Hager Your daily source for news, delivered straight to your social media feed.

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የ...
02/05/2023

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ
በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የዋጋ ማስተካከያው ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን ሚኒስቴሩ ለመገናኛ ሚዲያዎች የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚሁ መሠረት፡ -
ቤንዚን ----------- 69 ነጥብ 43 ብር በሊትር
ነጭ ናፍጣ ----------- 71 ነጥብ 08 ብር በሊትር
ኬሮሲን ----------- 71 ነጥብ 08 ብር በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ ----------- 66 ነጥብ 60 ብር በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ ----------- 57 ነጥብ 84 ብር በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ ----------- 56 ነጥብ 50 ብር በሊትር

"አማራ ክልልን የጦርነት ቀጠና ማድረግ የሚፈልጉ አካላት በአስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ"  አብንአብን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። የክልሉ የፋኖ ታጣቂዎች ከመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል...
02/05/2023

"አማራ ክልልን የጦርነት ቀጠና ማድረግ የሚፈልጉ አካላት በአስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ" አብን

አብን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። የክልሉ የፋኖ ታጣቂዎች ከመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ጸጥታ ኃይሎች ጋር በአኹኑ ወቅት የገቡበትን መካረር ለማርገብ፣ ከጸጥታ አካላቱ ጋር ንግግር እንዲጀምሩም ፓርቲው ጥሪ አድርጓል። ፓርቲው፣ ከፌደራልና ክልል መንግሥታት፣ ከምሁራን፣ ከተቃዋሚ ፓርቲዎችና ከአገር ሽማግሌዎች የተውጣጣ አካል ከክልሉ ሕዝብ ጋር "በአንገብጋቢ አጀንዳዎች" ዙሪያ እንዲወያይ፣ መንግሥት የውይይት በሩን እንዲከፍትና በክልሉ ውስጥ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ "ያላግባብ የታሠሩ" አካላት እንዲፈቱም ጠይቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካል የሆነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ውስጥ የሚያቀርበውን የምግብ እርዳታ ማቋረጡን የረድኤት ሠራተኞች ለአሶሺየትድ ፕሬስ ተናገሩ።የዓለም ምግብ ...
02/05/2023

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካል የሆነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ውስጥ የሚያቀርበውን የምግብ እርዳታ ማቋረጡን የረድኤት ሠራተኞች ለአሶሺየትድ ፕሬስ ተናገሩ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ትግራይ ውስጥ የሚያካሂደውን የእርዳታ አቅርቦት ያቋረጠው ከሳምንታት በፊት ለተረጂዎች በሚቀርብ የምግብ እርዳታ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ስርቆት ለማጣራት ውሳጣዊ ምርመራ ለማካሄድ እንደሆነ አራት የእርዳታ ሠራተኞች ገልጸዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለሁለት ዓመት በአውዳሚ ጦርነት ውስጥ በቆየችው የሰሜን ኢትዮጵያ ክልል ትግራይ ውስጥ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከሌሎች አጋሮቹ የሚገኘውን የምግብ እርዳታ ለተረጂዎች የማቅረብ ኃላፊነት ያለበት አካል ነው።

አራት የእርዳታ ሠራተኞች ለአሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል እንደገለጹት የእርዳታ ምግብ ተገቢ ላልሆነ አላማ እየዋለ መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ድርጅቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ትግራይ የሚያደርገውን የእርዳታ አቅርቦት በጊዜያዊነት አቋርጧል።

ይህንንም መረጃ ሌሎች ሦስት የእርዳታ ሠራተኞች ለዜና ወኪሉ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ሁሉም በጉዳዩ ላይ ለጋዜጠኞች መረጃ የመስጠት ፈቃድ ስለሌላቸው ስማቸው እንዲጠቀስ እንዳልፈለጉ ኤፒ ገልጿል።

Adresse

Im Schlüssel
Heppenheim
64646

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Hager erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Service Kontaktieren

Nachricht an Hager senden:

Teilen


Andere Medien- und Nachrichtenunternehmen in Heppenheim

Alles Anzeigen