Bernos Publishers

Bernos Publishers -Preschool and kindergarten Literacy and numeracy curricula
- Children Stories in different local languages
- Teachers Training
- Transcription

18/01/2025

ቅድመ ምንባብ መጽሃፍ 2... የዚህን ሳምንት ታሪክ ለልጆቻችሁ እነሆ

መልካም የጥምቀት በአል ለሁላችንም።

09/01/2025

እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን የልደት በአል አደረሳችሁ።

በተቻለን አቅም በሳምንት አንድ ቅድመ _ንባብ መጽሃፍትን (በቪዲዎ) ለልጆችዎ እንለቃለን።
የቅድመ_ምንባብ መጽሃፍት ማለት ገና ማንበብ ካልጀመሩ ልጆች ጀምሮ በጥቂቱ ማንበብ እስከ ጀመሩ ልጆች (3-8 አመት) የሚሆኑ መጽሃፍት ናቸው። ጥቂት ቃላት እና ብዙ ስዕሎች አሏቸው። አላማቸውም ስዕላትን አይተው እንዲያነቡ፣ የቃላት እውቀታቸውን መጨመር እና የልጆችን የማንበብ ልምድ መገንባት ነው።

የመጀመሪያውን መጽሃፍ እነሆ። እባካችሁ ለልጆቻችሁ አንብቡላቸው ለእኛም አስተያየታችሁን ስጡን።

04/01/2025

እንኳን አደረሳችሁ።
የልጆቻችሁን የገና ስጦታ አዘጋጅተናል። 4 አስደሳች የተረት መፅሀፍ አዘጋጅተናል። ደውሉልን 0930276767

02/01/2025

ሰላማችሁ ይብዛ!
ከዚህ ግሩፕ ብዙ ወላጆች እየደወላችሁ ልጆቻችሁን እንግሊዝኛ ንባብ ማስተማር ከየት መጀመር እንዳለባችሁ ትጠቁናላችሁ። ማንበብ በእርግጥ የሚጀምረው በፊደላት ሳይሆን በስእል ነው። እሱን ለሌላ ግዜ እናስተላልፈው እና ልጆች ለማንበብ የፊደላትን ድምፅ ለይተው ማወቃቸው መሰረታዊ እና ግዴታ ነው። ብዙ ልጆች የእንግሊዝኛ ድምፆችን በትምሀርት ቤት የሚማሯቸው ልክ አይደሉም። ለምሳሌ 'b' በጣም አጭር 'ብ' የሚል ድምጽ እንጂ በተለምዶ 'ብ+እ" አይደለም። በተለምዶ አስተማሪዎችን ከድምፆቹ ጋር የሚጨምሩት 'እ' የሚል ድምጽ አለ። ለማንኛውም ይህች አጭር ቪዲዎ የእንግሊዝኛ ፊደላትን ድምፅ እንድትለዩ እና ልጆቻችሁንም በትክክለኛው መንገድ እንድታስተምሩ ይረዳችኋል። በዛውም ድምፆቹን ለመጥራት አፋችንን እንዴት መክፈት እንዳለብን ከቪዲዎው መማር እንችላለን።
በርኖስ አሳታሚዎች ነን!

23/12/2024
ሰላማችሁ ይብዛበርኖስ አሳታሚዎች ነን።
22/12/2024

ሰላማችሁ ይብዛ
በርኖስ አሳታሚዎች ነን።

15/12/2024

መልካም ሰንበት!
የFoundation Level መፅሀፎቻችንን የገዛችሁ አጠቃቀሙን በጠየቃችሁን መሰረት ይኸው።

ምስጋናባለፈው ቅዳሜ Yeneta Academy የተማሪ_አስተማሪ_ወላጅ ውይይት ቀናቸው ነበር። በት/ቤቱ አስተዳደር ወ/ሮ ቴሪ መልካም ፈቃድ አማካኝነት እኛ በርኖስ አሳታሚዎች መጽሃፎቻችንን ለኬ...
09/12/2024

ምስጋና
ባለፈው ቅዳሜ Yeneta Academy የተማሪ_አስተማሪ_ወላጅ ውይይት ቀናቸው ነበር። በት/ቤቱ አስተዳደር ወ/ሮ ቴሪ መልካም ፈቃድ አማካኝነት እኛ በርኖስ አሳታሚዎች መጽሃፎቻችንን ለኬጂ ወላጆች አቅርበን ነበር። በቦታ የታዘብናቸው ነገሮች ።

* የግቢው ማህበረሰብ ከጥበቃ ጀምሮ፣ ረዳት መምህራን፣ መምህራን፣ አስተባባሪዎች እና አስተዳደሯ ላደረጉልን መልካም አቀባበል እና እንክብካቤ እናመሰግናለን። ሁሉም በሙሉ በተነቃቃ ስሜት እና ደስታ ነበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩት።
* የወላጅች ለልጆቻቸው አጋዥ መጽሃፍትን የመግዛት ፍላጎትን አስተውለናል። እንዲሁም ሁሉም በሚባል ደረጃ ወላጆች የልጆቻቸውን የንባብ ደረጃ ጠንቅቀው ያውቃሉ፣ ያ ማለት በምን አይነት አጋዥ መጽሃፍት ማገዝ እንዳለባቸው ያውቃሉ ማለት ነው።
* አንዳንድ ወላጆችም ልጆቻቸውን እንዴት ማገዝ እንዳለባቸው ግዜ ወስደው ሲያወሩን ነበር።
* ተማሪዎቹ መጽሃፍት ተደርድረው ሲያዩ ሮጠው መጥተው ነበር ሲያነቡ የነበሩት። የተማሪዎችን ከፍተኛ የማንበብ ፍላጎት አስተውለናል።
በአጭሩ...የ Yeneta Academy ኬጂ ማህበረስብ በሙሉ ላደረጋችሁልን ትብብር እናመሰግናለን። እንዲሁም ለት/ቤቱ ባለቤት እና አስተዳድር ቴሪ ለመልካም ፈቃድሽ ከልብ እናመሰግናለን።

Cheers ለወደፊት አብሮ መስራታችን!

ምን ታስባላችሁ?
03/11/2024

ምን ታስባላችሁ?

ምስጋናያለፈው አርብ እና ቅዳሜ በማልድ ትምህርትቤት (MALD Educational Support) የወላጅ እና የአስተማሪ ምክክር ቀን ነበር። ከውይይቱ በተጨማሪ በማልድ አስተዳደር መልካም ፈቃድ...
03/11/2024

ምስጋና
ያለፈው አርብ እና ቅዳሜ በማልድ ትምህርትቤት (MALD Educational Support) የወላጅ እና የአስተማሪ ምክክር ቀን ነበር። ከውይይቱ በተጨማሪ በማልድ አስተዳደር መልካም ፈቃድ ጥቂት የልጆች መማሪያ መሳሪያ አዘጋጆች (እኛ በርኖስ አሳታሚዎችን ጨምሮ) መሳሪያዎቻችንን እንድናስተዋውቅ እና እንድንሸጥ ተጋብዘን ነበር። ልዪ ምስጋና ለትምሀርት ቤቱ አስተዳደር _ ቆንጂት ሞገስ። በዚህ ሁለት ቀናት ያስተዋልናቸውን ጥቂት ነገሮች እናካፍላችሁ።
1. ትምህርት ቤቶች ከሚያቀርቧቸው መማሪያ መሳሪያዎች ተጨማሪ ሌሎች የልጆች መማሪያ መሳሪያዎችን እና የማስተማሪያ መንገዶችን ለመቀበል ሁሌም በራቸውን መክፈት አለባቸው። (የአገሪቱን የት/ት ህግ እንገነዘባለን)
2. ወላጆች ሁሌም ለልጆቻቸው የተሻሉ የመማሪያ መሳሪያዎችን ለማግኘት ዝግጁ መሆናቸውን አስተውለናል፣ አድንቀናልም። አብዛኞቹ ወላጆችም ተጨማሪ መሳሪያቸውን ለማወቅ ስልኮቻችንን ወስደው የእነሱንም ሰጥተውን ነው የሄዱት። የወላጆችን ከፍተኛ የንባብ መጽሃፍትን ፍላጎት አስተውለናል።
3. በቦታው ላይ ላልተገኙ ወላጆች መምህራን ምን ያህል አይን እና አፍ ሆነው ያዩትን መሳሪያዎች እየደወሉ ሲገልፁላቸው እና ክፍል ውስጥ ቀን በቀን ለሚያገኟቸው ለልጆቻቸው ምን ያህል እንደሚጠቅማቸው ሲያስረዱ አይተናል።
4. የትምህርት ቤቱ መስተዳድር፣ ወላጆች እና መምህራን በሙሉ የበለጠ መጽሃፍት እንድናመርት እና ገበያው ላይ እንድናቀርብ መነሳሳትን ፈጥረውብናል፣ ሁላችሁንም እናመሰግናለን።

ሰላም። እንደ እኛ ቅዳሜ እና እሁድን ያዘዛችሁንን መጽሃፎች ከቦታ ቦታ ስናደርስ እና ስንወያያችሁ ያሳለፍነው አይነት አስደሳች የሳምንት መጨረሻ እንደነበራችሁ እናምናለን። በባለፈው በጠየቃችሁ...
13/10/2024

ሰላም። እንደ እኛ ቅዳሜ እና እሁድን ያዘዛችሁንን መጽሃፎች ከቦታ ቦታ ስናደርስ እና ስንወያያችሁ ያሳለፍነው አይነት አስደሳች የሳምንት መጨረሻ እንደነበራችሁ እናምናለን። በባለፈው በጠየቃችሁን ጥያቄ መሰረት የልጆቻችሁን የንባብ ደረጃ የምትለዩበት ትንሽ ፈተና መሳይ መመዘኛ አዘጋጅተንላችኋል። ቀጥሎ ያለውን ሊንክ በመጫን ያውርዱና የልጆቻችሁን የንባብ ደረጃ ይወቁ። ከዛም ምን አይነት መጽሃፍት መግዛት እንዳለባችሁ እና በምን መንገድ ማገዝ እንዳለባችሁ በቀላሉ ትረዳላችሁ። https://drive.google.com/file/d/1kuqGwU6cWVKmQ9IfDnFhFAsMqzljFGrc/view?usp=drive_link

Address

Haile Garment Square
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 18:00
Tuesday 08:00 - 18:00
Wednesday 08:00 - 18:00
Thursday 08:00 - 18:00
Friday 08:00 - 18:00
Saturday 08:00 - 18:00

Telephone

+251979819273

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bernos Publishers posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Bernos Publishers:

Videos

Share

Category