ሞጃ/Moja tube

ሞጃ/Moja tube Talent

29/09/2022
27/09/2022

ማዲንጎን አፈወርቅ ትላንት ምሽት ክለብ ስራ ላይ ነበር። ዛሬ ጠዋትም ወደአንድ ክሊኒክ የሄደው መኪናውን እየነዳ ነው። ክሊኒኩ ውስጥ ከገባ በኋላ ግን እስትንፋሱ በመቆሙ በኦክስጂን ጭምር ለማትረፍ ተሞክሮ አልተሳካም። አሁን አስከሬኑን ይዘን ወደ ሆስፒታል እየሄድን ነው። ተጨማሪ መረጃ እነግራችኋለሁ።
የቅርብ ጓደኛው ለዘሐበሻ የላከው

27/09/2022

I love sharing my little knowledge with my people. In this channel, I make videos that help students and researchers in their Research, Thesis, and ...

24/09/2022

ግእዝ ዘ-ኢትዮጵያ
*************"
ሀ ማለት ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ማለት ነው፡፡
ሐ ማለት ሐመ ወሞተ በእንቲአነ ማለት ነው፡፡
ኀ ማለት ኀብአ ርእሶ ማለት ነው፡፡
ሁ ማለት ኪያሁ ተወከሉ ማለት ነው፡፡
ሑ ማለት ሰብሑ ለሥመ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኁ ማለት እኁዝ አቅርንቲሁ ማለት ነው፡፡
ሂ ማለት አስተይዎ ብሂዐ ማለት ነው፡፡
ሒ ማለት መንጽሒ ማለት ነው፡፡
ኂ ማለት ዘልማዱ ኂሩት ማለት ነው፡፡
ሃ ማለት ሃሌ ሉያ ማለት ነው፡፡
ሓ ማለት መፍቀሬ ንስሓ ማለት ነው፡፡
ኃ ማለት ኃያል በኃይሉ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሄ ማለት በኵለሄ ሀሎ ማለት ነው፡፡
ሔ ማለት ሔት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኄ ማለት ኄር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ህ ማለት ህልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሕ ማለት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኅ ማለት ኅብስት ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ሆ ማለት ኦሆ ይቤ ወመጽአ ማለት ነው፡፡
ሖ ማለት ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኆ ማለት ኆኅተ ገነት ወልድ ማለት ነው፡፡
ኈ ማለት ኈለቈ አዕፅምትየ ማለት ነው፡፡
ኋ ማለት ሰንኋቲ ሥጋ ሰብእ ማለት ነው፡፡
ኌ ማለት ይኌልቍ አሥዕርተ ማለት ነው፡፡
ኊ ማለት በኊበኊ ሥጋ አዳም ማለት ነው፡፡
ኍ ማለት ዑጽፍት ወኍብርት ማለት ነው፡፡
ለ ማለት ለብሰ ሥጋ ዚአነ ማለት ነው፡፡
ሉ ማለት ሣህሉ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሊ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ላ ማለት ላሜድ ልዑል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሌ ማለት መቅለሌ ዕጹብ ማለት ነው፡፡
ል ማለት መስቀል ዘወልደ አብ ማለት ነው፡፡
ሎ ማለት ዘሀሎ እምቅድም ማለት ነው፡፡
መ ማለት መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሙ ማለት ሙፃአ ሕግ ማለት ነው፡፡
ሚ ማለት ዓለመ ኀታሚ ማለት ነው፡፡
ማ ማለት ፌማ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሜ ማለት ሜም ምዑዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ም ማለት አምላከ ሰላም ማለት ነው፡፡
ሞ ማለት ሞተ በሥጋ ማለት ነው፡፡
ሰ ማለት ሰብአ ኮነ ከማነ ማለት ነው፡፡
ሠ ማለት ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ማለት ነው፡፡
ሱ ማለት ፋሲልያሱ ማለት ነው፡፡
ሡ ማለት መንበረ ንግሡ ማለት ነው፡፡
ሲ ማለት ዘይሴሲ ለኲሉ ዘሥጋ ማለት ነው፡፡
ሢ ማለት ሢመተ መላእክት ማለት ነው፡፡
ሳ ማለት ሳምኬት ስቡሕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሣ ማለት ሣህል ወርትዕ ማለት ነው፡፡
ሴ ማለት ለባሴ ሥጋ ማለት ነው፡፡
ሤ ማለት ሤሞሙ ለካህናት ማለት ነው፡፡
ስ ማለት ልብስ ለዕሩቃን ማለት ነው፡፡
ሥ ማለት ንጉሥ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሶ ማለት መርሶ ለአሕማር ማለት ነው፡፡
ሦ ማለት አንገሦ ለአዳም ማለት ነው፡፡
ረ ማለት ረግዓ ሰማይ ወምድር በጥበቡ ማለት ነው፡፡
ሩ ማለት በኵሩ ለአብ ማለት ነው፡፡
ሪ ማለት ዘይሰሪ አበሳ ማለት ነው፡፡
ራ ማለት ጌራ መድኃኒት ማለት ነው፡፡
ሬ ማለት ሬስ ርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ር ማለት ርግብ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሮ ማለት ፈጠሮ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቀ ማለት ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ወውእቱ ቃል ኀበ
እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቁ ማለት ጽድቁ ለኃጥእ ማለት ነው፡፡
ቂ ማለት ፈራቂሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቃ ማለት ቃልየ አጽምዕ ማለት ነው፡፡
ቄ ማለት ሰዋቄ ኃጥአን ማለት ነው፡፡
ቅ ማለት ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቆ ማለት ቆፍ ቅሩብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቈ ማለት ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን ማለት ነው፡፡
ቊ ማለት ቊርባነ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ቍ ማለት ቍየጺሁ አዕማደ ባላቅ ማለት ነው፡፡
ቌ ማለት ቀነተ ሐቌሁ ለኀጺበ እግረ አርዳኢሁ ማለት
ነው፡፡
በ ማለት በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኵሉ ዓለም ማለት ነው፡፡
ቡ ማለት ጥበቡ ለ

07/09/2022

የ2015 ዓ.ም ባሕረ ሐሳብ
የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ስሌት
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምሕረት + ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ) = 2015 + 5500 =7515
ወንጌላዊ ፦ በዓመቱ የሚሾም ወንጌላዊ ማለት ነው፡፡
ዓመተ ዓለም፥4
7515 ÷ 4 = 1878
1878 ፦ መጠነ ራብዒት ይባላል፡፡
1878×4=7512
7515-7512=1341 ደርሶ ቀሪ 3
ቀሪው ' 1 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
ቀሪው ' 0 ' ከሆነ (ያለ ቀሪ ከተካፈለ)ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል።
ስለዚህ ቀሪው '3' ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ ሉቃስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ ይባላል።
•••
ዕለተ ቀመር፦ መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ነው፡፡
ዕለተ ቀመር= ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት÷7
= 7515 + 1878 =9393
= 9393 ÷ 7 = 1341 ደርሶ ቀሪ 6 ይሆናል
ቀሪው '0 'ከሆነ ሰኞ
ቀሪው '1' ከሆነ ማክሰኞ
ቀሪው '2 'ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው '3 'ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው '4 'ከሆነ ዓርብ
ቀሪው '5 'ከሆነ ቅዳሜ
ቀሪው '6 'ከሆነ እሁድ መባቻ ይሆናል። በመሆኑም ዘንድሮ ቀሪው '6' ስለሆነ ዕለተ ቀመር
እሑድ ይሆናል።
•••
መደብ = ዓመተ ዓለምን በዐቢይ ቀመር(532) በማዕከላዊ ቀመር(76) እና በንዑስ ቀመር(19) በማካፈል ማግኘት እንችላለን
1.7515፥532=14 ደርሶ ቀሪ 67
2.67 ለ ማዕከላዊ ቀመር ወይም ለ 76 መካፈል ስለማይችል ቀጥታ ለንዑስ ቀመር (19) ይካፈላል።
67 ፥19=3 ደርሶ 10 ይቀራል።
ስለዚህ መደብ 10 ይሆናል፡፡
•••
• ወንበር =መደብ ሲቀነስ አንድ ነው(አሐደ አእትት ለዘመን የሚል አዋጅ አለና ላለፈው መሸኛ ለሚመጣው መቀበያ) ።
መደብ - 1=ወንበር (10 - 1= 9) ይሆናል።
በዚህም መሠረት ወንበር 9 ነው እንላለን
• አበቅቴ ፦ጥንተ አበቅቴን በዘመኑ ወንበር አባዝተን ከ 30 በላይ ከሆነ በ30 ገድፈን ቀሪውን ከ30 በታች ከሆነ ደግሞ የመጣውን ቁጥር በመጠቀም እናገኛለን።
አበቅቴ =11×9=99
99፥30= 3 ደርሶ ቀሪው 9 ይሆናል ስለዚህ የዘንድሮው አበቅቴ 9 ነው እንላለን።
አበቅቴን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ያለፈው ዘመን አበቅቴ ላይ ጥንተ አበቅቴን (11) በመጨመር የሚገኘው ቁጥር ከ30 በላይ ከሆነ ለ 30 በማካፈል ቀሪውን ከ30 በታች ከሆነ ደግሞ የመጣውን ቁጥር በመጠቀም ማግኘት እንችላለን ። ይህም ማለት
የ2014 ዓ.ም አበቅቴ 28 ነበር፤ ስለዚህ የ2015 ዓ.ም አበቅቴን ለማግኘት 28+11=39
ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 9 ስለሆነ አበቅቴ '9' ይሆናል ማለት ነው።
• መጥቅዕ፦ ጥንተ መጥቅዕን በዘመኑ ወንበር አባዝተን በ 30 በመግደፍ(በማካፈል) እናገኛለን።
መጥቅዕ = 19×9 = 171
171 ÷ 30= 5 ደርሶ ቀሪው '21 'ስለሆነ መጥቅዕ ዘንድሮ '21 'ይሆናል።
መጥቅዕን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ያለፈውን ዘመን መጥቅዕ ከጥንተ መጥቅዕ ላይ( 19 ) በመጨመር የሚገኘው ቁጥር ከ30 በታች ከሆነ ራሱ ከ30 በላይ ከሆነ ለ 30 ተካፍሎ ቀሪው የዘመኑ መጥቅዕ ይሆናል። ይህም ማለት የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ 2 ነበር፤ ስለዚህ የ2015 ዓ.ም መጥቅዕን ለማግኘት
2+19=21 ስለዚህ የ2015 መጥቅዕ '21' ይሆናል ማለት ነው።
“አበቅቴ ወመጥቅዕ ክልዔሆሙ ኢይበዝኁ እም ሠላሳ ወኢይውኅዱ እም ሠላሳ ወትረ ይከዉኑ ሠላሳ ፤
አበቅቴ ቢበዛ መጥቅዕ ቢያንስ መጥቅዕ ቢበዛ አበቅቴ ቢያንስ ከሠላሳ አይበዙም ከሠላሳ አያንሱም”
ይህም ማለት በሌላ አገላለጽ መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረዉ ውጤቱ ከሠላ

29/08/2022

የጣርማ-በር /የጣር-ማህበር/ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ
።።።።።
በሸዋ በተጉለት ሞጃ ከአዲስ አበባ 180 ኪ.ሜ ከደብረብርሃን ደግሞ 50 ኪ.ሜ ርቀት የጣርማበር ዋሻ አናት ላይ የሚገኘው የጣርማበር ደብረ-ምህረት ቅድስ ጊዬርጊስ ቤተ- ክርስቲያን አቀማመጡ ከፍተኛ ተራራ ላይ ነው ፡፡ ተራራው ሁለት ሲሆን በሰሜን በኩል የሚገኘው ተራራ ጣሊያን የሬድዮ መገናኛ ተክሎ ይጠቀምበት ነበር፡፡ አሁን በቅርብም ድራጋድየስ የሚባል የመንገዱ ስራ ድርጀት ከከንቦልቻ እስከ ጣርማበር አዲሱን መንገድ ሲሰራ የመገናኛ ሳተላይት ተክሎ ተጠቅሞበታል ፡፡
በዚሁ ተራራ ላይ ፈረንጆች ሁል ጊዜ ለጉብኝት የሚገኙበት እና ፖራሹት ወጥረው ተነስተው ወደ ቆላው አንጃበው ይወርዱበታል በደቡብ በኩል የሚገኘው ተራራ በአሁን ሠዓት ከፍተኛ ፖወር ተሠርቶበት የራድዮ አገልግሎት እየሠጠ ነው ፡፡ ይህ ታሪካዊ ቤተ -ክርስቲያን በዚህ
በሁለት ተራራ መካከልና በዋሻው አናት ላይ ይገኛል ፡፡ በቤተ-ክርስቲያኑ ሆነው ይፋትን በሙሉ እስከ አዋሽ ድረስ ይመለከታሉ ከቤተ-ክርስቲያኑ ግራና ቀኝ የሚገኘው ተራራ ብርቅዩ የዱር አራዊትን ዝንጀሮ ከቤተ ክርስቲያኑ በኃላ በኩል ዋልያ ይገኛሎ፡፡ ወደታች በምስራቅ እና በደቡብ ጣልያን የቀደደው ወደ ደሴ እና አዲስ አበባ መሿለኪያ የጣርማበር ዋሻን ይጎበኛሉ፡፡ወደ ቤተክረስቲያኑ ገቢረ ታአምር ስንመለስ ከቤተ -ክርስቲያኑ በስተ ደቡብ በኩል የሚገኘው ተራረ መሀል ላይ ከ7 ቦታ ላይ የሚፈልቅ ወደ ምስራቅ በኩል የሚፈስ የቅዱስ ጊወርጊስ ፀበል ይገኝበታል፡፡ በዚህ ተራራ ከፀበሉ እስከ ቤተ-ክርስቲያኑ በሚገኘው ቦታ ላይ 60 ሽህ ቅዱሳን እንዳሉበት የበቁ አባቶች በተደጋጋሚ ምስክርነታቸውን ተናግረዋል ፡፡
በዚህ ፀበል ብዙ ምዕመናን ተፈውሰዋል እየተፈወሱም ይገኛሉ በተለይም በህክምና የማይበገረውን አጋንት የተቆራኛቸውን በሽተኞች በየጊዜው የሚፈወሱበት እጅግ በጣም ብዙዎች ምስከርነት ሰጥተዋል ፡፡ ይህ ጥንታዊ ቤተ-ክርስቲያን የጣርማበር ደብረ ምህረት ቅዱስ ጊወርጊስ ፈጣን ስለት ሰሚ ታቦት በመሆኑ በ1888 ዓ.ምአጼሚኒሊክ ወደ አድዋ
ጦርነት ሲሄድ በዚህ ቤተክርስቲያን ካህናቱንና ስራዊቱን በቅፅር ቤተ ክርስቲያኑ ገብተው ፀሎት አድርስው ቃል ገብተው ተስለው ነበር ፡፡
‹‹ስለቱም ጣልያንን አድዋ ላይ ድል አድርጌ ከተመለስኩ የጭን ፈረሴን ከነ አሽከሬ እሰጥኀለሁ›› በማለት ቅዱስ ጊወርጊስን ተማጸነው ሄደው ድል አድርገው ሲመለሱም የጭን ፈረሳቸውን የጭራ ወንበር፤ አንድ ጦር፤ ሁለት አጎዛ፤ ከነ ዘውድ መሳ የሚባል አሽከራቸውን ለሙጋድ ፈላጭ ከጣርማበር ከተማ ስር ሁዳድ ከተባለው ቦታ 1 ጋሻ መሬት ለሙጋድ ፈላጭ ግፌት ከሚባል ቦታ 1 ጋሻ መሬት ንጉስ ምኒሊክ ሸልመውታል፡፡
ከዚህም ባሻገር በዚያን ዘመን የጣርማበር ቅዱስ ጊወርጊስ ብር መዝጊያው የሚል ስያሜ ተሠጥቶታል ፡፡ ምክንያቱም ፈጣን ስለት ስሚ በመሆኑም ምእመናን ስለታቸውን ሲደርስላቸው ጥሬ ብሩን በመዝጊያው በሚስማር አምጥተው እየለጠፉት ይገኝ ነበር ፡፡የፈቀደላችሁ የተመቻችሁ ደጁን ሳሙ ከበረከቱ ተካፈሉ።
#
አሜን !!

መልካም ቀን ተመኘሁ ወዳጆቼ።
።።።።
አቤል ወርቁ ዘ-ኮተቤ

24/08/2022

ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ እንዲሉ
ሕወሃት ጦርነቱን ገና ከመጀመሩ ጠጋግኖ ያሰለፋቸው ታንኮችና መድፎች እየተበላሹ ከጥቅም ውጭ እየሆኑ ሲሆን፡በዛሬው የውጊያ ውሎ በርካታ ታጣቂዎቹን አስጨርሶ በርካቶችንም ተማርከዋል። ገና ካሁኑም የተተኳሽ እና የነዳጅ እጥረት እንዳጋጠመው የታወቀ ሲሆን በዚህ ምክንያትም በርካታ ታጣቂዎቹ ለመከላከያ ሰራዊት እጅ እየሰጡ ይገኛሉ፡

ድል ለእናት ኢትዮጵያችን!

24/08/2022
24/08/2022

"የትግራይ ሕዝብ ችግሮችን ለመፍታት ሰላማዊ አማራጭ ዛሬም፤ ነገም ብቸኛው መፍትሔ ነው!" የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት "የትግራይ ሕዝብ ችግሮችን ለመፍታት ሰላማዊ አማራጭ ዛሬም፤ ነገም ብቸኛው መፍትሔ ነው!" ሲል ገልጿል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያወጣው መግለጫ ቀጥሎ ቀርቧል:-

መንግሥት ተገዶ የገባበትን የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት ያስችላሉ ያላቸውን እርምጃዎች ሲወስድ መቆየቱ ይታወቃል።

የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ከወረራቸው የአማራና የአፋር አብዛኞቹ አካባቢዎች ተገፍቶ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ መንግሥት፤

• ሙሉ የሠራዊትና ሎጂስቲክስ አቅም እያለው ወደ ትግራይ ክልል ከመግባት መቆጠቡ

• የተሳለጠና ያልተቋረጠ የሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል እንዲገባ የተናጠል ተኩስ አቁም ማድረጉና ምቹ ኹኔታን መፍጠሩ

• ለሰላም በር ይከፍታል በሚል እስረኞችን መፍታቱ

• የሰላም አማራጭንም አሟጦ ለመጠቀም እንዲቻል የሰላም አማራጭ ዐብይ ኮሚቴን በይፋ ወደ ሥራ አስገብቶ ግልጽ
አቅጣጫንም ማስቀመጡ

• አስፈላጊ የኾኑ መሠረታዊ ቁሳቁሶች ወደ ትግራይ እንዲጓጓዝ ማድረጉ

• በአሸባሪው ቡድን የወደሙ አገልግሎት መስጫዎችን በመጠገን በሦስተኛ ወገን በኩል ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ኾኖም አሸባሪው ቡድን ከውጪ ደጋፊዎቹ ጋር በመኾን ጦርነቱን የመቀጠል ከፍተኛ ፍላጎትን ሲያንጸባርቅ ቆይተዋል፡፡ ከበባውን እንሰብራለን፣ መተማመኛችን ክንዳችን ነው፣ የትግራይ መሬቶች ተወረዋል፣ እናስለቅቃለን፣ወዘተ በሚል ፉከራ ታጅበው ባለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ ትንኮሳዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በምዕራብ በኩል በተደጋጋሚሞክረው ሽንፈትን እየተከናነቡ ተመልሰዋል። በደቡብ ትግራይ በኩልም ተደጋገሚ ሙከራ ቢያደርጉም መንግሥት ሙከራቸውን እያከሸፈ ዋናው መፍትሔ የሰላም መንገዱ ነው በሚል ጉዳዩ እንዳይባባስ አድርጓል። ኾኖም ከመንግሥት በኩል የቀረቡለትን በርካታ የሰላም አማራጮች ኹሉ ወደጎን በመተው የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ታጣቂ ቡድን ሰሞኑን ሲፈጽም የሰነበተውን ትንኮሳ ገፍቶበት ዛሬ ንጋት ላይ በምሥራቅ ግንባር በቢሶበር፣ በዞብል እና በተኩለሽ አቅጣጫዎች ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ጥቃት ፈጽሟል። በወሰደው እርምጃም ተኩስ ማቆሙን በይፋ
አፍርሷል፡፡ የፈጸመው ጥቃትም ኾነ እሱን ተከትሎ ያወጣው መግለጫ አሰቀድሞ ለትንኮሳው ሲዘጋጅ እንደነበር ግልጽ ማሳያ ነው።

ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችንና መላው የጸጥታ ኀይላችን ከሽብር ቡድኑ የተሰነዘረውን ጥቃት በተቀናጀ መልኩ በድል እየመከቱት ይገኛሉ። የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት ከአሸባሪው ቡድን ለመጠበቅም በወትሮ ዝግጁነት ኹሉም የጸጥታ ኀይላችን በተጠንቀቅ ቆሟል።

ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እንደሚባለው ቀድሞም በተካኑበት የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሥራ ራሳቸዉ ተንኩሰው ራሳቸዉ እየጮሁ ይገኛሉ፡፡

ለሰላም እጁን የዘረጋዉን መንግሥት በሐሰት በመወንጀል “ድርድሩ አስቀድሞ ከሽፏል” በሚል ለተለያዩ ወገኖች ጦርነቱ እንደማይቀር ሲያደርጉ የነበረዉን ቅስቀሳ በማጠናከር የትግራይን ወጣት ዳግም ሊማግዱት በይፋ አዉጆ ወደ ጦርነት እየተንደረደረ ነው፡፡

ሰሞኑን ዓለም አቀፍ አጫፋሪዎቹ ካሸለቡበት ብቅ ብቅ ማለታቸውም የጦርነት ዝግጅቱን በፕሮፖጋንዳ ዘመቻ የማጀብ አካል መኾኑ ግልፅ ኾኗል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የትግራይን ወጣት ለማስጨረስ ሕወሓት የሚያደርገውን የጦርነት ጉሰማ እንዲያቆም ጠንካራ ግፊት ማድረግ ይኖርበታል፡፡

በሀገር ውስጥም ኾነ በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ከዚህ የጥፋት ኀይል የሚሰነዘረውን ጥቃት ለመመከትና ኢትዮጵያን የመበተን ግልጽ ዓላማ የያዘውን ይህንን የሽብር ቡድን የጥፋት ሙከራ ለማምከን በጋራ እንድንቆም መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።

የኹሉም ኢትዮጵያውያን ጥያቄ መፍትሔ ማግኘት የሚችለው በሰላማዊ መንገድ ብቻ መኾኑን በመገንዘብ ዛሬም ነገም የሰላም አማራጭ የመጀመሪያ መፍትሔ እንደኾነ መንግሥት ፅኑ እምነት አለው፡፡ ኾኖም አሸባሪዉ የሕወሓት ቡድን በትንኮሳው ከገፋበት ግን መንግሥት ሀገር የማዳን ሕጋዊ፣ ታሪካዊና ሞራላዊ ግዴታ ስላለበት እርምጃ አስፈላጊውን ለመዉሰድ ይገደዳል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ መንግሥትና የፀጥታ ኀይላችን ከነሙሉ ብቃትና ቁመናቸዉ በተጠንቀቅ ላይ ናቸው።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
አሚኮ

24/08/2022
23/08/2022
21/08/2022

enjoy it

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሞጃ/Moja tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category


Other Talent Manager in Addis Ababa

Show All

You may also like