Befikadu Degife Demeke

Befikadu Degife Demeke



  Ethiopia sweeps the 10,000m 🔥Gudaf Tsegay storms to the gold in 31:27.18 after a dramatic final in which Sifan Hassan ...
19/08/2023



Ethiopia sweeps the 10,000m 🔥

Gudaf Tsegay storms to the gold in 31:27.18 after a dramatic final in which Sifan Hassan crashes.

Gudaf Tsegay:- Gold
Letesenbet Gidey :- Silver
Ejgayehu Taye :- Bronze

19/08/2023

This glorious victory is beyond having medal for Ethiopia and Ethiopians.

Memory of the Ethiopian delegation of WAC Photo at national palace.

those who brought gold medals for Ethiopia are

Gidey
Tola
gebreselassie
Tsegaye

those who brought silver medals for Ethiopia are

Girma
Getachew
Geremew
Tsegaye

those who brought bronze medals for Ethiopia are

Abebe
Seyoum

We are so pleased by your result that you did at Oregon22 WAC.

Thank you for all what you have done for us and black people.

  በደብረ ሲና ማርያም  ቤተክርስቲያን ቡልቂ እንዲህ ተከብሯል ።ቡሄ_በሉቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ - - ሆየኛማ ጌታ - - ሆ የዓለም ፈጣሪ - - ሆየሰላም አምላክ - -ሆ ትሁት ...
19/08/2023

በደብረ ሲና ማርያም ቤተክርስቲያን ቡልቂ
እንዲህ ተከብሯል ።

ቡሄ_በሉ

ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ - - ሆ
የኛማ ጌታ - - ሆ የዓለም ፈጣሪ - - ሆ
የሰላም አምላክ - -ሆ ትሁት መሀሪ -ሆ

በደብረ ታቦር - - ሆ የተገለጠው - ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ - ሆ በርቶ የታየው -ሆ
ልብሱ እንደብርሃን -ሆ ያንፀባረቀው -ሆ
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(፪)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(፪)

ያዕቆብ ዮሐንስ-ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ-ሆ
አምላክን አዩት - - ሆ ሙሴ ኤልያስ - ሆ
አባቱም አለ - - ሆ ልጄን ስሙት - - ሆ
ቃሌ ነውና - - ሆ የወለድኩት - - ሆ
አዝ======

ታቦር አርሞንኤም-ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው- ሆ
ሰላም ሰላም - - ሆ የታቦር ተራራ - - ሆ
ብርሀነ መለኮት - ሆ ባንቺ ላይ አበራ -ሆ
አዝ======

በተዋህዶ - - ሆ ወልድ የከበረው - ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ - - ሆ ወልደማርያም ነው - -ሆ
ቡሄ በሉ - - ሆ ቡሄ በሉ - - ሆ
የአዳም ልጆች - - ሆ ብርሃንን - - ሆ ተቀበሉ - -ሆ
አዝ======

አባቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
እናቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
ከአጎቴም ቤት - - - ሆ አለኝ ለከት - ሆ
ተከምሯል - - ሆ እንደ ኩበት - - ሆ
አዝ======

የዓመት ልምዳችን - - ሆ ከጥንት የመጣው - - ሆ
ከተከመረው - ሆ ከመሶቡ ይውጣ - ሆ
ከደብረ ታቦር - - ሆ ጌታ ሰለመጣ - ሆ
የተጋገረው - ሆ ሙልሙሉ ይምጣ - ሆ
አዝ======
ኢትዮጵያውያን - -ሆ ታሪክ ያላችሁ - ሆ
ባህላችሁን - ሆ ያዙ አጥብቃችሁ - ሆ
ችቦውን አብሩት -ሆ እንዳባቶቻችሁ -ሆ
ምስጢር ስላለው -ሆ ደስ ይበላችሁ -ሆ

እንኳን አደረሳችሁ #ለደብረ _ታቦር

በቡዳፔስት ዛሬ ይጀመራል ድል ለኢትዮጵያ ✌19ኛው ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቡዳፔስት ሀንጋሪ ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 13/2015 ዓ.ም ይጀምራል።ዛሬ በ10,000 ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድርለተ...
19/08/2023

በቡዳፔስት ዛሬ ይጀመራል ድል ለኢትዮጵያ ✌

19ኛው ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቡዳፔስት ሀንጋሪ ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 13/2015 ዓ.ም ይጀምራል።

ዛሬ በ10,000 ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድር

ለተሰንበት ግደይ፣
ጉዳፍ ጸጋይ፣
እጅጋየሁ ታዬ እና ለምለም ሀይሉ

08/06/2023

የመውጫ ፈተና ተፈታኝ ከሆኑ!
በቀሪ ጊዚያችሁ!

1. የመውጫ ፈተናው አስፈላጊ መሆኑን አምኖ መቀበል (ልምድ እንዳላችሁ አለመርሳት ወደ ኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ለመግባት ተፈትናችሁ ያለፋችሁ ናችሁ (10ኛ እና 12ኛ ክፍል)፡፡ የመውጫ ፈተናውን በአይምሮ ደረጃ አምኖ አለመቀበል ጊዚያችሁን ይበላል፡፡

2. ለፈተና ይጠቅማል ብላችሁ ያሰባችሁበትን ክፍል ለይታችሁ መከለስ! ያላጣራችሁት ቦታ ካለ በደንብ ለፈተና በሚሆን መልኩ ማንበብ/መከለስ (በእያንዳንዱ የኮሌጅ ቆይታ ወቅት ለፈተና አንብባችሁ ሊሆን ስለሚችል ምን አልባት ክለሳ ማድረግ ሊበቃ ይችላል)፡፡

3. ከፈተናው ሁኔታ (ፎርማት) ጋር ፈጥኖ ለመግባባት መሞከር (ኦን ላይን ከሆነ መልመድ፤ ፈተናው ስለሚዳስሰው ነጥብ ማወቅ፤ ልምምድ ማድረግ፤ ሞዴል ፈተናዎችን በትኩረት መስራት፤ የጥያቄዎቹን ይዘት ለማወቅ መሞከር፡፡

4. የሚዘጋጁ የናሙና ፈተናዎችን በትኩረት መፈተን እና በደንብ መለማመድ የቀደመ የህግ እና የጤና መውጫ ፈተና ይዘቶችን ጠይቆ ልምዶችን መውሰድ፤ ምን አልባት ኦን ላይን ያሉ ናሙናዎችን እንደ መለማመጃ መውሰድ፡፡

5. የጊዜ መርሃ ግብር ማውጣት፤ በአንዴ ብዙ ለመሸፈን መሞከር ትኩረት ስለሚያሳጣ ቀሪ ጊዚያችሁን በጥብቅ ፕሮግራም መምራት (ከማህበራዊ ሚዲያ መቀነስ፤ ከጨዋታ መቀነስ፤ ከእንቅልፍ መቀነስ (በቀሪው ጊዜ ተቸግራችሁ ከቁጭት መዳን ትችላላችሁ) እና ለዚህ ፈተና የመጨረሻ አቅማችሁን መጠቀም፡፡

6. በዚህ ወቅቱ በቡድን ማጥናት፤ ሙከራዎችን መስራት፤ ሊያስረዷችሁ የሚችሉ ሰዎችን መፍጠር ያስፈልጋል፤ በከበዳችሁ ክፍል ላይ ጊዜ በማጥፋት ወደ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንዳትገቡ የሌሎችን እርዳታ ለመቀበል ክፍት መሆን አስፈላጊ ነው፡፡

7. ከወዲሁ እና በፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት ሊፈጠሩ የሚችሉ ስህተቶችን ቀንሱ የኮምፒዊተር አጠቃቀም፤ የማርፈድ፤ ጥሩ ስሜት ያለመፈጠር፤ የድካም፤ የመጨናነቅ፤ ወዘተ፡፡

አስታውሱ በአብዛኛው መለኪያ ፈተናውን ማለፍ በእናንተ ጥረት እና ዝግጅት ልክ ነው የሚወሰነው! ሳያጠኑ ለማለፍ መመኘትም ሆነ ሳያጠኑ ወድቆ ቅር መሰኘት አዋጪ Rational አይሆንም!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Befikadu Degife Demeke posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share