደረጋችሁ እናመሰግናለን፡፡

በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በበቂ ዝግጅትና በሀላፊነት ስሜት በብቃት ለሰራችሁ መላው የከተማችን የጸጥታ አካላት፣ የሰላም ሰራዊት አባላት እንዲሁም የደንብ ማስከበር አገልግሎት ምስጋናችንን እናቀርባለን!!የከተማችን አዲስ አበባ ወጣቶች በዓሉ በመከባበርና በመተሳሰብ በአብሮነት እንዲከበር ስላደረጋችሁ እናመሰግናለን፡፡
በየደረጃው የምትገኙ አመራሮች ይህ በዓል ያለአንዳች እክል በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በትጋትና በንቃት በየተመደባችሁበት ሃላፊነታችሁን ስለተወጣችሁ እናመሰግናለን!!

ወደከተማችን በዓሉን ለመታደም የመጣችሁ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ይህ በዓል የጋራችን መሆኑን በተግባር በማረጋገጥ ላሳያችሁት ታላቅ የአብሮነት ተምሳሌትነት እንዲሁም ለከተማችን ሰላም ለነበራችሁ ሚና እናመሰግናለን!!
የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ለማበላሸት የሚፈልጉ የውጪ ሃይሎች በዚህ በዓል እንከኖችን በመፈለግ የሃገራችንን ገፅታ ለማበላሸት ቢቋምጡም አጠቃላይ የሚድያ ተቋማትና የሚድያ ባለሙያዎቻች ትክክለኛ የበዓሉን መልካም ገፅታ አጉልታችሁ ስለዘገባችሁና የህዝቡን አብሮነት በሚገባ ስላሳያችሁ እናመሰግናለን!!
አሁንም ቢሆን እንግዶቻችን እንዳመጣጣቸው ወደየአካባቢው በሰላም እስኪመለሱ ድረስ በተጀመረው የእንግዳ ተቀባይነት ስሜት እስከመጨረሻው ድረስ በትጋት እና በቅንጅት መስራታችንን እንድንቀጥል እና በነገው እለት የሚከበረው የሆራ አርሰዴ በዓልም በሰላም እንዲጠናቀቅ ፣ ሁላችንም ይበልጥ ተጠናክረን በትብብርና በሃላፊነት ስሜት ሃላፊነታችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ!

በድጋሚ ለሁላችንም መልካም የኢሬቻ በዓል ይሁንልን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!

IRREECHAA 2015🌼🌼🌼
01/10/2022

IRREECHAA 2015🌼🌼🌼

ማዲንጎ ራሱን ለሀገሩ የሰጠ ለትውልዱ ትልቅ አሻራ ያስቀመጠ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤመስከረም 19/2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ማዲንጎ ...
29/09/2022

ማዲንጎ ራሱን ለሀገሩ የሰጠ ለትውልዱ ትልቅ አሻራ ያስቀመጠ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

መስከረም 19/2015 (ዴይሊ ሚዲያ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ማዲንጎ ራሱን ለሀገሩ የሰጠ ለትውልዱ ትልቅ አሻራ ያስቀመጠ ነው” ሲሉ ገለጹ፡፡

ከንቲባ በማዲንጎ አፈወርቅ የአስከሬን ሽኝት ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት “ማዲንጎ በስጋ ቢለየንም በስራው ህያው ነው“ ብለዋል፡፡

የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘው ተሻገርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃፊዎች በአስክሬን ሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

የአርቲስት ማዲንጎ አጭር የስራና የህይወት ታሪክ የቀረበ ሲሆን የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው “ለህብረብሔራዊ አንድነት፣ ለፖን አፍሪካኒዝም ያቀነቀ እና ታሪክ የሰራ ነው“ ብለዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነም ከደርግ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ለሀገር ጥሪ ምላሽ መስጠቱንና ሰራዊቱን የጦር ቀጠና በመሄድ ማነቃቃቱን ገልፀው ለቤተሰቦቹ እና አድናቂዎቹ መፅናናትን ተመኝቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ድምፃዊ ዳዊት ይፍሩ የድምፃዊው ስራና ልዮ ሙያዊ ችሎታ ሲሆን የአርቲስቱ ልጅ ዲቦራ ማዲንጎም የስንብት ንግግር አድርጋለች።

አንጋፋው አርቲስት መሀሙድ አህሙድን ጨምሮ ሌሎችም ታዋቂ አርቲስቶች በማዲንጎ ህልፈት የተሠማቸውን መሪር ሀዘን ገልፀዋል።

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daily Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share