Durbete Achefer Press -አቸፈሬው

Durbete Achefer Press -አቸፈሬው ስለ አቸፈር እናውራ! ለውጥም እናመጣለን!

ነገ በአቸፈር ሰማይ ስርበሊበን ከተማ ይመረቃል።አይቀርም!!!
17/09/2022

ነገ በአቸፈር ሰማይ ስር
በሊበን ከተማ ይመረቃል።
አይቀርም!!!

በግንባር በመገኘት በሙያቸው እያገለገሉ ያሉ  #የዱርቤቴ ሆስፒታል ዶክተሮች‼️አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ እና  #የአማራው ህዝብ ከፍ ሲልም ሃገራችን ላይ የተጋረጠብንን አደጋ ለመቀ...
16/09/2022

በግንባር በመገኘት በሙያቸው እያገለገሉ ያሉ #የዱርቤቴ ሆስፒታል ዶክተሮች‼️

አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ እና #የአማራው ህዝብ ከፍ ሲልም ሃገራችን ላይ የተጋረጠብንን አደጋ ለመቀልበስ እየተዋደቀ ያለውን የአማራን ልዩ ሃይልን፣ ፋኖን፣ ሚሊሻን እና የመከላከያ ሰራዊቱን የኃላ ደጀን ሆኖ የነፍስ አድን ስራን ለመስራት ውድ ህይወታቸው ሰጥተው፣ ህይወት እየታደጉ ያላችሁ #የዱርቤቴ ሆስፒታል ዶክተሮችና የጤና ባለሙያዎች እናመሰግናቸዋለን💚‼️

ከዕለት ተዕለት ህዝብን ከማገልገልና ህይወት ከማዳን እና ከመታደግ ስራችሁ በተጨማሪ፡ #የአማራውን ህዝብ ብሎም ሀገርን ለማዳን መስዋእትነት መክፈል ያለበት ሠራዊቱ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም የሙያ መስክ የተሰማራው ሠራተኛ ጭምር ቢሆንም በህክምናው ዘርፍ ግንባር ቀደም ሁናችሁ፤ ለሀገሩ መስዋእት ለሚሆን ወታደር፣ ህይወቱን ለመታደግ እና በሙያችሁ መስዋዕት ለመሆን የሄዳችሁ የሆስፒታሉ ዶክተሮቻችን አይዞን በርቱልን።

❤️ግንባር ላይ ያሉ #የዱርቤቴ ሆስፒታል ዶክተሮች፡

1.Mr. Kifle Ayanaw
2.Dr. Ayalew Desta
3. Mr.Muluken Abere(CEO)
4.Dr. Genetu Terefe
5.Mr. Kassahun Ferede
6.Dr. Abrham Manaye

እግዚአብሔር ይጠብቅልን

አዲሱ አንዳርጌ ይባላሉ።በጎጃም ክፍለ ሃገር በአቸፈር አውራጃ ነዋሪ  ናቸው።51 አመታቸው ነው።እኒህ ታላቅ ሰው እጆቸ ሳይጽፉ አይኖቸ ሳያነቡ አይቀሩም በማለት 1ኛ ክፍል ተመዝግበዋል።አክቲቪ...
15/09/2022

አዲሱ አንዳርጌ ይባላሉ።
በጎጃም ክፍለ ሃገር በአቸፈር አውራጃ ነዋሪ ናቸው።
51 አመታቸው ነው።
እኒህ ታላቅ ሰው እጆቸ ሳይጽፉ አይኖቸ ሳያነቡ አይቀሩም በማለት 1ኛ ክፍል ተመዝግበዋል።
አክቲቪስቶች
ሚዲያዎቸ
የትምህርት ተቋማት የትምህር አብዮቱን ለማቀጣጠል እኒህን ታላቅ ሰው አጀንዳችሁ ብታደርጓቸው መልካም ነው።
መረጃው የGirum Misalie ነው።

14/09/2022

ታላቁን የአቸፈር ህዝብ በመሰረተ ልማት እያጎሳቆላችሁት ያላችሁ አካላት እባካችሁ ከድርጊታችሁ ታቀቡ።
ከዱርቤቴ አሹዳ ዝብህስት ጃዊ
ከዱርቤቴ አዲስ አለም ማማላ ጃዊ
ከዲርቤቴ ታድሶ ኳኩራ ሰከላ
ከ1997 ጀምሮ በጅምር ያሉ መንገዶችን መቸ ነው የምትጨርሷቸው?
አዳዲስ ትምህርት ቤት ጤና ጣቢያስ ሳተ ነው የምትገነቡት??
አስተዳደራዊ ዝርፊያውስ መቸ ነው የሚያቆመው?
በተለይ በጀትና መሬት
በየቀበሌው የምንሰማው መገዳደልስ መቸ ነው የሚቆመው???
ኧረ ተዉ ተው

✍ለመላው  #የአቸፈርና የኢትዮጵያ ህዝብ💚 ‼️🙏እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ🙏 #እንኳን ለዘመን~መለወጫ በዓል በሰላም  # አደረሳችሁ !! የሰው ልጅ ካንደበቱ በላይ ፍቅርን በተግባር ሲ...
10/09/2022

✍ለመላው #የአቸፈርና የኢትዮጵያ ህዝብ💚 ‼️

🙏እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ🙏

#እንኳን ለዘመን~መለወጫ በዓል በሰላም # አደረሳችሁ !! የሰው ልጅ ካንደበቱ በላይ ፍቅርን በተግባር ሲገልፅ የበለጠ ሰውነቱ ይረጋገጥለታል! ይህንን በዓል ምክኒያት በማድረግ አንዳችን ለሌላችን #በ2014 ከዚህ ቀደም የሰራነውም ሆነ የተሰራብንን እኩይ ነገር "ይቅር" በመባባል፤ መቻቻልን እና ፍቅርን በመስበክና በተግባር በማሳየት ለሌሎች አርዓያ ሆነን "ከጥላቻዊ" አስተሳሰብ ልንታደጋቸው ይገባል!!

አንዳችን ለሌላችን መድሀኒት እና ጌጥ ሆነን በመቻቻል መንፈስ የማንኖር ከሆነ አብሮነት ቃል እንጂ እውነት ሆኖ ሊያኖረን አይችልም!!

"ለራስህ የምትወደውን ለወንድምህ እስካልወደድክ አንተ አማኝ ልትባል አችልም"!! ጥላቻ ከተፈጥሮ ሳይሆን ከትምህርት እና ከአካባቢ የምንወርሰው እርኩስ መንፈስ ነው!!

ተግባርን እንጂ ሰውን መጥላት ስህተት ነው!! ግለሰቦች የሰሩትንም ጥፋት ለቡድኖች አናውርስ፤ ቡድንም ያጠፋው ጥፋት ለህዝብ/ለጎሳ አናውርስ፤ ሀሳብን በሀሳብ ሞግተን ዛሬን ከትላንት ፤ ነገን ደግሞ ከዛሬ የተሻለ ለማድረግ እንጣር!!

ከእኛ በፊት የነበረው የህዝባችን አብሮነት ከኛም በኋላ መኖሩ የግድ ነው!! ይህንን ሂደት እናስተጓጉለው ይሆናል እንጂ #ፈፅሞ እንዲቋረጥ ማድረግ አንችልም!! ተፈጥሮ በተቃራኒ ነገር የተሞላችው ሚዛኗን ለመጠበቅ ነው!! ተቃራኒ ነገር የጠፋ ቀን አለም ትጠፋለች !! ስለዚህ ልዩነት የጠፋ ቀን አለም ይጠፋል!! ልዩነት እንዳለ አምኖ ማቻቻል ነው እንጂ ማጥፋት መሞከር ሁሉንም ያጠፋል!!

አቸፈራውያን!!
#እወዳችኋለሁ...መልካም በዓል ይሁንላችሁ!!🥰

በዓሉን ስናከብር #አቅመ ደካማ ወገኖቻችን እና ጎረቤቶቻችንን አንርሳ!!!
መልዕክቴ ነው
አቸፈሬው

Durbete Achefer Press -አቸፈሬው
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻 አዲስ 🌻🌻
🌻🌻 ዓመት 🌻🌻️
🌻️🌹⁣🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊

 #በዓላት እና የአቸፈር የትራንስፖርት....‼️በዓላት ሲመጣ አብዛኛውን የሃገሬ ሰው ዘመድ ጥየቃ፣ በዓልን ከቤተሰብ ጋር ለማሳለፍ እናስብና ....  #ትራንስፖርቱን ስናስበው ሃሳብ እንቀይራ...
09/09/2022

#በዓላት እና የአቸፈር የትራንስፖርት....‼️

በዓላት ሲመጣ አብዛኛውን የሃገሬ ሰው ዘመድ ጥየቃ፣ በዓልን ከቤተሰብ ጋር ለማሳለፍ እናስብና .... #ትራንስፖርቱን ስናስበው ሃሳብ እንቀይራለን!

?

የአቸፈር ህዝብ በአጠቃለይ በመንገድ ችግር ተበድሏል፣ ቅኝ ተገዝቷል።
እኔን የሚገርመኝ ሁሉም ወረዳና ንዑስ ከተሞች ላይ ከፍተኛ የሆነ መኪና ቆሞ ይዉላል ነገር ግን ዉስን መኪኖች ደሞ ሰዉን እንደ እህል አነባብረዉ ይጭናሉ።

መኪና እኮ ሞልቷል ነገር ግን የትራንስፖርት መኪና ችግር ይመስል! ለ24 ሰዉ ብቻ በተፈቀደ መኪና እስከ 50_60 ሰዉ ይጭናሉ። የትራፊክ ስራዉ ምንድነዉ? ወይስ ወደ እዚያ ግድም የተመደበ የትራፊክ ፖሊስ የለም? ወይስ የመንግድ ትራንስፖርት ሀላፊ የለም?

የወረዳው መንገድ ትራንስፖርት ሀላፊዎች ካላችሁ ይህንን ጥያቄ መልሱልኝ!!

® "መኪና አለ ግን የለም" ይባላል፡ በፐርሰንት የሚሏት ነገር ደግሞ አለች? አንዳንድ ተሳፋሪም አሉ..አድረሰን እንጂ እንከፍላለን🤭፣ ችግር የለም እኛ እንጨምራለን) በማለት አጓጉል ልማዶች...... ?

አንዳንድ ምስጉን #ትራፊኮችም ሹፈሬቹም አሉ። ስራቸዉንም አበክረዉ እየሰሩ መሆኑን በአይኔ አይቻለሁ። ሹፌሮቹም ተሽቆጥቁጠዉ ነዉ የሚጭኑት ፣ መልካም ሰብዕናን የተላበሱ!!

➛➛➛..ወደ አሹዳ የበዓል መንገድ አይታሰብም...!

®የሚመለከተው አካል ቅደመ ጥንቃቄ አድርጉ! መልካም በዓል 🙏

 #አቼፈርና  #መስከረም ‼️( ድንቅ ባህላችን እና ትውፊታዊ የዘመን መለወጫ በዓል)አቸፈር ከጎጃም ወረዳዎች አንዱ ነው፡፡  #ከጣና ሐይቅ ምዕራብ ያለ ውብ አገር ነው፡፡ በሰሜን ምዕራብ የሰ...
09/09/2022

#አቼፈርና #መስከረም ‼️

( ድንቅ ባህላችን እና ትውፊታዊ የዘመን መለወጫ በዓል)

አቸፈር ከጎጃም ወረዳዎች አንዱ ነው፡፡ #ከጣና ሐይቅ ምዕራብ ያለ ውብ አገር ነው፡፡ በሰሜን ምዕራብ የሰሜን ጎንደሩ #አለፋ ፣ በደቡብ ምዕራብ #የአዊ ዞኖቹ ዳንግላና ጃዊ ያዋስኑታል፡፡ ጥቁር ከቀይ የያዘው ፣ ሜዳማ ለም አፈሩ የእህል ዘር እምቢ ብሎ የሚያበቅል እንደሆነ አገዳው ያስታውቃል፡፡ ለዚህ አብነት የ1928 ዓ/ ምቱን የጣልያን ወረራ ማንሳት ይቻላል፡፡ ጣልያኖች በወረራ ዘመን በለምነቱ ከጎመዡበት የጎጃም ግዛት አንዱ አቼፈር ነበር፡፡ #40 ሺህ የጣልያን ገበሬዎችን አስፍረው #ጣና ሐይቅን በመስኖ ጠልፈው በምርት ለመድለብ አስበው ነበር፡፡
°°°

#በቢትወደድ አያሌው መኮንን የሚመራው #የአቸፈር አረበኛ ግን የቅኝ ግዛት ክንፋቸውን ሰብሮ መለሳቸው፡፡ #40ሺህ የጣልያን ገበሬዎችን አቼፈር ላይ የማስፈር ህልማቸው ተቀበረ፡፡

#በአቸፈር ደግሞ 'አበደ አበደ' አለ፡፡ የአገሩ አምራችነት ማሳያ እንደገናም የመልካም ምኛት መሻቻ ነው፡፡ የጎመን ምንቸት ውጣ ፣ የገንፎ ምንቸት ግባ ተብሎ ዘመን ሲቀየር ወቅቱ ነውና ጋራ ሸንተረሩ በአደይ አበባ ያጊጣል፡፡ አዝዕርቱም ያሽታል፡፡ ችጋር በጳጉሜ ውሀ ታጥቦ በአዲስ ዓመት የመጥገብ ተስፋ ይወለዳል፡፡ ምንኛ ደስ ይላል የባላገር ኑሮ፣ ወተቱ ከማጀት እሸቱ ከጓሮ፤ የሚባለው ስለ ተፈጥሮ ማማር ብቻ ሳይሆን እሸቱ በትኩስ ተቆርጦ ስለሚላመጠው እህል ጭምር ነው፡፡

በአቸፈር በርዕ አውድ አመት የቅዱስ ዮሀንስ ዋዜማ እናቶች ከስድስት ሰአት በሗላ አይተኙም፡፡ ምጣድ አግመው እንጀራ ይጋግራሉ፡፡ ቃተኛ ይቀባሉ፡፡ ቂጣም ይጋገራል፡፡ ቂጣውም ፣ እንጀራውም ቃተኛ ተቀብቶ ለየራሱ ይጨፈቃል፡፡ ከጭፍቆው ላይ አይብ ወይም እርጎ ይጨመርበታል፡፡ ልጆች ከቂጣው ወይም ከእንጀራው ወይም ከሁለቱ እንደየ ምርጫቸው በሳህን ይደረግላቸዋል፡፡ደግሞ በልጆች ቁጥር ልክ ጥሬ ወተት በግሬራ ይሆናል፡፡ ግሬራ ከቅል የሚዘጋጅ የወተት መያዣ ነው፡፡ ቅሉ ተሟሽቶ ከከብት ጭራ ደምበኛ ሆኖ የተፈተለ ማንጠልጠያ በዳርና ዳር ለመያዣ ይበጅለታል፡፡ ከሌሎች ማሰርያዎች ለምሳሌ ከእንጨት ልጥ ወይም ከቆዳ የከብቱ ጭራ የተመረጠበት የበለጠ ቻይ ስለሆነ ነው፡፡ ከከብት ቆዳ የሚዘጋጀው ማሰርያ ወይም ማንገቻም በጥንካሬው የሚታማ አይደለም፡፡ ነገር ግን የቆዳ ማንገቻው ውሀ ሲነካው ፣ ፀሐይ ሲመታው በቀላሉ ይገራል ፣ ይቆረፍዳል ፣ ለአያያዝም ያስቸግራል፡፡ በዚያ ላይ በአግባቡ ካልተያዘ አይጥና ብልም ይበለዋል፡፡ የከብት ጭራው ከዚህ ሁሉ ነፃ ነው፡፡ ቅሉ በቀንዱ በኩል ተቀንብቦ መራራው ይወጣል፡፡ ጨርሶ እንዲለቅ ለሳምንታት ውሀ ተሞልቶ ይዘፈዘፋል፡፡ በመጨረሻም ረመጥ ተጨምሮበት የበለጠ መራራውን እንዲበላው ይደረጋል፡፡ ከዚያም የተፈተለው የከብት ጭራ በክቡ ዳርና ዳር ተበስቶ ይታሰራል፡፡ ይህ የቅሉ መጠን ሲያንስ ግሬራ ወይም የወተት ማለቢያ ፣ የቅሉ መጠን ሲያድግ ደግሞ ጉርና ወይም የወተት መግፊያ ይሰኛል፡፡
••••

#የአህያ ሆድ ሲመስል እንዲሉ አቸፈሮች ጎህ ሲቀድ ወይም ከሌሊቱ አስር ሰዓት ጀምሮ ወጣቶች ፍትፍታቸውን ይዘው ወደ ማሳ ይወርዳሉ፡፡ የሌሊቱ ግርማ እንዳይከብዳቸው የሚሄዱበት ማሳ ርቀት በእድሜያቸው ልክ ይወሰናል፡፡ የቤቱ የብኸር ልጅ ከታናናሾቹ ጋር መክሮ ራሱን ጨምሮ የሚሄዱበትን ማሳ ይደለድላል፡፡ ህፃናት ለደህንነታቸው ሲባል በቅርብ ካለ ማሳ ወይም ከጓሮ 'አበደ አበደ' እንዲሉ ይመደባሉ፡፡ ጩኸቱ ከቤት እንደወጡ ይጀምራል፡፡ ከማሳው እስኪደርሱም ይጮሀሉ፡፡ ማሳው ደርሰው ፍትፍታቸውን እየበሉም ይጮሀሉ፡፡ በልተው ሲጨርሱ ፀሀይ በምስራቅ በኩል የጣና ሐይቅ ላይ የሸረሪት ድር የመሰለ ሐምራዊ እሳት የሚተፋ ቀለበቷን ትዘረጋለች ፥ ያን ጊዜ ጩኸታቸውን ለሚቀጥለው ዓመት አቆይተው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፡፡
የአበደ አበደ ጩኸት ፥
አበደ አበደ የጤፉ ጎተራ ተቀደደ (((እውውውው!!)))
አበደ አበደ የዳጉሳው ጎተራ ተቀደደ (((እውውው!!)))
አበደ አበደ የሽንብራው ጎተራ ተቀደደ (((እውውው!!)))🙆‍♀🙆‍♀🙆‍♀🥰
የሚል ነው፡፡ ጎተራው ተቀደደ የሚለው የምርቱን መትረፍረፍ ፣ የጎተራውን ሞልቶ መፍሰስ ያሳያል፡፡ መጭው ወቅት የጥጋብ መሆኑንም ይተነብያል፡፡

'የአበደ አበደ' መልካም ምኞት ድምቀቱ የቅዱስ ዮሐንስ እለት ይሁን እንጂ እረኞች ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ያስቡታል፡፡ # ባለቅኔው መንግስቱ ለማ ፥
የመስቀል ወፍና የአደይ አበባ ፣
ማን ያውቃል ቀጠሮ እንዳላቸው መስከረም ሲጠባ ፤
እንዳለው እረኛች የምድርን በአደይ አበባ ማጌጥ ፣ የመስቀል ወፍን መከሰት ሲያዩ እነሱም ጋራና ሸንተረር እየመታ በሚወነጨፍ አስረቅራቂ ድምፃቸው የዘመን መለወጫ ፍትፍታቸውን እያሰቡ የአበደ አበደ እውታቸውን ይለቁታል፡፡ የእረኞች የዋዜማ እውታ የሚሰማው በአብዛኛው በምሽት ነው፡፡
ወጣቶች ከመብላታቸው በፊት ከያዙት ፍትፍት ከሁሉም አይነት እየዘገኑ ማሳቸውን ይረጫሉ፡፡ ሰው ከእህል ነውና የተሰራው አብዝተህ ምርት ስጠን ማለታቸው ነው፡፡ ርጭቱ ሌላም ምሳሌ አለው፡፡ አሁን ለአፋችን ያልነውን እህል በአሮጌው አመት እንደሰጠኸን ሁሉ ይኼን የዘራነውንም በአፈር አልብሰህ ፣ በውሀ አርሰህ ፣ ሞትን በብቅለት ለውጠህ ይኸው አሽቶ አየነው፡፡ አሁንም ከበረድና ከተባይ ጠብቀህ ፣ በፀሐይ አብስለህ ታበላናለህና እናመሰግናለን ማለት ነው፡፡ ምስጋናው በሌላ ዘውግ ሲታይ እድሜ ነው፡፡ ህፃናት የመስቀል እለት ጎህ ሲቀድ ጠምቦራቸውን በእሳት ለኩሰው ወደ ደመራ ይወጣሉ፡፡ ደመራው ያለበት ቦታ እስኪደርሱ ስለማያስችላቸው እየሮጡ ነው፡፡

በጉዟቸው ጊዜ፥
እዮሄ እዮሀ
እሰይ መስቀል ጠባ ፣
እሞታለሁ ብየ ስባባ ፤
እዮሄ እዮሀ
አይዞሽ ነብሴ
ደረሰልሽ ገብሴ
እዮሄ እዮሀ
አትኩራ ገብስ
ጎመን ባወጣው ነብስ
እዮሄ እዮሀ😍
እያሉ አምላካቸውን በዝማሬ ያመሰግናሉ፡፡

በመሰረቱ የእዮሀ ምስጋና የዜማው ረቂቅነት ፣ የግጥሙ አብሮነትን የመሻት ፣ ሞትን በአምላክ ሀይል የመናቅ፣ ርሀብን በእሸት ጉልበት የማሸነፍ ሀይል ያለው ነው፡፡ ደግሞ የመኖርን ተስፋና የተስፋውን እውን መሆን እንደገናም አሁንም ለመጭው ዘመን በሰላም አድርሰኝ የሚል ለፈጣሪ የሚቀርብ ተማፅኖ አለው፡፡
ክረምት የገበሬው የአመት ቀለብ የሚያልቅበት፣ ጎታውን ጠርጎ የሚበላበት፣ ለዘር ያስቀመጣትን ለመሬት አደራ ሰጥቶ ሆዱን በጎመን ደልሎ የሚከርምበት ወቅት ነው፡፡ ያም አልፎ ተስፋ የሚያደርገው መስከረም እሸት ይዞለት ይመጣል፡፡ በዘመን መለወጫ እለት የጎመን ምንቸት ውጣ የገንፎ ምንቸት ግባ የሚባለውም ጎመንን የሚተካው ገብስ በበሶም ፣ በገንፎም ስለሚበላ ነው፡፡ በመስከረም የበቆሎ እሸትም ሌላው ደራሽ የአርሶ አደሩ ነብስ አድን ነው፡፡ በሽታውን፣ ችግሩን ሁሉ እንጎሮጎባሽ እያለ በችቦ የተስፋ ብርሃን ለኩሶ ያበራል፡፡ የበቆሎ እሸት ቆርጦ በመስቀሉ የደመራ እሳት ጠብሶ እዚያው መብላት ይጀምራል፡፡ እንዲያውም አባቶች እንደሚሉት እንጎሮጎባሽ እንኳን ጓሮ ገባሽ፣ እንኳን እሸት ለመቁረጥ አበቃሽ ማለት ነው፡፡ ጎህ ሲቀድ የሚለኮሰው ደመራ ወደ ምስራቅ ከወደቀ የጥጋብ ዘመን ነው ይባላል፡፡

የልጆች የአዲስ አመት የፍትፍት ርጭት የጥጋብ ዘመን ምኞትም በዚህ ይረጋገጣል፡፡ ደመራውን የከበበው ሰውም ረመጡን በባዶ እግሩ እየረገጠ
'ልመደው ቆላውን ፣ ልመደው ደጋውን' እያለ ጤንነትን ለራሱ ይመኛል፡፡ ይኼ የመስቀል የእዮሀ ዜማ ሲበዛ ጀሮ ገብ ነው፡፡ ለዚህ ነው ጨዋታ ከማለት ይልቅ ዝማሬ ያልኩት፡፡ በአዲሱ አመት የመጀመሪያ ቀን የሚደረገው የፍትፍት ርጭት ምሳሌም ዘመናትን ቀድሰህ እንዳለፈው ሁሉ ሳትለየን ከዚህ አድሰኸናል፡፡ ደግሞም ቸርነትህ ብዙ ነውና የከርሞ ሰው በለን ዳግም በፍትፍት እናመሰግንሀለን ማለት ነው፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ እለት የ'አበደ አበደ' ፍትፍት ያልተባለበት ማሳ ውሀ ሳይጠጣ ቀረ ይባላል፡፡ ሞተ ከዳ ወይም ባለቤት የሌለው ካልሆነ በስተቀር ማሳው ሳይረገጥ አይውልም፡፡ በተለያየ ምክንያት ሁሉንም ማሳ ያላደረሰ ሰው ካለ የመስቀል እለት ፍትፍት ይዞ ቀሪ ማሳውን ይረጫል፡፡ የመርጨቱ ማሰርያ የአገሩ አምራችነትና የምርቱ በሰላም ጎተራ የመግባት ምሳሌ ነው፡፡

✍~~~ተፃፈ በ ጋዜጠኛ Kalkidan Girmaw Gebeyaw 😍🙏‼️

 #መረጃ ‼️  #የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ❗️ከጳጉሜ 2/2014 ዓ/ም ጀምሮ ኤሌክትሪክ መብራት የተቋረጠው   በ66 ኪቪ ቮልት ከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ  #በመሸንቲ ዙሪያ ኢን...
08/09/2022

#መረጃ ‼️ #የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ❗️

ከጳጉሜ 2/2014 ዓ/ም ጀምሮ ኤሌክትሪክ መብራት የተቋረጠው በ66 ኪቪ ቮልት ከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ #በመሸንቲ ዙሪያ ኢንሳ አከባቢ 6 ትላልቅ የኤሌክትሪክ ምስሶዎች በመውደቃቸው፡

*አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ሙሉ በሙሉ፣
*ምዕራብ ጎጃምና መተከል ዞኖች በከፊል መቋረጡን የእንጅባራ የመብራት ሀይል አገልግሎት መስጫ ማዕከል አስታውቋል ።

✍️ ተቋሙ አሰራሩን በደንብ ሊፈትሽ ይገባል፡ በአንድ አመት ብቻ ከ 10 በላይ ዝርፊያዎች እና ብልሽቶች... 🤔⁉️

( መረጃው፡ የአዊ ኮሙኒኬሽን)

እነሆ የምስራች!!!
07/09/2022

እነሆ የምስራች!!!

መልካም ነገር 1 በእለተ ሰንበትእለተ ሰንበት ከቀኖች መካከል የተመረጠ ቀን የመጀመሪያ ስልክ ሲደወል ሰንበት ነውና መልካም ነገር ይዞ ብቅ ማለቱ አይቀርም ።የመጀመሪያው  የምስራች  አቅመ ደ...
28/08/2022

መልካም ነገር 1 በእለተ ሰንበት

እለተ ሰንበት ከቀኖች መካከል የተመረጠ ቀን የመጀመሪያ ስልክ ሲደወል ሰንበት ነውና መልካም ነገር ይዞ ብቅ ማለቱ አይቀርም ።

የመጀመሪያው የምስራች አቅመ ደካማ የሠንበት አራስ ለመጠየቅ አሰብን ቤቷ ድረስ ሄድን አየናት እና የሚያስፈልጋትን መዝግበን ተመለስን ። ወዲያውኑ ሰማኸኝ አዘነ ለሚባል አባይ ግድብ ለሚሰራ ወንድማችን ደወልነ ማርያም ይማርሽ በሉልኝ በማለት የፍራሽ እና የብርድ ልብስ መግዣ 2,200 ብር አስገባልን ገዛነ

በመቀጠልም እኛ የአማራ ወጣቶች ማህበር አባላት ከኛ ምን ይጠበቃል ብለን ተነጋገርነ እና 2,000 ብር ሰበሰብነ ለተወለደው ህፃን ሁለት ልብስ እንዲሁም ሁለት የፕላስቲክ ሳፋወችን ገዝተን ስንመለስ ድንገት የሁል ጊዜ በጎ አድራጎት አጋዣችን ያደለው መድሐኒት መደበር ለህፃኑ ደረጃ አንድ የማጥቢያ ጡጦ እና ሁለት የተሻሉ የህፃኑ ሳሙና በመስጠት ሰንበትን በመልካም ነገር እንድናሣልፍ አደረጉን ።
👉 ልዩ ምክጋና ለወንድማችን ሰማኸኝ አዘነ ፣ ለወጣት ማህበሩ አባላት ፣ ለሐብቱ አስቀናው እና ለያደለው መድሐኒት መደብር

"   "‼️~~~ያለዉን ለሌለዉ መስጠት ከእግዚአብሔር  መሰጠት ነዉ ምክንያቱም  ለመስጠት ግዴታ ገንዝብ ያለዉ መሆን፣ ሀብታም መሆን ብቻ አይደለም እና።ሀብት ኖሯቸዉ ገንዘብ ሞልቷቸዉ የማይሰ...
24/08/2022

" "‼️

~~~
ያለዉን ለሌለዉ መስጠት ከእግዚአብሔር መሰጠት ነዉ ምክንያቱም ለመስጠት ግዴታ ገንዝብ ያለዉ መሆን፣ ሀብታም መሆን ብቻ አይደለም እና።

ሀብት ኖሯቸዉ ገንዘብ ሞልቷቸዉ የማይሰጡ እንዳሉ ሁሉ ከእለት ጉርሳቸዉ የዘለለ ገቢ የሌላቸዉ በርካቶች ሲሰጡ ይስተዋላሉ፤ ይህ ከእግዚአብሔር መሰጠት እና መታደል ነዉ።

ለ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን በደቡብ አቸፈር ወረዳ እና በዱርቤቴ ከተማ እንዲሁም ቀበሌዎች እገዛና ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎቻችን አንድ ደብተር ዋጋ አላት በማለት፣ ብዙ ወገኖቻችን ድጋፋችሁን እያሳያችሁን ነው!

የዘንድሮውን ከበፊቱ ለየት የሚያደርገው #በህልውና ዘመቻው ምክንያት ወላጆቻቸውን ያጡ መኖራቸውም ጭምርነው ህመማቸውን ኑ አብረን እንታመም ጊዜው አሁን ነው እሱም በእኛ እጅ ነው!!

ይቀጥላል.......

አሉን በርካታ ደጋፊዎች‼️
💚በርካታ ባለሃብቶች አሉን
💛በርካታ የመንግስት ሰራተኞች አሉን
❤️በርካታ ወጣቶች አሉን
➠በዉጭዉም አለም የሚኖሩ ደጋግ እህት ወንድሞችም አሉን...

N.B ''በ2015 ዓ.ም አንድም ተማሪ በመማሪያ ቁሳቁስ ምክንያት ትምህርቱን መዘንጋት የለበትም!!''

( Melak Bekalu Girum Misalie Getalem Mekete )

ጸጸት!እ.ኤ.አ. በ1993 በሱዳን በተከሰተው ረሃብ ወቅት  በረሃብ  ልትሞት የምታጣጥር ህጻን ሴት ልጅ  ነብሷ ወጥቶ ዘንጥሎ ሊበላት በጥንብ አንሳ የተከበበችውን ፎቶ ግራፍን አንስቶ ለአለም...
24/08/2022

ጸጸት!
እ.ኤ.አ. በ1993 በሱዳን በተከሰተው ረሃብ ወቅት በረሃብ ልትሞት የምታጣጥር ህጻን ሴት ልጅ ነብሷ ወጥቶ ዘንጥሎ ሊበላት በጥንብ አንሳ የተከበበችውን ፎቶ ግራፍን አንስቶ ለአለም ያሰራጨው ጋዜጠኛ በ1993 አ.ም ነበር።

ፎቶግራፉን ያነሳው የደቡብ አፍሪካዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ኬቨን ካርተር ሲሆን በኋላም የፑሊትዘር ሽልማትን ለዚህ 'አስደናቂ' ፎቶ አነሳስ ችሎታው አሸንፏል እውቅናንም አግኝቷል።

ይሁን እንጂ ኬቨን ባገኘው ስኬት የመደሰት እድሉ ጥቂት ወራት ብቻ ኖነበር ምክንያቱም ከጊዜ በኋላ በጭንቀት ተውጦ በጸጸተ ይቃጠል ጀመር!

ድንቅ ስራውን እያጣጣመ ዘወትር በአለም አቀፍ ደረጃ በዋና ዋና የዜና ማሰራጫዎች እና ኔትወርኮች ላይ እንዲህ ላለው 'ልዩ' የፎቶግራፍ ጥበብ ስለሚከበር ስሙ በአለም ገነነ። ጭንቀቱ ግን በረታ።

የመንፈስ ጭንቀት የጀመረው በአንድ ወቅት በአንድ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ቃለ ምልልስ እያደረገ ሳለ ከአድማጮች አንድ ሰው ስልክ ደውሎ ፎቶውን ከአነሳህ በኋላ በዚህች ጎስቋላ በረሀብ የተጎዳች ህጻን ላይ ምን ተፈጠረ? ብሎ ሲጠይቀው ነበር።

ኬቨን እንዲህ ሲል መለሰ: - "ፎቶውን ካነሳሁ በኋላ በረራ ስለነበረኝና ቸኩዬ ስለነበርና ግዜ ስላልነበረኝ ከዛ በኋላ በህጻኗ ላይ የተፈጠረውን አላውቅም ለማወቅምም አልጠበቅኩም..."

ሰውየውም "በዚያን ቀን ሁለት ጥንብ አንሳዎች ነበሩ ማለት ነው ፤ አንደኛው ካሜራ ነበረው።' ሲል መልሶለት ቴሌፎኑን በንዴት ዘጋበት።

ኬቨን ስለዚያ አረፍተ ነገር ያለማቋረጥ ማሰቡና ቁጭቱ ሊድን የማይችል የህሊና ቁስል አስከተለበት። እራሱን ጠላ ከህሊናው ጋር መታረቅ ተሳነው። በመጨረሻም እራሱን አጠፋ።

ኬቨን ካርተር ዛሬ ትንሿን ልጅ አንሥቶ ወደ የተባበሩት መንግስታት የምግብ ማእከል ቢወስዳት ኖሮ ዛሬ በህይወት ሊኖር እና የበለጠ ሊከበር ይችል ነበር።

ከዚህ ምን እንማራለን?።
በተለይ አሁን ቴክኖሎጂው ረቆና መጥቆ በቀላሉ ኮሚኒከት በምናደርግበት ወቅትና በሶሻል ሚዲያው የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በየሰከንዱ በምናወቅበት ሁኔታ፣ ከመጥፎና ከይምሰልና "ከውሸት ከውሸት" እንራቅ እውነትን እንጠጋው እንቅረበው ሁሌም መልካም ነገርን ብቻ እናድርግ።

በምናደርገው ነገር ሁሉ ስለሌሎች እናስብ እና ለሰው ልጅ እንዴት ጥቅም መስጠት እንደምንችል እናስብ።

የእርዳታ እጃችንን ዘርግተን እንባን ማበስ የምንችለው አገራችንና ህዝባችን የገጠመውን ችግር የጋራ ችግራችን መሆኑን ተረድተን የችግራችን የመፍትሄ አካል መሆን ስንችል ብቻ ነው።

እውቀትን፣ ሃብትን ወይም ሹመት ስንፈልግ እንዴት ህዝቡን የበለጠ ተጠቃሚ ማድረግ እንደምንችል እናስብ።

ዞር ብለን የእኛን የፍጥነት ዕርዳታ ዕጆችን የሚሹ ስንቶች አሉ ብለን እንጠይቅ?

መልካም ቀን
~~~// ~~~~

✍️...አቅም ለሌላቸውና ወላጆቻቸውን በሞት ለተነጠቁ ተማሪዎች የምናሰባስበው የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ በጡሩ ሁኔታ እየሔደ ነው ከተጀመረ ዛሬ አምስተቀኑን ይዟል!ለዚህ መልካም ነገር የተሳተፍ...
22/08/2022

✍️...አቅም ለሌላቸውና ወላጆቻቸውን በሞት ለተነጠቁ ተማሪዎች የምናሰባስበው የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ በጡሩ ሁኔታ እየሔደ ነው ከተጀመረ ዛሬ አምስተቀኑን ይዟል!

ለዚህ መልካም ነገር የተሳተፍችሁትን በሙሉ እያመሰገንን ከታሰበው አላማና ከትምህርት ቁሳቁስ ጭማሬ ጋር ተያይዞ ገና ብዙ ይቀረናል። ስለዚህ ሁላችንም የበኩላችንን እንውጣ የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆቻችን በደብተርና እስክብሪቶ ችግር ከትምህርት ገበታቸው እንዳይሰተጓጎሉ ሁላችንም የበኩላችንን እና የተቻለንን እናድርግ❗️

" 50 ሎሚ
ለ50 ሰው ጌጡ
ለአንድ ሰው ደግሞ ሸክሙ " አንዲሉ አበው እኛም፡

⭕️ አንድ ሰው የአንድን ተማሪ ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ ችሎ ቢያስተምር (ከእለት ወጫችን ላይ ቀንስ አድርገን ) ለእኛ በጣም ቀላልና ቀላል ነገር ሲሆን ለተማሪወቹ ግን ትልቅና ከባድ ነገር ነው የምናደርግላቸው ስለዚህ እባካችሁ በተለይ የማድረግ አቅሙ እያላችሁ መልእክቱን እያያችሁ ባላዬ የምታልፍ ወገኖቻችን የድርሻችሁን ትወጡ ዘንድ እኔ እና የበጎ ስራ አሰባሳቢ ኮሚቴዎች ዝቅ ብለን እንጠይቃችኃላን።

እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ሰላም ለህዝባችን ፍቅር ያድልልን🙏

ደጉ ገራገሩ  #የገጠር ሰው 💚‼️የገጠር ሰው፦● እዴት አደርህ ስትለው እግዚአብሔር ይመስገን።● እዴት ዋልክ ስትለው እግዚአብሔር ይመስገን።● እዴት አመሽህ ስትለው እግዚአብሔር ይመስገን።በቀ...
21/08/2022

ደጉ ገራገሩ #የገጠር ሰው 💚‼️

የገጠር ሰው፦
● እዴት አደርህ ስትለው እግዚአብሔር ይመስገን።
● እዴት ዋልክ ስትለው እግዚአብሔር ይመስገን።
● እዴት አመሽህ ስትለው እግዚአብሔር ይመስገን።

በቀን ከ፲ ጊዜ በላይ ፈጣሪው የሚያመስግን ደግ ህዝብ ነው። ስራ ሲለፋ ቸር አውለኝ ብሎ። ሲተኛም ቸር አሳድርኝ ብሎ። ቢበላም ባይበላም ተመስገን እያለ የሚኖር ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ህዝብ ነው።

ደጉ ገራገሩ #የገጠር ሰው እኮ በእንግድነት ብትሄድበት እቅፍ አድርጎ ስሞ። እግርህን አጥቦ ያጠበውን እግርህን ስሞ በፈገግታ ተሞልቶ ያለውን እቅርቦ አብልቶ አልጋውን ለቆ አንተን ከአልጋው ላይ የሚያስተኛ ግሩም ሰው ነው።ቸገርኝ ብለህ ብትሄድበት የበሰለ እህል ውሃ ሳይቀር የሚያካፍልህ ነው።

® ስለ ገጠር ሰው ብዙ ማለት ይቻላል።
ባጠቃላይ በሀገሩ በእምነቱ በሚስቱ የማይደራደር ቆራጥ ህዝብ ያለ የት ነው ካላቹህኝ #ገጠር ነው።

እንኳን እህል ውሃ እቅርቦ ሲሳይ፣
ገጠር ፍቅሩ ብቻ ያጠግብ የለም ወይ!

ያጠግበኝ ነበር ፍቅር እና ለዛው፣
ይሄ ያገሬ ሰው ይሄ ገራገር ሰው፣
እርሱ እየተራበ "አርሶ የሚያጎርሰው"!

ደጉ የገጠር 'ሰው'💚

Durbete-Achefer Press

መልካም መልካሙ 'የምንሰማበትና የምንሰራበት' ዕለተ ሰንበት ይሁንልን🙏የዛሬዋን ዕለተ ሰንበት፡ የትምህርት መማሪያ አጥተው ትምህርት ለመጀመር ጭንቀት ላይ ያሉትን ታዳጊዎች የምንረዳባት፣ የወላ...
21/08/2022

መልካም መልካሙ 'የምንሰማበትና የምንሰራበት' ዕለተ ሰንበት ይሁንልን🙏

የዛሬዋን ዕለተ ሰንበት፡ የትምህርት መማሪያ አጥተው ትምህርት ለመጀመር ጭንቀት ላይ ያሉትን ታዳጊዎች የምንረዳባት፣ የወላጆቻቸውን ምርቃት የምናገኝበት ቀን ያደርግልን‼️

💚 ቤተ~ክርስቲያን 👌🙏

💚መልካም ዕለተ ሰንበት❤️🙏

ተጀመረ ‼️"አንድ ደብተር ለአንድ ተማሪ"ለደቡብ አቸፈር ወረዳ እና ዱርቤቴ ከተማ ማህበረሰብ፣ እንዲሁም በሃገር ውስጥም ሆነ ውጭ ያላችሁ ለጋሽ ወገኖቻችን በሙሉ፡  #ከተባበርን የማንሻገረው ...
19/08/2022

ተጀመረ ‼️

"አንድ ደብተር ለአንድ ተማሪ"

ለደቡብ አቸፈር ወረዳ እና ዱርቤቴ ከተማ ማህበረሰብ፣ እንዲሁም በሃገር ውስጥም ሆነ ውጭ ያላችሁ ለጋሽ ወገኖቻችን በሙሉ፡ #ከተባበርን የማንሻገረው መከራ፣ የማንወጣው ዳገት፣ የማናልፈው ፈተና አይኖርም!
አንድም ተማሪ በደብተርና እስክቢርቶ እጥረት ምክንያት ከትምህርቱ መስተጓጎል የለበትም!! እየተረዳዳን፣ እየተደራጀን፣ እየተመካከርን፣ ነገን ዛሬ እንስራ፣ ለመጭው ትውልድ መከባበርን፣ መተባበርን፣ መረዳዳትና መተዛዘን በነቢር ሳይሆን በገቢር እናስተላልፍ!

ኣካውንቱ በ 3 ኮሚቴዎች ተከፍቷል፡
® በመምህር ጌጣለም መከተ፡ የመምህራን ማህበር ሰብሳቢ
® በመምህር መላክ በቃሉ፡ የ ዱ/2ኛ/ደ እና መሰ ት/ቤት ሱፐርቫይዘር
® በመምህር ግሩም ምሳሌ፡ የሁልጊዜ የበጎ አድራጎት ተሳታፊ እና የወጣቶች ማህበር ተወካይ፡

ኮሚቴዎች፡ መምህር ግሩም እና መላክ በ 400 ብር ጀምረውታል!

◉ የሂሳብ ቁጥር፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ 1000493895331
◉ ስም፡ ግሩም ምሳሌ እና መላክ በቃል እና ጌጣለም መከተ

♥ በቁሳቁስ ድጋፍ ለማድርግ የምትፈልጉ፡ ዱርቤቴ ከተማ ዘንድ ቦታ ተዘጋጅቷል!

ድጋፉ ከእኔ ይጀምራል #አንድ ደርዘን ደብተር በቁሳቁስ መልኩ ለመስጠት ቃል አገባልሃለሁ🙏

ወገኖቻችን አለን በሉን እስኪ!

ደጉን የአቸፈር ሕዝብ ዘር አምካኝ ደላሎችና ዘር አምካኝ አመራሮች እንዴት እንደበሉት የምርመራ ጋዜጠኛ ጓደኞቻችን በማዳበሪያ ዘረፋ ዙሪያ በአሚኮ ይፋ ያደረጉት እውነት ማሳያ ነው። የሚገርምኮ...
18/08/2022

ደጉን የአቸፈር ሕዝብ ዘር አምካኝ ደላሎችና ዘር አምካኝ አመራሮች እንዴት እንደበሉት የምርመራ ጋዜጠኛ ጓደኞቻችን በማዳበሪያ ዘረፋ ዙሪያ በአሚኮ ይፋ ያደረጉት እውነት ማሳያ ነው።
የሚገርምኮ ነው! ሁሉም ሲጠየቅ
👉"እኔ አይደለሁም!"
👉"እኛ አይደለንም!"
👉"እኔ እውቅና የለኝም!"
👉"የህብረት ስራ ማህበሩ ችግር ነው!"

ችግሩ የህብረት ስራ ማህበር ጽ/ቤቱ ብቻ ነው?
አቸፈር ውስጥ ከወገናችን ሰነድ እየተሰረቀ፣ መሬት እየተዘረፈ፣ ተቋማት እየተመዘበሩ እንዴት ዝም እንበል?

ሌባና ዘራፊን ማስቆም አካባቢን ማልማት ነው። በዚህ እሳቤ በይስማላ ከተማ የተፈፀሙትን የሰነድ እና የተቋማት ዘረፋዎች ለማስቆም ማህበራችን ብዙ ጥረን አድርጎ መረጃና ማስረጃችን በወረዳ ደረጃ እንዴት ጀሮ ዳባ ልበስ እንደተባለ ጋዜጠኛ አስፋውን ጨምሮ የምናውቀው ሀቅ ነው።

እንግዲህ ያላመናችሁ እመኑ አርሶ አደር ወገናችን አብቁተ ተበድሮ በየህብረት ስራ ማህበሩ እንዲህ ይዘረፋል?

👍የእውነት ጠበቃ የአቤ ጉበኛ ልጅ ጋዜጠኛ አስፋው ሙቀት እግዚአብሔር ይባርክህ።

👌ክፍል 2 ነገ ምሽት 2:40 በአሚኮ ይቀጥላል!

( የይስማላ ከተማ እና የአካባቢዋ ልማት ማህበር)

ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ!!!ድንቅ የአሳዬ ደርቤ መጽሐፍ!!!!
18/08/2022

ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ!!!
ድንቅ የአሳዬ ደርቤ መጽሐፍ!!!!

የበጎ አድራጎት ጥሪ❗️ ‼️"አንድ ደብተር ለአንድ ተማሪ"“በምናገኘው ነገር እንኖራለን፣ በምንሰጠው ነገር ደግሞ ሰውን እናኖራለን” -Winston Churchill~~~በደቡብ አቸፈር ወረዳ እና...
17/08/2022

የበጎ አድራጎት ጥሪ❗️ ‼️

"አንድ ደብተር ለአንድ ተማሪ"

“በምናገኘው ነገር እንኖራለን፣ በምንሰጠው ነገር ደግሞ ሰውን እናኖራለን” -
Winston Churchill
~~~
በደቡብ አቸፈር ወረዳ እና ዱርቤቴ ከተማ ማህበረሰብ በጎ አድራጎት ተግባር እንቅስቃሴ ውስጥ የምትተጉ ወጣቶች እና ባለሀብቶች በሙሉ " #እኔ እያለሁ አንድም ተማሪ በትምህርት ቁሳቁስ አይቸገርም!" በሚል መሪ መልዕክት የትምህርት ቁሳቁስ ግብዓት ማሰባሰብ ለመጀመር አስበናል፣ ከጎናችን ናችሁ💪 ‼️

የእናንተን ይሁን አይተን እንቀጥላለን!
~~~
በአሁን ጊዜ በእጅህ ካለው መልካም ነገር አንዱም እንኳን ከሰዎች መዋጮ ውጪ እጅህ እንዳልገባ እንዳስታውስህ ፍቀድልኝ፡፡ የአንድ ሰው የመወለድ፣ የማደግ፣ የመማርና ሰርቶ የማደር ሁኔታ ከሌሎች ሰዎች ጋር የተሳሰረ ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎች በሌሎች እርዳታ ኖሩ፣ ተደራጁ፣ ተሻሻሉ፤ ከዚያም በእነሱ እርዳታ ደግሞ ሌላውን አኖሩና አለፉ፡፡ ተተኪዎቹም እንዲሁ ከሌላው የተረከቡትን ይዘው ቀጠሉና ለሌላው አቀበሉ፡፡ ይህ የኑሮ ዑደት ቀጣይና የማያቋርጥ ነው፡፡
እውነታው ሲሰበሰብ፣ ከሌሎች በተቀበልነው ነገር ለመኖር የመቻላችንን ያህል፣ እኛ ደግሞ በምንሰጠው ለሌሎች ሰዎችን እናኖራለን፡፡ ጊዜው መጥቶልን ራሳችንን እስከምንችል ድረስ ለሕልውናችን የተደገፍንበት ሰው እንደነበረ እሙን ነው፡፡ ራሳችንን ቻልን ባልንበት ጊዜ እንኳ አሁም ከሌላው ሰው መዋጮ ውጪ ማድረግ የማንችላቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ አሁን ደግሞ በእኛ ሁኔታ ላይ የሚደገፉ ሰዎች መኖራቸውን ማስታወስ የእኛ ተራ ነው፡፡ በሌላው ሰው ድጋፍ ኖረን በእኛ ድጋፍ ደግሞ ሌላውን የማኖርን ምስጢር እንግፋበት፡፡

መልዕክቴ ነው‼️

ሃሳብ አስተያየት ስጡን።

"ኑ ይሄን ድንቅና   ተመልከቱ" አመስግኑም ‼️የእናታችን እማዋይሽ ጎቤ ከልመና እና ከሰቆቃ ህይወት ለመታደግ የሚደረገው በጎ አድራጎት አጠቃላይ ስራችን የተመለከተ፡✔️ አካውንቷ ውስጥ፡ እስ...
15/08/2022

"ኑ ይሄን ድንቅና ተመልከቱ" አመስግኑም ‼️

የእናታችን እማዋይሽ ጎቤ ከልመና እና ከሰቆቃ ህይወት ለመታደግ የሚደረገው በጎ አድራጎት አጠቃላይ ስራችን የተመለከተ፡

✔️ አካውንቷ ውስጥ፡ እስካሁን 143, 670.01 ብረ ገቢ ሆኗል! መልካም ስራችን የሳበው ቅንና ደግ ወንድማችን፡ #መስፍን ተሾመ ወደ አስተባባሪ ቅን ወንድማችም ዘላለም ሃይሌ 15,156 ብር አስገብቷል( ለጊዜው የተጠቀምነው ይሄን ብቻ ነው)

® እስካሁን የተሰሩ ስራዎች፡
*አልጋ = 2800. * የእርሷ ብርድ ልብስ
* ፎም/ፍራሽ= 2500 * የእርሷ እና የልጁ ልብስ
* አንሶላ= 600 * እርሷ ዘንድ አብራት ላለችው እህት ልብስ
* ጤፍ( 50 ኪ.ግ)= 2200 * የተለያዩ አስቤዛዎች ወዘተ....
በአጠቃላይ፡ ከወንድማችን ከመስፋን የተላከው ብር እና ወንድም ዘላለም ተጨማሪ ከ 400 ብር በላይ ከኪሱ በመጨመር ጊዚያዊና ቋሚ ዕቃዎችን 15,610 ብር ወጭ ተደርጎ ተገዝቷል። ዝርዝሩን አያይዘናል!

➽ዋናው አላማችን እና ስራችን እርሷን ከልመና ስራ የማንሳትና እና ቋሚ ገቢ ያለው ስራ እንድትጀምር ማግባባትና ወደ ስራ ለማስገባት፣ ቅን አስተባባሪዎች ደገመን ሰለቸኝ ሳይሉ ፣ የእናታችን ትንሽ አስቸጋሪ ባህሪያት ተቋቁመው እየሰሩበት ይገኛል። በቀጣይ ወርም ወደ እናታችን ሂሳብ የገበውን ብር ስራ እንትጀምር በሂደት ላይ ናቸው፣ እይመቻቹም ይገኛል (እናታችን የባህሪይ ለውጥ ካሳየችን በኃላ ማለት ነው)፤ በዚህም አካውንታቸው ጋር ያለው ብር እስካሁን አልተነካም። በቀጣይ ስራ ሲጀምሩ ለእናንተ የምናደርስ ይሆናል።

የእናታችን #ሙሉ መሸሻ እስካሁን፡ 150, 390 ብር ደርሷል! ይሄንም ዝርዝር ሁኔታ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል🙏

ምንም እንኳን "የመልካምነት ክፍያው ህያው ቢሆንም" ካለ እናንተ እርዳታ እዚ አንደርስም ነበረ እና፤ ሁላችንም በዚህ ቅን፣ ሰናይ፣ ለህሊና እረፍት የሚሰጥ፤ ዋጋው በሰማይም በምድርም ከፍ ያለውን በጎነት በተግባር የተሳተፋችሁ እግዚአብሔር ይጠብቅልን፣ ክብሩን ያድልልን የእርሳቸው #ምርቃት በያላችሁበት ይድርስ እንላለን🙏

® የዚህ መልካምና ቅን ተግባር አስተባባሪዎች፡ ወንድም ፣ እንዲሁም ወንድማችን #ፋሲካው ደርሰህ፤ በዚህ የሩጫ ዘመን የግል ጉዳያቸውን ወደ ጎን ትተው እየሰሩት ያለው ስራ እንዲህ በቀላሉ ዘርዝሬ አልጨረሰውም፣ ብቻ ግን ፈጣሪ ክብሩን ያድልልን አመስግኑልኝ!

ይሄን ድንቅ ስራ 🙏

✅የደራሲ አቤ ጉበኛ አጭር የህይወት ታሪክ⤵~~~~~~~~~~ደራሲ አቤ ጉበኛ በምዕ/ጎጃም ዞን በ አቸፈር ወረዳ ልዩ ስሙ ኮረንች በአታ በተባለ ቀበሌ ከአባቱ ከአቶ አቤ ጉበኛ አምባየና ከእናቱ...
14/08/2022

✅የደራሲ አቤ ጉበኛ አጭር የህይወት ታሪክ⤵
~~~~~~~~~~
ደራሲ አቤ ጉበኛ በምዕ/ጎጃም ዞን በ አቸፈር ወረዳ ልዩ ስሙ ኮረንች በአታ በተባለ ቀበሌ ከአባቱ ከአቶ አቤ ጉበኛ አምባየና ከእናቱ ከወ/ሮ ይጋርዱ በላይ ሰኔ 25 ቀን 1925 ዓ.ም ተወለደ፡፡

አቤ ጉበኛ ወላጅ እናቱን በሞት የተነጠቀው ገና የ3 ዓመት ህፃን በነበረበት ጊዜ ሲሆን እድሜቸው 17 ዓመት አልሞላም ነበር፡፡
አቤ እናቱን በሞት ያጣው ገና በህፃንነት እድሜው ስለነበር በእናቱ ሞት በጣም ይሰማው ነበር፡፡ በመሆኑም ከጎለመሰ በኋላ ስለእናቱ የሚከተለውን ግጥም ገጥሟል፡፡

እግዚአብሄር ባያድለኝ እናትን እንድጠቅም
ወዴት ብየልርዳት እናቴን አላቅም
እናቴን በድንገት ተነስተሸ ባይሽ
ማሜቴ ልልሽ እማማ ልልሽ
ከሰላሳ ስርቅ እኔ እንኳ ልጅሽ
አንቺ አስራ ሰባትን ሳትደርሽ ቀረሽ

ደራሲ አቤ ጉበኛ ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ በመጀመሪያ የአብነት ትምህርቱን በይስማላ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ዜማውን ፣ ዳዊቱን ፣ ቅኔውንና አቋቋሙን ለ12 ዓመታት የተከታተለ ሊቅ ነበር፡፡ ቅኔ አዘራረፋቸውንም ሰምቶ አቃንቶ ያሰተካከላቸው መምህሩ “እሱ አቤ ጉበኛ ሳይሆን አቤ ጉደኛ ነው” ብለውታል፡፡

አቤ ከሀይማኖታዊ ትምህርት በተጨማሪ የዘመናዊ ትምህርቱን በዳንግላ ከተማ ይከታተል የነበረ ሲሆን በ1946 ዓ.ም ዳንግላን ትቶ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ባዕታ ቤተ ክርስቲያን ተጠግቶ እንደ ቆሎ ተማሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡

አቤ ድቁናን፣ ቅስናን፣ ቅኔን አጠቃሎ ያውቅ ስለነበር አዲስ አበባ ሀና ማርያም በመርጌታነት ተቀጥሮ ቀሳውስትን፣ ዲያቆናትንና መዘምራንን ይመራ ነበር፡፡

ገና ዳንግላ ዘመናዊ ትምህርት በመማር ላይ እያለ የጀመረውን የአማረኛ ግጥም የመፃፍ ፍቅሩን በማጠናከር በ24 ዓመቱ ሚያዚያ 12 ቀን 1949 ኣ.ም በታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ልቡ ገበሬው ዘንድ መሆኑን የሚያመለክት በህብር መንገድ አንድነት ያለውን ተቀሜታ በግጥሙ በመግለጽ በጋዜጣው እንዲወጣ አድርጓል፡፡

በዚሁ ጋዜጣ ግንቦት 10 ቀን 1949 ዓ.ም “የሀዘን እንጉርጉሮ” በሚል የፃፈው ግጥሙ በውስጡ ያመቀውን ከመተንፈስ ወደ ኋላ የማይል ደራሲ መሆኑን አመላክቷል፡፡

በ1949 ዓ.ም መጨረሻም “ከመቅስፈት ሰራዊት ይጠንቀቅ ሰውነት” በሚል ርዕስ አነስተኛ የግጥም መፅሐፍ አሳትሟል፡፡ ይህንን ክህሎቱን በማየትም በ1951ዓ.ም በ26 ዓመቱ በማስታወቂያ ሚኒስቴር በጋዜጠኝነት ተቀጥሮ ሰርቷል፡፡

በዚህ ያልተወሰነው አቤ በ1953 ዓ.ም ባሳተመውና “የሮም አወዳደቅ” የሚል ስያሜ በሰጠው የተውኔት መፅሀፉ ገበሬው በአፄ ኃይለ ስላሴ ስርአት ያለውን ብሶት ቁልጭ አድርጎ ማሳየቱ አቤ ጉበኛ ህይወቱን ለሚያምንበት ዓላማ አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነበር፡፡

በወቅቱም የነበረውን ግፈኛ ስርአት በማውገዝ ከፃፋቸው በርካታ ፅሁፎች ባሻገር በ1955 ዓ.ም ባወጣው “የአመፅ ኑዛዜ” በተሰኘው ልብ ወለድ መፅሀፉ ተምረውም ሆነ ሰርተው ሀብት ያገኙ ሰዎች ድሀ ወገኖቻቸውን እንዲረዱ አሳስቧል፡፡የጭቆናና የድህነት ቀንበር የተሸከሙት ወገኖችም ነፃ የመውጣታቸው ጉዳይ አጠያያቂ አለመሆኑን ገልጿል፡፡

አቤ ቀደም ሲል በፃፋቸው መፅሀፍት ሳይወሰን በ1956 ዓ.ም ሀምሌ ወር ላይ “ሰይፈ ነበልባል” የተሰኘውን መፅሀፉን አሳትሟል፡፡መፅሀፉ እንደ አልወለድም ከሽያጭ ይታገዳል ይቃጠላል የሚል ጥርጣሬ በህዝቡ ላይ ስለነበር መፅሀፉን ለማግኘት ከፍተኛ ርብርብ ነበር፡፡ በሁለት ተከታታይ ወራት ብቻ ለ4 ጊዜ በተደጋጋሚ ታትሟል፡፡

መጽሀፉ በደርግ ዘመነ መንግስትም እስከ 1968 ዓ.ም ድረስ የተሸጠ ሲሆን የሚመጣውን የደርግ አገዛዝም ቀድሞ ተችቷል፡፡ ይህ መፅሀፍ በኢትዮጲያ የስነ- ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ 25‚000 ኮፒ ታትሞ የተሸጠ ስለነበር በሀገሪቱ በከፍተኛ ስርጭት የመጀመሪያው ነበር፡፡ በዚህ መጽሀፍ ከአልወለድም በጠራ መልኩ ለኢትዮጲያ ምን አይነት መንግስት እንደሚያስፈልጋት አትቶበታል፡፡

አቤ ጉበኛ የሚፅፋቸው ፅሁፎች ለመንግስት አስቸጋሪዎች በመሆናቸው በ1955 ዓ.ም አልወለድምን በፃፈበት ወቅት ይደረግበት የነበረው ክትትልና ይህን መፅሐፍ ከፃፈ በኋላም በ1957 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ የተጠናከረ ክትትል እንዲደረግበት በመንግስት ባለስልጣናት ደብዳቤ ተፅፏል፡፡

በብዕሩ ነፃነቱን ለማስፈን የሚታገለው አቤ ጉበኛ ጨቋኙንና አስከፊውን የአገዛዝ ስርአት በብዕር ዱላ ደብድቧል፡፡ መነግስትም አቤ የሚገባበትን የሚወጣበትን እያነፈነፈ አሳድዶታል፡፡ ይህን ሁሉ ውጣ ውረድ ተቋቁሞ ትግሉን ያካሂድ የነበረው አቤ ከፖለቲካ ይልቅ ማህበራዊ ትችት የሰጠበትንና የዘመኑን አሰቃቂ የህይወት ገፅታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው “ከልታማዋ እህቴ” የተሰኘውን አጭር ልብወለድ ጥር4 ቀን 1957 ዓ.ም አሳትሟል፡፡

ፖለቲካዊ፣ ማበራዊና ሀይማኖታዊ ትችቶችን በፅሁፎቹ የሚሰነዝረው አቤ እያካሄደ ባለው የብዕር ውጊያ ባለመርካቱ ሌት ከቀን ለሚያንገበግበው የሀገሩ ጉዳይ እልባት ለመስጠት ተግባራዊ ትግል ማድረግን መረጠ፤ወደ ተግባርም ገባ፡፡

በ1957 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ በተካሄው የህዝብ እንደራሲነት ምርጫ ለመወዳደር የ50 ሰዎችን የድጋፍ ፊርማ አገኘ፡፡ ህጋዊ ፈቃድም ተሰጥቶት ዘመቻውን አጧጧፈ፡፡ ህዝቡም በነቂስ ወጥቶ እርሱን ለመምረጥ አሰፈሰፈ፡፡ዳሩ ምን ያደርጋል የሀገሪቱ የነፃነት ታጋይ አቤ ጉበኛ ሰኔ 21ቀን 1957 ዓ.ም ድንገት ሳይታሰብ በፀጥታ ሀይሎች ተያዞ ብዙ ስቃይና እንግልት ደረሰበት በምርኩዝ ለመሄድም ተገደደ፡፡

ደፋሩ ደራሲ አቤ ጉበኛ ከሚወደው የኢትዮጲያና የአዲስ አበባ ህዝብ ተነጥሎ በብርቱ ጥበቃና ቁጥጥር ስር ሆኖ በሚከተሉት አኳኋን በግዞት እንዲኖር ተፈረደበት፡፡

➣በቀን 3 ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ እየሄደ እንዲፈርም ተወሰነ፣
➣በከተማው ውስጥ የሚዘዋወርባቸው ቦታዎችና ስዓቶች ተወሰኑ፣
➣ለጥበቃ ምቹ የሆነ ቦታ እንዲከራይ ተደረገ፣
➣በህዝብ መሰብሰቢያና መጠጥ ቤት እንዳይገባ ተከለከለ፣
➣ከአድመኞችና ተጠርጣሪ ከሆኑ ሰዎች ጋር እንዳይገናኝ ተደረገ፣
➣ከውጭ ሀገር ሰዎች ጋር እንዳይገናኝ ሆነ፣
➣ለቤተሰብም ሆነ ለመንግስት የሚፅፈው ደብዳቤ መመርመር እንዳለበት ተወሰነ፣
➣በእጁ በወር ከ50 ብር በላይ እንዳይይዝ ተደረገ፣

➣ጠቅላላ የዕለት ሁኔታውንና የሚያደርገውን ግንኙነት ሁሉ የሚከታተል ተቆጣጣሪና ተጠባባቂ በስውር ተመድቦ ስለ አጠቃላይ ሁኔታው በየ3ወሩ ሪፖርት እየተደረገ ኑሮውን በጎሬ ከተማ እንዲገፋ ተደረገ፡፡

በሀቀኝነቱ ፣ በሀገር ወዳድነቱና ለነፃነት ባለው ፅኑ ፍቅር ለከፋ ስቃይ የተዳረገው አቤ ከ4 ወር ተኩል በኋላ “ሞቻ የሰው ልጅ መሞቻ” ወደ ተባለው አስከፊ ቦታ ተወረወረ፡፡ የሰው ልጅ ሊሸከማቸው የማይችሉ ችግሮችን ተሸከመ፡፡

አቤ በግዞት ላይ እያለም በርካታ ደብዳቤዎችን በመፃፍ መንግስትን ከመተቸት ወደ ኋላ አላለም ነበር፡፡ የደረሰበትንም በደል እንደሚከተለው ገልጿል፡፡ “እኔ የማንም መጫዎቻ ሆኛለሁ፤ እኔ በፍፁም ተሰቃይቻለሁ፤ በኑሮየ ካለብኝ ችግር ሌላ እኔን ለማበሳጨት የሚፈፀሙብኝ ተግባሮች ብዙ ናቸው፤ ምናለ መንግስት ያሰበብኝን ንፁህ ቅጣት ቢፈፀምብኝ? ምናለ በኢትዮጲያዊነቴ ባላፍር? ምናለበት በሀገሬ ፍትህና ሰብአዊ መብት ተስፋ ሳልቆርጥ ብሞት” በማለት ነበር የደረሰበትን እንግልት የገለፀው፡፡

በ1958 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤም መብቱ ያለአንዳች ፍርድ መገፈፉን፣ እየደረሰበት ያለው ችግር በጦር ሜዳ የተማረከ ጠላት እንኳ የማይፈፀምበት መሆኑን ጠቅሶ በረሀብ ከሚጠቃ ይልቅ ምግብ እያገኘ እንዲታሰር ጠይቋል፡፡

በ1958 ዓ.ም መጋቢት ወር ላይ በፃፈው ደብዳቤ በሀገሪቱ ያለው መንግስት ብሔራዊና ሰብአዊ መብት ገፋፊ፣ ንፁሃንን ከወንጀለኛው አብልጦ የሚቀጣ፣ ሩህሩህ ወገኖቹን አፍቃሪ ዜጋን በጭካኔ የሚያሰቃይ መሆኑን በመጠቆም ስርአቱን አውግዟል፡፡

የአቤ ጥያቄዎች ምላሽ አላገኙም እጣፈንታው መታሰር ፣ መገረፍ ፣ መራብ ፣ መጠማት ፣ መጋዝ ፣መዋከብ ብቻ ሆነ፡፡ በህጋዊ መንገድ ሀሳቡን ለገለፀው በሰላማዊ መድረክ በሀገሪቱ ፖለቲካ ለመካፈል ጉዞ ለጀመረው አቤ ጉበኛ በሰዎች ስልጣናዊ ፣ ኢኮኖሚያ ስግብግብነት ለዚህ በቃ፡፡

ግዞተኛውና መንግስታዊ ህገ ወጥነትን ለማጋለጥ ብርቱ ብዕራዊ ትግል ያደርግ የነበረው ደራሲ አቤ ጉበኛ እስከ 1961 ዓ.ም ለ3 ተከታታይ አመታት በእስራትና በግዞት ቆይቷል፡፡ በ1969 ዓ.ም በፃፈው ፅሑፍ በታሰረባቸው 3 ዓመታት በበሽታ፣ በርሀብና በግዞት መማቀቁን አስፍሯል፡፡ ሞቻ ከተማ የግዞት ዘመኑን የገፋበት ኮረብታማ ቦታ ላይ የተሰራ ስለነበር ያ ቤት ዛሬ “ኮረብታማ” ሆቴል ይባላል፡፡

የመጀመሪያው ልጁን ሚካኤል አቤን ያፈራው በዚህ የግዞት ወቅት ነበር፡፡ አቤም የግዞት ህይወቱን መራራነት በሚከተለው ቅኔ ጠቁሟል፡፡

መቱንም አላየሁ ፣ ጉሬንም አላየሁ ፣
እናንተ ዘመዶቼ አልሞትኩም ሞቻለሁ፡፡

አቤ በ1961 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ ከግዞት እንደወጣ በሁለት ቀን ውስጥ ማለትም መስከረም 22 ቀን 1961 ዓ.ም “የሀሜት ሱሰኞች” የተሰኘውን መፅሀፍ አሳትሟል፡፡ በመፅሀፉ ግጥሞና ወጐ የተካተተበት ሲሆን ሀሳቡንም በትዝብትና በንዴት ገልጾበታል፡፡ በግዞት እያለ ስለ እርሱ የተነሱ የሀሰት ወሬዎችንም ተችቶበታል፡፡

በግዞት ቆይቻለሁ ስቃይና እንግልት ይብቃኝ በሚል ፍርሀት አድሮበት የብዕር ጦርነቱን ከማካሄድ ወደ ኋላ ከማለት ይልቅ ያጧጧፈው አቤ ጉበኛ መጋቢት 30 ቀን 1961 ዓ.ም “አንድለእናቱ” የተሰኘውን መፅሀፍ አሳትሟል፡፡

አቤ ከአማረኛ ልቦለድ ታሪኮች ውስጥ በስፋቱ የመጀመሪያ የሆነውን 602 ገፅ ባለው በዚህ መፅሐፍ አፄ ቴውድሮስን የአንድነትና የእድገት ተምሳሌት አድርጎ በመሳል የአገሪቱን አንድነት የሚያጠናክር ፣ ፈጣን ቴክኖሎጅ የሚያስገኝ መሪ በሚያስፈልጋት ስአት የነበረው አመራር ቀርፋፋ መሆኑን በመጥቀስ የአፄ ሀይለስላሴን መንግስት ክፉኛ ነቅፏል። መፅሀፉ በወጣቱ ትውልድ ዘመን በጣም የተወደደ ስለነበር እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ በተደጋጋሚ ታትሟል፡፡

አቤ ህዳር 30/1962 ዓ.ም “መስኮት” የተሰኘውን የግጥም መድበሉን ያሳተመ ሲሆን በመፅሐፉም ነባሩን ኢትዮጲያዊ ግጥምና ቅኔ አይነት በየፈርጁ ተንትኖ በፊውዳል ኢትዮጲያ ፍትህ ማግኘት የማይታለም መሆኑን አስቀምጧል፡፡
አቤ “የሀሜት ሱሰኞች ፣ መስኮት ፣ ጐብላንድና አጭበርባሪው ጦጣ” በተሰኙ ፅሁፎቹ ስነጽሁፋዊ ሂሶችን ሰንዝሯል፡፡

በአጠቃላይ አቤ ከግዞት መልስ ሙሉ ጊዜውን ለድርሰት በማዋል ከመፅሀፍ ሽያጭ ብቻ በሚያሰገኘው ገቢ የሚተዳደር ብቸኛ ኢትዮጲያዊ ፀሀፊ ለመሆን በቅቷል፡፡

አቤ ጉበኛ “ዋን ሀንድረድ ግሬት ላይቭ” ወይም “አንድ መቶ ታላቅ ህይዎቶች” የተሰኘውን የእንግሊዘኛ መፅሐፍ የተወሰነ ክፍል “የህይወት ትርጓሜዎች” የሚል ርዕስ በመስጠት ተርጉሟል፡፡ ጊዜውም በ1963 ዓ.ም ነበር፡፡ሚያዚያ 10 ቀን 1964 ዓ.ም ባሳተመው “የረገፉ አበቦች” በተሰኘው ልብ ወለድ መፅሀፍ የአማረኛ ስነ-ፅሁፍ ከልጅነት ወደ ጉርምስና መሸጋገሩን በግልጽ አብስሯል፡፡

“እሬትና ማር” የተሰኘውን የግጥም መፅሀፍ መጋቢት 12 ቀን 1965 ዓ.ም የፃፈው አቤ ጉበኛ በዚህ ጊዜ የ3 ልጆች አባት ለመሆን በቅቷል፡፡ የመጀመሪያውን ወንድ ልጁን ከአሁን በፊት እንደጠቀስነው በግዞት ላይ እያለ የወለደው ሲሆን ሁለቱን ሴት ልጆቹን ከግዞት መልስ የወለዳቸው ናቸው፡፡

አቤ ጉበኛ ላመነበት ዓላማ ህይወቱን መስዋት ለማድረግ የተሰለፈው አቤ ጉበኛ የልጆች አባት ሲሆን ምን ይሰማው ይሆን? እስኪ ከራሱ የስንኝ ቋጠሮ እንረዳ፡፡

ወንድነት ደከመ ወኔ ተቀነሰ
ሰው ራሱ ሲሞት ለልጁ አለቀሰ፡፡
ሞትን የማይፈራው ያ ቆራጡ ጀግና
ልቡ ሁለት ሆነ ልጁ ከፈለውና፡፡
ለማፍሰስ የሚችል የቆለጥን አሞት
የህፃናት አፍ ነው ጎልዳፋው አንደበት፡፡
ያልወለደ አረደ ሲባል ለጨከነ
ያልወለደ አይፀድቅም ተብሏል በደፈና፡፡

ወንድ ልጁ ቢደፍርም ቢጨክን በራሱ
ልጁ ካለው በኋላ የራሱ አይድለም ነፍሱ፡፡

በ1968 ዓ.ም መጨረሻ ላይ “ፖለቲካና ፖለቲከኞች” የተባለውን ተውኔቱን በሀገር ፍቅር ቲያጥር ለህዝብ አቅርቧል፡፡ ተውኔቱ በምፀት የቧልት የአፃፃፍ ስልት የተፃፈ ሲሆን ተውኔቱም የፖለቲካዊና ፖለቲከኞችን አለመገጣጠም ፣ የነገሮችን ተገላቢጦሽ መሆን በማሳየት በወቅቱ የነበሩ ባለስልጣናትን በምፀት ተችቷል፡፡

ምንም እንኳ ተውኔቱ ታይቶ ሳይጠገብ እንዲቋረጥ ቢደረገም፡፡
አይን ያወጣ ጭፍጨፋ በሚካሄድበት የቀይ ሽብር ዘመን፣ ጥርስ እየተነከሰበት ባለበት ስዓት ራሱን ለመስዋእትነት ማዘጋጀቱን አወጀ፡፡ ገሀድም አወጣ፡፡ አቋሙን በተግባር ለመተርጎም ሰላማዊ የብዕር ፍልሚያውን አጧጧፈው፡፡ ለህዝብ አይበጅም ያለውን ስርዓት በፅናት ተዋጋው፡፡ አቤ ህይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ ያየውንና ያሥተዋለውን በግልፅ ለህዝብ ከመተንፈስ ወደኋላ አላለም፡፡

ይህንንም በተለያየ መልኩ ይገልፅ ነበር ለአብነት ለመጥቀስ ያህል፡-
በአንድ ወቅት አቤ “ሰፊ ህዝብ ማለት ምን ማለት ነው?” ተብሎ ሲጠየቅ “ቢገድሉት ቢገድሉት የማያልቅ” በማለት ነበር የመለሰ፡፡
በአብዮት በዓል ቀን ሴት ልጁን ሁለት የተለያዩ ቀለማት ያላቸው የእግር ሹራብ አልብሷታል፡፡ ታዲያ ምነው አቤ? ብለው ሲጠይቁት “አለምና ሶሻሊዝም እንዲዚህ የማይገናኙ ናቸው” ብሎ ነበር የመለሰው፡፡

አቤ በህይወት ዘመኑ ከ27 በላይ መፅሀፍቶችን የፃፈ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፦
❶ከመቅፅፈት ሰራዊት ይጠንቀቅ ሰራዊት
➋የሮም አወዳደቅ
➌ቂመኛው ባህታዊ
➍የአመፅ ኑዛዜ
➎አልወለድም
➏የፍጡራን ኑሮ
❼ዘ ሳቬንጅ ገርል
❽የራሄል እንባ
❾ሰይፈ ነበልባል
❿አንድ ለእናቱ
⓫መስኮት
⓬ዕድል ነው በደል
⓭የሀሜት ሱሰኞች
⓮ጎብላንድ
⓯አጭበርባርው ጦጣ
⓰የህይወት ተርጓሚዎች
⓱የረገፉ አበቦች
⓲እሬትና ማር
⓳የደካች ወጥመድ
⓴መሬት የማነው
21ዲፌንስ
22 ፖለቲካና ፖለቲከኞች .....

በአጠቃላይ ደራሲ አቤ ጉበኛ ለሚወዳት አገሩና ለህዝቦቹ ይጠቅማል ያለውን በማድረግና በብዕሩ ጨቋኙንና ግፈኛውን የአገዛዝ ስርአት በመቃወሙ የካቲት 1/ 19 72 ተደብድቦ ተገደለ ፤ የካቲት 4 /19 72 በይስማላ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስርአተ ቀብሩ የተፈፀመ ሲሆን መታሰቢያ ሀውልቱም በዚህ ቤተ ክርስቲያን በር ላይ ይገኛል፡፡

Durbete Achefer Press -አቸፈሬው

 #እልባት አልባዋ የሆስፒታል ሽሮ ፈሰስ መንገድ ...🤔⁉️አስፋልት ለብለብና ፥ ሽሮ ፈሰስ አስፋልት የሚለቀን ግን መቼ ነው? በአማራ ክልል የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክቶች ሲጀመር እንደመስቀል...
13/08/2022

#እልባት አልባዋ የሆስፒታል ሽሮ ፈሰስ መንገድ ...🤔⁉️

አስፋልት ለብለብና ፥ ሽሮ ፈሰስ አስፋልት የሚለቀን ግን መቼ ነው?

በአማራ ክልል የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክቶች ሲጀመር እንደመስቀል ወፍ ህዝብ ብዙ ከተሰቃየና ካለቀሰ በኃላ ለጩኸት ማስተንፈሻ ፥ ከስንት አንዴ ጣል የሚደረጉ ናቸው፡፡ ሲቀጥል እነዚህ በስንት አመት አንዴ የሆነ ቦታ ላይ ሊተገበሩ የተያዙ የመንገድ ፕሮጀክቶች ደግሞ ፥ " አስፋልት ጎረድ ጎረድ ፥ አስፋልት ለብለብና ሽሮ ፈሰስ አስፋልት " የሚባሉት የአስፋልት አይነቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ከፍተኛ የህዝብ መዋለ ንዋይ ፈሶባቸው የሚሠሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ፥ ዘመን ተሻጋሪ ሀገራዊ ፋይዳ በሚሠጡበት የጥራት ደረጃ ታስቦ የሚሠሩ ሳይሆን "ፖለቲካዊ ትርጉም ተሠጥቷቸው!" ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ታቅደው የሚገነቡ በመሆናቸው ፥ መንግሥት " ከእንትና እስከእንትና የሚዘልቅ ፥ ይሄን ያህል ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት በዚህን ያህል ቢሊየን፣ ሚሊዮን ብር ተሠርቶ ተመረቀ፡፡ " የሚለውን ዜና አስተጋብቶ ባልጨረሰበት ቅፅበት ፤ መንገዶቹ "ከአገልግሎት መስጫ ክልል ወጭ!" መሆናቸውን ይጀምራሉ፡፡

የገፈቷ ቀማሽ፡ የሆነችው #መዘጋጃ ↔️ ሆስፒታል ያለው የዘመነ ህዎት ሽሮ ፈሰስ መንገድ ለተሽከርካሪዎች አስቸጋሪ ሆኖብናል" ይላሉ! የባጃጅ አሽከርካሪዎች እና ዕለት ተዕለት በዚህ መንግድ አልፈው የሚጓዙ የህዝብ ጫኝ ተሽከርካሪ የያዙ ሹፌሮች❗️

➲መንገዱ...✍️
ከዚህ በፊትም ብዙ ጥቆማዎች ይደርሳሉ!

✔️ መንገዱ ወጣ ገባ ስለሚበዛው የጋሪ እና ተሽከርካሪ ግጭት አለ፣
✔️ ተመላላሽ የሆስፒታሉ ሰራተኞች Part Time ስራ አስቸጋሪ ሆኖብናል፣
✔️ ባጃጆች በዚህ መንግድ ከተጓዝነን ተለዋዋጭ ዕቃ መግዛታችን ነው፣
✔️ ሆስፒታል ሪፈር ተብለው በባጃጅ ሲጓዙ በመንገዱ ምክኒያት ነፍሰጡር ሴቶች ልጆቻችን አጠናል፣

ወዘተ!...❗️የሚሉ አቤቱታዎች ይመጣሉ!

የከተማ አስተዳደሩ ዋናው መንግድ እስኪገነባ፡ በባለሙያ የተጠና የመንገድ ማስተካከል ቢደርግበት የሚል መልዕክት አለኝ!

💮መፍትሄው ምን ይሁን ...የሚለውን አስተያየቶችን አስቀምጡልን✍️

Cc፡
South Achefer Woreda CommunicationS
Durbete Town Prosperity

(ፎቶው፡ "በአንድ የባጃጅ አሽከርካሪ የተላከ ሲሆን ትናንት ባነሳነው ሃሳብ የዎጋ መጋነን እንዳለ እና ይሄን ያደረግነው መንገዱ የተበላሸ ሰለሆነ፡ በእየቀኑ ጋራጅ እየገባን ነው")

•••• ደመ: ነፍጠኛ•••• ‼️    የሀሁ ጌታ- የጦሩ መሪ     የሰላም አራሽ: ፍቅር ዘማሪ     ባንድ ዘምቶ - መካች - ጠላት አስጎሪ።ነፍጠኛ ማለት ዘራፉ ያለለት ቀልብ ሰራቂ እንደ ...
13/08/2022

•••• ደመ: ነፍጠኛ•••• ‼️

የሀሁ ጌታ- የጦሩ መሪ
የሰላም አራሽ: ፍቅር ዘማሪ
ባንድ ዘምቶ - መካች - ጠላት አስጎሪ።

ነፍጠኛ ማለት

ዘራፉ ያለለት ቀልብ ሰራቂ
እንደ ግራምጣ መሀል ሰንጣቂ
ሲነካ እንደ ንብ የሚናደፈዉ
አንዱን በአንዱ ላይ የሚያናጥፈዉ

ቀድሞ የነቃ: አንበሳ ገሪ
አምኖ ሚዘራ አንዱን ፈጣሪ
የራሱን ሳይፈቅድ - የማያስነካ
በሰው ቤት ድግስ - የማያቦካ

ይህ ነው : ለኔ ነፍጠኛ ማለት !
ሰፊ እንደ ዋርካ የወደደለት

ወጉን ጠባቂ ሀቅ የማይደፋ
ለማተቡ ሟች የሀገር ተስፋ
አገኝሁ ብሎ ሰዉ የማይበድል - በተረኝነት: የማይጋፋ

ይህ ነዉ ለኔ ነፋጠኛ ማለት
እሱ እየሞተ ሀገር ሚሰፋ

ነፍጠኛ ማለት

በሰላም ቀዳሽ በአዛን የሚያድር
የአገር ዘበኛ - አራሽ ወታደር
ሰላቶ ገሪ - አጫጅ በመውዜር
እንዳራስ ነብር- እትት ያለ ዘሎሚጎመር
ይኄነው ጓዴ ነፍጠኛ ማለት
ከተፍ የሚለው - የጨነቀለት
ሀገር ሲደፈር ወገን ሲበደል ሰዉ የጠፋለት !!



እኛ ኃገርን ፣ከነ ክብሩ፣ ሳያስደፍሩ ያቆዪን፣ ደመ: ነፍጠኞች እንጅ!! እጃችን እያጣመርን ጥይት ሳይተኮስ :እንደ አይጥ ጉድጓድ የምንደበቅ " በበታችነት ስሜት : የምንኳትን:ንፍጣሞች " አይደለንም!!

ካልገባህ :-
የቅርቡን ገድል ጠይቅ ህውኃት ምስክር ናት !!

ዮቶር ግዮዎናዊው ✍️🙏

ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ ( ክፍል ~2)*** አቸፈር‼️3. ከንጉሥ ጠብራስ ኃይሉ የጎጃሙ ንጉስ ተክለኃይማኖት ልጅ ናቸዉ፡፡ ንጉስ ተክለኃይማኖት ራስ በዛብህና ደጃዝማች በለዉ የሚባሉ ሌሎች ...
13/08/2022

ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ ( ክፍል ~2)
***
አቸፈር‼️

3. ከንጉሥ ጠብ

ራስ ኃይሉ የጎጃሙ ንጉስ ተክለኃይማኖት ልጅ ናቸዉ፡፡ ንጉስ ተክለኃይማኖት ራስ በዛብህና ደጃዝማች በለዉ የሚባሉ ሌሎች ልጆች ነበሯቸዉ፡፡ ንጉስ ተክለኃይማኖት በሞቱ ጊዜ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የጎጃም ግዛትን ለራስ ኃይሉ ሰጧቸዉ፡፡ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሰ ነገስት ህይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ በሚለዉ አንደኛ መፅሀፋቸዉ እንዳሰፈሩት ራስ ኃይሉ ጎጃምን እንዲገዙ ሲሾሙ ደጃዝማች ስዩም ይባሉ ነበር፡፡

በ1901 ዓ/ም የእቴጌ ጣይቱን የእህት ልጅ ወ/ሮ አሰለፈችን ሲያገቡ የራስነት ማዕረግ ተሰጣቸዉ፡፡ ስማቸዉም ስዩም መሆኑ ቀርቶ ኃይሉ ተባሉ፡፡
ደጃዝማች ከበደ ተሰማ የታሪክ ማስታወሻ በሚለዉ ስራቸዉ ላይ እንደከተቡት ልዑል ራስ ኃይሉ ልጅ እያሱን ከታሰሩበት ከፊቼ እንዲያመልጡ በተደረገዉ ሸንጎ ዉስጥ በመገኜታቸዉ ችሎት ፊት ቀርበዉ የሞት ፍርድ ከተፈረደባቸዉ በኋላ ሞቱ በእስራትና ሀብት በመዉረስ ተለዉጦ የፍርዱን መሻሻል ለልጃቸዉ ለወ/ሮ ሰብለ ወንጌል ተልኬ የነገርኳቸዉ እኔ ነኝ ይላሉ፡፡..
ራስ ኃይሉ ልጅ እያሱን ከእስር እንዲያመልጡ የተባበሯቸዉ በሁለት ምክንያት ነዉ፡፡ አንደኛ ልጃቸዉ ወ/ሮ ሰብለ ወንጌል የልጅ እያሱ ባለቤት ናቸዉ፡፡ ሁለተኛ ጣልያኖች ስልጣን እንሰጣችኋለን ብለዉ ደልለዋቸዋል፡፡ ይህን እዉነት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሰ ነገስት ህይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ላይ፡-
ራስኃይሉ በጎጃም የሚያልፉትን ኢጣልያኖች ሁሉ በመልካም አቀባበል እየተቀበሉ ይሸኟቸዉ ነበር፡፡ ከዚህም በቀርታምሚያለሁ እያሉ በደሴ ወይም በጎንደር ወደሚቀመጡት የኢጣልያ የንግድ ወኪልና ሀኪም ይመላለሱ ነበር፡፡ …ኢጣልያኖች ልጅ እያሱ ከሚጠበቁበት አምልጠዉ እንዲወጡ ያደርጉ እንደሆን እርሳቸዉ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑእርስዎም ቢሆን በጎጃምና በበጌ ምድር ባይሆን ባባትዎ ግዛት በጎጃም ይነግሳሉ፡፡ ልጅዎም እቴጌ ትባላለች… እያሉአሰምነዋቸዋል.. ሲሉ ይከሷቸዋል፡፡

በዚህ ምክንያት ራስ ኃይሉ በ1924 ዓ/ም ተነስተዉ ራስ እምሩ ኃይለሥላሴ በጎጃም ተሾሙ፡፡ ራስ እምሩ ሲሾሙ ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ ከራስ እምሩ የአቸፈር ወረዳ ግብር ሰብሳቢዎች ጋር ተጋጩ፡፡ መላከ ኃይል ይመኑ እንደነገሩኝ የራስ እምሩ ቀረጥ ሰብሳቢዎች እነ ቀኝ አዝማች መከተ ጎባዉ ቁንዝላ ዙርያ ግብግቢት ማህበረ በኩር ላይ ቀረጥ ይሰበስባሉ፡፡ ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ ደግሞ የአስሩ ደብር ወንድየ ህዝብ በነፃ እንዲኖር እንጂ እንዲቀረጥ አይፈልጉም፡፡

በዚህ ምክንያት ግጭት ዉስጥ ገብተዉ ሳለ ቀኝ አዝማች ባብል ከወንበርያ ማርያም ወደ ማዕከላቸዉ ሞከል ሲመለሱ የቀኝ አዝማች መከተ ጎባዉ አሽከሮች አስቆሟቸዉ፡፡ በልለፍ አታልፈም ግጭት ቀኝ አዝማች ባብል የቀኝ አዝማች መከተ ጎባዉን ሶስት ሰዎች አንዘራ ላይ ገደሉባቸዉ፡፡
ሰዎቻቸዉ የተገደሉባቸዉ ቀኝ አዝማች መከተ ጎባዉ ለራስ እምሩ ከሰሷቸዉ፡፡ ቀኝ አዝማች ባብል አልቀርብም በማለታቸዉ ራስ እምሩ ከንጉስ ትዕዛዝ የሚያመልጥ የለምና ባለበት ይደምሰስ የሚል ትዕዛዝ አዉጥተዉ ጦር አዘመቱባቸዉ፡፡ ቀኝ አዝማች ወደ ራስ አባይ ፣ ወደ ተራራ ዮሀንስ ፣ ወደ ደቅ ፣ ወደ ደልጊ መስቀለ ክርስቶስ(ጎጃን ጫካ) በታንኳ ሲንቀሳቀሱ ቆዩ፡፡

በመጨረሻ ራስ እምሩ ቀኝ አዝማች ባብል ደስታን የሚደመስስ ጦር በበላይ ቢረሳዉ አዝማችነት ከመናገሻቸዉ ደብረ ማርቆስ ላኩባቸዉ፡፡ መላከ ኃይል ይመኑ ቸኮል እንደነገሩኝ ራስ እምሩ ቀኝ አዝማች ባብልን ለመያዝ ምሽጋቸዉ የሞከል ጫካ መመንጠር አለበት የሚል ዉሳኔ ላይ ደረሱ፡፡ ሞከልን ለማስመንጠር ከዘማች ወታደሩ ቁጥር የሚበልጥ ምሳር ፣ መጋዝ ፣ መቆፈርያ ፣ ማጭድ ጨምረዉ ጫኑ፡፡

የጦሩ አዝማች በላይ ቢረሳዉቀኝ አዝማች ባብልን አቅም ለማዳከም በመጀመርያ ጦሩ የባብልን የእርስት ቦታዎች እንዲበላቸዉ አደረገ፡፡ መላከ ኃይል ይመኑ እንዳነሱልኝ ወንበርያ ማርያም ፣ ወንበርያ እየሱስ ፣ መተኮል ኪዳነ ምህረት ፣ አሲኗራ አቦና ትሎማ ገብርኤል ከአስሩ ደብር ወንድየ ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ የእርስት ቦታዎች ናቸዉ፡፡
የበላይ ጦር ክረምት ነበር ወደ አስሩ ደብር ወንድየ የገባዉ፡፡ በዚያ ላይ በላይ ቢረሳዉ በሚያድርበት ቤት ለመመገብ ሞሰብ ሲከፍት ከሁለት እስከ አምስት ጠገራ ብር እጁን ሞሰቡ ዉስጥ ሲሰድ ካላገኔ አይበላም፡፡ አይ አንተ ሞሰብ ጦሜን አሳደርኸኝ ብሎ ይገፋዋል፡፡ ወዲያዉኑ ማዕድ ያቀረበዉ ሰዉ ታስሮ ያድራል፡፡ በማግስቱ የግራ በሬዉን ሽጦ በቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል፡፡
ከዚህ የተነሳ ሁሉም የአስሩ ደብር ወንድየ ሰዉ በላይ ቢረሳዉ ፊት ማዕድ ሲያቀርብ ሞሰቡ ዉስጥ ከሁለት እስከ አምስት ጠገራ ብር ያስቀምጥ እንደነበር መላከ ኃይል ይመኑ ቸኮል ነግረዉኛል፡፡

ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ የበላይ ቢረሳዉ ጦር በህዝቡ ላይ በደል እያደረሰ መሆኑን ሰሙ፡፡ ጦሩ እርስታቸዉን አሲኗራን በልቶ ወደ መተኮል ኪዳነ ምህረት ሲገባ የበላይ ቢረሳዉን ማደርያ ያጠኑት ቀኝ አዝማች ባብል ንጋት ላይ ለሽንት ሲወጣ በርቀት መተዉ ጣሉት፡፡

ቀኝ አዝማች የበላይ ቢረሳዉን አስከሬን ፎረሄ እየሱስ በክብር አስቀበሩት፡፡ ለዘመቻ የተላከዉን ጦር አረጋግተዉ ወደ ደብረ ማርቆስ መለሱት፡፡ መላከ ኃይል ይመኑ እንደነገሩኝ ቀኝ አዝማች የንጉስ ትዕዛዝ ነዉ በሚል የሰራዊቱን የጦር መሳርያ አልገፈፉትም፡፡ ሞከልን ለመመንጠር የመጣዉን የስራ መሳርያ ግን ለአካባቢዉ ሰዉ አከፋፍለዉታል፡፡
ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ ከንጉስ እንደራሴዎች ጋር በተጣሉበት ጊዜ በግዛታቸዉ አስሩ ደብር ወንድየ ሰዉ አልተሾመባቸዉም፡፡ በወቅቱ ጣልያን ኢትዮጵያን ለመዉረር ዝግጅት ላይ ነበረች፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንዲህ ባለ ጊዜ በረባ ባልረባዉ ጀግኖችንማራቅ አልፈለጉም፡፡ በመሆኑም ራስ እምሩ ለቀኝ አዝማች ባብል ደስታ ይቅርታ አድርገዉ እንዲያስገቧቸዉ አስታወቋቸዉ፡፡

ራስ እምሩ ቀኝ አዝማች ባብልን ለይቅርታ አስጠሯቸዉ፡፡ ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ ከግንቦት እስከ ሀምሌ 1927 ዓ/ም ደብረ ማርቆስ ከርመዉ ከራስ እምሩ ይቅርታቸዉን ተቀብለዉ መጡ፡፡..
4. የጎጃም ጦር በሽሬ
ጣልያን መስከረም 21 ቀን 1928 ዓ/ም ረቡዕ እለት መረብን ተሻግሮ ወደ አድዋ ከተማ መንገድ ጀመረ፡፡ መስከረም 22 ቀን 1928 ዓ/ም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የክተት አዋጅ አስነገሩ፡፡ መስከረም 26 1928 ዓ/ም አድዋ በጣልያን ተያዘች፡፡ ራስ እምሩ የጎጃምን ጦር ይዘዉ በጥቅምት 1928 ዓ/ም ከደብረ ማርቆስ ተነሱ፡፡
የአማራ ጥንታዊት ጀግኖች አርበኞች ማህበር ሊቀ መንበር አቶ ዳኝነት አያሌዉ እንደነገሩኝ የጎጃም ጦር ወደ ሽሬ ግንባር የተጓዘዉ በአቸፈር ነዉ፡፡ ራስ እምሩ በዚያዉ በጥቅምት ወር 1928 ዓ/ም አቸፈር ገብትዉ አሹዳ አቦ ተቀመጡ፡፡ አሹዳ ላይ ፊት አዉራሪ መኮንን ዋሴ ተቀበሏቸዉ፡፡ ፊት አዉራሪ መኮንን ዋሴ በአምስት አመቱ የጣልያን የወረራ ዘመን የአቸፈር አርበኞች መሪ የነበሩት የቢትወደድ አያሌዉ መኮንን አባት ናቸዉ፡፡ ቢትወደድ አያሌዉ መኮንን ደግሞ የአሁኑ የአማራ ጥንታዊት ጀግኖች አርበኞች ማህበር ሊቀ መንበር የአቶ ዳኝነት አያሌዉ አባት ናቸዉ፡፡

ልዑል ራስ እምሩ ከአሹዳ አቦ ወደ ፎረሄ እየሱስ ተሻገሩ፡፡ ፎረሄ ላይ የአስሩ ደብር ወንድየ ምክትል ገዥ ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ ተቀበሏቸዉ፡፡ ራስ ፎረሄ ላይ ድንኳን ተክለዉ ሶስት ቀን ተቀምጠዋል፡፡ መላከ ኃይል ይመኑ እንደነገሩኝ ሀሙስ ገበያ የቆመችዉ በራስ ነዉ፡፡ ራስ እምሩ ከሄዱ በኋላ ህዝቡ ራስ እምሩ ድንኳን ላይ እንገናኝ እያለ ቀጠሮ መያዝ በመጀመሩ ፎረሄ ከተማ ልትመሰረት ችላለች፡፡
ልዑል ራስ እምሩ ከፎረሄ እየሱስ ተነስተዉ ወንበርያ እየሱስ ላይ ደበሩ፡፡ ወንበርያ እየሱስ የጎንደር ድንበር ላይ የሚገኝ የጎጃም አካል ነዉ፡፡ በሪሁን ከበደ እንዳሰፈሩት ወንበሪያ እየሱስ ላይ ተጠቃሎ የገባዉ የራስ ጦር 25 ሺ ነበር፡፡
በጎጃም የጦር ወግና ስርዓት የእነሴና እነብሴ እና የአቸፈር ጦር ቀዳሚዎች ናቸዉ፡፡ አቶ ዳኝነት እንዳነሱልኝ የጎጃም ጦር አሰላለፍ ላይ በአባታችሁ ቅደሙ ሲባል የአቸፈር ጦር ግራ ክንፍ ፣ የእነሴና እነብሴ ጦር በቀኝ ክንፍ ፣ ከመሀል ዋናዉ የጦሩ አዝማች ከኋላ ደጀን የዳሞት ጦር ሆነዉ ይሰለፋሉ፡፡ ሁለቱ የአቸፈርና የእነሴና እነብሴ ጦሮች ጦር ቀማሽ ይባላሉ፡፡ ምንጊዜም ጠላትን ከፊት ለፊት መጀመርያ የሚገጥሙት እነሱ ናቸዉ፡፡
ወደ ሽሬ ግንባር በዘመተዉ የጎጃም ጦር ዉስጥ የታቀፈዉ የአቸፈር ጦር በዉስጡ አራት ክፍሎች ነበሩት፡፡
1ኛ. የአሩሲ ንዑስ ወረዳ ጦር ሲሆን የተመራዉ በግራዝማች አያሌዉ መኮንን ነዉ፡፡ አሩሲ ንዑስ ወረዳ በጊዜዉ 28 ደብር አገር ነበር፡፡ ከይስማላ በታች አሹዳን አማክሎ ያለ የአቸፈር ግዛት ነዉ፡፡
2ኛ. የድንስር ደግባሳ ንዑስ ወረዳ ጦር ሲሆን የተመራዉ በተለያዩ የጎበዝ አለቆች ነዉ፡፡ አቶ ዳኝነት እንደነገሩኝ በዚህ ጦር ዉስጥ ፊት አዉራሪ የሽዋስ ፅጌና ፊት አዉራሪ ደምለዉ ጀምበሩ በመሪነት ነበሩበት፡፡ ዛሬ ድንስር ደግባሳ በሊበን ከተማ ዙሪያ ያለ የአቸፈር ግዛት ነዉ፡፡
3ኛ. የዱር ቤቴ ንዑስ ወረዳ ጦር ሲሆን የተመራዉ በቀኝ አዝማች ሙሉነህ ተሰማ ነበር፡፡ በዚህ ጦር ዉስጥ ግራዝማች አይን እንግዳ ብርሌ ነበሩ፡፡ የዱር ቤቴ ንዑስ ወረዳ በዱር ቤቴ ከተማ ዙርያ ያለዉ የአቸፈር ግዛት ነዉ፡፡
4ኛ. የአስሩ ደብር ወንድየ ንዑስ ወረዳ ጦር የተመራዉ በቀኝ አዝማች ባብል ደስታ ነበር፡፡ የራማ የጦር ግምጃ ቤትም ሲሰበር የአቸፈርን ጦር የመሩት ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ መሆናቸዉ ምናልባትም የአቸፈር ጦር ወደ ሽሬ ግንባር ሲዘምት አዝማቹ ቀኝ አዝማች ባብል ደስታ መሆናቸዉን ያመላክታል፡፡
በሪሁን ከበደ የአፄ ኃይለ ሥላሴ ታሪክ በሚለዉ መፅሀፋቸዉ ላይ ልዑል ራስ እምሩከስሜኑ ጦር አዝማች ደጃዝማች አያሌዉ ብሩ ጋር ሲገናኙ 25 ሺ ጦር ነበራቸዉ፡፡ ነገር ግን ከዚሁ ጦር ግማሽ የሚሆነዉ ከደጃዝማች ገሰሰ በለዉ ጋር ከድቶ ተመልሶባቸዋል ሲሉ አስቀምጠዋል፡፡
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሰ ነገስት ደግሞ በራስ እምሩ ስር ወደ ሽሬ ግንባር የዘመተዉ የጎጃም ጦር 10 ሺ መሆኑን ህይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ በሚለዉ አንደኛ መፅሀፋቸዉ ላይ አስፍረዋል፡፡ ከሁለቱ ምንጮች እንደምንረዳዉ ወደ ሽሬ ከዘመተዉ የጎጃም ጦር ዉስጥ 15 ሺ የሚሆነዉ ከድቶ ተመልሷል፡፡ የጎጃም ጦር ራስ እምሩን ለምን ከዳቸዉ የሚለዉን ሁለቱም አላስቀመጡትም፡፡
ደጃዝማች ከበደ ተሰማ የታሪክ ማስታወሻ በሚለዉ መፅሀፋቸዉ ላይ፡-
ራስ ኃይሉ ልጅ እያሱን ከእስር ቤት እንዲያመልጡ ለድተዋል ተብለዉ ተከሰዉ ስለነበር ፤ ነገሩ እዉነት ሆኖ በመገኘቱ በጥፋታቸዉ ተፈርዶባቸዉ የነበረዉ ሞት በእስራትና በብትን በመዉረስ ተለዉጦላቸዉ በእስር ተቀመጡ፡፡ በዚህና ሌሎች ምክንያቶች እነ ደጃዝማች ገሰሰ በለዉ ፣ እነ ፊት አዉራሪ ታምራት ተንኮሌ መርተዉት በራስ እምሩ መሪነት ዘምቶ የነበረዉ የጎጃም ጦር ከልቡ አስቦ ጠላትን ሊወጋ ያልፈለገ ነበርና ለጊዜዉ የዘመተ መስሎ ከተጓዘ በኋላ ከጦሩ ግንባር ላይ በመክዳት ተመልሷል ሲሉ ጦሩ የከዳበትን እዉነተኛ ምክንያት አስፍረዋል፡፡..
4.1. የሰለክለካ ጦርነት
ሰለክለካ ሽሬ አዉራጃ ዉስጥ የሚገኝ ቦታ ነዉ፡፡ በልዑል ራስ እምሩ ኃይለ ስላሴ የሚመራዉ የጎጃም ጦር እና በደጃዝማች አያሌዉ ብሩ የሚመራዉ የስሜን ጦር የሰፈሩበት የግዳጅ ቀመና ነበር፡፡
በሪሁን ከበደ እንዳስቀመጡት ራስ እምሩና ደጃዝማች አያሌዉ ጠለምት ወረዳ ብራ ዋስያ ከተገናኙ ጊዜ ጀምሮ የተከዜን ቁልቁለት ወርደዉ ፣ አቀበቱን ወጥተዉ ከታህሳስ እስከ የካቲት 1928 ዓ/ም ቤተ-ማርያም ላይ ሰፍረዉ ቆዩ፡፡ ከዚያም ከቤተ-ማርያም 15 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኜዉ አዲጎሎ ሰፈሩ፡፡
ከዚያ ራስ እምሩ ወደ ሰለክለካ ሄደዉ አፍጋግህ በሚገኜዉ አዲቅማልክ ዋሻ ገቡ፡፡ በሪሁን ከበደ እንደፃፉት ራስ በጣልያን ድል ሆነዉ እስኪመለሱ ድረስ የሰለክለካን ጦርነት እየተዋጉና እያዋጉ የመሩት እዚህ ምሽግ ዉስጥ ሆነዉ ነዉ፡፡
4.2. የራማ ጦርነት
ህይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ላይ እንደሰፈረዉ በተንቤንና በሽሬ በኩል የሚዋጋዉ የኢትዮጵያ ጦር በታህሳስና ጥር 1928 ዓ/ም ድል እየቀናዉ ስለሄደ አክሱምና አድዋን ከጣልያኖች እጅ ለማስለቀቅ ፣ ወደ መቀሌም ለመቃለብና ለማቋረጥ ጥቂት ቀርቶት ነበር፡፡ ራስ እምሩ በሽሬ ወረዳ በአክሱም ምስራቅና ደቡብ ሆኖ በትጋት ይጠባበቅ ነበር፡፡
በሽሬ ግንባር የነበረዉ የጣልያን ጦር ሰራዊት እስከ 25 ሺ ተገምቷል፡፡ ጣልያኖች በአክሱምና በአድዋ ለነበረዉ ጦራቸዉ ከአስመራ ቀጥሎ ተፈላጊ የሆነዉን ስንቅ ፣ ትጥቅና አልባሳት የሚያከማቹት በራማ የጦር ግምጃቤት ነበር፡፡ የምሽጉን ዋናነት የደረሱበት ራስ እምሩ አደጋ ጥለዉ የሚቆጣጠሩ ጠንካራ ሰዎችን መረጡ፡፡
በሪሁን ከበደ እንዳስቀመጡት የራማ ምሽግን ለመስበር ሻለቃ ዮሃንስ አብዱ የጦሩ ዘመቻ መሪ ፣ ከጎጃም ጦር ቀኝ አዝማች ባብል ደስታና ግራዝማች ደሴ ፣ ከሽሬዉ ደጃዝማች ገብረ መድህን ባርያዉ ጦር ዉስጥ የሀገሩ ባላባት የሆኑት ቀኝ አዝማች ኃይለ ሥላሴ አምባዉ በመንገድ መሪነት ተሳትፈዋል፡፡
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሰ ነገስት ህይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ በሚለዉ መፅሀፋቸዉ ላይ ስለ ራማ ምሽግ መሰበር የሚከተለዉን አስፈረዋል፡፡
በየካቲት 11 ቀን 1928 ዓ/ም ራስ እምሩ ከጦር ሰራዊቱ ከፍሎ ወደ መረብ ልኮ ነበር፡፡ ከአስመራና ከአድዋ መንገድ መገናኛ ላይ ሲደርሱ በራማ ምሽግ ያሉት ጣልያኖች መብራት አበሩባቸዉ፡፡ ወዲያዉ ተኩስ ጀምረዉ ነበርና አምስት ሰዎች ገደሉባቸዉ፡፡ ጥቂቶችም ቆሰሉ፡፡ ኢጣልያኖች ግን 45 ሰዉ ገደልን ፤ የቆሰሉትም ከመቶ ይበልጣሉ ብለዉ አዉርተዋል፡፡
የራስ እምሩ ወታደሮች ግን በጥንቃቄና በድፍረት ቀርበዉ አደጋ ስለጣሉባቸዉ በራማ ያሉት ኢጣልያኖች ከሞቱትና ከቆሰሉት በቀር በፍጥነት እየሸሹ አመለጡ፡፡ በዚያም የተገኘዉ የጦር መኮንኖች ልብስና ጠመንጃ ፣ ብዙ መትረየስ ከብዙ ጥይት ጋር ለብዙ ቀን የሚበቃ ስንቅ ነዉ፡፡
በማግስቱ የሞቱት የኢጣልያ ወታደሮች ሬሳ እስከ 400 ከቆጠሩ በኋላ ፤ የኢጣልያ ወታደሮች እንደገና መጥተዉ አደጋ እንዳይጥሉባቸዉ ስለሰጉ ወደ ሽሬ ተመለሱ፡፡ ራስ እምሩ ይህንን በቴሌ ግራም ስላስታወቀን በማስታወቂያ እንዲወጣ አደረግን፡፡
ሶስት ቀን በፈጀዉ የራማ ጦርነት የጣልያን ጦር ግምጃ ቤትና ጦር ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡ በሪሁን ከበደ በጦርነቱ 141 የጠላት ሹማምንትና ወታደር ሲሞት 5 ነጭ በህይወት መማረካቸዉን አስፈረዋል፡፡ አቶ ዳኝነት ደግሞ በራማ ግዳጅ 144 ሰዉ ከጠላት ወገን ሲሞት 6 መማረኩን ነግረዉኛል፡፡

ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ መጋቢት 22 1928 ዓ/ም ማይጨዉ ላይ ተሸነፉ፡፡ በዚህ ጦርነት ራሳቸዉ ንጉሱ አርሊኮን የሚባል አዉሮፕላን የሚጥል የጦር መሳርያ ይዘዉ ተዋግተዋል፡፡ ሚያዝያ 22 ቀን 1928 ዓ/ም አርብ እለት ከአዲስ አባባ ተነስተዉ ወደ እስራኤል ተጓዙ፡፡ በዚህን ጊዜ የጦር ሰራዊቱ ተበተነ፡፡ በየ ትዉልድ ሀገሩ እየተመለሰ አርበኝነት ጀመረ፡፡ ቀኝ አዝማች ባብል ደስታም ወደ አስሩ ደብር ወንድየ ተመልሰዉ ሞከል ላይ ትግላቸዉን ጀመሩ፡፡

ክፍል ~3 ይቀጥል..?
Durbete-Achefer Press

Adresse

Berlin

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Durbete Achefer Press -አቸፈሬው erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Service Kontaktieren

Nachricht an Durbete Achefer Press -አቸፈሬው senden:

Videos

Teilen


Andere Medien- und Nachrichtenunternehmen in Berlin

Alles Anzeigen