11/18/2023
ሰሞነኛ ትርክት የግሌ ምልከታ ለመግለጽ
አንድ የሆነ ሰው በመንገድ ላይ ሰክሮ እየተንገዳገደ ቢያዩት ጫት ይዞ እየቃመ እራሱንም ቢረሳ .. የምያዩት ሁሉ ሰዎች በዚህ ድርጊቱ ይስቃሉ ይዝናናሉ ...አልፎም ዘፈን ከዘፈነ ስሜታቸው ይነሳሳል ያጨበጭባሉ ይሰሙትማል ...ይዝናኑበታል
አያችሁ ሰው ለጭፈራ ለዘፈን ይዘጋጃል በዛው ልክ እውነት ስነገር ግን እውነትን የመሸከም አቅም የለውም
✍️ ይህ የሚሆነው ለምን ይመስላቸዋል ..👉ሰው ውስጥ አመፅ ..ስድብ ..ዘፈን ..የራስ ምኞት ..አለ ስለዚህ የሰው ልጅ በባህሪው እራሱን መገደብ አይፈልግም በዚሁ ምክንያት #ሕይወትን አይፈልግም .....
👉 ሕይወት የሆነው ወንጌል ሲሰበክ ወደሆነ ሀይማኖት ጎራ ይመድብሀል አልፎም ይነቅፋል የራሱ ስሜት የእደመራው ይናገራል ለስሜቱ ተገዥ ይሆናል ... እውነትን ከራሱ ጋር ማዋሃድ ይከብደዋል ...
👉 ክርስቶስ እየሱስ ከመጀመሪያው ጀምሮ ወደምድር ስመጣ አገልግሎቱን የጀመረው ...👉 እየተገፋ
👉 እየተሰደበ 👉እያባረሩት 👉 እየተናቀ 👉 የተተፋበት 👉 አየመቱት
#በመጨረሻም ደግሞ 👉እየገደሉት ነው ሕይወትን የሰጠን / የሰበከው ....
✍️ ይህ ደግሞ የወንጌል እውነታው ነው ...
✍️ በመሰረቱ ወንጌል የሆነ ቦታ / ሀገር ሲሰራ ሲሰበክ .. #ክርክር ..ቁጣ... እምቢተኝነት ...ከሌለው ወንጌል አይደለም #ወንጀል እንጂ ምክንያቱም ይሄ #ወንጌል ነው 🙏🙏🙏
👉 ወንጌል ምንም ጊዜ ክርክር ይኖረዋል ..እስከ ክርስቶስ ምፅዓት ድረስ..ይቀጥላል ....
ሰዎች በልባቸው ዉስጥ 👉በደል አለ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር አይፈልጉም ከእግዚአብሔር ጋር ሰላምን መጣል /መሆን አይፈልጉም ይከብዳቸዋል .. የቅድስና ኑሮ ዋጋው ውድ መሆኑን ያውቃሉ .. ለዚህ ዝግጁ አይደሉም በአብዛኛው ...
👉 ስለዚህ ብዙ መከልከል የሚገባው ነገር እያለ # ወንጌልን ለመከልከል ለመቃወም ይነሳሉ ...
ወዳጆቼ የየትኛውም ሀይማኖት ተከታዮች ብትሆኑ አንድ ነገር አምናለሁ እግዚአብሔር የማይፈልግ ከእናንተ እንደሌለ .. ሁሉም እግዚአብሔር ይፈልጋሉ ..
አብዝታችሁ ጌታ እየሱስን ፈልጉ .... ወንጌል ያሸንፋል ..
👉 ፀጋው ይረዳናል 🙏🙏...
በመጨረሻም ... ማለት የሚፈልገው ነገር ቢኖር .. በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚጠራው የእግዚአብሔር ስም ነው .. የእየሱስ ስም ነው ..... ሁሉ ዉሸት ቢመስል እንኳን ..የተጠራው የተተነበየዉ የእየሱስ ስም ልዮነት ያመጣል .....
በከተማው የእየሱስ ስም በስልጣን በሀይል መጠራቱ በቂ ነው ...ከበቂም በላይ ነው ....
✍️ ተባረኩልኝ እወዳችኋለሁ ..
🙏🙏🙏