Fíŕěŵ Těŵâĥďő

Fíŕěŵ Těŵâĥďő ተዋህዶ እምነቴ
ኢየሱስ አባቴ
ማርያም እናቴ
መላእክት ጠባቅዬ
ቅዱሳን አማላጆች
የአገልግሎት ዘመንን ባርክልኝ አምላክ ���
followers page 😍🙏😍

   የኢጃት ሱባዔ ጉባኤ ተማሪዎች ተመረቁ | ጃንደረባው ሚድያ  |ኅዳር 2017 ዓ.ም.|አዲስ አበባ - ኢትዮጵያየኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በ2016 ዓ.ም. በአራተኛ እና አምስተኛ ዙር ...
19/11/2024


የኢጃት ሱባዔ ጉባኤ ተማሪዎች ተመረቁ

| ጃንደረባው ሚድያ |ኅዳር 2017 ዓ.ም.|
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በ2016 ዓ.ም. በአራተኛ እና አምስተኛ ዙር ሱባዔ ጉባኤ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አዳራሽ ያስተማራቸውን 2000 ተማሪዎች እንዲሁም በሦስተኛ ዙር የምእመናን የቅዳሴ ተሰጥኦ ትምህርት ያሰለጠናቸውን 100 ተማሪዎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በቦሌ መድኃኔዓለም ዓውደ ምሕረት በደመቀ ሁኔታ አስመረቀ። ከተማሪዎቹ መካከል ከልጆቻቸው ጋር የተማሩ ወላጆች አራስ ሆነው የተማሩ እናቶችም ይገኙበታል::

በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ የጃን ሱባዔ ጉባኤ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሕያው መኮንን እንደገለጹት በኢጃት ከሚተገበሩ መፍትሔ ተኮር ፕሮጀክት መካከል አንዱ የሆነው ሱባዔ ጉባኤ የተሰኘው የትምህርት መርሐ ግብር ሲሆን ሱባዔ ጉባኤ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በሰረገላ ላይ ሆኖ ለአጭር ጊዜ ለመዳን የሚያበቃውን ትምህርት በዲያቆኑ ፊልጶስ ተምሮ "እነሆ ውሃ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድነው?" የሚል መፍትሔን እንዳቀረበ የእኛም ትውልድ የ28 ቀን የሰረገላ ላይ ትምህርትን ወስዶ ከምሥጢራት እንዲካፈል የቤተ ክርስቲያንን ችግር "እነሆ መፍትሔ" በማለት እንዲፈታ ማስቻል ነው" ብለዋል። ምንም እንኳን የትምህርቱ ቀናት ከጥልቁ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት አንጻር የቅምሻ ያህል ቢሆንም በሳምንታዊ ኮርሶች መለኪያ ሲታይ የአንድ ዓመት ሥልጠና የሚፈጀውን ያህል 53 ሰዓታት የሚፈጅ ሲሆን ትምህርቱን በእይታ የተደገፈ በማድረግ ጥራቱን ከፍ ለማድረግ የተቻለ ሲሆን በትምህርቱም አዳዲስ መምህራንን በየጊዜው ማፍራት ተችሎአል ብለዋል::

የጃን ቅዳሴ አስተባባሪ የሆኑት መምህር ኃይለኢየሱስ ተሻለ በበኩላቸው ምእመናን ከቅዳሴ ከሚርቁባቸው ምክንያቶች ዋነኛው ተሰጥኦውን አለማወቃቸው መሆኑን ገልጸው ቅዳሴ ማስቀደስ የዚህ ትውልድ ልዩ ምልክት እንዲሆን እና ሥርዓተ ቅዳሴን ለምዕመናን በማስተዋወቅ ሳያስቀድስ መኖር የማይችል ትውልድን ለመፍጠር ፕሮጀክት ቅዳሴ ተቀርጾ ላለፉት ዐራት ዓመታት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም በ2017 የቅዳሴ ተሰጥኦ የቪድዮ ትምህርት እንደሚጀመርም አስታውቀዋል::

ኢጃት እስካሁን አራተኛ እና አምስተኛ ዙር ተማሪዎችን ጨምሮ ከ5000 በላይ ተማሪዎችን አስተምሮ ያስመረቀ ሲሆን ከ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት ጋር የጋራ ሥምምነት በመፈራረም ሱባኤ ጉባኤ የሰንበት ት/ቤት የመግቢያ ትምህርት እንዲሆን በመስማማት ከ2500 በላይ ተማሪዎች ሱባዔ ጉባኤን ተምረዋል:: በ6ኛ ዙር ተማሪዎች ቀድመው ተመርቀው ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎት ተቀላቅለዋል።

የኢጃት ሥራ አመራር ቦርድ ሰብባቢ የሆኑት ዲ/ን ዶ/ር ዳዊት ከበደ የ28ቀኑ የሱባዔ ጉባኤ ትምህርት ዓላማ ቤተክርስታያንን ጠንቅቃችሁ እንድታውቋት ሳይሆን ቢያንስ ቀረብ ብላችሁ እንድታዩአት ፥ ተጠይቃችሁ መመለስ ቢያቅታችሁ ቤተክርስቲያኔ መልስ አላት ብላችሁ በድፍረት መናገር እንድትችሉ ማስቻል መሆኑን በመግለጽ እንደ ባሕር ጥልቅ የሆነውን የቤተክርስቲያናችንን ትምህርት ቀረብ ብላችሁ እንድትማሩ ፣ ከንስሓ እና ከሥጋ ወደሙ ዘውትር እንዳትርቁ ፣ የድኀነታችሁ ምልክት የሆችው ማዕተባችሁን እስከ ዕለተ ሞታችሁ ድረስ ከአንገታችሁ ለቅጽበት እንዳይለያችሁ በማለት ለተመራቂዎች የአደራ መልእክት አስተላልፈዋል።

ጀግና መምህር ይገባሀል ዲ/ን ሄኖክHenok Haile ለመቄዶንያ የብራንድ አምባሳደር ተብዬ በመሰየሜ እጅግ ታላቅ ክብርና ዕድለኛነት ይሰማኛል:: እግዚአብሔር በደዌ እየደቆሰ ዋጋውን በምድር ...
09/11/2024

ጀግና መምህር ይገባሀል ዲ/ን ሄኖክ
Henok Haile

ለመቄዶንያ የብራንድ አምባሳደር ተብዬ በመሰየሜ እጅግ ታላቅ ክብርና ዕድለኛነት ይሰማኛል::

እግዚአብሔር በደዌ እየደቆሰ ዋጋውን በምድር እንዳይቀር እያደረገለት ባለው ውድ ወንድማችን በክቡር ዶ/ር ብንያም አማካኝነት የተመሠረተውን ይህንን ቅዱስ ሥፍራ በተለያዩ አጋጣሚዎች የማየት ዕድል ነበረኝ::

መቄዶንያን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁ ቀን የተሰማኝን የጥፋተኝነት ስሜት ልገልጸው አልችልም:: ምጽዋትን በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ መስበክ ቀላል ነው:: እንደብንያምና አብረውት እንደሚያገለግሉ ወንድሞችና እኅቶች ራስን መመጽወት ግን ከባድ ነው::

ከአረጋውያኑና ከአእምሮ ሕሙማኑ ጋር አብረው እየኖሩና አብረው እያደሩ ፤ ለማየት የሚቀፍፍ ቁስል ያለባቸውን በፍቅር እያቀፉና እየመገቡ ፤ መጸዳጃ ቤት መሔድ የማይችሉና በዳይፐር የሚጠቀሙ በሺህ የሚቆጠሩ ሕሙማንን ከአልጋቸው ሳይነሡ እንዲጸዳዱ መርዳትና ማጠብ ፤ ከየትኛው ሆስፒታል በላይ በሺህ ከሚቆጠሩ ከአእምሮ ሕሙማን ጋር ያለ ምንም ልዩ ጥበቃ አብሮ መዋልና ማደር ዮሐንስ 4:38፤ ነዳያንን ለማገልገል ነዳይ ሆኖ መኖር የቻሉትን ብንያምና አብረውት ያሉ ሰዎች ማየት ብቻ ንስሓ እንድትገባና ምንኛ ጨካኝ ልብ ነው ያለኝ እንድትል የሚያደርግ ነው::

መቄዶንያ የአእምሮ ሕሙማንና አረጋውያንን መርዳት ብቻ ሳይሆን ከረዳቸውና ጤናቸው ከተመለሰ በኋላ እዚያው መቄዶንያ ተቀጥረው እንዲሠሩ በማድረግ ሕይወታቸውን ከተረጂነት ወደ ረጂነት የሚቀይር ተቅዋም በመሆኑ በዚያ ሥፍራ ማን ተረጂ ማን ረጂ መሆኑን ለመለየት እንኳን ግራ ይገባል::

መቄዶንያ በመላው ኢትዮጵያ 44 ቅርንጫፎች ያሉት ከወደቁበት የተነሡ ሰዎች ወደ አእምሮአቸው ሲመለሱ ወደ ሥራ የሚገቡበት ብዙ ሥልጠና ያለው በሆስፒታል ደረጃም ብዙ ቁጥር የሚያስተናግድ ሥፍራ ነው:: በመሥራት ላይ ያሉትና የፊታችን የካቲት 1 2017 ዓ.ም. በሰይፉ ኢቢኤስ ዩቲዩብ ቻናል በሚደረግ የገቢ ማሰባሰቢያ ይጠናቀቃል ተብሎ በሚጠበቀው ግዙፍ ሆስፒታልና የአረጋውያን ማእከል ሲጨመርበት ትልቁ የድሆች መጠጊያ መሆኑ የማይቀር ነው::

መቄዶንያ ውስጥ ከሚረዱ አረጋውያንና ሕሙማን መካከል ብዙ መነኮሳት ካህናትና ዲያቆናት እንዳሉ ሁሉ በርካታ ሼሆችና የእስልምና ምሁራንም ብዙ ናቸው:: ክርስቲያኖች በየዕለቱ ኪዳን የሚያደርሱበት ፣ ሙስሊሞች የሚሰግዱበት ፣ ፕሮቴስታንቶች የሚያመልኩበት የተለያየ ሥፍራ ተዘጋጅቶላቸው እምነታቸውን በየመምህሮቻቸው ይማራሉ::

መቄዶንያ በአጭሩ የተቀደሰውን የምጽዋት ሥራ የሚሠራ መንፈሳዊ ሥፍራ ሺህዎች ቤተሰብ የሆኑበት ባንሳለመውም የተባረከ ትንሽ ቤተ ክርስቲያን (Microcosm of the Church) ነው:: በቤተክርስቲያን ታሪክ ይህን ዓይነቱን ሥራ የሠራው ቅዱስ ባስልዮስ ሲሆን ሕሙማንን እያስታመመ አረጋውያንን እየረዳ የነበረበት ሥፍራ ባዚልያድ ይባል ነበረ::

መቄዶንያዎች በዛሬው ዕለት የብራንድ አምባሳደር ብለው ሲሰይሙኝ መጀመሪያ ላይ አእምሮዬ ላይ የመጣው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል :- "እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኋችሁ፤ ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ” የሚለው ቃል ነው:: (ዮሐ. 4:38) እነርሱ ሕይወታቸውን ለሠጡለት ቅዱስ ዓላማ ተላላኪ እንድሆን በመመረጤ ደስ ቢለኝም ውጊያው በድል ሊጠናቀቅ ትንሽ ሲቀረው ትግሉን የተቀላቀለ የድል አጥቢያ አርበኛ የመሆን ስሜት ግን አላስተረፈኝም::

እነሱ ቁስል እየጠረጉ ፣ የአረጋውያንን የታመመ እግር እያሹ ስለሚውሉ አንዳንድ ቅስቀሳ ለማድረግ ጊዜ የላቸውምና ሞልቶ ከፈሰሰ ጊዜህ ላይ እስቲ ቁምነገር ሥራና ጽደቅ ሲሉኝ ሊምረኝ ሰበብ እየፈለገ ያለውን አምላክ አመስግኜያለው :: የምጽዋት አርበኞቹን የርኅራኄ ጀግኖቹን መቄዶንያዎችንም ከልብ አመሰግናለሁ:: (በተለይ በትዕግሥት በመደወልና በመወትወት የዚህ ዕድል ተካፋይ ያደረገችኝን የመቄዶንያ ሚድያና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ሐረገወይንን አመሰግናለሁ)

ያሸከሙኝን ኃላፊነት ስቀበል ባዶ እጄን ላለመሔድ ያህል "ባዚልያድ" የተሰኘ በጥንታዊትዋ "መቄዶንያ" ስም የተሰየመ መጽሐፍ ለአምባሳደርነት "እንደ ሹመት" ደብዳቤ አቅርቤያለሁ:: ሙሉ ገቢው ለመቄዶንያ ሕንፃ የሚውለው ባዚልያድ መጽሐፍ በቅርቡ በእጃችን ይገባል::

ለሁለት ዓመት በብራንድ አምባሳደርነት እንዳገለግል የሠጡኝን ዝርዝር ሥራ ይዤ እንዲህ እናድርግ ብዬ ለማስተዋወቅ ብሞክር እንግዲህ እንዳትታዘቡኝ:: ምክንያቱም ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የመቄዶንያ ብራንድ አምሳደር

ጥቅምት 30 2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

  ለቸሩ  #መድኀኔዓለም   Ten Unknown Facts About  1. Founding and History: BMW, Bayerische Motoren Werke AG, was founded in 191...
05/11/2024

ለቸሩ #መድኀኔዓለም


Ten Unknown Facts About

1. Founding and History: BMW, Bayerische Motoren Werke AG, was founded in 1916 in Munich, Germany, initially producing aircraft engines. The company transitioned to motorcycle production in the 1920s and eventually to automobiles in the 1930s.

2. Iconic Logo: The BMW logo, often referred to as the "roundel," consists of a black ring intersecting with four quadrants of blue and white. It represents the company's origins in aviation, with the blue and white symbolizing a spinning propeller against a clear blue sky.

3. Innovation in Technology: BMW is renowned for its innovations in automotive technology. It introduced the world's first electric car, the BMW i3, in 2013, and has been a leader in developing advanced driving assistance systems (ADAS) and hybrid powertrains.

4. Performance and Motorsport Heritage: BMW has a strong heritage in motorsport, particularly in touring car and Formula 1 racing. The brand's M division produces high-performance variants of their regular models, known for their precision engineering and exhilarating driving dynamics.

5. Global Presence: BMW is a global automotive Company

6. Luxury and Design: BMW is synonymous with luxury and distinctive design, crafting vehicles that blend elegance with cutting-edge technology and comfort.

7. Sustainable Practices: BMW has committed to sustainability, incorporating eco-friendly materials and manufacturing processes into its vehicles, as well as advancing electric vehicle technology with models like the BMW i4 and iX.

8. Global Manufacturing: BMW operates numerous production facilities worldwide, including in Germany, the United States, China, and other countries, ensuring a global reach and localized production.

9. Brand Portfolio: In addition to its renowned BMW brand, the company also owns MINI and Rolls-Royce, catering to a diverse range of automotive tastes and luxury segments.

10. Cultural Impact: BMW's vehicles often become cultural icons, featured in fi

Ten Unknown Facts About  1. Founding and History: BMW, Bayerische Motoren Werke AG, was founded in 1916 in Munich, Germa...
05/11/2024

Ten Unknown Facts About

1. Founding and History: BMW, Bayerische Motoren Werke AG, was founded in 1916 in Munich, Germany, initially producing aircraft engines. The company transitioned to motorcycle production in the 1920s and eventually to automobiles in the 1930s.

2. Iconic Logo: The BMW logo, often referred to as the "roundel," consists of a black ring intersecting with four quadrants of blue and white. It represents the company's origins in aviation, with the blue and white symbolizing a spinning propeller against a clear blue sky.

3. Innovation in Technology: BMW is renowned for its innovations in automotive technology. It introduced the world's first electric car, the BMW i3, in 2013, and has been a leader in developing advanced driving assistance systems (ADAS) and hybrid powertrains.

4. Performance and Motorsport Heritage: BMW has a strong heritage in motorsport, particularly in touring car and Formula 1 racing. The brand's M division produces high-performance variants of their regular models, known for their precision engineering and exhilarating driving dynamics.

5. Global Presence: BMW is a global automotive Company

6. Luxury and Design: BMW is synonymous with luxury and distinctive design, crafting vehicles that blend elegance with cutting-edge technology and comfort.

7. Sustainable Practices: BMW has committed to sustainability, incorporating eco-friendly materials and manufacturing processes into its vehicles, as well as advancing electric vehicle technology with models like the BMW i4 and iX.

8. Global Manufacturing: BMW operates numerous production facilities worldwide, including in Germany, the United States, China, and other countries, ensuring a global reach and localized production.

9. Brand Portfolio: In addition to its renowned BMW brand, the company also owns MINI and Rolls-Royce, catering to a diverse range of automotive tastes and luxury segments.

10. Cultural Impact: BMW's vehicles often become cultural icons, featured in fi

ለደጁ ይብቃችሁ   አሜን አሜን አሜን የምደርሳችሁ በሙሉ    #ገጽ
03/11/2024

ለደጁ ይብቃችሁ
አሜን አሜን አሜን የምደርሳችሁ በሙሉ #ገጽ

24/10/2024




📖የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መግቢያ📖✞ክፍል ሁለት✞መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ?ከክርስቶስ ልደት በፊትም ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ...
21/04/2024

📖የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መግቢያ📖
✞ክፍል ሁለት✞
መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ?
ከክርስቶስ ልደት በፊትም ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ አጋማሽ ጀምሮ ማለትም እስራኤላውያን ከምርኮ ከተመለሱና ቤተ መቅደሱም ካነጹ በኋላ እዝራ መጻሕፍቶችን አሰባሰበ የአይሁድ መምህራንም (ረበናት)ጉባኤ አድርገው መጻሕፍቶቹን በማጥናት በአንድ ጥራዝ ባይጠቀልሉትም 39 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍቶችን ለይተው አጸደቁ፡፡በኋላ በግሪክ ግዛቶች ይኖሩ የነበሩ አይሁዳውያን ዕብራይስጥ ስለማይችሉ በግሪክ እንዲተረጉሙላቸውና መጻሕፍቱ በቤተ መጻሕፍት ተተርጉመው እዲቀመጡ በንጉስ ትእዛዝ ዕብራይስጥና ግሪክኛ አቀላጥፈው የሚናገሩና የሚጽፉ 72(ሰባ ሊቃናት) ሰዎች ተመርጠው በ300ዓ.ዓ ገደማ ወደግሪክኛ ሲተረጉሙ ከ39 ሌሎች ተጨማሪ መጻሕፍትንም ጨምረው ተረጎሙ፡፡

ነገር ግን ይህ በ90 ዓ.ም የግሪኮቹና የእየሩሳሌሞቹ አይሁዶች ከ39ኙ መጻሕፍት ውጭ በተጨመሩት ላይ ተነጋግረው በአንድ ሐሳብ ተስማሙ እሱም “የተዛባ የታሪክ አቀራረብና የሐሳብ መቃረን አለባቸው፣ከባቢሎን ስደት መልስ በኋላ ማለትም ከ539 ዓ.ዓ በኋላ ደግሞ እግዚአብሔር ነቢይ አልላከም የእግዚአብሔር ዝምታ ጊዜ ስለነበር በመንፈሱ መሪነት ተጽፈዋል ብለን አንቀበልም” በሚል 39ኙን አጸኑ፡፡አንዳንድ ክርስቲያኖች ከሰባ ሊቃናቱ ግሪክኛ ቅጂ አይሁዳውያኑ ያልተቀበሏቸውንም ጭምር ይጠቀሙ ነበር፡፡ በብሉይ ኪዳን ማለትም የሙሴ ሕግ መዝሙራትና ነቢያት ስለ ክርስቶስ ስለሚመሰክሩ ይጠቀሙባቸው ነበር(ሉቃ 24፥44) ፡፡በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ግን ምንም አገልግሎት አልነበረም የጋራ አምልኮም ቢሆን ትምህርት ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ብቻ እንጂ በመጽሐፍ አልነበረም፡፡

የኋላ ኋላ ግን በተለያየ ሁኔታና በተለያየ ምክንያት ወንጌልና መልእክታት ከ50-100 ዓ.ም ባሉት በተለያዩ ዓመታትና በተለያዩ ቦታዎች ውስጥ በሐዋርያቱ ተጻፉ፡፡መልእክታቱ ከአንዷ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሌላኛይቱም ይተላለፉ ነበር ፡፡ ሐዋርያት በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ላይ እንደ አይሁዳውያኑ የተወሰነ የመጻሕፍት ቁጥር አላስቀመጡም፡፡ከሐዋርያት በኋላ ማለትም ከ100 ዓ.ም ወዲህ በሐዋርያት ሥም ብዙ መጻሕፍቶች ይጻፉ ጀመር ይህም ማለት የሐዋርያው እገሌ ወንጌል ወይም መልእክት እየተባለ ይጻፍ ነበር::በዛን ጊዜ የነበሩት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በብሉይ ኪዳን ላይ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ማለትም ወንጌላትና መልእክታት ወስነው እውቅና ለመስጠት በጣም ተቸገሩ ምክንያቱ በሐዋርያት ስም የተጻፉት መጻሕፍት ከመብዛታቸውና የሐሰት ትምህርቶችን ከመያዛቸው የተነሳ ብዙ ክርክር በማስነሳታቸው ነበር::የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ማለትም ወንጌላትና የሐዋርያት ትምህርት ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጋራ አንድ ላይ በማድረግ በሙሴ ሕግ በነቢያትና በመዝሙራት የተነገረለት መሲሕ ፍጻሜው በወንጌላትና በመልእክታት እንዴት እንደሆነ እያስማሙ አማኞችን ለማስተማር ለማንበብም እንዲያመች በአንድ ጥራዝ መሆን አስፈለገ::

✍የተገኙት መጻሕፍት ብዙ ጥናትና ምርምር ከተካሄደባቸው በኋላ ግን ቅዱስ አትናቴዎስ በስሩ ያስተዳድራቸው ለነበሩ የእስክንድርያ አብያተ ክርስቲያናት ከ39ኙ የአይሁድ ብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ላይ 27 የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በማጽደቅ እንዲጠቀሙ ወሰነ::

✍የሎዶቅያ ሲኖዶስ በ364 ዓ.ም ከአይሁድ ቀኖና 22 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት እንዲሁም ባሮክና የኤርሚያስ መልእክት በመጨመር ከ26 የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት(ራዕየ ዮሐንስን በማውጣት) ሲያጸድቅ

✍የካርቴጅ ሲኖዶስም በ397 ዓ.ም በአይሁድ ቀኖና ላይ አንዳንድ

ሰንበት ••ክቡር ነውሰንበት•ቅዱስ ነው ሰንበት የእግዚአብሔር ነው።ሰንበት •• እሁድ ነው ከሰንበት በረከት ረድኤት ይክፈለን።🙏❤
14/10/2023

ሰንበት ••ክቡር ነው
ሰንበት•ቅዱስ ነው ሰንበት የእግዚአብሔር ነው።
ሰንበት •• እሁድ ነው
ከሰንበት በረከት ረድኤት ይክፈለን።🙏❤

  "ወር በገባ በ8 መታሰቢያቸው ነው በ8 ዓመታቸው ያላቸውን ገንዘብ ትተው ምድራዊውን ሳይሆን ሰማያዊውን ጊዜያዊ የሆነውን ሳይሆን ዘላለማዊውን የእግዚአብሔርን መንግስት ሽተው ወደ አባ በብኑ...
18/09/2023



"ወር በገባ በ8 መታሰቢያቸው ነው በ8 ዓመታቸው ያላቸውን ገንዘብ ትተው ምድራዊውን ሳይሆን ሰማያዊውን ጊዜያዊ የሆነውን ሳይሆን ዘላለማዊውን የእግዚአብሔርን መንግስት ሽተው ወደ አባ በብኑዳ ገዳም ገብተዋል።

እስከ 17 ዓመታቸው ረድዕ ሆነው እያገለገሉ ስርዓተ ምንኩስናን ከተማሩ፤ ከተረዱ በኋላ የምንኩስናን ማዕረግ ተቀብለዋል።

ስለ እግዚአብሔር ፍርድ እንዲሁም ስለ ሰው ልጆች ይቅርታ 40 ዓመት በመሬት ላይ ተኝተው ስጋቸው ከመሬት ጋር ተጣብቆ ሣር እስኪበቅልባቸው ድረስ ጸልየዋል።

ጌታችንም ስለ መታመናቸው እና ስለ ተጋድሏቸው አክብሯቸዋል ።

👉 ቃል ኪዳናቸውም ፦

ልጅ ለሌላት መኻኒቱ ፣ በገድላቸው ብትባረክ ፣ ጸበላቸውን ብትጠጣ፣ በጻድቁ ምልጃ ቃልኪዳን ፤ እንደ እግዚብሔር ምህረት እና ቸርነት ልጅ ታገኛለች።

ታህሳስ 8 በዓለ ልደታቸው
ሐምሌ 8 ቀን በተወለዱ በ 270 ዓመታቸው አርፈዋል።

በቅንነት ቴሌግራም ይቀላቀሉ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
የጻድቁ አባታችን አቡነ ኪሮስ
ምልጃና በረከታቸው አይለየን
🙏🙏🙏
አሜን አሜን አሜን

️🌹📘 #የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታሪክ ባጭሩ 🌹📌 አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ልጅ አጥተው 3...
15/09/2023

️🌹📘 #የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታሪክ ባጭሩ 🌹

📌 አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡

♨ በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ፡፡

♨አባታችን ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል።

♨በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ፡፡
አባታችን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል፡፡
♨መላእክት በአክናፈ እሳት ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል፡፡

♨ለፅንሰትከ ፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በብሥራተ መልአክ ለተፀነስነከው መፀነስና በወርኃ ታኀሣሥ ለተወለድከው ልደትህ ሰላም እላለሁ።

🙏ክቡሩ አባት ሆይ ስለ ዓለሙ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጌትነቱ ልደት ተርሴስ ግብር እንደገበረ፤እኔም ፍጹም ልባዊ የእጅ መንሻ ወርቅ አቀርብልሃለሁ።

💙ለተኃፅኖትከ፥ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የቤተ ክርስቲያን መብራት የምትሆን የተመረጠች የክብርት እናትህን ጡት ባለመጥባት በመንፈስ ቅዱስ እንክብካቤ ስለ አደግኸው አስተዳደግህ ሰላም እላለሁ።


የአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከትታቸው አይለየን አሜን

ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን

ቴሌግራም ነው ተቀላቀሉ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሰበር መረጃኤጲስ ቆጶሳት ነን ብለው በተገኙ 26 መኖከሳት ላይ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላለፈ ***የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤ...
23/01/2023

ሰበር መረጃ

ኤጲስ ቆጶሳት ነን ብለው በተገኙ 26 መኖከሳት ላይ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላለፈ
***

የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት የአስተዳደር ጉባኤ ዛሬ ማለዳ ላይ በዋለው ስብስባ ትላንት ጥር 14 በወሊሶ ከተማ በተደረገው ህገ ወጥ ሲመት

እራሳቸውን ኤጴስ ቆጶሳት ብለው የገለጡ ከተለያዩ አድባራት እና ገዳማት የተውጣጡ 26 መኖኮሳት ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላልፏል።

በእዚህ መሰረት

1ኛ .ሁሉም መኖከሳት ከደምወዝ ታግደው እንዲቆዩ
**

2ኛ. የሚያንቀሳቅሱት የገዳማት እና አድባራት ሂሳብ ካለ እንዲታገዱ
**

3ኛ. ከእዚህ በፊት ወደሚያገለግሉት የአገልግሎት መዋቅር እንዳይመለሱ
**

4ኛ.በየትኛው የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አድባራት እና ገዳማት እንዳይገኙ ውሳኔ አስተላልፏል።

ፍትሕ መንፈሳዊ ውሳኔዎችን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀጣይ በሚያደርገው ስብሰባ ይወስናል ተብሎ ይጠብቃል።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

"ዮም በርህ ሠረቀ ለነ ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ ""ዛሬ ብርሃን ወጣልን ፤ ሰማይ እና ምድር መሸከም የማይችሉትን የድንግል ማኅፀን ተሸከመው" (ቅዱስ ያሬድ) በመላው ዓለ...
06/01/2023

"ዮም በርህ ሠረቀ ለነ ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ "
"ዛሬ ብርሃን ወጣልን ፤ ሰማይ እና ምድር መሸከም የማይችሉትን የድንግል ማኅፀን ተሸከመው" (ቅዱስ ያሬድ)

በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ምዕመናንና ምዕመናት

ደካማ ባሕርያችንን ተዋሕዶ ሰው የሆነ ፤ በሥራው ጌትነቱን የገለጠ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለ፳፻፲፭ ዓ.ም በዓለ ልደቱ በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ።

የሰው ልጅ ከአምላኩ የተሰጠውን ትዕዛዝ በመተላለፍ እና ፍፁም ታዛዥነትን ወደ ጎን በመተው ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ በሆነ መልኩ የገባበትን ስህተት ተከትሎ በሰው ፍጥረት ሁሉ ላይ የመጣው ሞት በጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን የሞት ማሰሪያው ተቆርጦ ጠፋ የሰው ልጅም በክርስቶስ ኢየሱስ መወለድ ነጻ ሆኖ በላዩ ተጭኖበት የኖረው የዲያብሎስ ቀንበር ጠፍቷል ፤ ተደምስሷል።

መድኅነ ዓለም ክርስቶስ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል እንደተባለ የሰው ልጅ በኃጢአቱ ምክንያት ተሰነካከለ ፣ ትዕዛዙን ባለመስማት ከገነት ተሰደደ ፤ ነገር ግን ሰውን የሚወድ ደረሰልን (ሃ.አበው) ።

ሰውን ሰው ማዳን ስለተሳነው በመልአክ ወይም በነቢይ ሳይሆን ፤ እርሱ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ አድኖናል።

የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው ፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው። (፩ ቆሮንቶስ ፲፭ ፥፵፯) እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ በአዳም ምክንያት የመጣብን ሞት በሁለተኛው አዳም ተደምስሶ ነጻ ወጥተናል ይኸውም ሁለተኛው አዳም ክርስቶስ ከመሬት መሬታዊ ሳይሆን ከሰማይ በመሆኑ ነው።

የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች
ምዕመናንና ምዕመናት

የጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን እጅግ የሚደንቅ ልዩ ምስጢር ነው። የማይታመም እርሱ ከመለኮቱ ሳይለይ የሚታመም ሥጋን ተዋሕዷል።

ዳግመኛም በሉዓላዊ ዙፋን የሚኖር ታላቁ እና ገናናው አምላክ በጎል ተጣለ ፤ ሥጋን ከመዋሐዱ አስቀድሞ የማይዳሰስ ወልድ ዋሕድ እርሱ ዛሬ ሥጋን ተዋሕዶ ተዳሠሠ።

እጅግ በሚያስደንቅ መልኩ የኃጢአትን ቁራኝነት የሚያጠፋ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ !

በመሆኑም እነዚህን እና የማይመረመሩ የእርሱን ሥራዎች በመመልከት ከፍለን የማንጨርሰው ውለታ ያለብን በመሆኑ ምስጋና እና አምልኮን ልናቀርብለት ይገባል።

ይህንን የጌታችን እና አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል በምናከብርበት ጊዜ የተራቡትን በማብላት ፣ የተጠሙትን በማጠጣት ፣ የታረዙትን በማልበስ ፣ በጦርነት ቀጠና ውስጥ የቆዩ ወገኖቻችንን በመርዳት ሊሆን እንደሚገባ አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ሄኖክ
Firew

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሚድያዎች Follow, Subscribe ,Like በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ?✔️የሚከተሉት የእኔ ግብዣ ሲሆኑ ሌሎችንም እውነትን ከሀሰት በመለየት እንድ...
04/01/2023

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሚድያዎች Follow, Subscribe ,Like በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ?

✔️የሚከተሉት የእኔ ግብዣ ሲሆኑ ሌሎችንም እውነትን ከሀሰት በመለየት እንድትሸምቱ ምክሬ ነው።⛪️🙏

✝️ EOTC(የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን)
✝️ ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቭዥን
✝️TMC(Tewahido Media Center/ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል)
✝️ ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ (HTM)

የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/

@ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከልተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል - Tewahedo Media Center - TMCTewahedo Media Centerተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል - Tewahedo Media Center - TMCTMC

ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ /Hamere Tewahedo Mediaሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ /Hamere Tewahedo Media
ዲያቆን ሙሉቀን ግርማ ❤🙏❤
Firew Tewahdo

ታህሳስ ፲፱(19)እንኳን አደረሳቹ!!!ከቅዱስ ገብርኤል ክብር የተነሳ ምድር በራች{ራእ ፲፰  ÷፩  }18፥1እንኳን ለመጋቤ ሐዲስ ሊቀ መልእክት  ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ  ክብር በዓሉ በሰላም...
27/12/2022

ታህሳስ ፲፱(19)
እንኳን አደረሳቹ!!!
ከቅዱስ ገብርኤል ክብር የተነሳ ምድር በራች
{ራእ ፲፰ ÷፩ }18፥1
እንኳን ለመጋቤ ሐዲስ ሊቀ መልእክት ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብር በዓሉ በሰላም አደርሳችሁ አደርሰን አሜን!
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡
ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱሳን ሰማእታት ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡፡
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን የቅዱሳን መላእክትን ወርኃዊና ዓመታዊ በዓላቸውን በፀሎትና በምሥጋና ታከበራለች፤ በተለይ ታህሣሥ 19 ቀን የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን (ሠለሥቱ ደቁቅን )ከዕቶነ እሳት ( ከነደደ እሳት ) ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው
ሊቀ መላአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዛሬም ለኛም ይድረስ
በምናውቀውና በማናውቀው መንገድ በሀራችን በህዝባችን ላይ ከምነድ እሳት በምልጃው በተራዳይነቱ ያድነን አሜን
በረከት ረድኤት አይለየን
✞✞✞✞✞✞✞ሰናይ ሚዲያ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ሰናይ ቀን የሰናይ ሚዲያ

📕  አምላክ ያደረጉት ተአምር🌹📘📘•••ወር በገባ በ9 ታስበው የሚውሉ የአባታችን የአቡነ ብፁዐ አምላክ ታአምር ይህ ነው፡ ልመናውና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ከአቡነ ዮሐንስ በኃላ በተሾ...
17/12/2022

📕 አምላክ ያደረጉት ተአምር🌹📘

📘•••ወር በገባ በ9 ታስበው የሚውሉ የአባታችን የአቡነ ብፁዐ አምላክ ታአምር ይህ ነው፡ ልመናውና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ከአቡነ ዮሐንስ በኃላ በተሾመው በአባ ሠረቀ ብርሃን ዘመን ወደ ደብረ ቢዘን ከአባቱና ከወንድሞቹ ጋር በገባ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምረው ዘንድ ለአባ ጴጥሮስ ተሰጠ፡፡

☞የትምህርት ቤት ለጆች ወንድሞቹ ቀኑበት፡፡ ለምን ከእኛ ጋራ እየተማረ እንደ
እኛ አይፈጭም አሉ፡፡ አባ ጴጥሮስም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ብፁዐ አምላክ ሆይ
እዳያዝኑብህ እንደ ወንድሞችህ የምትፈጨውን ውሰድ አለው፡፡
☞የዋህ የሆነ ብፁዐ አምላክም እሺ አምላክህ በጸሎትህ ያስችለኝ አለ፡፡
የሚፈጨውንም ወሰዶ ተኛ በነቃም ጊዜ ተፈጭቶ አገኘው እግዚአብሔር
አመሰገነ ለሰውም አልተናገረም፡፡
☞ለብዙ ጊዜ እንዲህ በሆነበት ጊዜ ጓደኞቹ የተማሪዎች አለቃ ከፈጩት ዱቄት
የሚሰጠው አለ ብለው ተጠራጠሩ፡፡ እስኪ መጣም ሦስት ሦስት ሁነን እንጠብቅ
ከመካከላችን ነቅቶ እህል ወስዶ ዱቄትን የሚሰጠው አለ አሉ፡፡ ሦስት ሦስት
ሁነው ሲጠብቁ የፈጭታዎች
መንቂ ደረሰ፡፡
☞የእየራሳቸውንም ሊፈጩ እሳትን አበሩ፡፡ የብፁ አምላኮ እህል ግን ተፈጭቶ
አገኙት፡፡ ተደንቀውም አትናገሩ፡፡ ሁለትኛ ሦስተኛ እንዲህ የሚሆን እንደሆነ እንይ
አሉ፡፡ እንዲህም ሆነ፡፡ በምሽት በየተራቸው ለብፁ አምላክ የተከፈለውን እህል
ያስቀምጣሉ፡፡
☞ ሦስት ሦስት ሁነውም ይጠብቃሉ፡፡ በነቁም ጊዜ ተፈጭቶ ያገኙታል፡፡ ከዘህ
በኃላ ለመምህሮቻቸው ተናገሩ፡፡
☞እነሱም እንደ ልጆች አድርገው ሦስት ሦስት ሆነው ጠበቁትና ሥራውን
እንግለጥበት አሉ፡፡ ግን ሥራውን አስትተን የቤተ ክርስቲያን ተልኮና መጻሕፍትን
ማንበብ እናዝዘው አሉ፡፡
☞እሱም ጌቶቼ በመፍጨቴ ካልተደስታችሁ ምግብ ማብሰል ወይም ሌላ ሥራ
የወደዳችሁን በቤተ ክርስቲያን ምልከታ ላይ እና መጻሕፍትን ማንበብን እዘዙኝ
አላቸው፡፡
☞ውሃ መቅዳትን አዘዙት፡፡ አባታችንም ብፁዐ አምላክ ቀድቶ ሊሸከም ባነሣው
ጊዜ ውሃው ከራሱ ላይ አንድ ክንድ ከፍ ከፍ አለ ይህን አይተው አደነቁ፡፡
☞ዳግመኛ ዕንጨትም ሊለቅም ሄደ፡፡ በጸሎት ሰዓት ሊጸልይ ሲቆም ዕንጨቶች
የሚበቃውን ያህል ይሰበሰቡለታል፤ ሊሸከምም ሲያስር አንድ ክንድ ከራሱ ላይ
ከፍ ከፍ አለ፡፡
]ወደ ኀላ ባለጊዜም ሊጠብቁት ወንድሞቹ ተመለሱ፡፡ ይህንንም አይተው አደነቁ
መክረንም እስክናዝዝህ ድረስ ታገስ አሉት፡፡ ብሩክ ሁን መንፈስ ቅዱስ
እንደሰየመህ ብፁዕ ሁን አሉት፡፡
]☞የብጹ አቡነ አምላክ ወዳጆቹን እግዚአብሔር በጸሎቱ ይቅር ይበላቸው
ለዘላለሙ አሜን፡፡
☞(ገድለ አቡነ ብፁዐ አምላክ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞ Firew tewhado

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fíŕěŵ Těŵâĥďő posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share