15/01/2023
የዶ/ር ናዲያ ይመርን ህይወት እንታደግ‼️
==========================
ህክምና ስንማር ከዶ/ር ናዲያ ጋር አንድ ባች ነበርን። ለክፍል ልጆች ሁሉ ከፍተኛ አክብሮት አላት። ለሁላችንም እጅግ መልካም ጓደኛችን ናት። ለታካሚዎቿ ያላት ፍቅር ግን የተለየ ነው። ዲውቲ ያደርን ቀን አብዛኞቻችን ወደ ቤት ለመሄድ እንቸኩላለን። እሷ ግን ዲውቲ አድራ እንኳ ታካሚ ከመጣ እስከ ምሽት ያለ ተራዋ ትቀጥላለች። በተለይ ለወሊድ የሚመጡ እናቶችን አይታ ማለፍ አይሆንላትም። ከህክምናው ባሻገር የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ከቻለች ሰው ልካ ካልሆነም ራሷ ሱቅ ሄዳ ስትገዛላቸው ይገርመን ነበር።
አንድ የማይረሳኝ የዶ/ር ናዲያን ታሪክ ልንገራችሁ። አንዲት እናት ብዙ ደም ፈሷት ዶ/ር ናዲያ ደም ለገሰቻት። ህክምና ውስጥ ብዙዎቻችን ለታካሚዎቻችን ደም ስለምንሰጥ አያስገርምም። ከ15 ቀን በኋላ ሌላ ደም የሚያስፈልጋት እናት ነበረች። ደም የሚሰጣት ጠፋ። የታካሚዋ ዘመዶች "እኔ ራሴ የለኝም" ብለው እንቢ አሉ። እኛም በቅርብ ሰጥተን ስለነበር ልንሰጣት አልቻልንም። ዶ/ር ናዲያ "እኔ ሰጣለሁ" አለች። "አንቺ ከሁለት ሳምንት በፊት ሰጥተሻል። ሶስት ወር መቆየት አለብሽ።" አልናት። "ሁለት ሶስት ቀን ቢደክመኝ ነው። ሰውነቴ ይተካል። ደግሞ ሚሪንዳ በደንብ እጠጣለሁ።" ብላ በሁለት ሳምንቷ ድጋሚ ደም ለግሳ የወላዷን ህይወት አተረፈች።
ዶ/ር ናዲያ በማህፀን እና ፅንስ ስፔሻላይዝ ስታደርግ አብረናት የተማርነው ሁላችንም አልገረመንም። ከድሮ ጀምሮ ለእናቶች ልዩ ፍቅር እንዳላት እናውቃለን። ስፔሻላይዝ ካደረገች በኋላ እናቶችን የተሻለ መርዳት ጀመረች። በአንድ ለሊት 12 እናቶችን በቀዶ ጥገና አዋልዳ ለተጨነቁ ቤተሰቦች የምስራች አብስራ ታውቃለች።
ዶ/ር ናዲያ አደጋ አጋጠማትና የጀረባዋ አጥንት ተሰበረ። ከወገብ በታች ፓራላይዝድ ሆነች። የምትወደውን ስራ መስራት አቆመች። ወገቧን ለማከም ብዙ ጥረት ተደረገ ግን ሊሻላት አልቻለም‼️አሁን የምትገኝበት አለርት ሆስፒታል የሀኪሞች ቦርድ ወደ ውጭ ሄዳ እንድትታከም ወስኗል። ስለሆነም ቱርክ ሀገር ሄዳ መታከም እንድትችል የተጠየቀችው ገንዘብ 22 ,000 USD (1.25 ሚሊየን ብር በላይ) ነው‼️
እኔ የምችለውን አደርጋለሁ። ደግነቷን አውቀዋለሁ‼️ ሁላችንም የምንችለውን ያህል አግዘን ህይወቷን እንታደግ‼️ ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር እናድርግ።
ናዲያ ይመር ሰይድ
1000507299548
የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ