Hager ሃገር

Hager  ሃገር Your Window to Ethiopia's Political, Social, and Economic Realities Shaping the Narrative of Ethiopian Affairs with Honest Journalism.
(2)

የሚኒስትሮች ም/ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈየሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 37ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ምክር ቤ...
27/06/2024

የሚኒስትሮች ም/ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 37ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
1. በመጀመሪያ ምክር ቤቱ የተወያየው የእንስሳት ጤና እና ደህንነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡
ሀገራችን ከእንስሳት አለም አቀፍ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ እንድትችል ያለንን የእንስሳት ሀብት ማወቅ ፣ የእንስሳት ጤና እና ደህንነትን ማስጠበቅ፣ ከእንስሳት ወደ ሰው፣ ከሰው ወደ እንስሳት ተላላፊ በሽታን መከላከል፣ ድንበር ተሻጋሪ የእንስሳት በሽታዎች ቁጥጥር ስርዓት በበቂ ሁኔታለመተግበር እና የምርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የህግ ማእቀፍ ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡
በዚሁም መሰረት የዘርፉን ተዋናዮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችል ግልጽ የእንስሳት ጤና እና ደህንነት ክትትል እና ቁጥጥር ስርአት የሚዘረጋ ረቂቅ አዋጅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም በአዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በኢትዮጵያና በኩዌት መካከል በስራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ አዋጅ ላይ ነው፡፡
ስምምነቱ በኩዌት በቤት ሰራተኝነት ተሰማርተው የሚገኙ እና በቀጣይም ከአሰሪዎች ጋር የሥራ ውል ውስጥየሚገቡ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መብታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል ሕጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖር፣ በአገሪቱ የሚገኙ ዜጎቻችን ክብር፣ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው እንዲሁም በሁለቱ መንግስታት መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያግዝ ነው፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትእንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
3. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የኤሌክትሮኒክ ፊርማን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 1072/2010 ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እና ለአስተዳደሩ እንደ የስልጣናቸው አዋጁን የሚያስፈጽሙበት ዝርዝር ህግ የማውጣት ውክልና በግልፅ ባልሰጠባቸው ጉዳዮች ላይ ህግ የማውጣት ውክልና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እና ለአስተዳደሩ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
4. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የሳይበር ደህንነት ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡
ነባሩ ፖሊሲ ለበርካታ አመታት በስራ ላይ የቆየ በመሆኑ የፖሊሲ አቅጣጫ የሚያስፈልጋቸው አዳዲስ ዓለም አለምቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ሃገራዊ የሳይበር ደህንነትጉዳዮች በዘርፉ ውጤታማነት ላይ ተፅዕኖ የፈጠሩ በመሆኑ፤ የግል እና የመንግስት ቅንጅታዊ እና የትብብር አሰራር በግልጽ ማስቀመጥ በማስፈለጉ እና ሌሎችም ዋና ዋና የትኩረት መስኮችን ያካተተ ግልጽ የአፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ዘዴ ያለው ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ምክር ቤቱ በፖሊሲው ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
5. ብሄራዊ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት ጉዳይ ነው፡፡
አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ (AI) በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከተዋወቀበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ሀገራት ከጥቃቅን የመዝናኛ እና የመገልገያ ዘዴዎች እስከ ብሔራዊ ደኅንነትና መረጃ አገልግሎት ላሉ ቁልፍ ጉዳዮች እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡
ሀገራችንም ቴክኖሎጂውን በይበልጥ ለማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አገልግሎት ለማዋልና የሀገር ደህንነትን በማስጠበቅ በዘርፉ ተወዳዳሪ አቅምን ለመፍጠር ተቋም ከማቋቋም ጀምሮ በርካታ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም ቀሪ ስራዎችን መስራት ይጠበቅባታል። የተጀመረውን ለማስቀጠል፣ ዘርፉን ለማሳደግ፣ መንግስት በዘርፉ ሊደርስ የፈለገበትን ግብ ለማመላከት እና ዘርፉ የሚገራበትን አቅጣጫ ለማሳየት በሚረዳ መልኩ ብሄራዊ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱ በፖሊሲው ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶች ታክለውበት ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
6. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በጤና ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ወቅቱ የደረሰበትን የህክምና አገልግሎቶች ታሳቢ ያደረገ፣ የጤና አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል እና የጤና አገልግሎት አስተዳደር ስርዓትን የሚዘረጋ ግልጽ እና ወጥ የሆነ የሕግ ማእቀፍ በስራ ላይ ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
7. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው የመድሀኒት ፈንድ እና የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይነው፡፡
ጥራታቸው የተረጋገጠ መሠረታዊ መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋና ዘላቂነት ባለው መልኩ ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ ማቅረብ የሚያስችል ዘመናዊ የመድኃኒት አቅርቦት ሠንሰለት ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
8.በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የጤና ፋይናንስ ስትራቴጂ ላይ ነው፡፡
ሀገራችን በአለምአቀፍ ደረጃ የፈረመችውን የዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካትና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎትን መሠረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስፈልገዉን በቂ እና ቀጣይነት ያለው የሀብት አሰባሰብ እና የወጪ አሸፋፈን ስርአት መዘርጋት የሚያስችል የጤና ፋይናንስ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱ በስትራቴጂው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ተሽከርካሪ በሰረቀችው ግለሰብ ላይ  ክስ ተመሰረተባት፡፡ ግለሰቧ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት መቅረቧን  አዲስ አበባ ፖሊስ  አስውቋል፡፡ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ  ክፍለ ከተማ...
27/06/2024

ተሽከርካሪ በሰረቀችው ግለሰብ ላይ ክስ ተመሰረተባት፡፡
ግለሰቧ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት መቅረቧን አዲስ አበባ ፖሊስ አስውቋል፡፡
ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ቢጫ ፎቅ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ መኪና ሰርቃ በፖሊስ ክትትል የተያዘችው መና ከበደ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ በመተላለፍ የማይገባትን ብልፅግና ለማግኘት ንብረትነቱ የግል ተባዳይ የሆነው
የሰሌዳ ቁጥር 3 B 23912 አ/አ ተሽከርካሪ በመስረቋ ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ልኮ ክስ እንዲመሰረትባት ማደረጉን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ግለሰቧ ተለቃለች እንዲሁም ወንጀሉን ሳታውቅ ነው የፈፀመችው የሚሉ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛል፡፡
የግል ተበዳይ መኪናቸው መሰረቁን ለፖሊስ ያመለከቱ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ግለሰቧም ተሽከርካሪውን ለእረጅም ሰዓት ይዛ መሰወሯ ታሳቢ በማድረግና ድርጊቷም በማስረጃ በመረጋገጡ ዓቃቤ ህግ በተሽከርካሪ ስርቆት ክስ መመስረቱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
Via አዲስ አበባ ፖሊስ

ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ በአሜሪካ መግለጫቸው ምን አሉ?“200 ሚ. ብር ጉቦ እንድንከፍል ተጠይቀናል””ፍትህ ለፐርፐዝ ብላክ“ የተሰኘ ዘመቻ ተጀምሯልለጠ/ሚኒስትሩ ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋ...
22/06/2024

ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ በአሜሪካ መግለጫቸው ምን አሉ?
“200 ሚ. ብር ጉቦ እንድንከፍል ተጠይቀናል”
”ፍትህ ለፐርፐዝ ብላክ“ የተሰኘ ዘመቻ ተጀምሯል
ለጠ/ሚኒስትሩ ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል
የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ፣ ከትላንት በስቲያ ከአገር ወጥተው አሜሪካ የገቡ ሲሆን፤ ከአገር ለመውጣት የተገደዱት ለደህንነታቸው በመስጋት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ረፋዱ ላይ በስካይፒ ከአሜሪካ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ፤ “የዛሬዋ ቀን ለእኔ ከባድ ናት፤ በግፈኞች ከአገር እንደወጣ በመገደዴ የልጄ ክርስትና ላይ ለመገኘት አልቻልኩም፤” በማለት ነው የጀመሩት፡፡
ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ ሰዓት በፐርፐዝ ብላክ ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝተው፣ የኩባንያቸውና የራሳቸው የግል የባንክ ሂሳብ ለ3 ሳምንት ያህል ምክንያቱ ሳይነገራቸው መታገዱን ለጋዜጠኞች ያሳወቁት ዶ/ር ፍስሃ፤ በዚህ ሳምንት ደግሞ ከአሜሪካ ሆነው በደረሰባቸው ማስፈራሪያና ጫና ከአገር ለመውጣት መገደዳቸውን ተናግረዋል፡፡
የኩባንያቸው የባንክ ሂሳብ በማያውቁት ምክንያት ተዘግቶ እንቅስቃሴው መስተጓጎሉን የተመለከተ መግለጫ ለጋዜጠኞች መስጠታቸውን ተከትሎም፣ ብዙ አሳዛኝና ከባድ ነገሮች መከሰታቸውን ጠቁመዋል፤ ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡
“ክሱ ባይደርሰንም የተዘረዘሩብን ክሶች በጣም የሚያስገርሙ ናቸው” ያሉት ዶ/ር ፍስሃ፤ “በወንጀል የተሰበሰበ ገንዘብ፣ ህገወጥ የመሣሪያ ዝውውር፣ ፋኖዎችን በገንዘብ መርዳት፣ ወዘተ-- የሚሉ ፈጽሞ ከእኛ ጋር የማይገናኙ ወንጀሎች መሆናቸውን ተረድተናል” ብለዋል፤ በመግለጫቸው፡፡
የዘረዘሯቸው ወንጀሎች በሙሉ ዋስትና የማያሰጡ ናቸው ያሉት ዶ/ር ፍስሃ፤ ዛሬ የሚከበረውን የልጄን ክርስትና ትቼ አገሬን ለቅቄ ለመውጣት የተገደድኩት ለደህንነቴ በመስጋቴ ነው፤ ብለዋል፡፡
“ኩባንያችን ሁሉንም ነገር የሚሰራው መቶ ፐርሰንት ህጉን ተከትሎ ነው፤በዚህ በኩል የሚወነጅሉበት ነገር ሲያጡ ነው ጉዳዩን ፖለቲካዊ ያደረጉት፡፡” ይላሉ፤ ሥራ አስፈጻሚው፡፡
ሆኖም የተዘረዘሩት ክሶች በሙሉ እኛን አይመለከቱም የሚሉት ዶ/ር ፍስሃ፤ በተደጋጋሚ እንደገለጽነው እኛ ኢኮኖሚያዊ እንጂ ፖለቲካዊ ፍላጎትና ዓላማ የለንም - ብለዋል፡፡ “ፐርፐዝ ብላክ የተቋቋመው የድሃ ገበሬውንና በአጠቃላይ የጥቁር ህዝቦችን ኢኮኖሚያዊ አቅም በማሳደግ ክብሩን ለማስመለስ ነው፤ ዓላማውና ፍላጎቱም ይሄው ነው፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ሰውን ብቻ ሳይሆን ገንዘብንም ማገት ተጀምሯል ያሉት የብላክ ፐርፐዝ መሥራች፤ ከአራት ሳምንት በላይ የባንክ ሂሳባችን የታገደበትን ምክንያት ያወቅነው በዚህ ሳምንት ነው ይላሉ - የባንክ ሂሳብ እግዱ እንዲነሳ 200 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን በመግለጽ፡፡ ክፍያውን የጠየቀው ማን እንደሆነ ለይተው ባይገልጹም፣ የስልክ ልውውጥ ማስረጃ እንዳላቸው ግን ዶ/ር ፍስሃ ተናግረዋል፡፡
“የጠየቁት ገንዘብ ከተሰጣቸው የታገደው ሂሳብ እንደሚለቀቅ፣ ወደፊት አብረውን እንደሚሰሩ፣ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ሁሉ በቀላሉ እንደሚያቀርቡልን ሁሉ ቃል ገብተዋል፡፡” ሲሉም አክለዋል፡፡
የተጠየቀውን ክፍያ የማልፈጽም ከሆነ ግን እንደሚያስሩኝ ነግረውኛል ብለዋል፡፡ “ዶ/ር ፍስሃ፤ አንድ ህይወት እኮ ነው ያለህ፤ ያለበለዚያ እናስርሃለን፤ እንገድልሃለን” ሲሉም አስፈራርተውኛል ያሉት ዶ/ር ፍስሃ፤ ህይወቴን በማጣት ለፐርፐዝ ብላክም ሆነ ለባለአክሲዮኖች የማተርፈው ነገር ስለሌለ ከአገር ለመውጣት ተገድጄአለሁ፤ ብለዋል፡፡
ይኼ በአፍሪካ ትልቁ የሆነው ሙስና ሲፈጸም ጠ/ሚኒስትሩ ያውቃሉ ብዬ አላምንም ያሉት ሥራ አስፈጻሚው፤ 20 ሺ ባለአክሲዮን ላቡን ጠብ አድርጎ የገነባው ኩባንያ ሲፈርስ ዝም ብለው ማየት የለባቸውም ነው ያሉት፡፡ “ፍትህ ተጓድሏል ስንላቸው ፍትህ ሊያሰፍኑና ለደህንነታችን ዋስትና ሊሰጡን ይገባል” ሲሉም ጠ/ሚኒስትሩን ጠይቀዋል፡፡
“ሌት ቀን የምንሰራው የድሃው ገበሬያችን ህይወት እንዲለወጥ ነው፤ የኑሮ ውድነት ታሪክ እንዲሆን ነው፤ የሽንኩርት ዋጋ እንዲረክስ ነው” ያሉት የኩባንያው መሥራች፤ በምላሹ ያገኘነው ግን ከአገር ተገድዶ መውጣትን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ እኔን የሚያሳዝነኝ ታሪክ ራሱን መድገሙ ነው ሲሉም - ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በኢህአዴግ ዘመን እንዲሁ ከአገር ለመውጣት መገደዳቸውን አስታውሰዋል፡፡
ይሄ ሁሉ ሆኖም እኛ ከማንም ጋር መካሰስና መዋቀስ አንፈልግም፤ ሥራችንን በሰላም መቀጠል ነው የምንሻው ሲሉ የተናገሩት የፐርፐዝ ብላክ ሥራ አስፈጻሚው፤ ይህን ለማድረግ ግን ጠ/ሚኒስትሩ ለደህንነታችን ዋስትና እንዲሰጡን እንፈልጋለን ብለዋል - ዶ/ር ፍስሃ፡፡ “ዋስትናችንን ሊያረጋግጡልን የሚችሉት ጠ/ሚኒስትሩ ብቻ ናቸው” ሲሉም አክለዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ፣ ከዛሬ ጀምሮ “ፍትህ ለብላክ ፐርፐዝ” የተሰኘ ዓለማቀፍ ዘመቻ መጀመሩን ያስታወቁት ዶ/ር ፍስሃ፤ የዘመቻው ዓላማም ህጋዊ ሌብነትን (የኢኮኖሚ ሽብርን) በጋራ መታገል ነው ብለዋል፡፡
የባንክ ሂሳባችን በመታገዱ ሳናጣ እንድናጣ ሆነናል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ለመላው ኢትዮጵያውያን ባቀረቡት የድጋፍ ጥሪ፣ የታገደው ገንዘባችን እስኪለቀቅ ለሰራተኞቻችን ደሞዝ መክፈል እንድንችልና ይህቺን ክፉ ቀን እንድናልፍ ከጎናችን ቁሙልን ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል፤ የፐርፐዝ ብላክ ቦርድ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሃላፊነት ሽግሽግ ማድረጉ ተነግሯል፡፡ በዚህም መሠረት ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ የቦርዱ ሊቀመንበርና የዓለማቀፉ ፐርፐዝ ብላክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲሆኑ የተወሰነ ሲሆን፤ የቀድሞው የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ም/ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ኤርምያስ ብርሃኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲሆኑ መወሰኑ ታውቋል፡፡

የፐርፐዝ ብላክ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ ከሃገር ሸሽተዋል።200 ሚሊዮን ብር ጉቦ እንድንከፍል ተጠይቀናል!የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ መሰደዳቸውን ...
22/06/2024

የፐርፐዝ ብላክ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ ከሃገር ሸሽተዋል።

200 ሚሊዮን ብር ጉቦ እንድንከፍል ተጠይቀናል!

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ መሰደዳቸውን ገለፁ። ዛሬ ሰኔ 15/2016 ዓም ከአሜሪካ ሆነው በሰጡት መግለጫ የተለያዩ ጫና ሲደርስብን ነበር በተለይ የድርጅቱ አካውንት መታገዱን ይፋ ካደረግን በኋላ የተለያዩ ወንጀሎችን እኔ ላይ በመለጠፍ እኔን ለማሳሰር ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ብሏል።

በህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውር ትሳተፋለህ፣ ፋኖን ትደግፋለህ እና በርካታ ክሶች እንደቀረበባቸው ገልጿል።

በተለይ 200 ሚሊዮን ብር ጉቦ ከከፈልን የባንክ አካውንታችን እግዱ እንደሚነሳልን ተጠይቀን ፍቃደኛ ስላልሆንን ትታሰራለህ ተብያለሁ ሲሉ ዶ/ር ፍሰሃ ገልጿል። ስለዚህ የእኔን ደህንነት ለማረጋገጥ የመጀመሪያ እርምጃ ከሀገር መውጣት ስለሆነ ወደ አሜሪካ ተሰድጃለሁ ብለዋል።

ፍትህ እስኪገኝ ሁሉንም አማራጭ እንጠቀማለን ተስፋ አንቆርጥም ይህ ሁሉ እኛ ላይ ሲደርስ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ያውቃሉ ብዬ አላስብም ብለዋል። ስለዚህ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጣልቃ ገብተው በመጀመሪያ ደረጃ እኔ ሀገሬ ገብቼ እንድሰራ እና ለድርጅቱ የሰላም ዋስትና እንዲሰጡኝ እጠይቃለሁ ከእሳቸው ውጪ ማንንም አላምንም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩን ለማግኘት ሶስት አመት ሙሉ ጠይቀናል እሳቸውን ማግኘት አልቻልም፣ እሳቸው ወደ እኛ መጥተው ሊያነጋግሩን ይገባ ነበር ከተበደልን በኋላ ዝም ሊሉን አይገባም ነበር የ1600 ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አንችልም ጾሙን ማደር የለበትም ሲሉ ዶ/ር ፍሰሃ ቅሬታቸውን ገልጿል።

በሰላም መስራት ነው የምንፈልገው፣ ከማንም ጋር መጣላት አንፈልግም የእኛ መርህ ኑ አብረን እንስራ ነው የተፈጠረው በሰላም ይፈታ ብለዋል። በቀጣይ በሽምግልና ችግሩ እንዲፈታ እናደርጋለን እንዲሁም የአሜሪካ ኤምባሲ ጣልቃ ገብቶ ከመንግስት ጋር መነጋገር የሚቻልበት አማራጭ እንደሚፈልጉ ተናግሯል።

ባለ አክሲዮኖች ተረጋጉ እስከመጨረሻው ድረስ እንታገላለን ፍትህ እንድናገኝ ሁሉም ድምፅ ማሰማት እንደሚገባው መልዕክት አስተላልፏል።

በመላው አለም የሚገኙ ዜጎች በፍቃደኝነት በውጪ ሀገር በተከፈተ አካውንት ድጋፍ እንዲያደርጉ የችግር ጊዜ አብራችሁን እንድትቆሙ ብለዋል።

ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ጨምሮ ሁለት ጋዜጠኞች ከእስር ተለቀቁ፡፡የኢትዮ ኒውስ ዋና አዘጋጅ፣ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም የጸጥታ ኃይሎች አራት ኪሎ ከሚገኘው ቢሮው አካባቢ...
17/06/2024

ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ጨምሮ ሁለት ጋዜጠኞች ከእስር ተለቀቁ፡፡

የኢትዮ ኒውስ ዋና አዘጋጅ፣ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም የጸጥታ ኃይሎች አራት ኪሎ ከሚገኘው ቢሮው አካባቢ ይዘው እንዳሰሩት የስራ ባልደረባው እና ባለቤቱ በወቅቱ ተናግረው ነበር።

ሌላኛው ጋዜጠኛ ቴድሮስ ዘርፉ በተመሳሳይ ለእስር ተዳርጎ ባሳለፍነው ቅዳሜ ከእስር ሲለቀቅ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ደግሞ ዛሬ ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከእስር ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀሉን ጠበቃቸው ታለማ ግዛቸው እና የስራ ባልደረባው በለጠ ካሳ ለአል ዐይን አረጋግጠዋል፡፡

እንደ ጠበቃ ታለማ አስተያየት ጋዜጠኞቹ በአፋር ክልል በሚገኘው አዋሽ አርባ እስር ቤት እና በአዲስ አበባ ክስ ሳይመሰረትባቸው ታስረው ቆይተዋል፡፡

የሚኒስትሮች ም/ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈየሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡1. ምክ...
14/06/2024

የሚኒስትሮች ም/ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር የ2ኛ ዙር የከተሞች የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ተጨማሪ ብድር ለማግኘት የተፈረመውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በብድር የተገኘው 207,200,000 የአሜሪካ ዶላር ሲሆን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የሳኒቴሽንና ሃይጂን አገልግሎት ተግባራትን ለማሻሻልና የዘርፉን የማስፈጸም አቅም ለማጠናከር የሚውል ነው፡፡ ብድሩ ወለድ የማይታሰብበት፣ 0.75% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልበት ሆኖ 6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ምክር ቤቱ ብድሩ ከአሀራችን የብድር አስተዳደር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም መሆኑን በማረጋገጥ ረቂቅ አዋጁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የንብረት ታክስ በከተሞች ነዋሪ በሆነው ሕዝብ መካከል ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ለማስፈን፤ የመንግስት አገልግሎቶችን በተሻለ ጥራትና በዘመናዊ ዘዴ ማቅረብ ለማስቻል እና የከተማ መሰረተ ልማት ማሻሻያዎችን በቀጣይነት ለመተግበር የሚወጣውን የኢንቨስትመንት ወጪ በንብረት ዋጋ ማደግ ምክንያት በሚጣል ታክስ አማካኝነት ለመሰብሰብ የሚያስችል ነው፡፡ አዋጁ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ተፈጻሚነት የሚኖረው ሲሆን፤ ክልሎችም ይህንን አዋጅ መሰረት በማድረግ ከተጨባጭ ሁኔታቸው ጋር በተጣጣመ አኳኋን የየራሳቸውን የንብረት ታክስ ህግ እንዲያወጡ ያስችላል። በዚሁ መሰረት ይህንን ለማስፈጸም የሚረዳ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
3. በ3ኛ ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሪፎርም እና የካፒታል ማሳደጊያ ዕቅድ ላይ ነው፡፡ የባንኩን የሀብት ጥራት ለማሻሻል እና በአስተማማኝ መልኩ የካፒታል መጠኑን በማሳደግ ለኢኮኖሚው ዕድገት እና ልማት የሚያደርገውን አስተዋጽኦ ዘላቂነት ባለው መልኩ ተግባራዊ እንዲያደርግ ለማስቻል የሚረዱ የውሳኔ ሃሳቦች ለሚኒስትሮች ም/ቤት ቀርበዋል፡፡ እነዚህም የባንኩን አስተዳደራዊ ውጤታማነት ማጎልበት፤ የሂሳብ መግለጫዎቹን ጠንካራና ተቀባይነት ባለው መልኩ እንዲዋቀር ማድረግ እና የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ የሚረዳ የመንግሥት የፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻል የሚሉ ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ በማሻሻያ እቅዱ ላይ ተወያቶ ወደቀጣይ ተግባር እንዲገባ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
4. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ባለፉት 16 ዓመታት በስራ ላይ የቆየው አዋጅ ሁሉንም የልማት ተዋናዮች ያሳተፈ የብልጽግና ዕቅድ ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ፣ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮና መርሆች አንጻር፣ ከአቻ ማዕከላዊ ባንኮች መልካም ተሞክሮ፣ከገንዘብ ፖሊሲ ውጤታማነት እንዲሁም በፋይናንስ ራስን ከመቻል አንጻር ክፍተቶች ያሉበት በመሆኑ፤ ባለፉት አመታት በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰቱ በርካታ የኢኮኖሚ፣ የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂና የጂኦ-ፖለቲካ ለውጦች በመኖራቸው፤ የባንኩን ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት የማስፈን፣ ዋጋን የማረጋጋት እና ለኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ የማድረግ ተልዕኮ ለማሳካት አዋጁን ማሻሻል እንደሚገባ ስለታመነበት ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በሁዋላ ግብአቶችን ታክለው ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
5. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው ስለባንክ ስራ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ባለፉት አመታት በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ የኢኮኖሚ፣ የቴክኖሎጂ፣ የአደረጃጀትና የአሠራር እና የመንግስት ፖሊሲ ለውጦች በመኖራቸው፤ ሀገራችን ለረጅም ጊዜ ዝግ አድርጋው የነበረውን የባንክ ስራን ለውጭ ሀገራት ክፍት ማድረጓን ተከትሎ ይህንን ለመምራት፣ የፍቃድ አሰጣጥን ለመወሰን እና ለማስተዳደር የሚያስችል የህግ እና የቁጥጥር ስርአት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን ታክለውበት ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
6. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የልማት ፕሮጀክቶች ከመተግበራቸው በፊት የአካባቢና ማህበረሰብ ተጽእኖ ግምገማና ጥናት እንዲካሄድባቸው በማድረግ ተጽእኖዎቹን አስቀድሞ በመተንበይ አሉታዊ ተጽእኖዎችን ለማስቀረት ወይም ለመቀነስ መተግበር ስላለባቸው ስራዎች የሚደነግግ እና የአካባቢ ጥበቃ ቁጥጥር አሰራርን በተቀናጀ መልኩ ስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ወጥ የሆነ ሀገራዊ የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ትኩስ ወሬ!!በላይ በቀለ ወያ ተፈቷልክስ ሳይመሰረትበት ለረጅም ወራት በእስር የቆየው ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ዛሬ ከእስር መፈታቱን እህቱ ሰላም በቀለ መረጃ አድርሳናለች::
13/06/2024

ትኩስ ወሬ!!
በላይ በቀለ ወያ ተፈቷል
ክስ ሳይመሰረትበት ለረጅም ወራት በእስር የቆየው ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ዛሬ ከእስር መፈታቱን እህቱ ሰላም በቀለ መረጃ አድርሳናለች::

መልዕክት- ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች!...በበይነ መረብ (Online) የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያበአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ ...
02/06/2024

መልዕክት- ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች!...

በበይነ መረብ (Online) የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ

በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወረቀት አልባ በማድረግ የዲጂታል ጉዞውን አንድ ምዕራፍ ጀምሯል። ይሄንንም ጉዞ የተሳካ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ለተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀው ማስፈንጠሪያ (URL) ከፈተናው በፊት ገብተው የሚለማመዱበት ሲሆን የፈተናው እለት ደግሞ መፈተኛ ይሆናል። ስለሆነም ከዚህ በታች በምትፈተኑበት የፈተና ክላስተር ፊትለፊት በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመግባት መለማምድ ትችላላችሁ፡፡ እስካሁን username እና password ያለገኘ ተፈታኝ ካለ፣ ከዚህ በፊት ለትምህርት ቢሮዎች ስለተላከ፣ ከየትምህርት ቤቱ አስተባባሪዎች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ክላስተር አንድ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር፡ https://c2.exam.et
ሲዳማ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et
ትግራይ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et

ክላስተር ሁለት
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et
ጋምቤላ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et
አማራ ብሄራዊ ክልል፡ https://c3.exam.et

ክላስተር ሶስት

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et
ሀረሪ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et
አፋር ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 1
• አዳማ ከተማ: https://c4.exam.et
• አጋሮ ከተማ: https://c4.exam.et
• አምቦ ከተማ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ አርሲ: https://c4.exam.et
• ምዕራብ አርሲ: https://c4.exam.et
• አሰላ ከተማ: https://c4.exam.et
• ባሌ: https://c4.exam.et
• ባቱ ከተማ: https://c4.exam.et
• ቤሾፍቱ ከተማ: https://c4.exam.et
• ቦረና: https://c4.exam.et
• ቡሌ ሆራ ከተማ: https://c4.exam.et
• ቡኖ በደሌ: https://c4.exam.et
• ዶዶላ ከተማ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ባሌ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ቦረና: https://c4.exam.et
• ጉጂ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ሐረርጌ: https://c4.exam.et
• ምዕራብ ሐረርጌ: https://c4.exam.et
• ሆለታ ከተማ: https://c4.exam.et
• ሆሮ ጉዱሩ: https://c4.exam.et
• ኢሉባቦር: https://c4.exam.et

ክላስተር አራት
ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 2
• ጅማ: https://c5.exam.et
• ጅማ ከተማ: https://c5.exam.et
• ቄለም ወለጋ: https://c5.exam.et
• ማያ ከተማ: https://c5.exam.et
• መቱ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሞጆ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሞያሌ ከተማ: https://c5.exam.et
• ነጆ ከተማ: https://c5.exam.et
• ነቀምት ከተማ: https://c5.exam.et
• ሮቤ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et
• ሰንዳፋ በኬ: https://c5.exam.et
• ሻኪሶ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሻሸመኔ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሸገር ከተማ: https://c5.exam.et
• ሸኖ ከተማ: https://c5.exam.et
• ምስራቅ ሸዋ: https://c5.exam.et
• ሰሜን ሸዋ (ኦሮሚያ): https://c5.exam.et
• ደቡብ ምዕራብ ሸዋ: https://c5.exam.et
• መዕራብ ሸዋ፡ https://c5.exam.et
• ምስራቅ ወለጋ፡ https://c5.exam.et
• መዕራብ ወለጋ፡ https://c5.exam.et
• መዕራብ ጉጂ፡ https://c5.exam.et
• ወሊሶ ከተማ፡ https://c5.exam.et

በተጨማሪም ተማሪዎች ዋናውን ፈተና ለመፈተን ዋናው ዌብሳይት ላይ ሲገቡ ምን ማድረግ አለባቸው የሚለውን አጭር ትምህርታዊ ምስል በዚህ መመልከት ይችላሉ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=PdAu-FI-Q5M

How to take the Grade 12 Online National Exam

ግልጽ ደብዳቤለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን አዲስ አበባጉዳዩ:- የምክክር ተሳትፎ እና አጀንዳዎች ማቅረብን ይመለከታል፡፡ኢትዮጵያ አገራችን ለተከታታይ አሥርት ዓመታት ከኖረችበት፣ በአኹኑ ...
31/05/2024

ግልጽ ደብዳቤ
ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን
አዲስ አበባ
ጉዳዩ:- የምክክር ተሳትፎ እና አጀንዳዎች ማቅረብን ይመለከታል፡፡
ኢትዮጵያ አገራችን ለተከታታይ አሥርት ዓመታት ከኖረችበት፣ በአኹኑ ወቅት ደግሞ እጅግ ከተወሳሰበውና ከከፋው ምስቅልቅል ብሎም ሕልውናዋን በመፈታተን ደረጃ ላይ ከደረሰው ቀውስ ብቸኛው መውጫ መንገድ ኹሉን አቀፍ አገራዊ ምክክር በማድረግ እንደ አገር በዋና ዋና ጉዳዮቻችን ዙሪያ የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሆነ በጽኑ እናምናለን። ይህንኑ እምነታችንን በሀሳብ ደረጃ ሳይሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች በተገቢው መልኩ በተግባር ለማንጸባረቅ ጥረት አድርገናል፤ እያደረግንም እንገኛለን።
የዚህ ጥረት ዋነኛ መገለጫ ከሆኑት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ከጅምሩ አግባብ በሌለው የአጸዳደቅ ሂደት እንዲሁም በኮሚሽነሮች አሰያየም ላይ የነበረውን ቅሬታ በመግለጽና የአዋጁ አጸዳደቅም ሆነ የኮሚሽነሮቹ አሰያየም ትክክል ስላልሆነ “ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ውድቅ መሆን አለበት” በሚል በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ ከፍተኛ ክርክር በተካሄደበት ወቅት በእኛ በኩል “የተሳሳተውን እያረምንና የተጣመመውን እያቀናን ሂደቱን እየደገፍን መሄድ ይገባናል” የሚል ጽኑ አቋም በመያዝ ይህን ለአገር ብቸኛ የመፍትሔ ማስገኛ ተግባር ተሰነካክሎ እንዳይቀር ያላሰለሰ ድጋፍ ስንሰጥ መቆየታችን ጉልህ ማሳያ ነው።
የምክክሩ ስኬታማነት ኹሉን አቀፍ መሆን በመቻሉ ላይ በእጅጉ እንደሚወሰን በማመን ለኮሚሽኑ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ከምክክሩ ሂደት ራሳቸውን ያገለሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ወደ ምክክር ማምጣት ትልቅ ተግዳሮት ቢሆንም ‘እንደ ፈለጋቸው ይሁኑ’ ተብሎ የሚተው ጉዳይ አለመሆኑን በመግለጽ ኮሚሽኑ በዚህ ረገድ ትርጉም ያለው ሥራ በመሥራት በአገራችን በሕጋዊ መልኩ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ ኹሉም የፓለቲካ ፓርቲዎች የምክክሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ባገኘነው አጋጣሚ በሙሉ ለማሳሰብ ጥረት አድርገናል። የምክክር ኮሚሽን ሥራውን እያከናወነ ባለበት ኹኔታ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት ባልተፈታበት ትርጉም ያለው ምክክር ማድረግ እንደማይቻል ለኮሚሽኑ በተደጋጋሚ መግለፃችን ይታወሳል።
ይህን አስመልክቶ በተለይ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እጅግ ከፍተኛ የሆነ ውጊያ እየተካሄደ ባለበት ኹኔታ መከራ የተፈራረቀባትን የአገራችንን መጻኢ እጣ ፋንታ ምክክሩ ሳይሆን የጦርነቱ ሂደት ሊበይን የሚችል መሆኑን ገልጸን የምክክር ኮሚሽኑ ወደ ምክክር ዘልሎ ከመግባት አስቀድሞ የአገራችንን ሕዝብ 2/3ኛ ያህል በያዙት በአማራና በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በኃይል የበላይነት ሳይሆን በድርድር ተቋጭቶና ፖለቲካዊ መፍትሄ ተበጅቶለት ወደ ታቀደው አገራዊ ምክክር መሄድ እንደሚገባን ለዚሁም ሥልጣኑንን በጨበጠው መንግሥት ላይ ጫና በማድረግ የእርስ በርስ ጦርነቱ መቋጫ እንዲያገኝ በተደጋጋሚ ጊዜያት ኮሚሽኑ በጠራቸው ስብሰባዎችም ሆነ በግል ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ሥጋታችንን ለመግለጽና መልእክታችንን ያለመታከት ለማስተላለፍ ሞክረናል።
በተመሳሳይ መልኩ ይህንኑ መልእክታችንን ለተከታታይ ጊዜያት ባወጣናቸው መግለጫዎች አገርም ጸንታ ልትቀጥል የምትችለው ምክክሩም የተፈለገውን ፍሬ ሊያፈራ የሚችለው የደፍጥጠው፣ ፍለጠው ቁረጠው መሰል ንግግሮችን ወደ ጎን በመተው አገር ከገባችበት የእርስ በርስ ጦርነት በሰለጠነ መልኩ ካለ ቅድመ ኹኔታ ከአገር ውጪ ሊደረግ በሚገባ ኹሉን አቀፍ ድርድርና በሚደረሰው ስምምነት መሠረት ለጦርነቱ እልባት በመስጠት ቀጣዩን እርምጃ መጓዝ እንደሚገባን ግልጽ የሆነ አቋማችንን ስናንጸባርቅ ቆይተናል፤ አኹንም ድረስ ይኸው አቋማችን የጸና መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሚሽኑ በክልል ደረጃ የአጀንዳ ልየታ ውይይቶችን ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንና ለዚሁም በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት ፳፩ ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት በሚደረጉ ስብሰባዎች የአጀንዳ ልየታ የሚያደርግ ጉባዔ መጥራቱ ይፋ ተድርጓል፤ ጥሪው ለእኛም ደርሷል።
የሚደረገው ምክክር ስልጣን የጨበጠ አካል በቀጥታም ሆነ በስውር የሚመራው ውይይት መሆን እንደሌለበት እናምናለን። በእኛ እሳቤ ይህ ምክክር በሥራ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥት በመሠረታዊ መልኩ እስከ ማሻሻል አስፈላጊም ከሆነ እስከ መለወጥ ድረስ የሚያዘልቅ እንደሆነ ብናምንም በሥራ ላይ ያለው የአሸናፊዎች ሕገ መንግሥት ዓይነት ተግባር እንዳይፈጸምና እንደ አገር ዳግም ስህተት እንዳንሠራ ከፍተኛ ሥጋት ያለን መሆናችንን በይፋ ለመግለጽ እንወዳለን።
በፓርቲያችን እይታ አገር ልትመክርበት ይገባል ብለን የምናስባቸው የምክክር አጀንዳዎች ወቅት የማይለውጣቸውና ወጥነት ያላቸው፣ መንግሥት ብንሆን ልንተገብራቸው ይገባል ብለን ያስቀመጥናቸው ነጥቦች ስለሆኑ ከአጀንዳ ልየታው ጋር ችግር የሌለንና ይህንኑ ያቀረብን መሆናችንን ኮሚሽኑ እንዲያውቀው የአገራችን ሕዝብም እንዲረዳልን እንወዳለን።
አጀንዳዎቻችንን የማቅረቡ ሂደት እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚደረገው የምክክር መድረክ፣
1. አገር በከፍተኛ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባለችበት ኹኔታ ምክክርም ጦርነትም በአንዴ ማድረግ የማይቻል መሆኑ፣ ከአገራት ተሞክሮ እንዲህ ባለ ኹኔታ የሚደረግ ምክክርም ውጤታማ እንደማይሆን ታውቆ በተቃራኒ ወገን የተሰለፉ ወንድማማቾችን እያጨራረሰ የሚገኘው የእርስ በርስ ጦርነት በድርድር ፖለቲካዊ መፍትሄ ሳይበጅለት፤
2. በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በየእሥር ቤቱ ታጉረው ባሉበትና ፍትሕ ተነፍጓቸው የሰቆቃ ሕይወት በሚገፉበት፤
3. የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ለምክክሩ ጭምር ጉልህ አስተዋጽዖ ማድረግ የሚችሉ ወገኖቻችን ያለ ፍርድ በየእሥር ቤቱ በሚማቅቁበት፤
4. አገር በአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ባለችበት፤
5. በምክክሩ ከመሳተፍ ራሳቸውን ከመጀመሪያው ጀምሮ ከሂደቱ ያገለሉትን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ምክክር ማምጣት ባልተቻለበትና በመሳሰሉ ምክንያቶች
ምክክሩ አገራችን በእጅጉ የምትሻውን አገራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ያስገኝላታል ብለን አናምንም። ስለሆነም እነዚህ ኹኔታዎች አጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ምክክር እስከሚደረግበት ባለው ጊዜ በቀዳሚነት መፍትሄ አግኝተው ሊፈቱ ካልቻሉና ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ካልተቻለ ፓርቲያችን በምክክሩ ለመሳተፍ የሚቸገር መሆኑን አጽንዖት ሰጥተን ለኮሚሽኑ እየገለጽን ሕዝባችንም አቋማችንን እንዲረዳ በትህትና እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
እናት ፓርቲ
ግንቦት ፳፫ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም.

28/05/2024

''ከዕብድ ጋር እንደራደርም'' አርበኛ ዘመነ ካሴ ዛሬ የሰጠው መግለጫ

25/05/2024

ESCFE2024
Gent ,Belgium
የ ESCFE ሊቀመንበር አቶ አሳየኸኝ ጥላሁን 19ኛውን ዓመታዊ የፌዴሬሽናችን ፌስቲቫል አስመልክተው ለፌዴሬሽኑ ወዳጆች በሙሉ ያስተላለፉትን መልዕክት ከዝግጅቱ ቦታ ቪዲዮ ጋር እንድትመለከቱ ስንጋብዝ ሁላችሁም ለቤልጅየም ጉዞ እየተዘጋጃችሁ እንደሆነ ተስፋ በማድረግ ነው
የሜዳው አድራሻ ‼️
Sportdienst Ronse 't Rosco
Leuzesesteenweg 241,
9600 Ronse, Belgium
🛑 ከጌንት ከተማ ሜዳው ድረስ እንዲሁም ከሜዳው ወደ ጌንት እንግዶቻችንን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያመላልልሱ በፌዴሬሽኑ የተዘጋጁ ባሶች ሲኖሩ ተጨማሪ የባቡር አቅርቦቱ እንዲጨምር እየተሰራበት ነው ።
🛑 በጉርፕም ሆነ በተናጠል መኪና ይዛችሁ የምትመጡትን እናበረታታለን 🚘 በቂ የሆነ ፓርኪን ቦታ አለ ።
ESCFE2024
Gent , Belgium

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራ በምትገኝበት ቀጠና “ጦርነት ለመቀስቀስ የሚያሴሩ ኃይሎች አሉ” ሲሉ ወነጀሉ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ “ጠቅላይ እና ሁሉን ልቆጣጠር ባይ ኃይ...
25/05/2024

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራ በምትገኝበት ቀጠና “ጦርነት ለመቀስቀስ የሚያሴሩ ኃይሎች አሉ” ሲሉ ወነጀሉ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ “ጠቅላይ እና ሁሉን ልቆጣጠር ባይ ኃይሎች” ሲሉ የጠሯቸው አካላት፤ ሀገራቸው በምትገኝበት ቀጠና “ሌላ የጦርነት ዑደት ለመቀስቀስ እያሴሩ ነው” ሲሉ ወነጀሉ። ኤርትራ ሊያጋጥማት ለሚችሉ ሁሉም አይነት ጦርነቶች “ዝግጁ” መሆኗንም ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ይህን ያሉት፤ ኤርትራ ነጿነቷን ያወጀችበት 33ኛ ዓመት ክብረ በዓል ትላንት አርብ ግንቦት 16 በአስመራ ስቴዲየም በተከናወነበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው። ሶስት ሰዓት ገደማ በፈጀው በዚሁ ክብረ በዓል፤ ባለፉት ዓመታት እንደነበሩት ተመሳሳይ መርሃ ግብሮች ሁሉ ወታደራዊ ሰልፎች፣ የወጣቶች ስፖርታዊ ትርኢቶች እና የሙዚቃ ዝግጅቶች ቀርበዋል።
አስራ ሶስት ደቂቃ ከፈጀው የኤርትራው ፕሬዝዳንት ንግግር አብዛኛውን ሽፋን ያገኘው፤ ኢሳያስ በከዚህ ቀደም ንግግሮቻቸውም ሆነ ቃለ መጠየቆቻቸው ላይ በስፋት ሲተነትኑ የሚደመጡት የዓለም አቀፍ ፖለቲካ አሰላለፍ እና የልዕለ ኃያላን ውድቀት ጉዳይ ነው። ፕሬዝዳንቱ በትላንቱ ንግግራቸውም ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያ በኋላ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በ“አዲሱ ዓለም አቀፍ ስርዓት” ቅርጽ የያዙትን ርዕዮተ ዓለሞች እና ፖሊሲዎች አንስተዋል።
ከሩሲያ እስከ ቻይና፣ ከታይዋን እስከ ሆንግ ኮንግ፣ ከአሜሪካ እስከ ፍልስጤም፣ ከኔቶ እስከ አውሮፓ ህብረት፣ ከቀይ ባህር እስከ ኤደን ባህረ ሰላጤ የተዳሰሱበት የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ንግግር፤ መቋጫውን ያደረገው የኤርትራ ጎረቤቶችን ጉዳይ በማንሳት ነው። “በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በውስጣዊ ጉዳዮቻችን ላይ የቀረበ ተጽዕኖ እና ጫና የሚያሳድሩ፤ በጎረቤቶቻችን እየታዩ ያሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና አዝማሚያዎች፤ በእርግጥም በርካታ ናቸው” ብለዋል ኢሳያስ።

ተቋርጦ የነበረው  የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በካይሮ ተጀመረየሶስትዮሽ ድርድሩ ከዚህ በፊት በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አቡዳቢ ሲደረግ ቆይቶ ረቂቅ ስምምነት ማዘጋጀት ላይ ደርሶ የነበረ...
27/08/2023

ተቋርጦ የነበረው የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በካይሮ ተጀመረ

የሶስትዮሽ ድርድሩ ከዚህ በፊት በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አቡዳቢ ሲደረግ ቆይቶ ረቂቅ ስምምነት ማዘጋጀት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ከዚያ ወዲህ ድርድሩ ሳይካሄድ መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡
ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በግብፅ ባደረጉት ጉብኝት ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ጋር በደረሱት ስምምነት መሰረት የሶስትዮሽ ድርድሩ ዳግም መጀመሩ ነው የተገለጸው፡፡

ድርድሩ የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት እና የወደፊት የመልማት መብት ባስከበረ መልኩ ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት መከናወኑም ተገልጿል

26/08/2023

🎉✨እንኳን ደስ አለን! ✨🎉
የቡዳፔስት ሌላ ክስተት!
ጀግናዋ 🏃🏽‍♀️አትሌት አማኔ በሪሶ ወርቅ 🥇
ጀግናዋ 🏃🏽‍♀️ አትሌት ጎተይቶም ገብረስላሴ ብር 🥈
ለሀገራቸው አስገኝተዋል። ✨🎉

እጅግ አስቸጋሪ በሆነው የ42 ኪሎ ሜትር ርቀት የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያ ሌላኛውን የቡዳፔስት ክስተት አስመዝግባለች፡፡ ፈታኝ እና እልክ አስጨራሽ በሆነው የማራቶን ውድድር በሴቶች ኢትዮጵያ የወርቅ እና ብር ሜዳሊያ አሸንፋለች፡፡

ቴክኖ ሞባይል አዳዲስ የስፓርክ 10 ሲሪየስ ስልኮች በኢትዮጵያ ይፋ አደረገትራንስሚሽን ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር (ቴክኖ ሞባይል) ቴክኖ ስፓርክ 10 (Tecno spark 10) አዲ...
12/05/2023

ቴክኖ ሞባይል አዳዲስ የስፓርክ 10 ሲሪየስ ስልኮች በኢትዮጵያ ይፋ አደረገ
ትራንስሚሽን ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር (ቴክኖ ሞባይል) ቴክኖ ስፓርክ 10 (Tecno spark 10) አዲስ ሞዴል ምርት በይፋ አስመረቀ።
ዛሬ ግንቦት 4/2015 ዓ.ም በማራቶን ሕንፃ በተከናወነው የምርት ምረቃና ማስተዋወቅ መርሐግብር ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ70 በላይ ዓለምአቀፍ ገበያዎች ላይ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያፈራው ቴክኖ ሞባይል ዛሬ በተከፈተውና ለሁለት ቀናት በሚቆየው ዝግጅት የስፓርክ 10፣ ስፓርክ 10ሲ እና ስፓርክ 10 ፕሮ ሞዴሎች ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል።ስልኮቹ የተጠቃሚውን ፍላጎት ከግምት በማስገባት ዘመናዊ የፊት ለፊት ካሜራን፣ ወቅታዊ ዲዛይን እና ፈጣንና ፕሮሰሰር በመጠቀም ለተገልጋዮች መቅረቡን ገልጷል።
ስፓርክ 10 ሲሪየስ ስልክ ሞዴል ስልኮች ድንቅ ምስሎችን እንዲያነሱ ታስቦ የተሰሩ ናቸው ተብሏል።
ትራንስሚሽን ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር (ቴክኖ ሞባይል) ጎሮ አካባቢ በሚገኘው አይሲቲ ፓርክ ያስገነባው ዘመናዊ ፋብሪካ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ዓይነት የስልክ ምርቶችን በመገጣጠም ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ገበያዎች ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል።

አንጋፋዋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም ድካም በአጸደ ሥጋ ተለየች።ድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ ከ1953 ዓ.ም መጀመሪያዎቹ ዓመታት ጀምሮ እስከ 1980ዎቹ አካባቢ ከ200...
12/05/2023

አንጋፋዋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም ድካም በአጸደ ሥጋ ተለየች።
ድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ ከ1953 ዓ.ም መጀመሪያዎቹ ዓመታት ጀምሮ እስከ 1980ዎቹ አካባቢ ከ200 በላይ ዘፈኖችን ያበረከተች አንጋፋ ድምጻዊ እንደነበረች በእሷ ሥራዎች ላይ ከፍተኛ አሻራ ያኖሩት አንጋፋ ው አርቲስት ተስፋዬ አበበ ተናግረዋል።
ጽምጻዊት ኂሩት በቀለ በፖሊስ ሠራዊት የሙዚቃና የቲያትር ክፍል ለ35 ዓመታት አገልግላለች። ኂሩት በአብዛኛው የአገር ፍቅርን ከሚቀሰቅሱ ዘፈኖቿ መካከል «ኢትዮጵያ» ፤ ስለሕይወት ካዜመቻቸው ደግሞ «ሕይወት እንደ ሸክላ» ፣ የሚለውና ሌሎች ጆሮገብ የሙዚቃ ሥራዎቿ አሁንም ድረስ ተወዳጅነትን ያልተለያቸው ድንቅ ሥራዎቿ ናቸው። ኂሩት በቀለ ወደ 40 የሚጠጉ የሙዚቃ ሸክላዎችንና 14 ካሴቶችን እንደታተሙላት አርቲስት ተስፈዬ አበበ ገልጸዋል።
ድምጻዊት ኂሩት በቀለ የመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈችው በ83 ዓመቷ ሲሆን የ7 ልጆች እናት፤ እና ቅድመ አያትም ነበረች።
ኃገር ሚዲያ በድምጻዊት ኂሩት በቀለ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቿና አድናቂዎቿ መጽናናትን ይመኛል።
ፎቶ ከማሕበራዊ ድረገጽ የተወሰደ

ሀላፊው በቢሯቸው ውስጥ ተገደሉ!የቂርቆስ ክፈለ ከተማ ወረዳ ሰምንት ዋና ስራ አሰፈጻሚ እና የአማራ ብልጽግና አባል የሆኑት አቶ አለባቸው ዋለ በቢሯቸው ውስጥ መገደላቸው ተገለፀ፡፡ዋና ስራ አ...
12/05/2023

ሀላፊው በቢሯቸው ውስጥ ተገደሉ!
የቂርቆስ ክፈለ ከተማ ወረዳ ሰምንት ዋና ስራ አሰፈጻሚ እና የአማራ ብልጽግና አባል የሆኑት አቶ አለባቸው ዋለ በቢሯቸው ውስጥ መገደላቸው ተገለፀ፡፡
ዋና ስራ አሰፈጻሚውን በመግደል የተጠረጠረው የአካባቢው የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ባልደረባ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡
ተጠርጣሪው ሀላፊውን በሽጉጥ ከገደለ በኋላ ከአንድ ግብረአበሩ ጋር እንደተያዙም ታውቋል።

Adresse

Schulstasse
Lorsch
64653

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Hager ሃገር erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Service Kontaktieren

Nachricht an Hager ሃገር senden:

Videos

Teilen


Andere Medien- und Nachrichtenunternehmen in Lorsch

Alles Anzeigen