29/09/2025
#ነዳጅ ላይ ግብር ተጣለ!
በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ የ30 በመቶ ግብር በተያዘው በጀት ዓመት ተግባራዊ መደረግ ይጀምራሉ ተባለ‼
የገንዘብ ሚኒስቴር ከ2018 የበጀት ዓመት ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ 30 በመቶ ግብር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ማረጋገጡ ተሰምቷል። ይህ አዲስ ግብር 15 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና 15 በመቶ የኤክሳይዝ ቀረጥን የሚያካትት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ይህ እርምጃ በአገሪቱ የፋይናንስ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑና የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አንዱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል።
ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ባቀረቡት አጠቃላይ የዜጎች በጀት ዉስጥ፣ በተያዘው በጀት ዓመት ተግባራዊ የሚደረጉ የግብር አይነቶችን በዝርዝር አስቀምጠዋል።
በዚህ መሰረት፣ ከነዳጅ ላይ ከሚጣለው አጠቃላይ 30% የኤክሳይዝ ታክስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ በተጨማሪ፣ የንብረት ታክስ ይገኙበታል። እንዲሁም አማራጭ አነስተኛ ታክስ እና የቅድመ ግብር ክፍያ በተመሳሳይ መልኩ በ2018 በጀት ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን ካፒታል ጋዜጣ ለመረዳት ችሏል።
ነዳጅ በማዕከላዊነት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ የግብር ጭማሪው የዋጋ ግሽበቱ እንዲባባስ ያደርጋል የሚል ስጋት ሲከሰት እንደነበር ይታወሳል።
hashtag hashtag hashtag