Yohannes Mulu

Yohannes Mulu I am Global digital literacy Professional. "nothing happens until someone sells something"

ስራ ቅጥር ፍለጋ በየታፔላው፣ በየ ሰሌዳው መንከራተት ይብቃችሁ ዉድ ቤተሰቦቼ እኔ የትም ገብቼ እዚሁ እለጥፍላችኋለሁ ብቻ እናንተ ቤጁን ብቻ አርጉ

የቢዝነስ ባለቤት ከሆናችሁ የ FACEBOOK Ad አሰራር በአጭር ጊዜ በመማር የራሳችሁን ቢዝነስ ማስተዋዎቅ ትችላላችሁ። ከነፃ የክፍያ ካርድ ጋር የፌስቡክ Ad አሰራር ከ ሀ እስከ ፖ ስልጠና...
02/12/2024

የቢዝነስ ባለቤት ከሆናችሁ የ FACEBOOK Ad አሰራር በአጭር ጊዜ በመማር የራሳችሁን ቢዝነስ ማስተዋዎቅ ትችላላችሁ። ከነፃ የክፍያ ካርድ ጋር የፌስቡክ Ad አሰራር ከ ሀ እስከ ፖ ስልጠና ተዘጋጅቷል።
የሚያስፈልጋችሁ ሞባይል ስልክ ብቻ ነው።
ስልጠናው Online ለ አንድ ሳምንት ነው። አስፈላጊ ሲሆን 1 to 1 Assistance እስከ 5 ወር ድረስ ይኖራችኋል።
ይህ ስልጠና
1ኛ, ለትላልቅ ቢዝነስ መሪዎች
2ኛ ለሪል ኢስቴት ባለቤቶች
3ኛ, ለሪል ኢስቴት ሴልሶች
4ኛ, ለትናንሽ ሱቆችና አገልግሎት ሰጪዎች
5ኛ, ለOnline ነጋዴዎች
6ኛ, ለሶሻል ሜዲያ ማርኬተሮች እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጄ ተግባራዊ ስልጠና ሲሆን። ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በየራሳችሁ ፌስቡክ ፔጅ የማስታወቂያ አሰራርን የምትማሩበት ነው።

ስልጠናው የሚያካትታቸው;-
1, ግራፊክስ ዲዛይይን አሰራር በቀላል መንገድ
2ኛ, ኮንተንት ክሬሽን
3ኛ, ማስተር ካርድ አወጣጥ
4ኛ, ፌስቡክ Ad አሰራር እና
ለ እያንዳንዱ ሰልጣኝ ለ አምስት ወር የሚቆይ ነፃ ድጋፍ...

ለተጨማሪ መረጃ ለመመልከት ከ 80 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትን የቲክቶክ አካውንት እና ከ 5 ሺህ በላይ ተከታይ ያሉትን ቴሌግራም ቻናል መመልከት ትችላላችሁ

TikTok Account
https://www.tiktok.com/?_t=8rsGBLb3pTD&_r=1

Telegram channel
https://t.me/yohannesmulu1

ለመመዝገብ
በTelegram
t.me/yohannesmulu

በስልክ
0913171017
ይደውሉልን

Achieved Diploma in Global Digital Literacy

Join My Telegram channel👇
02/12/2024

Join My Telegram channel
👇

Check out my TikTok Account👇
02/12/2024

Check out my TikTok Account
👇

84.7k Followers, 66 Following, 354.8k Likes - Watch awesome short videos created by yohannes mulu

NEW SERVICES COMING SOON... ✌️
01/12/2024

NEW SERVICES
COMING SOON... ✌️

30/11/2024

በ2024 ከተከሰቱ የሳይበር ጥቃቶች ውስጥ 40 በመቶ የሚሆነው በራንሰምዌር ቡድኖች የተሰነዘረ መሆኑ ተገለጸ

በ2024 እ.ኤ.አ ከተሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች ውስጥ 40 በመቶ የሚሆኑት ጥቃቶች የተፈጸሙት በቁጥር አምስት (5) በሆኑ የራንሰምዌር ቡድኖች የተፈጸሙ መሆናቸው ተገለጸ ፡፡ እነዚህም የራንሰምዌር ቡድኖች RansomHub፣ PLAY፣ LockBit 3.0፣ MEOW፣ እና Hunters International የሚሰኙ ሲሆን ፤ በ2024 ከተከሰቱ የሳይበር ጥቃቶች 40 በመቶ የሚሆነው የሳይበር ጥቃት የተፈጸመው በእነዚሁ ቡድኖች መሆኑን ኮርቨስ (Corvus) የተሰኘው የሳይበር ደህንት የኢንሹራንስ ተቋም ይፋ ባደረገው ጥናት አመላክቷል፡፡

የኢንሹራንስ ኩባንያው የ2024 ሶስተኛ ሩብ አመት የሥጋት ሪፓርት እንደሚያመለክተው የራንሰዌር ስነ- ምህዳር በመከፋፈሉ ምክንያት የራንሰምዌር ስጋት ደረጃ ከፍ ያለ እንደሆነ ጠቁሟል። በጥናቱ መሠረት በዓለም ላይ ያሉ አጠቃላይ ንቁ የራንሰምዌር ቡድኖች ቁጥር 59 ደርሷል።

ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ሴማንቴክ (Symantec) በተሰኘው የሳይበር ደህንነት አገልጎት ሰጪ ተቋም የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው RansomHub ስኬታማ የሳይበር ጥቃቶች ከመሰንዘር አንፃር ከፍተኛው የራንሰምዌር ስራ መሆኑን አመልክቷል።

ምናባዊ የግል አውታረ መረብ (ቪፒኤን) ተጋላጭነቶች እና ደካማ የይለፍ ቃሎች 30 በመቶ ለሚጠጉ የራንሰምዌር ጥቃቶች አስተዋፅዖ አድርጓል።
ተቋማት እንዲሁም የቢዝነስ ኩባንያዎች የራንሰምዌር ጥቃቶችን ለመከላከል ከባለዙ ወገን ማረጋገጫ (multi factor Authentication) በላይ በሚዘልቁ ባለ ብዙ ሽፋን የደህንነት አቀራረቦች (multi-layered security approaches) መከላከያ መንገድን ማጠናከር እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡

ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com//featured
ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet
ትዊተር (X)፦ https://twitter.com/INSAEthio
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/?_t=8qBKkyp092r&_r=1
የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት ነጻ የስልክ መስመር፡ 933

ባህል ተዛማች ነገር ነው። ባህላችንን ማዛመት እንችላለን፣ የተዛመተ ባህልም ሰለባ ልንሆን እንችላለን። ዋናው ነገር ግን ባህል እንዲዛመት የሚያደርገው በባለ ባህሉ በሚሰጠው ትኩረት እና የራሱ...
19/11/2024

ባህል ተዛማች ነገር ነው። ባህላችንን ማዛመት እንችላለን፣ የተዛመተ ባህልም ሰለባ ልንሆን እንችላለን። ዋናው ነገር ግን ባህል እንዲዛመት የሚያደርገው በባለ ባህሉ በሚሰጠው ትኩረት እና የራሱ የባህሉ ተፈላጊነት ነው። ስለዚህ የኔ አስተያየት ሰው የሚመቸውን ይመርጣል እና የተመቸውን ባህል ሊቀበል ይችላል። ባህልን ለማዛመት ግን ብዙ ጥረት ይፈልጋል። ባህላችንን እናዛምት፣ ባህልም ያለትግል እንቀበል።

በፈረንጅ አፍ ‘ስፒድ ዴቲንግ’ ይባላል። የአማርኛ አቻ የለውም። በአቋራጭ መተጫጨት ነው-ነገሩ። ፖለቲካዊ ቋንቋ ይመስልብናል እንጂ ‘የትዳር ማሳለጫ’ ሊባል ይችላል። ነገሩ ‘የፍቅር...

https://vm.tiktok.com/ZMh4mqLc6/ይህን ቪዲዮ አይቼ በጣም ገረመኝ፣ አሳዘነኝ እና አሳሰበኝ!ስለ አዕምሮ ዕድገት፣ ስለ ህይወት ክህሎትና ስለ ማነቃቃት ህዝባችን ምን አይነት ...
05/11/2024

https://vm.tiktok.com/ZMh4mqLc6/
ይህን ቪዲዮ አይቼ በጣም ገረመኝ፣ አሳዘነኝ እና አሳሰበኝ!
ስለ አዕምሮ ዕድገት፣ ስለ ህይወት ክህሎትና ስለ ማነቃቃት ህዝባችን ምን አይነት አመለካከት እና አስተሳሰብ እንዳለውና አረዳዱ ምን ያክል ዝቅተኛ እንደሆነ ያሳያል። በመሰረቱ መነቃቃት የሚያስፈልገው ለደነዘዙ ሳይሆን ራሳቸውን ለማንቃት ለሚሞክሩ መሆኑ ገባኝ። አውቆ የተደበቀ ቢጠሩት አይሰማም! ከመንቃትና ራስን ለመለወጥ ከመነሳት ይልቅ ጭራሽ ማላገጥና ማሾፍ ሆነ ስራቸው። የሰው ልጅ ስላላዎቀው የራሱ ማንነት ማወቁና በተፈጥሮ ሰው ሆኖ ሲወለድ አብሮት ያለውን ችሎታና አቅም ካልተረዳና ካላወቀ እንዴት ሊለወጥ ይችላል። ይሁንና የሚማሩና ራሳቸውን ለማሻሻል የሚጥሩ ሰዎችን በነፃነት እራሳቸውን እንዳያሳድጉ እንቅፋት ለመሆን መሞከር ምን ሊባለ ይችላል?
አላውቅም

2355 likes, 67 comments. “ ”

27/10/2024

ሽያጭ ላይ ነን!! አሐቲ ድንግል

ሀሁ መጻሕፍት መደብር
*****************************************************************
የፀሐይ ብርሃን በጠቢባን ጥበብ ይሰፈራል፤ የጨረቃም ውበት ይመጠናል፤ ሰማይና ምድር በአድማስ፣ ባሕርም በናጌብ ይወሰናል። የእመቤታችንን ክብር ግን መመጠንና መወሰን ይቅርና ማን ሊመረምረው ይቻለዋል? ''ሊቁ መኑ ዘይክል ነቢበ ዕበይኪ" እንዳለ ገናንነትሽን ማን ይናገራል እያልን ስለ እሷ የተነገረውን ሁሉ በመደነቅ እናነባለን። ሊቃውንቱ ለእመቤታችን ውዳሴ በመጽሐፍ የሚያኖሩት ለኀሊና ማቅኛ እንዲሆን ነው እንጅ ከዚያ በኋላስ ኅሊና አስቦ ወደማይደርስበት ጥልቅ ባሕረ ውዳሴ መግባት ነው።የአበቦችን ውበት በምድረ በዳ፣ ከዋክብትን በሰማይ ላይ በጥበቡ የገለጠ አምላክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም በሊቃውንት አንደበት ይገልጣታል። ቅዱስ ኤፍሬምን አፈ በረከት ቅዱስ ዮሐንስን አፈ ወርቅ ያሰኛቸው የድንግል እመቤታችን ውዳሴ ነው። እስከ ዕለተ ምጽአት የሚነሣው ትውልድ እንዲያመሰግናት በትንቢት የተነገረላት ሉቃ 1:48 ይፈጸም ዘንድ ዛሬ ባሉ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አንደበትም በጉባኤ፣ በማኅሌት፣ በቤተ መቅደስ ትመሰገናለች።

ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን እመቤታችን “ያስተበፅዑኒ ኩሉ ትውልድ" ብላ ከተናገረችላቸው አንዱ ናቸው። ለዚህም ምስክሬ ትምህርታቸው ነው። በዐውደ ምሕረት "የምድር ጌጥ" ይሏታል። በጉባኤ ቤት "ብርሃንኪ የዐቢ እምብርሃነ ፀሐይ” ይሏታል። በበዐታቸው "ሰአሊ ለነ ቅድስት" ይሏታል። ዛሬ ደግሞ ተነቦ የማይጠገብ ውዳሴዋን በመጽሐፍ አቅርበውልናል።

ይሄ መጽሐፍ በትውፊት የምናወርሰው፥ ነገር ግን እያየነው የተደረሰ አዲሱ አርጋኖን ነው። ቅድመ ዓለም በአምላክ ኅሊና ከታሰበው ድኅረ ዓለም በነቢያት እስከተነገረው፥ በመላእክት ከተዘመረው በሐዋርያት እስከተሰበከው ሊጠቀስ የሚገባው ተጠቅሷል። የእመቤታችን ነገር ሐረግ ነው፤ በነካነው ጊዜ ሁሉ ብሉያትን ሐዲሳትን ሊቃውንትን ያንቀሳቅሳል።

ርእሰ ሊቃውንት እንደ ሐረግ ሳቢ አንድ ጥቅስ በመዘዙ ጊዜ የመጻሕፍት ሁለንተናቸው ይንቀሳቀሳል። ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈ መጽሐፍ ሁሉ እመቤታችን የሌለችበት መጽሐፍ አይገኝም።ይህን መጽሐፍ ባነበባችሁ ጊዜ ይህንን እውነት ትረዱታላችሁ። "አሐቲ ድንግል" አንድ መጽሐፍ ብቻ አደለም። ትርጓሜ፤ ድርሳን፤ ምዕላድ፤ ውዳሴም ነው። ሁልጊዜ የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳንን ስብከት ስሰማ የምመኘው ይህንን መጽሐፍ ነበር። አንዳንዴ ስብከት መሆኑን ረስቼ መጽሐፍ የሚያነቡልኝ ይመስለኝ ነበርና። እነሆ የተመኘሁት መጽሐፍ በብራና ተጠቅሎ በቤተ መጻሕፍት ተጥሎ አገኘነው። ከእኔ ጋራ የተወለደውን የመጻሕፍት ንጉሥ ታዩ ዘንድ ኑ!

ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር

ሀሁ መጻሕፍት መደብር
**********************************************************

በመደብራችን ሁሉም አይነት መጻህፍት ይገኛሉ። የትምህርት መርጃ መጻህፍት፣ የልብወለድና የታሪክ መጻህፍት፣ መንፈሳዊና አለማዊ መጻህፍት፣ የግጥምና የወግ መጻህፍት፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ እሳቤ መጻህፍት፣ የፍልስፍና እና የስነልቦና መጻህፍት ሁሉም አሉ። ሀሁ መጥታችሁ የፈለጋችሁትን ብቻ ሳይሆን የረሳችሁትንም መጻህፍት ታገኛላችሁ። ከእናንተ የሚጠበቀው ግዜ ወስናችሁ መምጣት ብቻ ነው።

ሌላው በመደብራችን ከ20—50% ቅናሽ አለ። አስር መጽሀፍ ለሚገዙ ደንበኞቻችን ደግሞ አንድ መጽሀፍ በነጻ እናበረክታለን። ስትጎበኙን በደስታ፣ በቅልጥፍና እናስተናግዳችኋለን። ባላችሁበት ሆናችሁ መረጃ ለመጠየቅ ካሻችሁም ስልኩን አንስታችሁ ሀሎ በሉን።

በመደብራችን ሀሁ መጻህፍት ሁሉንም አይነት መጽሀፍ ያገኛሉ፦

የቆዩ እና አዲስ
መንፈሳዊም ሆነ አለማዊ
ክላሲክም ሆነ ዘመናዊ
የታሪክ፣ የፍልስፍና፣ ልብወለድ፣ የትምህርት፣ የስነልቦና፣ የሃይማኖት፣ ግለታሪክ ወዘተ

ሀሁ መጻህፍት መደብርን
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/?_t=8mYzg7vMRJ0&_r=1
በቴሌግራም https://t.me/fanab123
እንዲሁም በራሱ የፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/hahubook?mibextid=ZbWKwL
ማግኘት ይቻላል።

የፈለጋችሁትን መጽሀፍ እዘዙን፣ ጠይቁን። በቅልጥፍና፣ ከ20-50% በሚደርስ ቅናሽ፣ በደስታ እናቀርብላችኋለን።

አስታውሱ! በመደብራችን 10 መጻህፍት ለሚገዛ 1 መጽሀፍ በነጻ እንሰጣለን።



አድራሻ ቁ.1 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን

ስ.ቁ 0911006705/0924408461

27/10/2024

ያለንበት ሁኔታ በጨረፍታ!

06/10/2024
Exciting news! 🎓🎓I've just completed my diploma in Global Digital Literacy from Alison. This course has equipped me with...
02/10/2024

Exciting news! 🎓🎓
I've just completed my diploma in Global Digital Literacy from Alison. This course has equipped me with valuable skills to navigate the digital world confidently and effectively. I'm excited to apply my knowledge and make a positive impact online.

28/09/2024

መምህር ኤስድሮስ የተባሉት ሊቅ ያስተማሩትን የመንፈስ ልጃቸዉን ሲመክሩ እንዲህ አሉት፡፡

"ልጄ ከመሃይም አትጣላ ፣ ደጋፊው ብዙ ስለሆነ ያሸንፍሃል"

ከ ይሰማዕከ ወርቁ

27/09/2024

🔥 Self-confidence is key. 🔥⁣⁣⁣

ለአደባባይ በዓላት ‹‹በሰላም ተከብሮ ዋለ›› የዜና ርእስ መሆኑ ይቅር(በአማን ነጸረ)እንደ መስቀልና ጥምቀት ያሉ የአደባባይ በዓላት ሲደርሱ ስለበዓሉ ትርጉምና አከባበር ከሚነገረው ይልቅ ስለ...
25/09/2024

ለአደባባይ በዓላት ‹‹በሰላም ተከብሮ ዋለ›› የዜና ርእስ መሆኑ ይቅር
(በአማን ነጸረ)

እንደ መስቀልና ጥምቀት ያሉ የአደባባይ በዓላት ሲደርሱ ስለበዓሉ ትርጉምና አከባበር ከሚነገረው ይልቅ ስለ ፀጥታና ሰላም የሚነገረው ዜና መበርከት ይጨንቃል፡፡ በዓላት በተጋነነ የፀጥታ ድባብ (securitization) ሲያልፉ ያፍናል፡፡

እንደ ሚዲያ፣ ዜናዎቹ የበዓሉን ትርጕም አጉልተው የሰላሙ ነገር ንዑስ ርእስ ቢሆን ጥሩ ነው፡፡ የፀጥታና ሰላም ሰበካው፣ የማስጠንቀቂያው ጋጋታ ለበዓሉ ገጽታ የስጋት ጥላ ያላብሳል፡፡ መስቀል የጥል ግድግዳ የፈረሰበት የሰላም ምልክት ነው፡፡ ‹‹ትእምርተ ሰላምነ›› እንለዋለን፡፡ በዚያ መንፈስ ቢታይ እንወዳለን፡፡
--
የአደባባይ በዓላት ሲደርሱ ‹‹ወቅታዊ ጉዳይ›› እየተባለ ወጣቶችን በየጣቢያው ማቆያዎች አስሮ ለማቆየት የትኛው ሕግ እንደሚፈቅድ አልተገለጠልንም፡፡ ስጋት ካለ ማሳወቅ፣ መምከር፣ ባስ ካለም አስጠንቀቆ መልቀቅ ያንጻል፡፡ ከዚያ ባለፈ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሌለበት አደገኛ ልማድ እየሆነ የመጣው ‹‹ወቅታዊ ጉዳይ›› በሚል ሰበብ የሚደረግ እስር የሕግም የሞራልም ድጋፍ የለውም፡፡ ለበዓሉ አክባሪዎች ሕሊናን ይረብሻል፡፡
--
አሁንም፡- ‹‹በሰላም ተከብሮ ዋለ›› ዜና ባይሆን ደስ ይለናል፡፡ ‹‹በመላ ኢትዮጵያና ኦርቶዶክሳውያን ባሉበት ሁሉ በታላቅ ድምቀት ተከበረ›› እንዲባል ነው የምንፈልገው፡፡ በዓልን በሰላም ማክበር ዜናም ሆነ ሰበር ዜና አይደለም፡፡ ለሺህ ዓመታት በጨዋነት ሲከበር ኖሯል፣ ይኖራልም፡፡
--
ሀባ ሰላማ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ
በአማን ነጸረ

Best Ethiopian 100 birr!
24/09/2024

Best Ethiopian 100 birr!

Address

Piazza
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yohannes Mulu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yohannes Mulu:

Share