mehamedjiwad

mehamedjiwad MM

23/11/2024

መቱ ዩኒቨርስቲ ያላችሁ የአማራ ተማሪዎች ጥንቃቄ አድርጉ‼️ የተሸረበ ሴራ አለ‼️

12/08/2024
12/11/2023

ጋናዊው አጥቂ ራፋኤል ድዋሜና በጨዋታ መሐል ሕይወቱ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልባኒያ ሊግ ሲጫወት የነበረው ጋናዊው አጥቂ ራፋኢል ዳዋሜና ራሱን ስቶ ከወደቀ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን የአልባኒያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

የ28 ዓመቱ ራፋኤል ለአልባኒያ ሱፐርሊግ ተሳታፊው ኢግናቲያ ክለብ ከፓርቲዛኒ ጋር እየተጫወተ እያለ ነው ተዝለፍልፎ በወደቀበት ሕይወቱ ያለፈው፡፡

ተጫዋቹ ከዚህ በፊት ከልብ ሕመም ጋር በተያያዘ እግር ኳስ መጫወት እንዲያቆም ተነግሮት እንደነበር ቢ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

ድዋሜና በዘንድሮው የውድድር ዘመን በአልባኒያ ሊግ ዘጠኝ ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ተጫዋች ነበር፡፡
የወጣቱን አጥቂ ድንገተኛ ሕልፈት ተከትሎ በአልባኒያ ሊግ የሚደረጉ ጨዋታዎች ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፈዋል፡፡

የአልባኒያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በተጫዋቹ ሕልፈት የተሰማውን ሐዘን ገልጾ÷ ለቤተሰቦቹ እና ለመላው ጋናውያን መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

ድዋሜና በ2017 ብራይተንን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ቢደርስም ከልብ ጋር በተያያዘ የሕክምና ምርመራውን ባለማለፉ ስምምነቱ መቋረጡ ይታወሳል፡፡



ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

11/11/2023

ግልፅ ከመሆኑ ብዛት የተሰወረብን እውነታ!…
ዱንያ ሶስት ቀን ናት።
ትናንት ኖረን አልፈነዋል!
ዛሬ ቋሚ አይደለም!
ነገን አናውቀውም!
:
የዱንያ እንግልት፣ ስቃይ ሲጠናብህ ለነፍስህ ይህን ንገረው። ዱንያ ጠፊ ናት!
ዱንያችንን ለማሳመር መትጋታችን የአላህ ትእዛዝ ነው። በዚህች ዓለም ውስጥ ለሰዎች የሚጠቅም አንዳች ነገር ማበርከት ቢያቅተን የሰው ሸክም እንዳንሆን የምንችለውን ለማድረግ እንለፋለን እንጂ የምድር ዓለም እንዳትጠፋ ማድረግ የምንችለው አንዳች ነገር የለም!
:
አንድ ቀን የለፋንለትን ሀብት፣ ዝና፣ ስልጣን… ለተተኪ ትተን እንሰወራለን። ለአኺራችን ካሳለፍነው መልካም ስራ ውጪ ቅንጣት ነገር ይዘን አንጓዝም።
:
ከሰዎች ጋር በቁስ ልንወዳደር ወደ ምድር አልመጣንም!
ወደ ዱንያ የመጣነው ልትጓዝ ነው። ቋሚ አይደለንም። የምንቆይ ከመሰለንም ለማያልቀው የአኺራ ጉዞ የምንሰንቅበት ጊዜ ብቻ ነው። ለዚያ ጉዞ የሚጠቅመው ስንቅ ደግሞ አላህ የሚወደውን መፈፀምና የርሱን ውዴታ መሸመት ብቻ ነው። ከዚያ ውጪ ሁሉም ቅዠት ነው! ለመጪው ከባድ ጉዞ ምንም ፋይዳ የለውም!

11/11/2023

የምዕራባውያን ማዕቀብ ሩሲያ የራሷን አቅም እንድታሳድግ ዕድል ፈጥሯል - ዲሜትሪ ፔስኮቭ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሉት ማዕቀብ ሞስኮ የራሷን አቅም በሚገባ እንድትጠቀም አስችሏታል ሲሉ የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ገለጹ፡፡

ቃል አቀባዩ የምዕራባውያን ሀገራት ከሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ጋር ተያይዞ በሞስኮ ላይ የጣሉት ዘርፈብዙ ማዕቀብ መልካም እድሎችን ይዞ እንደመጣ ተናግረዋል፡፡

ማዕቀቡ ሞስኮ ሀገር በቀል እውቀቶችን በትኩረት በመጠቀም ከውጪ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በራሷ አቅም እንድትተካ አስችሏል ነው ያሉት፡፡

ሩሲያ የተጣለባትን ዘርፈ ብዙ ማዕቀብ መቋቋም መቻሏም ምዕራባውያንን ክፉኛ ማስደንገጡን አንስተዋል፡፡

በአንጻሩ ማዕቀቡ በምዕራባውያን ሀገራት ኩባንያዎች ላይ 250 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ኪሳራ ማድረሱን ነው ያስረዱት፡፡

ከዚህ ባለፈም የአውሮፓ ሀገራት ከሩሲያ ጋር የነበራቸው የነዳጅ ንግድ ግንኙነት መቋረጥ ሀገራቱ ለአሜሪካ ውድ የሃይል አቅርቦት ጥገኛ እንዲሆኑ አስገድዷቸዋል ብለዋል፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሴርጌ ላቭሮቭ በበኩላቸው÷የተጣለውን ማዕቀብ ተከትሎ ሞስኮ ከምዕራባውያን ጫና ነጻ የሆነ የንግድ ሥርዓት እንደምትገነባ ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሰረትም አዳዲስ የንግድ ኮሪደሮችና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ለማቋቋም እንደወሰነች መናገራቸውን አር ቲ ዘግቧል፡

11/11/2023

የኢትዮጵያ ኡለማዎች

[ክፍል 1]

ከእስልምና አብይ መገለጫ ጉልህ አንጸባራቂ መልኮች መካከል ዋነኛው እና ቀዳሚው ለእውቀት እና ለአዋቂዎች የሰጠው ሁነኛ ስፍራ ነው።

ለዚህም ከቃላቁ ቅዱስ ቁርዓን ጀምሮ የውዱን ነብይ አስተምህሮ እየጠቀስን እውቀት እና ዒስላም
ዒስላም እና እውቀት የማይነጣጠሉ መንታ ገጽታዎች ስለመሆናቸው ለእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች መገናገሩ ለቀባሪ ሞት ማርዳት ይሆናል።

ዒስላም ለእውቀት እና ለአዋቂዎች የክብር ካባ ያለብሳል። ይሾማል፣ ይሸልማል ፣ ያልቃል በከፍታ ማዕበል ያናውጣል ።በትውልዶች መሐል ከዘመን ዘመን እያሻገረ ህያው ያደርጋል።

አዎ ! ዒልም ፋና ነው ፣ ብርሐን ነው፣ እንደ ሙሳ ዓለይሒ ሰላም ብትር የነጻነት መንገድን ማመላካቻ መሳሪያ ነው ።

እንደ አዩብ ዓለይሒ ሰላም የምትታገሰው፣ እንደ ነብዩላሒ ዒብራሒም የምትጸናው፣ እንደ ዩኑስ ዓለይሒ ሰላም ፍጹም በጌታህ እና በጌታህ ብቻ የምትተማመነው የጥልቅ እውቀት ባለቤት ስትሆን ነው ።

ዓሊያማ እንደ አቡ ለሐብ፣ እንደ አቡ ጀህል ሐቅ ከፊትህ እንደ ጸሐይ ደምቆ እየፈካ በክህደት ሐዲድ ሽምጥ ትጋልባለህ።

አንብብ! ብሎ ገና ከጅምሩ ወደ እውነት እና ጥበብ የጠራህን ድንቅ መለኮታዊ እምነት በድንቁርናህ ሐያል መዳፍ ልትገዳደረው ትሞክራለህ በመሐይምነት አረንቋ መዘፈቅ ይኸው ነው ውጤቱ ሌላ አይደለም ።

በምድር ላይ የዒልምን ጸጋ የተቸሩ የምጡቅ አዕምሮ ባለቤቶች እና በጀነት የሚሞሸሩ መኳንንቶች ጥቂቶች ናቸው ።

እነዚያ የተመረጡ የምድር ጉልላቶች እና ጌጦች ደግሞ የነቢያት ወራሴ አምሳለ ነቢያት የሆኑት ዑለሞች ናቸው ከዱንያ ዝባዝንኬ እና ብርቅርቅ አለም ተገልለው ነፍሳቸውን ለኪታብ የሰጡ ለአላህ ሱ.ወ ሲሉ የመነኑ የመላዓክት አይነት ጠባይ ያላቸው ጠቢባን ናቸው ።

ታዲያ እነዚህን ታላላቅ ጠቢብ ዑለሞች ስናነሳ ዒስላምን ገና እግሮቹ ሳይጠኑ እና ከአንቀልባ ሳይወርድ እቅፍ ድግፍ አድርጋ ያሳደገችውን የክፉ ቀን ደራሹ አጉራሹ የሆነችውን ሐበሻን እና እንቁ ዑለሞቿን አለማንሳት ፈጽሞ አይቻልም እና ለሐገራቸው እና ለዓለመል ዒስላም አያሌ አበርክቶ ያመረቱትን በቅጡ ያልተዘከሩትን እና ሐገር የመሠረቱ ታላለቅ ዓሊሞችን አንድ ሁለት እያልን አቅማችን በፈቀደ ልክ እንዘክራለን አብራችሁን ቆዪ።

እነሆም የሐገራችን እምብርት እና የታሪክ ማዕከል ከሆነው ታላቁ ንጉስ ነጃሺ ጀምሮ ልዩ መለያችን እና ባንዲራችን ከሆኑት ቢላል ዒብኑ ረባህ በረካን
ጨምሮ ሌሎች ሐበሾችን እያነሳሳን በትዝታ ወደ ሗላም ወደ ፊትም እየቀዘፍን ዑለሞቻችንን እናወሳለን ።

በኢትዩጽያ ለጀግንነቱ አቻ ያልተገኘለት ታላቁ ዒማሙ አህመድ ዒብራሒም እና እሱን ያፈለቀችው ውቢት የ1000 ዓመቷ የምስራቅ አፍሪቃዋ ሐረር እና ዑለሞቿ ንጉሷን አሚር አብዱላሒን ጨምሮ ይታወሳሉ ።

ውቢቷ ሐረር ከሐረር እስከ ሸዋ፣ ከሸዋ እስከ ወሎ
ጅማ፣ ነገሌ ቦረና፣ ባሌን ጨምሮ በመላ ኢትዩጽያ እንደ ሐረር ያለች በሒጃቧ ያጌጠች ውብ ከተማ አለመኖሯን የታሪክ ምሁራን ያስረዳሉ ። በቅርብ ግዜ ወደ አኼራ የተሻገሩት ታላቁ ዓሊም ሼህ አደም ቱላ የሐረር ውጤት ናቸው።

የአርጓባ ምድር ያበቀላቸው ታላቁ ሸህ ሸህ አባዬ ሾንኬ እና ከ 500 - 900 ዓመት እድሜ እንዳለው የሚቆጠረው መንደራቸው በትናንት ታሪካችን ውስጥ በጉልህ የሚወሳ አሻራችን ነው።

በወሎ ዝነኞቹን ሙፍቲ ዳውድ እና ሙፍቲ ራያ ፣ሼህ ጫሊን ጨምሮ የአንይ እና የዳንይ እንዲሁም የጀማ ንጉስ እና የኢትዩጽያ ዓሊሞች ማምረቻ ማዕከል የሆነው ዳና ዛሬም እስከ ሙሉ ክብሩ እንዳለ ነው።

በደቡብ ታላቁ ሼህ ሼህ ዒሳ ቃጥባሬ ከትውልድ ቀያቸው ተሻግረው አዲስ አበባን በዲን ብርሐን ያነጹ ታላቁን የኑር መስጂድ ያስገነቡ አለፍ ሲልም በጎጃም መስጂድ ያሳነጹ ታላቅ ሙጃሒድ ነበሩ።

በጅማ ታላቁ የዲን ሰው ንጉስ አባጂፋር በባሌ ታላቁ ሸህ ኑር ሁሴን በጎንደር ሼህ ዓሊ ጎንደር ሶማሌን፣ አፋርን ጨምሮ በኢትዩጽያ ሰማይ ስር ተውሒድ ያነገሱ ፣ የዒስላምን ውብ ገጽታ ያመላከቱ ዲናቸውን እና ሐገራቸውን በአርበኝነት ያስከበሩ ታላላቅ ዓሊሞችን መጥቀስ ይቻላል።

ከጥንቶቹ ሸህ ጦለሐ ጃዕፈር፣ ሐሠን ዒንጃሞ፣ ሸህመሐመድ ሻፊ እና በዘመናችን የሚታወሱት ታላቁ የሐዲስ ሊቅ ሼህ ሙሐመድ ራፊዕ፣ታላቁ ሼህ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ፣ ታላቁ ሼህ ሸይኸ ሰዒድ ሷዲቅ ታላቁ ሁለገብ ዓሊም ሐጂ ዘይኑ ሼህ ሙቀና፣ ታላቁ ሼህ ሼህ ታጁዲን ሙሐመድን የጂስር ሼህን ጨምሮ ቁጥር እና ስፍር የሌላቸው ታይታ የማይሹ ለጌታቸው ያደሩ ስጋቸው እንጂ ነፍስያቸው በዱንያ የሌለ ኪታብ እንጂ ሌላ ወዳጅ የሌላቸው የአላህ ወዳጆች ዛሬም ድረስ ይገኛሉ።

አዲሱ ትውልድ የቀደሙትን አባት ዓሊሞች እና ሸሆች ፈለግ በመከተል የዲኑ ዘብ መሆን ይጠበቅበታል። በተለያዩ የሐገራችን ክፍሎች ያሉትን ዓሊሞችን መንከባከብ እና አደራቸውን መቀበል ይገባዋል ። ትውልድ የሚቀጥለው የዒልም ችቦ በመወራረስ ነው እና።

ይቀጥላል ..



11/11/2023

የእስራኤል ታንኮች በጋዛ ውስጥ ያሉ ሆስፒታሎችን ከበዋል
**************************
በጋዛ የሚገኘው አል ሺፋ ሆስፒታል ከ24 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አምስት ጊዜ ጥቃት እንደተሰነዘረበት የአካባቢው የጤና ኃላፊዎች ገልጸዋል።

በጋዛ ከተማ እና በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኙ ሆስፒታሎች “ሆን ተብሎ በተደረገባቸው ጥቃት” በነዳጅ እጥረት እና በኤሌክትሪክ እጦት ሙሉ በሙሉ ከአግልግሎት ውጭ እየሆኑ ናቸው ተብሏል።

በጋዛ የሚገኘው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ቢሮ ሆስፒታሎቹ የኤሌክትሪክ ኃይል ስለተቆረጠባቸው በቬንትሌሽን ታግዘው የሚታከሙ ታማሚዎች “ሁሉም ሊሞቱ ይችልሉ" ሲል አስጠንቅቋል።

የእስራኤል ሚሳይሎች እና መድፎች ከጦርነቱ የሸሹ ሰዎች የተጠለሉበትን የጋዛ ትምህርት መትተው ቢያንስ 50 ሰዎች መሞታቸውንም አልጀዚራ ዘግቧል።

ወደ ደቡብ ጋዛ የሚወስደውን ዋና መንገድ ይዘው ሲሸሹ የነበሩ ሰዎች ላይም ጥቃት መሰንዘሩን የዓይን ምስክሮቹ ተናግረዋል።

10/11/2023
እውነተኛ አጋር
09/11/2023

እውነተኛ አጋር

ሩሲያ ለአፍሪካ ሀገራት 25 ሺህ ቶን የስንዴ ድጋፍ ላከች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ለአፍሪካ ሀገራት 25 ሺህ ቶን የስንዴ ድጋፍ መላኳን የሀገሪቱ ጉምሩክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የስንዴ ድጋፉን የጫኑ መርከቦችም በጥቁር ባህር በኩል ወደ አፍሪካ ጉዞ መጀመራቸው ነው የተገለጸው፡፡

የስንዴ አቅርቦቱ ቱርክ ከደረሰ በኋላ በሀገሪቱ በሚገኙ ዱቄት ፋብሪካዎች ተዘጋጅቶ ወደ አፍሪካ ሀገራት እንደሚሰራጭም አር ቲ ዘግቧል፡፡

ይሁን እንጂ የነጻ ስንዴ አቅርቦቱ ለየትኞቹ የአፍሪካ ሀገራት እንደሚሰራጭ በመረጃው አልተጠቀሰም፡፡

በሩሲያ ቅዱስ ፒተርስበርግ በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን÷ ሩሲያ ለአፍሪካ የምታደርገውን የሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክር እንደምትቀትል መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በዚህ ወቅትም ፕሬዚዳንት ፑቲን ለስድስት የአፍሪካ ሀገራት የምግብ እህል በነጻ ለማቅረብ ስምምነት ተፈራርመው ነበር፡፡

በፈረንጆቹ 2022 ላይ ሩሲያ 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ቶን በላይ የምግብ እህል ወደ አፍሪካ መላኳን ዘገባው አስታውሷል።

በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ 6 ወራትም 10 ሚሊየን ቶን የምግብ እህል ለአፍሪካ ማቅረቧ ነው የተመላከተው፡፡



ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

የኢቶጵያን ኢኮኖሚ ያደቀቁ የውጭ ዜጎች ነቼው ለዋጋ ግሺበት የዳረጉን ሁላቀር አድርገውናል ።!!
09/11/2023

የኢቶጵያን ኢኮኖሚ ያደቀቁ የውጭ ዜጎች ነቼው ለዋጋ ግሺበት የዳረጉን ሁላቀር አድርገውናል ።!!

ጀግና የማይለወጥ ተሥፍ አሥቆራጭ መንግሥት
09/11/2023

ጀግና የማይለወጥ ተሥፍ አሥቆራጭ መንግሥት

⭕የዋልያዎቹ የቀድሞ አሰልጣኝ በአሜሪካ መቅረታቸው ተሰማ !

👇

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ቴክኒካል ዳይሬክተር እና የብሔራዊ ቡድኑ ጊዜያዊ አሰልጣኝ የነበሩት ኢንስትራክተር ዳንኤል ገ/ማርያም ወደ አሜሪካ ሄደዋል እንደማይመለሱም ተናግረዋል ። የቴክኒክ ዳይሬክተሩ ስራ እና ሀላፊነታቸውን አቀላጥፎ ለመስራት ምቹ ሁኔታ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ስር ባለመኖሩ ምክንያት ላይመለሱ አሜሪካ መኮብለላቸው ተሰምቷል ። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ቴክኒካል ሀላፊነት ስር የሚገኙ ሀላፊዎች አቶ ቴዎድሮስ ፍራንኮ አሜሪካ ላይ መቅረታቸው ይታወቃል ወ/ሮ አልማዝ ፍስሀ ደግሞ በአውስትራሊያ ለስብሰባ ብለው እዛው እንደቀሩ ይታወቃል አሁን ደግሞ ተረኛው ቴክኒካል ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ዳንኤል ገ/ማርያም ሆነዋል ። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን በድጋሚ ቴክኒካል ዳይሬክተር አልባ ሆኗል ፤ በዚህ ቦታ ላይ ስራቸውን ለመስራት የሚቀጠሩ ባለሞያዎች ለምን ከሀገር ይወጣሉ ለምንስ ይሰደዳሉ ?

መረጃው @ ስፖርት ዞን-

07/11/2023

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when mehamedjiwad posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share