Ethiopian passport services

  • Home
  • Ethiopian passport services

Ethiopian passport services Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian passport services, Digital creator, .

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ  ፅ/ቤት አገልግሎት መስጠት ጀመረ። ከሰኔ 11፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት የጀመረ ሲሆን በጊዜያዊነት የጀመራቸው አገል...
18/06/2024

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ከሰኔ 11፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት የጀመረ ሲሆን በጊዜያዊነት የጀመራቸው አገልግሎቶ ፓስፓርት ማደስ፣ የጠፋ ፓስፖርት መተካት፣ የተበላሸ ወይ እርማት የመስጠት አገልግሎቶች ናቸው።

The Mekelle branch of the Immigration and Citizenship Service is now open and offering services. Currently, the branch provides passport renewals, lost passport replacements, and replacements for damaged passports.

——

አዋሳ፣ አዳማ እና ድሬዳዋ ቅርንጫፍ  ፓስፖርታችሁን የምትወስዱ ደንበኞቻችን ባመለከታችሁበት ኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚያወጣው ኘሮግራም መሰረት በመገኘት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ ...
31/05/2024

አዋሳ፣ አዳማ እና ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፓስፖርታችሁን የምትወስዱ ደንበኞቻችን ባመለከታችሁበት ኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚያወጣው ኘሮግራም መሰረት በመገኘት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ወደ ተቋማችን ስትመጡ ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት  ሶስት ረቂቅ አዋጆችን ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መራግንቦት 22 ፣ 2016 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ29ኛ መደበኛ ስብ...
31/05/2024

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ሶስት ረቂቅ አዋጆችን ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መራ
ግንቦት 22 ፣ 2016 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ29ኛ መደበኛ ስብሰባው ሶስት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 354/9 ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ረቂቅ አዋጁ ለዜጎችና ለውጭ አገር ዜጎች የጉዞ ሰነድ፣ ህጋዊ የይለፍ ፈቃድ ጊዜያዊና ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ ለመስጠት፣ በህግ የተከለከሉ ሰዎች በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር እንዳይወጡና ወደ አገር እንዳይግቡ ቁጥጥር በማደረግ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመቆጣጠር የሀገርን ብሔራዊ ደህንነትና ሉአላዊነት ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ምክር ቤቱ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት 354/9 ማሻሻያ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 19/2016 አድርጎ በሙሉ ድምጽ ለውጭ ግንኙነትና ለሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ መርቷል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት ከተቀመጡት መሰረታዊ መብቶች አንዱ የሆነውን የዜጎችን የመዘዋወር ነፃነት ማስከበር ያስችል ዘንድ ለኢትዮጵያውያንና ለውጭ አገር ሰዎች ሕጋዊ የጉዞ ሰነድና ቪዛ ለመስጠትና ለማረጋገጥ እንዲሁም ብሔራዊ መታወቂያን በመስጠት የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያግዝ ረቂቅ አዋጅ መሆኑን ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡

ምክር ቤቱም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንደገና ማቋቋሚያ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 20/2016 አድርጎ ለዝርዝር ዕይታ ለውጭ ግንኙነትና ለሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቷል፡፡ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ አጭር ማብራሪያ የሰጡት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ የረቂቅ አዋጁ ዋና ዓላማ አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ ተደራሽ፣ ግልጽና ውጤታማ ለማድረግ ሲሆን የአፈፃፀም ስልቱ ህገ-መንግስቱን መሠረት ያደረገና ዘለቄታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ የመልካም አስተዳደር መርሆዎችና አሰራሮች በሁሉም ዘርፍ ተግባራዊ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያግዝ ረቂቅ አዋጅ መሆኑን ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡

የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባን አስመልክቶ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 21/2016 ሆኖ ለዝርዝር ዕይታ ለህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ ተመርቷል፡፡

የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ የተመሩትን ረቂቅ አዋጆች ካላቸው ሀገራዊ ፋይዳና ጠቀሜታ እንዲሁም ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ ያላቸውን መስተጋብር ቋሚ ኮሚቴዎቹ ትኩረት ሰጥተው በዝርዝር እንዲያዩት ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

——

ደሴ፣ ጅግጅጋ፣ ሰመራ፣ ሆሳዕና፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ጅማ እና ባህር ዳር ቅርንጫፍ  ፓስፖርታችሁን የምትወስዱ ደንበኞቻችን ባመለከታችሁበት ኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚያወጣው ኘሮግራም መሰረ...
30/05/2024

ደሴ፣ ጅግጅጋ፣ ሰመራ፣ ሆሳዕና፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ጅማ እና ባህር ዳር ቅርንጫፍ ፓስፖርታችሁን የምትወስዱ ደንበኞቻችን ባመለከታችሁበት ኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚያወጣው ኘሮግራም መሰረት በመገኘት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ወደ ተቋማችን ስትመጡ ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።

——

ለፓስፖርት አገልግሎት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች 1.  #ለአዲስ ፓስፖርት ጠያቂዎች  1.1 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ጠያቂዎች   የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም፣  አገል...
30/05/2024

ለፓስፖርት አገልግሎት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
1. #ለአዲስ ፓስፖርት ጠያቂዎች

1.1 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ጠያቂዎች
 የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም፣
 አገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ ወይም፣
 ውጭ አገር ነዋሪ ሆነው በሊሴፓሴ የገቡ ከሆነ ወደአገር በገቡ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ
ሊሴፓሴውን ይዘው በመቅረብ መስተናገድ ይችላሉ፡፡

1.2 #እድሜያቸው ከ18 አመት በታች ለሆኑ አዲስ ፓስፖርት ጠያቂዎች

o ፓስፖርት ሲጠየቅ ህፃኑ በአካል መቅረብ አለበት፣
1.2.1 ወላጆች ይዘው ሲቀርቡ ማሟላት ያለባቸው
 እድሜው ከ6 ወር በታች ለሆነ ህፃን የሆስፒታል የልደት ማስረጃ በማቅረብ የሚስተናገዱ ሲሆን
ከ6 ወር በላይ ለሆናቸው ህፃናት በወሳ„ኩነቶች የተዘጋጀ የልደት ሰርተፊኬት ማቅረብ
ይኖርባቸዋል፣
 መጠኑ ¾ የሆነ የህፃኑ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣
 የወላጅ የቀበሌ /የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት/፣
ፓስፖርት ለመቀየር በሚቀርብ ጥያቄ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች

#እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ፣

1 የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ ወይም ገጽቹ ያለቁ ፓስፖርት ለመቀየር o የቀድሞው ፓስፖርት ከነኮፒው ተያይዞ ሲቀርብ፣ 2 የጠፋ ወይም የተበላሸ ፓስፖርት ለመቀየር
- ፓስፖርቱ ከጠፋ የፖሊስ ማስረጃ ወይም ውጭ ሀገር የጠፋ ከሆነ የገቡበትን ሊሴፓሴ፣ - ፓስፖርቱ ከተበላሸ የተበላሸውን ፓስፖርት ከነኮፒው አያይዞ ማቅረብ፣ ያስፈልጋል።

3 ለፓስፖርት እርማት የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች
- ስም ለመለወጥ የፍ/ቤት ማስረጃ፣
- ፓስፖርቱ እና ለእርማት የሚያስፈልጉ መረጃዎች (የልደት ሰርትፍኬት) ዋናው ከነኮፒው መቅረብ አለበት፣ - ከ18 አመት በታች ለሆኑ የፓስፖርት እድሳት ጠያቂዎች
- የህፃኑ ፓስፖርት ዋናው ከነኮፒው፣
- ለማስፈፀም የቀረበው አባት ከሆነ የአባት የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም
የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ፣
- እናት ከሆነች የህፃኑን የልደት ሰርትፍጄት፣ የእናት የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት
ወይም የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ፣ ማቅረብ ያስፈልጋል።
የህጻኑ የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ ከወላጅ ውጭ በሞግዚት ፣ በተወካይ እና በጉዲፈቻ የቀረበ ከሆነ
የሞግዚትነት የውክልና የአሳዳጊነት ወይም ጉዲፈቻ አድራጊነት የተፈቀደበት ማስረጃ አግባብ ካለው
መንግስታዊ አካል ማቅረብ ያስፈልጋል።

#ማሳሰቢያ፡-
- በጊዜያዊ መታወቂያ አገልግሎት አንሰጥም፣


- ማንኛውም ባለጉዳይ የሚያቀርበው ሰነድ ህጋዊ እና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት፣
- በተጭበረበረ ሰነድ ለመስተናገድ መሞከር በህግ ያስጠይቃል፡፡

#ለግንዛቤዎ
1. በተደጋጋሚ ወደ ውጭ የሚመላለሱ በመሆኑ ምክንያት የፓስፖርቶ ገጾች ከፓስፖርቱ የአገልግሎት
ጊዜ በፊት ቢያልቅብዎ ባለ 64 ገጽ ፓስፖርት በአገልግሎት ላይ ያዋልን ስለሆነ መጠየቅ ይችላሉ።

2 ፓስፖርት #በአስቸኳይ ለማግኘት የሚያስገድድ ሁኔታ ቢገጥሞት ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ
እንዲሁም ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማሟላት የጠበቅበታል፦
 ለህክምና ከሆነ የሕክምና ማስረጃ
 የውጭ የትምህርት ዕድል ያገኙ የጀመሩት ፕሮሰስ የሚያሳይና የተምህርት ማስረጃ
 ለመንግስት ስራ ክሆነ የመስሪያቤቱ ደብዳቤና የመ/ቤት መታወቅያ
 የውጭ አገር ኗሪ ከሆኑ መኖሪያ ፍቃድ ወይም ቪዛ
 ለDV ደርሶት ፕሮሶስ የጀመሩ
 ኢምባሲ ቀጠሮ ካላቸው የኢምባሲ ቀጠሮ ማቅረብ የሚችሉ ከሆኑ
 መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሰሩ የድርጅቱ መታውቅያና የሚሄዱበት ምክንያት የሚገልጽ
ደብዳቤ ካቀረቡ፣

#ነጋዴ ክሆኑ
o የከፈሉበት LC
o የታደሰ ንግድ ፍቃድ
o ውል ያላቸው ከሆኑ ቅድሚያ መስተናገድ ይችላሉ።
3. መንግስት ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረገው ሕገወጥ ስደት በማስቆም ሕጋዊ የውጭ አገር የስራ
ስምሪት ለማጠናከር ቁጥጥር እና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።

#በመሆኑም ፓስፖርት ለማውጣት ወደ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ አገልግሎት
መስጪያ ማእከላት ለምትመጡ ዜጎች የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት
ይተበቅባቸዋል፦
ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 55 ዓመት ለሆኑ ዜጎች ላይ ከተዘረዘሩት መስፈርቶች(ምሳሌ የቀበሌ መታወቅያ)
በተጨማሪ፦

 የመንስግት ሰራትኛ መሆናቸው የመ/ቤት መታወቅያ
 ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
 በግል ድርጅት ተቀጣሪ ከሆኑ የመ/ቤቱ ደብዳቤና መታወቅያ
 መንግስታዊ በልሆኑ ድርጅቶች (NGO) ተቀጣሪ ከሆኑ የድርጅቱ ደብዳቤና መታወቅያ
 ለህክምና ለሚሄዱ የሕክምና ማስረጃ
 ለትምህርት ለሚሔዱ የተጻጻፉበት ማስረጀ
 ለጉብኝት ከሆኑ የግብዣ ደብዳቤ

4. #በሕጋዊ መንገድ ለሰራ ወደ ውጭ አገር የሚሄድ ማንኛውም ሰራተኛ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማሟላት የጠበቅበታል፦
ሀ) ቢያንስ የስምንተኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀ፣ እና
ለ) በሚቀጠርበት የሥራ መስክ አግባብ ካለው የምዘና ማዕከል (ቴክኒክና ሙያ) የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
ማስረጃ የያዘ፣ መሆን አለበት፡፡
ሐ) ዕድሜው ከ21 ዓመት በላይ የሆነ፣
መ) የጤና ምርመራ ያደረገ መሆን እንዳአበት ይደነግጋል።


#አዲስ አበባ ከሚገኘው የዋና መምሪያው ጽሕፈት ቤት በተጨማሪ ከዚህ ቀጥሎ በተገለጹት
ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችና እንዲሁም በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ማግኘት
ይችላሉ።
1 ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
2 ደሴ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
3 ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
4 ባህርዳር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
5 መቐለ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
6 ጅማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
7. ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
8. ሳመራ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
9. አዳማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

ለበለጠ መረጃ ወይም ለቅሬታ አድራሻችን
ነጻ ስልክ 8133
መደበኛ ስልክ 0111560167 ወይም 0118287216
website www.immigration.gov.et


Face book, MDINA Ethiopia
ኢሜይል support@ immigration.gov.et
ፖስታ 5741

ለክቡራን ደንበኞቻችንፓስፖርት ደርሷችሁ ለመውሰድ ወደተቋማችን ስትመጡ የተለያዩ ህገወጦች በለሊት መጣችሁ እንድትሰለፉ እና ለአላስፈላጊ ወጭ እንድትዳረጉ የተሳሳተ መረጃ እየሰጡ መሆኑን የተለያ...
30/05/2024

ለክቡራን ደንበኞቻችን

ፓስፖርት ደርሷችሁ ለመውሰድ ወደተቋማችን ስትመጡ የተለያዩ ህገወጦች በለሊት መጣችሁ እንድትሰለፉ እና ለአላስፈላጊ ወጭ እንድትዳረጉ የተሳሳተ መረጃ እየሰጡ መሆኑን የተለያዩ ጥቆማዎች እየደረሱን ይገኛሉ፡፡

ስለሆነም በመንግስት ስራ ሰዓት ብቻ ወደተቋማችን በመምጣት መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ወደተቋማችን ስትመጡ በስም መነሻ ፊደላችሁ መሰረት የምትስተናገዱ ስለሆነ በለሊት መሰለፍ የማይጠበቅባችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

__

ባህር ዳር፣ ጅግጅጋ፣ ጅማ፣ ሆሳዕና እና ድሬዳዋ ቅርንጫፍ  ፓስፖርታችሁን የምትወስዱ ደንበኞቻችን ባመለከታችሁበት ኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚያወጣው ኘሮግራም መሰረት በመገኘት ፓስፖርታች...
30/05/2024

ባህር ዳር፣ ጅግጅጋ፣ ጅማ፣ ሆሳዕና እና ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፓስፖርታችሁን የምትወስዱ ደንበኞቻችን ባመለከታችሁበት ኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚያወጣው ኘሮግራም መሰረት በመገኘት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ወደ ተቋማችን ስትመጡ ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ይፋዊ ገጾቻችንን እና ቻናሎቻችንን ብቻ ለታማኝ አገልግሎቶች እና ማስታወቂያዎች ይጠቀሙ።

Tajaajilli Immigireeshinii fi Lammummaa gamoo haaraa waajjira damee Jimmaatti eebbiseera.Sanbata Caamsaa 17/2016 bakka q...
30/05/2024

Tajaajilli Immigireeshinii fi Lammummaa gamoo haaraa waajjira damee Jimmaatti eebbiseera.
Sanbata Caamsaa 17/2016 bakka qondaaltonni Tajaajila Immigireeshinii fi Lammummaa Godina Jimmaa, Kantiibaan Magaalaa Jimmaa, Hogganaan Waajjira Badhaadhina Godina Jimmaa, Pireezidaantiin Yuunivarsiitii Jimmaa, abbootiin amantaa fi jiraattonni magaalaa Jimmaa affeeramanii argamanitti gamoon haaraan Dhaabbata lammummaa fi imigrationii damee jimmaa eebbifameera.

Daarektarri Daarektoreetii Qophii Sanadoota Imala Tajaajila lammummaa fi imigrationi Obbo Mulugeta Tadese Eebba gamoo kana irratti argamaniiru, dubbii isaaniitiinis Tajaajila ammayyaa fi dhaqqabamaa nageenya qabuu fi qulqullina qabu diriirsuun mirgoota bu’uuraa keessaa tokko ta’e mirga bilisummaa sochii mirkaneessuuf haaromsaa fi ijaarsi dhaabbilee walitti fufiinsa qabu hedduun gaggeeffamaa jiraachuu ibsaniiru.

Waajjira imigrationi damee Jimmaatti Hoggantuun Tajaajila Immigireeshinii fi Lammummaa Aadde Samiraa Khaliifaa akka jedhanitti, Waajjirri Karnaaf erga banamee waggoota hedduu ta'us, bakki tajaajila itti kennan mijataa ta'e dhabuu irraa kan ka'e rakkoon isaan mudachaa turuu fi amma gammachuu guddaan itti dhagahamu ibsani jiru.

Address


Telephone

+251916908629

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian passport services posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share