Ye-Sheger Demtse - VOS

  • Home
  • Ye-Sheger Demtse - VOS

Ye-Sheger Demtse - VOS News & Media Website

አቤል ብርሃኑ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የደረሰበትን መጉላላት በዚህ መልኩ አቅርቧል።ከወር በፊት እኔ ላይ የተፈፀመው ይህ ነው። ወደ ዋሽንግተን በረራ ነበረኝ ትኬቴ ቢዝነስ ክላስ ነው ተጠባባ...
21/07/2024

አቤል ብርሃኑ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የደረሰበትን መጉላላት በዚህ መልኩ አቅርቧል።

ከወር በፊት እኔ ላይ የተፈፀመው ይህ ነው። ወደ ዋሽንግተን በረራ ነበረኝ ትኬቴ ቢዝነስ ክላስ ነው ተጠባባቂ መንገደኛም አልነበርኩም ። እንዳውም የአየር መንገዱ የስታር አሊያንስ የጎልድ አባል ጭምር ነበርኩ ቼክ ኢን አድርጌ ቦርዲንግ ፓሴን ተቀብዬ ኢሚግሬሽን አልፌ ቢዝነስ ላውንች ቆይቼ በረራዬ ሲደርስ አውሮፕላኑ ውስጥ ልገባ ስል እንደማልችል ነገረቺኝ ለምን ለሚለው ጥያቄ የሰጠቺኝ ምላሽ ባንተ ቦታ ሰው ተቀምጧል ነበር ምላሿ እንዴ የምን ሰው ክው ነው ያልኩት በረራው ሙሉ ነው የገረመኝ ስርአት የጎደላት ሰራተኛ በመሆኗ "የማውቅልህ ነገር የለም" ብላ ቦርዲንግ ፓሴን ወረወረች ። እየተከራከርኩ የሚሰማኝ አጥቼ አውሮፕላኑ ዘግቶ ሄደ።

ልብ በሉ እኔ ተጠባባቂ መንገደኛ አይደለሁም ትኬቴን ይዤ የቀረብኩ የቢዝነስ ክላስ መንገደኛ የጎልድ አባልም ጭምር ነኝ ። አየር መንገዱ የፈፀመውን በደል በሰራተኞቹ የደረሰብኝን እንግልት ለመናገር አንድም የሚሰማኝ ሀላፊ አልነበረም ጭራሽ ሀላፊ የተባለው ይሳለቅብኛል (ከአንድ ወጣት በቀር )። እጅግ በጣም ተጉላልቼ በብራሰልስ ትራንዚት አድርጌ ጎዞዬን ቀጠልኩ።

ይህ ከብዙው በጥቂቱ ነው። ! ዛሬም ኢቺን እንኳን ሚዲያ ላይ መፃፍ ያሰብኩት አየር መንገዱ ለአንዲት የውጪ ተጠባባቂ መንገደኛ ሰጠ የተባለውን ምላሽ ስሰማ ነው።

በአንዳንድ ሰራተኞች ምክንያት ግዙፉ አየር መንገዳችን ችግር እንዳይገጥመው ፈትሹ ሰራተኞቻችሁን ፈትሹ !!

"ዶክተር አሸብር ሙያን ለሙያተኛ ትተው ከስፖርቱ ዞር ይበሉ! " ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ   | ጀግናው አትሌት  ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከሃትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ለኢ...
29/06/2024

"ዶክተር አሸብር ሙያን ለሙያተኛ ትተው ከስፖርቱ ዞር ይበሉ! " ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ

| ጀግናው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከሃትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ለኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ከስፖርቱ ገለል እንዲሉ መክሯል ።

ኃይሌ ፣ “እኔ ዶክተር ልሁን ብል ሠው ይስቅብኛል፤ የተከበሩ ዶክተር አሸብር ስፖርቱንና የኢትዮጵያን ህዝብ የሚወዱ ከሆነ ሙያን ለሙያተኛ ትተው ከስፖርቱ ዞር እንዲሉ እመክራለሁ” ሲል ምክር አዘል መልእክት አስተላልፏል ።

ፕሬዝዳንት ሩቶ ከፍተኛ አመጽ የታየበት ተቃውሞ ከገጠማቸው በኋላ የአገሪቱን ጦር አሰማሩየኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ማክሰኞ በመዲናዋ ናይሮቢ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ተቃዋሚዎች ከፖ...
26/06/2024

ፕሬዝዳንት ሩቶ ከፍተኛ አመጽ የታየበት ተቃውሞ ከገጠማቸው በኋላ የአገሪቱን ጦር አሰማሩ

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ማክሰኞ በመዲናዋ ናይሮቢ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ተቃዋሚዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ መሰል አመጽ እንዳይደገም ሁሉንም ሕግ አስከባሪ አሰማራለሁ አሉ።

ማክሰኞ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም. የኬንያ ፓርላማ ያጸደቀውን አዲስ የታክስ ሕግ ለመቃወም አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች የአገሪቱን ፓርላማ ወረው በእሳት ያቃጠሉ ሲሆን፣ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ቢያንስ አምስት ሰዎች ተገድለዋል።

ፖሊስ በከፍተኛ ቁጥር የወጡ ወጣቶችን ለመበተን ጥይት ተኩሶ በርካታ ሰዎችን ማቁሰሉ ተገልጿል።

ቀኑን ሙሉ ከዋለው ተቃውሞ በኋላ ማክሰኞ ምሽት የአገሪቱ ፀጥታ ኃይሎች በመዲናዋ በሚገኙ የተለያዩ ስፍራዎች እየተንቀሳቀሱ የሰልፉ መሪ እና አስተባባሪ ናቸው የተባሉ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ስለማዋለቸው ተሰምቷል።

ፕሬዝዳንት ሩቶ ማክሰኞ ምሽት 3 ሰዓት ላይ ከቤተ-መንግሥታቸው በሰጡት መግለጫ “የተደራጁ ሕገ-ወጥ ቡድኖች በሕግ አክባሪ ኬንያውያን ተከልለው የአገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አደጋ ላይ ጥለዋል” ብለዋል።

“ኬንያ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ በዴሞክራሲ ሥርዓቷ፣ በሕግ የበላይነት እና ሕገ-መንግሥታዊ ተቋማቷ ላይ ጥቃት ደርሷል” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የዚህ ዓይነቱ ክስተት “በብሔራዊ ደኅንነታችን ላይ ለሚደርሱ ከባድ አደጋዎች ምላሽ የምንሰጥበትን ሁኔታ የቀየረ ነው” ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ሩቶ “የትኛውንም ዋጋ ቢያስከፍል” መሰል አመጽ ዳግም እንዳይፈጠር የተቻለንን ፀጥታ አስከባሪ አሰማርተናል ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህን ይበሉ እንጂ ኬንያውያኑ ነገ ሐሙስ ሰኔ 20/2016 ዓ.ም. ሌላ የተቃውሞ ሰልፍ ከማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሐሳባቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

ማክሰኞ በአገሪቱ ፓርላማ የጸደቀው አዲሱ የቀረጥ ሕግ ኑሮ ያስወድድብናል ሲሉ የቆዩት ኬንያውያን ወጣቶች በኢንተርኔት አማካይነት ተሰባስበው ከአገሪቱ ፓርላማ ፊት ለፊት የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያስሙ ቆይተዋል።

መንግሥት በበኩለ ታክስ በመጨመር ተጨማሪ ብድር ከሌሎች ምንጮች መውሰድ ሳያስፈልገው ለአስፈላጊ የመንግሥት ወጪዎች እና አገልግሎቶች ገቢ ለማግኘት ዓላማ አድርጎ መሆኑን ገልጿል።

ዊልያም ሩቶ ሥልጣን ከተቆጣጠሩ ጀምሮ በርካታ አዳዲስ እና በሕዝቡ ተቀባይነት ያላገኙ ግብሮችን አስተዋውቀዋል።

በዚህም በኬንያውያን ዘንድ ‘ዘኪዮስ’ የሚል ስያሜን አግኝተዋል። በክርስትና አማኞች ዘንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካለ ዘኪዮስ ከሚባል ቀራጭ ጋር በማመሳሰል ነው።

ፕሬዝዳንቱ ግን አገሪቱን ካለችበት የ80 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ለማውጣት እና ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አዳዲስ ግብሮችን ተግባራዊ ማድረግ የግድ ነው ይላሉ።

ማክሰኞ ዕለት የተከሰተውን እና በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ኬንያውያን፣ የተለያዩ ተቋማት እና አገራት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ከዊሊያም ሩቶ በፊት ለሁለት የሥልጣን ዘመን ኬንያን የመሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መረጋጋት እና ሥነ ሥርዓት በአገሪቱ እንዲሰፍን ጥሪ አቅርበዋል።

“ሕዝብን ማድመጥ ምርጫ ሳይሆን በሕገ መንግሥታችን መርሆች የተደነገገው ግዴታ ነው” ያሉት የቀድሞ ፕሬዝዳንት መንግሥት የሕዝቡን ያድምጥ ሲሉ አሳስበዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፖሊስ በተቃዋሚዎች ላይ ከልክ ያለፈ ኃይል እንዳይጠቀም እንዲሁም ተቃዋሚዎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ ጠይቀዋል።

መቀመጫቸውን በኬንያ ያደረጉ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮች ትናንት ማክሰኞ “በኬንያ የተመለከትነው ያልተጠበቀ እና አስደንጋጭ ክስተት ነው” ብለዋል።

የብሪታኒያ፣ ካናዳ፣ ዴንማርክ፣ ጀርመን፣ አሜሪካ እና ኔዘርላንድስ ዲፕሎማቶች ተቃዋሚዎችን ለመቆጣጠር የተወሰደው እርምጃ አስደንጋጭ ነው ብለዋል።

“በተለይ ከኬንያ ፓርላማ ውጪ የተመለከትነው ትዕይንት አስደንግጦናል” ካሉ በኋላ፤ “ሁሉም አካላት የሕግ የበላይነትን የማክበር እና የማስክበር ኃላፊነት አለባቸው” ብለዋል።

ዘገባው የቢቢሲ ነው።

21/06/2024
ለካ እንደዚም አለ ወገን ትላንትና ማታ ነው Apr 28 2024 በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 2:20 ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት የደረስኩት business class  ካውንተር ላይ አንድ...
29/04/2024

ለካ እንደዚም አለ ወገን ትላንትና ማታ ነው Apr 28 2024 በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 2:20 ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት የደረስኩት business class ካውንተር ላይ አንድ ቀጭን የቀይ ዳማ ወጣት የኢትዮጵያ ፓስፖርቴን ሰጠሁት

* የት ነው የምትሄጂው አለኝ ?

* ደብሊን አልኩት

* በየት በኩል አለኝ በአየርላንድ ኤርፖርት
በስቶኮም በኩል አልኩት

ሲስተም ቼክ አላረገ ፓስፖርቴን አላየ መሄድ አትችይም ትራንዚት አይፈቀድም አለኝ እኔም ሁሌም
የምመላለስበት መንገድ ነው እኮ ወንድሜ አውሮፖ ውስጥ እስፔሻል ቪዛ የሚያስፈልገው ለለንደን ብቻ ነው አልኩት

በቃ ዞር በይ ሌላ ከስተመር ላስተናግድበት አለኝ እኔስ አልኩት የማውቀው ነገር የለም ሴኩሪቲ ከመጥራቴ በፊት አትረብሺኝ ዞር በይልኝ አለኝ

እሺ ጥራ በቃ ዞር አልልም አልኩት አንድ ኢሚግሬሽን የሚሰራ ወጣት በአጋጣሚ እያለፈ አይቶ እባክህን እየረበሸችኝ ነው ዞር አድርግልኝ አለው ወጣቱም ምንም ሳይናገር ጥሎ ሄደ እኔም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ ሄጄ ሱፐርቫይዘር ካለ አናግሩኝ ተቸግሬአለው አልኳቸው

አንድ የአየር መንገዱ ሰራተኛም ምን ልርዳዎት አረፍ ይበሉ አለኝ የሆነውን ነገርኩት ነይ እንሂድ ብሎ ወደ ካውንተሩ ሄድን

ምንድ ነው ይችላሉ እኮ መብረር ለምን አስቆምካቸው ብሎ ጠየቀው እራሱ ሲስተሙ ውስጥ ገብቶ ካየ በኃላ እንቢ ያለው ወጣት እንዲሰራ አዘዘው ወጣቱም ቼክኢን አደረገኝ ቆም ብዬ ብዙ አሰብኩ

የኢትዮጵያ ፓስፖርት በመያዜ ብቻ ሲስተም ቼክ ሳያደርግ አትበሪም በማለቱ መርህ አልባ ድርጊት በመፈፀሙ በጣም አዝኛለው

አፍሬያለሁም እኔ አንድ ቀንም ዜግነት ባለመለወጤ ፀፅቶኝ አያውቅም ሀገሬን ወዳታለው እንደዚ ያሉ ብራንዳችንን ክብራችንን መጠሪያችን የሆነውን ብቸኛው አየር መንገዳችን ስሙ እንዲጎድፍ ሰዎች እንዲማረሩበት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚሰሩ ግለሰቦች መኖራቸውን አውቄአለው

እኔ በሌላ አየር መንገድ business class ከምጏዝ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ቢሆን ብጏዝ እመርጣለው ብዙ ጥሩ ሰዎች ያሉበት ቤት ነው ግን ጥቂቶቹ ስርአት አልበኞች

የአየር መንገዱን መልካም ስም እያስጎደፉ ስለሆነ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል እላለው ሼር አድርጉ ለሚመለከተው አካል ይድረስ ውድ ኢትዮጵያን ተስፋ አትቁረጡ እስከ ጥግ ሂዱ መፍትሄ እስክታገኙ ሁላችንም የሀገራችን አንባሳደሮች ነን 🇪🇹

Via በረከት ገበሬዋ

😎😎😎

🌴🌴🌴

«ምንም አታመጡም አይነት አካሄድ ከፍላችሁ የማትጨርሱት እዳ ውስጥ ይዞችሁ ይገባል» ስትል አርቲስት ቤዛዊት መስፍን አስጠነቀቀች::"እስር ቤት ለሴት ልጅ እጅግ ከባድ ነው" በማለት አስተያየቷ...
28/04/2024

«ምንም አታመጡም አይነት አካሄድ ከፍላችሁ የማትጨርሱት እዳ ውስጥ ይዞችሁ ይገባል» ስትል አርቲስት ቤዛዊት መስፍን አስጠነቀቀች::

"እስር ቤት ለሴት ልጅ እጅግ ከባድ ነው" በማለት አስተያየቷን የጀመረችው ተዋናይት ቤዛዊት መስፍን ተዋናይት አዲስአለም ጌታነህ ጨምሮ ሌሎች ጎደኞቼ በገዛ ፍቃዳቸው እና ገንዘባቸው በየ ክፍለሀገሩ በመሄድ ወግ እና ልማዳቸውን ባህላቸውን የሚያስተዋውቁ ምንም ውስጥ የሌሉ ሴቶች ናቸው፣ ከዛሬ ነገ ይፈታሉ ብለን ብናስብም ይሄው እስከዛሬ አልተፈቱም እና እባካችሁ ሰው በሀገሩ በነፃነት እንዲኖር ፍቀዱለት በገዛ ሀገራችን እና ርስታችን አታሸማቁን በሀገራችን ተስፋ እንድንቆርጥ እንድንሰደድ አታድርጉን! ፍቱልን እህቶቻችን ሰትል አርቲስት ጓደኞቿ እንዲፈቱ በማህበራዊ ገጿ ላይ አስተላልፋለች::

እስከ ዛሬ በእህቶቼ ዙሪያ ምንም ያላልኩት ነገሮች እንዳይካበድባቸው በማሰብ ነው በማለት ዝምታዋን መስበሯን ገልጻለች።

«ህዝቡን ብታከብሩት እና ብትፈሩት ይሻላል ይሄ ምንም አታመጡም አይነት አካሄድ ከፍላችሁ የማትጨርሱት እዳ ውስጥ ይዞችሁ ይገባል» ስትል ቤዛዊት መስፍን ከዱባይ አስጠንቅቃለች።

Best pictureToday best photo
07/04/2024

Best picture

Today best photo








መንጌና ልጁ====
24/03/2024

መንጌና ልጁ
====

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ።ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግ...
06/02/2024

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን አስታውቃለች።

ቤተክርስቲያን ፤ ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና ሰጥተው እንደነበር አስታውሳለች።

ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው የሚገኙ መሆኑን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በአየር መንገድ አቀባበል ለማድረግ በተገኘበት ወቅት ማረጋገጡን ቤተክርስቲያን ገልጻለች።

" ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት የሚመለከተው የመንግስት አካል የቤተክርስቲያናችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አገር እንዲገቡ እንዲፈቀድላቸው እንዲደርግ " ስትል ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን አስተላልፋለች።

ጋዜጠኘ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የራሱን ህይወት እንዳጠፋ  ተነገረ።ባሳለፍነው ሳምንት በሞት ያጣነው ተወዳጀ  ጋዜጠኘ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ራሱን በገመድ አንቆ ህይወቱን እንዳጠፋ ኢትዮጲካሊ...
29/01/2024

ጋዜጠኘ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የራሱን ህይወት እንዳጠፋ ተነገረ።

ባሳለፍነው ሳምንት በሞት ያጣነው ተወዳጀ ጋዜጠኘ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ራሱን በገመድ አንቆ ህይወቱን እንዳጠፋ ኢትዮጲካሊንክ የተሰኘ የሬዲዮ ኘሮግራም አሳወቀ።

የዛሬ 6 ወር ገደማ ስኳር ህመም እንዳለበት ያወቀው ገነነ በተያያዥ በሽታ አንድ እግሩን ይቆረጣል ከዛ በኋላ ህይወት እንዳስጠላውና ሲንቀሳቀስ ባለቤቱ እሷ መኪና እየነዳች እንደምታደርሰው ኢትዮጲካሊንክ አሳውቆ። አንድ ቀን ግን ባለቤቱን ግዬን ሆቴል ስራ አለብኝ አድርሺኝ ብሏት አድርሳው ወደ ቤት ብትመለስም እሱ ግን ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ ስልኩን በማጥፋት ሆቴል ይዞ ተደብቆ ትንሽ ቀናትን ቆይቷል::

ከዛ ግን ለጋዜጠኛ ሰይድ ኪያር ደውሎ ያለበትን ቦታ ነግሮት ሰይድም ወዲያው መጥቶ ስኳሩ በጣም እንደወረደና ባለቤቱ ጋር ደውሎ ስኳሩ በጣም ወርዷል ሲላት ባለቤቱም " በቃ ሚሪንዳ " ይጠጣበት ብላ እንደመለሰች ከዛ ግን ሄዳ እንኳን እንዳላየችው ታውቋል::

ብቻውን እዛ ክፍል ውስጥ የከረመው ይህ ታላቅ ሰው ገነነ ምን እንደሆነ ለምን እንደዚህ ውሳኔ እንደወሰነ ባይታወቅም ራሱን በገመድ አንቆ እንደገለ በምርምራ ታውቋል።

በጣም የሚያሳዝነው ግን ባለቤቱ ሞቱን ስትሰማ ወደ አረፈበት ሆቴል በመሄድ ለፖሊስ መናገር ና ማሳወቅ ሲገባት ሬሳውን ወደ ቤቷ አምጥታ ስታለቅስ የጎረቤት ሰዎች ለፖሊስ አመልክቺ እንጂ ብለው ሲጠይቋት ለፖሊስ ያመለከተች ሲሆን ፖሊስም እንዴትት የሞተ ሰውን አስክሬን ለፖሊስ መናገር ና ማሳወቅ ሲጋባሽ አስክሬኑን ይዘሽ ወደ መኖሪያ ቤትሽ ትሄጃለሽ ብሎ አንድ ቀን እስር ቤት አውሏት እንደነበር የሬዲዬ ፕሮግራሙ ዘገባ አመልክቷል።

«ከታቦቱ መውጣት እና የሊቃውንቱ ዝማሬ ውጪ የጥምቀት በዓል የክርስቲያናዊ ለዛው ጠፍቷል» ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ የጥምቀት በዓል ራሳችንን ለማስደሰት የአመፃ ስራ የምንሰራበት እየሆነ ነው። ...
21/01/2024

«ከታቦቱ መውጣት እና የሊቃውንቱ ዝማሬ ውጪ የጥምቀት በዓል የክርስቲያናዊ ለዛው ጠፍቷል» ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

የጥምቀት በዓል ራሳችንን ለማስደሰት የአመፃ ስራ የምንሰራበት እየሆነ ነው። ጥምቀት እስካሁን ያልጠፋው ከታቦቱ መውጣት እና የሊቃውንቱ ዝማሬ ውጪ የጥምቀት በዓል የክርስቲያናዊ ለዛው ጠፍቷል። ሲሉ ዲያቆን መምህር ዮርዳኖስ አበበ ተናገሩ

አባቶቻችን "ለእግዚዓብሔር አስመስለህ ለአጋንንት አትሰዋ" ይላሉ ብዙዎቻችን ለእግዚዓብሔር አስመስለን መስዋዕት የምናቀርበው ለአጋንንት ነው።

ለምሳሌ የጌታ በዓል የጌታ ከሆነ መከበር ያለበት ጌታ እንደሚፈልገው ነው። ስከሩ፣ አዲስ ልብስ ልበሱ፣ ሎሚ ወርውሩ የሚል ህግ የለም። ኢትዮጵያዊያን የሚተጫጩት ድሮም በጥምቀት እለት ነው የሚሉ አሉ ጥምቀት መተጫጫ አይደለም። የጌታ መወለድ ዋጋ ብዙዎቻችን ገና አልገባንም። በግልፅ መነጋገር አለብን የጥምቀት ቀን ብዙ የሚዘል አለ የሚዘለው ለእግዚዓብሔር አይደለም ሲሉ ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ያላቸውን ቅሬታ ተናግሯል።

ትውልዱን ካላስተማርነው የጥምቀት በዓል የእግዚዓብሔር መሆን ቀርቶ አሁን ከግማሽ በላይ ሄዷል የሌላ በዓል ነው የሚሆነው። ይህን ሁሉ የምናገረው ትውልዱን እንድናስተምረው ነው ይህ የማይሆን ከሆነ በበዓሉ የምናገኘው በረከት የለም መቅሰፍት ነው።

የጥምቀት በዓል ለማድመቅ ውጪ ካሉ ሰዎች ብር አሰባስብልን ብለው ጠየቁኝ! ስንት ወገን ተርቦ ሜዳ ወድቆ የጥምቀት በዓል ለማድመቅ! በዲኮሬሽን እግዚዓብሔር ደስ አይለውም፣ ጥምቀትን እንደ ድሮ በስርዓተ ቤተክርስቲያን እናክብር ከእግዚዓብሔር አውጥተን የጠላት መጫወቻ አድርገነዋል የእኔ ስራ ማስተማር ነው ከዛ ውጪ ምንም ማድረግ አልችልም ሲሉ ዲያቆን ዮርዳኖስ መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

28/11/2023

"ምን ይውረድ"

24/11/2023

አብይ ለኢትዮጵያ አንገቱን አይደለም የአንገቱን ሐብል አይሰጥም። ለማንኛውም ፈጣሪ ይጠብቅህ ።

21/11/2023

ዳኒ ሲጨንቃት እውነቱን ተናገረች😆

ኢትዮጵያዊነት💪🏾💪🏾
17/11/2023

ኢትዮጵያዊነት💪🏾💪🏾

ኣማራ ፋኖ💪🏾
01/11/2023

ኣማራ ፋኖ💪🏾

"እየጨፈርን  #የናድነውን ቤት እያለቀስን አንሠራውም!""ሁላችንም ዘር አለን፡፡ ዘሩ ግን እኛ  #አይደለንም! እኛ  #ሰዎች ነን፡፡ ሰውነት  #ከመፈጠር እንጂ  #ከመወለድ አይጀምርምና ፈጣሪ...
25/09/2023

"እየጨፈርን #የናድነውን ቤት እያለቀስን አንሠራውም!"

"ሁላችንም ዘር አለን፡፡ ዘሩ ግን እኛ #አይደለንም! እኛ #ሰዎች ነን፡፡ ሰውነት #ከመፈጠር እንጂ #ከመወለድ አይጀምርምና ፈጣሪ ዘራችንን ኢትዮጲያ በምትባል ምድር ላይ ዘራው፡፡ ሲዘራው ኢትዮጲያ ማለት ሰዎች መሆኗን አወቅን፡፡ መነጣጠል እስከማንችል ተዋሃድን፡፡ ትናንት የሆነ የሰው ዲስኩር አንዳችንን ካንዳችን ካልለየሁ እያለ ሥያሜ አበጀልን፡፡ ፈጣሪን ለማረም ይመስል እኛም ሆሆሆ ብለን ተቀበልን፡፡ በሕንድ 2032 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ በቻይና 499 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ ምነው እኛ (ሰማኒያዋን) መሸከም አቃተን?ተራ በተራ መግዛታችንን ለበላይነት ተጠቀምንበት? ማንም ከማንም ጋር የሰውነት ጥል ሊኖረው አይችልም የዕውቀት ጥል እንጂ፡፡ ገና ስንወለድ ዘር ምን ይሁን ቋንቋ ምን ይሁን የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡ #የዕውቀት ጥል ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ እንጂ በጦር ሜዳ አይፈታም፡፡ ምክንያቱም #ይቅርታ እንጂ #በቀል ታሪክን አያርምምና፡፡ ቋንቋ የሚባልን ነገር ከመካከላችን አውጥተን ማሰብ ብንጀምር ዘረኝነት ሃሳብ ላይ እንጂ ደም ላይ እንደሌለ እንረዳለን፡፡ #እየጨፈርን የናድነውን ቤት #እያለቀስን አንሠራውም፡፡ ሁልጊዜ ጥፋት ካደረስን በኀላ እንዳጠፋን ምንረዳ ከሆነ ዞሮ መልሶ አለማወቅ ይሆንብናል፡፡ በመቻቻል ሳይሆን በፍቅር እንኑር መቻቻል አንድ ቀን ያሰለቸናል፡፡ ታገስኩህ ቻልኩህን ያመጣል፡፡ ፍቅር ግን እስከዖሜጋ ይሸከማል፡፡ ከሰውነት በላይ ምን ማንነት ኖሮ፤ የሁሉም መገኛ ያው አዳም ነው ዞሮ፤ የማይሻር ሽረን አይሆኑሽ ሆነናል፤ የማይድን ስናክም የማይሞት ገለናል፡፡አትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለሁላችንም በቂ ናት! እንወዳድ በፍቅር እንኑር፡፡"

ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ

በኬንያ የኑሮ ዉድነት ያስነሳዉ ተቃዉሞ አሳሳቢ ሆንዋልበኬንያ የተነሳው ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ። የተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ለመጪው ሰኞ አራተኛውን ሀገር አቀፍ የተ...
31/03/2023

በኬንያ የኑሮ ዉድነት ያስነሳዉ ተቃዉሞ አሳሳቢ ሆንዋል

በኬንያ የተነሳው ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ። የተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ለመጪው ሰኞ አራተኛውን ሀገር አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርተዋል። ወደ መዲና ናይሮኒ ያቀኑት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ልዩ መልዕክተኛ ሴናተር ክሪስ ኩንስ ውጥረቱን ለማብረድ ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱን የኬንያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኩንስ የሀገሪቱን ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ሺልዱዋ እና የተቃዋሚ መሪዉን ራይላ ኦዲንጋን አነጋግረዋል። የኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት መንግስት እንደተናገሩት የተቃውሞ ሰልፉን ከሚያስተባብሩት ከራይላ ኦዲንጋ ጋር "ስልጣንን በማካፈል" ዙሪያ ውይይት አይደረግም።
ከሳምንታቶች በፊት በኬንያ የሚታየዉን የኑሮ ዉድነት በመቃወም በተጠራ ሰልፍ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸዉ ይታወቃል ። ፖሊስ ሰልፉን በአስለቃሽ ጢስ እና ዉኃ በመርጨት በትኗል፤ ከፍተኛ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንም አስሯል። በታዋቂዉ ተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ የተመራዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ባለፈዉ መስከረም ወር ስልጣን ከያዙ ጀምሮ በሃገሪቱ ጣራ ላይ የደረሰዉን የኑሮ ዉድነት ማስተካከል አልቻሉም ሲል የተጀመረ ነዉ። በሃገሪቱ በተከሰተዉ ድርቅ እና በመሠረታዊ ነገሮች ላይ በሚታየዉ የዋጋ መናር ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኬንያዉያን በረሃብ እየተሰቃዩ ነው። ሃገሪቱ ላይ ተቃዉሞን የጠሩት የኬንያ የተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ በሃገሪቱ «ጣራ የነካዉን » የኑሮ ዉድነት፤ «በተሰረቀ የምርጫ ዉጤት» ስልጣን ላይ የሚገኙትን ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ማስተካከል አልቻሉም ሲሉ ዜጎች ተቃዉሞዋቸዉን እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

24/03/2023
አስጨርሱኝ   (በእውቀቱ ስዩም)አብቹ ወደ ስልጣን በመጣ ሰሞን  ለቀቅ ያረግሁትን   ሙገሳ ብጤ፥  ከማህደሬ ፈልፍላችሁ  በማውጣት “ ሙድ “ ለመያዝ የምትሞክሩ ሰዎች፥  ዲያብሎስ  በብርድ ...
19/03/2023

አስጨርሱኝ
(በእውቀቱ ስዩም)

አብቹ ወደ ስልጣን በመጣ ሰሞን ለቀቅ ያረግሁትን ሙገሳ ብጤ፥ ከማህደሬ ፈልፍላችሁ በማውጣት “ ሙድ “ ለመያዝ የምትሞክሩ ሰዎች፥ ዲያብሎስ በብርድ ቀን፥ ቆለጣችሁን በጋመ ወረንጦ ይያዝላችሁ ከማለት ውጭ ክፉ አይወጣኝም!

በጊዜው ከነበረው የማሽቃበጥ ፏፏቴ አንጻር ሲታይኮ የኔ ግሳጼ ነው ማለት ይቻላል: በጊዜው ማሽቃበጡን ከፊት ሆነው ሲመሩት ከነበሩት አርቲስቶች አንዱ በቅርቡ “ ይሄ ስሙን ልጠራው የማልፈልገው ሰውየ” ሲል ሰማሁት፤ ለሽንገላ የፈጠነ ለርግማንም የሚቀድመው የለም፤ እኛ ግን ዛሬም በሚሆነው አዝነን፥ ሂስ ስናቀርብ “ ክቡር ጠቅላይ ምኒስትር “ የሚል ማእረጋቸውን አንነሳቸውም ::

ብቻ የሆነውን ሁሉ ሳስበው የልጅነቴን አንድ ገጠመኝ ያስታውሰኛል :: በብላቴናነት ዘመኔ ፥ የሰፈራችን ኗሪዎች ፥ የገና በአል መዋጮ ሰብስበው ፥ ፍሪዳ ጥለው ይቀራመታሉ፤ የተረፈው ተደግሶ ከተበላ ከተጠጣ በሁዋላ፥ ታዳሚዎች ስእለት ማቅረብ ይጀምራሉ::

መጀመርያ የበውቄ አባት ጋሽ ስዩም ተነሱ: :

“በሚቀጥለው አመት ቢያደርሰን ቢያደርሳችሁ ከፍሪዳው በፊት እምንቃመሳት አንድ ጠቦት ፍየል አስገባለሁ”

እልልልል!

ጨብጨብ

ቀጥለው የመዋእለ ህጻናት መምህርት ወይዘሮ እታገኝ ተነሱና “በሚቀጥለው አመት ቢያደርሰን ቢያደርሳችሁ፥ አንድ ጥዋ የስጋ ማባያ ድቁስ አቀርባለሁ”

አነስ ያለ ፥ የተድበሰበሰ ጭብጨባ ተሰማ::

በማስከተል፥ የሰፈሩ ጋሪ ነጂ ጋሽ በላይ ብድግ አለና ለሁለት ደቂቃ ሳይናገር ዝም ብሎ ተገተረ፤ ከዝያ ከእንቅልፉ እንደመባነን አለና” በሚቀጥለው አመት ቢያደርሰን ቢያደርሳችሁ …ደስ ይለኛል “ አለና ተቀመጠ::

እድምተኛው አጉረመረመ::

መጨረሻ ወይዘሮ ማሚት ተነሱ፤ ሻሻቸውን ነጠላቸውን አስተካከሉ፤ ጠላ የረጠበውን ያፋቸውን ጠርዝ ጠራረጉ ፤

“ በሚቀጥለው አመት ፤ ቢያደርሰን ቢያደርሳችሁ፥ አንድ ጋን ጠጅ ...”

እድርተኛው አላስጨረሳቸውም ፤ እስከ ሰላሌ የሚሰማ ጭብጨባ ወረደ! ደን ጠባቂው አቶ ቢረሳውማ ነሽጦት ብድግ አለና ፥ ከ”ነጻ ርምጃ ወዲህ “ ተተኩሶ የማያውቀውን አብራራው ጠመንጃውን ወደ ሰማይ ደግኖ ሁለት ጥይት ለቀቀ! በጭብጨባው እና በተኩሱ መሀል ወይዘሮ ማሚት “ አስጨርሱኛ ! “ ሲሉ እሰማለሁ::

ጭብጨባው በረድ ሲል ፥ የባሩዱ መአዛ ገልል ሲል ፥ ማሚት እንዲህ አሉ፤

“ በሚቀጥለው አመት ቢያደርሰን ቢያደርሳችሁ አንድ ጋን ጠጅ የሚያስንቅ ፤ ማንቆርቆርያ ሙሉ ጠላ አቀርባለሁ”: :

 #ከአቶ ልደቱ አያሌው የቀረበ ጥሪ‼ ↪ዶ/ር ለማ መገርሳን፣ አቶ ደመቀ መኮንንን፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የመሳሰላችሁና “በቲም ለማ” ስም በለውጥ ሐዋሪያነት በህዝብ ስትሞገሱ የነበራችሁ ወ...
08/03/2023

#ከአቶ ልደቱ አያሌው የቀረበ ጥሪ‼

↪ዶ/ር ለማ መገርሳን፣ አቶ ደመቀ መኮንንን፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የመሳሰላችሁና “በቲም ለማ” ስም በለውጥ ሐዋሪያነት በህዝብ ስትሞገሱ የነበራችሁ ወገኖች - “ህይወታችንን ቁማር አስይዘን አመጣነው” ያላችሁት ለውጥ ከሽፎ ሀገሪቱ እናንተው ለስልጣን ባበቃችሁት መሪ እንዲህ ለአደጋ ስትጋለጥ የእናንተ ሚና በዝምታ አድፍጦ መኖር፣ ወይም የአገዛዙ ታዛዥና አገልጋይ መሆን ነበረበትን?”

↪አቶ አዲሱ ለገሰን፣ አቶ ተፈራ ዋልዋን፣ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይን፣ አቶ ኩማ ደመቅሳን፣ አቶ ህላዊ ዮሴፍን የመሳሰላችሁና የ17 ዓመቱ መራራ የትጥቅ ጥግል አካል የነበራችሁ ወገኖች - “ሙሉ የወጣትነት ዕድሜአችሁን በታጋይነት ያሳለፋችሁትና ብዙ ሺህ ጓዶቻችሁን በረሃ ላይ ቀብራችሁ የመጣችሁት ታገልንለት ያላችሁት ሀገርና ህዝብ እንዲህ በህልውና አደጋ ላይ ሲወድቅ የፖለቲካ ጡረተኛ ሆናችሁ
በዝምታና በትዝብት ለማየት ነበርን?”

↪ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን፣ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋን፣ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን፣ ዶ/ር በለጠ ሞላን የመሳሰላችሁ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር የሆናችሁና ሹመት ላይ የምትገኙ ወገኖች - “ለብዙ ዓመታት የደከማችሁበት የተቃውሞ ትግል የመጨረሻ ግብ የአምባገነን መሪ ሹመት ተቀብሎ የ አገዛዝ ስርዓት አጃቢና ተባባሪ ለመሆን ነበርን?”
ክብርት ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴን፣ ዶ/ር ዳንኤል በቀለን፣ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊን፣ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን፣ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያን፣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የመሳሰላችሁና ከፍተኛ የሞራል ልዕልናና የህዝብ አክብሮት ያተረፋችሁ ወገኖች - “የህይወት ዘመናችሁ የመጨረሻ ስኬት ከአምባገነን ስርዓት ሹመት ተቀብሎ የአገዛዝ መዋቢያ ጌጥ መሆን ነውን?”

↪በ27 ዓመቱ የትግል እንቅስቃሴ የፓርቲ አመራር፣ አክቲቪስትና ጋዜጠኛ ሆናችሁ በግንባር ቀደምትነት ስትታገሉ የምናውቃችሁ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ አርቲስት ታማኝ በየነን፣ አቶ አንዱዓለም አራጌንና አቶ የሺዋስ አሰፋን የመሳሰላችሁ ወገኖች - “የዛሬው አገዛዝ በሁለንተናዊ መልኩ ከትናንቱ አገዛዝ የባሰና የከፋ ሆኖ እያለ ዝምታን በመምረጥ ወይም ያልተገባ ሰበብ አስባብ በመስጠት ስርዓቱን ማባባል
ወይም በለሆሳስ መደገፍ የመረጣችሁት ቀድሞውንም የትግላችሁ የመጨረሻ ግብ የስርዓት ለውጥ ሳይሆን የህወሐት መውደቅና የጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ነበር ማለት ነውን?”

↪በአጠቃላይ ከዚህ በላይ የተጠቀሳችሁ ወገኖችና በስራችሁ ስኬት የህዝብ አድናቆትንና ክብር ያተረፋችሁ ተዋቂ ስፖርተኞች፣ የኪነ ጥበብ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ በተለያየ ደረጃ ሀገራችሁን ያገለገላችሁ የቀድሞ ባለስልጣናት፣ ወዘተ …ታዋቂና ባለዝና ብቻ ሳትሆኑ የሀገሩ ልሂቃንም ጭምር ናችሁና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የህዝቡ መሪዎች የመሆን ኃላፊነት አለባችሁ።

↔ዝናና ክብር ያለሀገርና ህዝብ ትርጉም የለውም። በሀገር መፍረስ ከሚመጣው አደጋም ማናችንም ተለይተን አንተርፍም። የወቅቱ ትግል ከፖለቲካ በላይ የሀገር ህልውና ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ቢያንስ ስለአገዛዙ ያለንን ተቃውሞ በድፍረትና በጋራ ‘ጮክ ብለን…’ ልናሰማ ይገባል። በአንድ አምባ-ገነን መሪ ምክንያት ሀገር ሲፈርስ ዝም ብሎ ማየት “ባላገር” ነኝ ብሎ ከሚያምን ማንኛውም ዜጋ አይጠበቅምና የታሪክና የትውልድ ሃላፊነታችንን በጋራ እንወጣ።

ልደቱ አያሌው
የካቲት 25 ቀን 2015 ዓ.ም

Esat tv

😆
04/03/2023

😆

የአገዛዙ መልክ ሜክ አፑ እየለቀቀ አሁን ትክክለኛ ገጽታው እየታየ ነው!በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ዛሬ የሆነው ወዴት እንደሚወስደን ለመግለጽ ነብይ መሆን አይጠይቅም። በሚኒሊክ አደባባይ የአድዋ ...
02/03/2023

የአገዛዙ መልክ ሜክ አፑ እየለቀቀ አሁን ትክክለኛ ገጽታው እየታየ ነው!በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን

ዛሬ የሆነው ወዴት እንደሚወስደን ለመግለጽ ነብይ መሆን አይጠይቅም። በሚኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል እንዳይከበር መደረጉ ነገ ምን ዓይነት እርምጃ ሊወስዱ ምልክት እያሳዩን እንደሆነ በግሌ ገብቶኛል። ጊዮርጊስ አጠገብ የቆመውን የሚኒሊክ ሀውልት ማፍረስ በቀጣይ የምንመለከተው ነገር እንደሚሆን አልጠራጠርም። የሀጫሉ ሞት ጊዜ ታስቦ እንደነበረ አስታውሳለሁ። አዲስ አበባን ስሟን ቀይሮ ወደ ኦሮሚያ ክልል የመጠቅለል ውሳኔም ከጠረጴዛ ላይ የተቀመጠ ፋይል ሆኗል። ከወደጨፌ ኦሮሚያ ሀሳቡ ተነስቶ አራት ኪሎ ቆይ ትንሽ ታገሱ ብሎ እንዳዘገየው ሽው የምትል መረጃ ከጆሮዬ ከጠለቀች ሰነባብታለች።

የኦሮሚያ ብልጽግና የኦነግን አጀንዳ አንድ በአንድ በማስፈጸም ላይ ይገኛል። ከእንግዲህ ሸኔ ሰው ማረድ አያስፈልገውም። ኦነግ ነፍጥ ተሸክሞ ጫካ ለጫካ መርመጥመጡ ትርጉም የለውም። በኢትዮጵያ ስም የሚምምል በገቢር ኢትዮጵያን የሚገዘግዝ መንግስት አጀንዳቸውን በቅደም ተከተል እያስፈጸመላቸው ነው። ጎበዝ፥ ኦነግ ሸኔ ብላችሁ በማጉሊያ መነጽር ሩቅ አትመለከቱ። ያርዳል፡ ይጨፈጭፋል ብላችሁ ስትርግሙት ስትከሱት ከኖራችሁት ቡድን ላይ የጠነቆላችሁትን ጣት አንሱት። ኦነግ ሸኔ የጦስ ዶሮ ነው።

ኢትዮጵያ ብርቱ አደጋ ላይ ናት። የተፈራው ነገር ድሆ ድሆ መጥቷል። የኢትዮጵያዊነት ካባ ለብሶ አራት ኪሎ የገባው አገዛዝ ቀስ በቀስ፡ እያስታመመ የመገዝገዝ ስራውን አከናውኖ አሁን በአደባባይ ተግባራዊ ወደማድረግ ምዕራፍ በይፋ ገብቷል። ለጨዋታ ማሳመሪያና፡ በድንዛዜ ውስጥ ላሉት፡ ዓይን ልቦናቸው በባዶ ትርክት ለተሸበቡት ወገኖች አሁንም 'ኢትዮጵያ አትፈርስም' ዲስኩር እየተለቀቀላቸው ጥቂት ጊዜያት መቆየቱ አይቀርም። ኢትዮጵያን የማወላለቁ ስራ ከጓዳ ወደ ደጅ መውጣቱን የሚያሳዩ ተግባራት በየዕለቱ እየበረከቱ መጥተዋል። መደባበቅ አያስፈልግም። በሀገር ጉዳይ መሽክርመሙ ዋጋ እያስከፈለ ነው። ይህ ሟርተኝነት አይደለም። ካስባለም እኔ ሟርተኛ ሆኜ ልቅር፡ ይሄን ሳልተነፍስ ከምቀር።

ኢትዮጵያን ለማዳን ጊዜው አልረፈደም። በጣም ከባድ ቢሆንም የማይቻል ግን አይደለም። መቃብር የማሱላትን ወደጥልቁ መቃብር የከተተች ተአምረኛ ሀገር ናት። አለቀላት ሲባል ብድግ ብላ የምትገዝፍ ድንቅ ሀገር ባለቤቶች ነን። አጎንብሰን ሊሆን ይችላል እንጂ አልተሰበርንም። መጀመሪያ በድንዛዜ ያሉ የቀሩ ወገኖች እንዲነቁ ማድረግ ቢቻል ጥሩ ነው። ካልሆነም ለውጥ ለማምጣት ጥቂት የቆረጡ በቂ ናቸው። እናስብ። ምን እየተደረገብን እንዳለ በጥልቅ እንመርምር። እየሆነብን ያለውን ከፍርሃት ወጥተን እንፈትሽ። ኢትዮጵያ ስሟ ደስ ስለሚለን፡ ስለምንወዳት አይደለም። ህልውናችን ስለሆነች እንጂ!

24/02/2023

የዩክሬን ወታደሮች ባክሙት ውስጥ አስደንጋጭ ነገር ገጠማቸው | ጆባይደን እንደለማዳቸው ወደቁ | አውሮፖውያን ሳይስማሙ ተበተኑ

ሰሞኑን ሰው ሁሉ በ19 ሚሊዮን ብር  ስለተገዛው  አዲሱ ባስ ሲያወራ ለምን ሄጄበት አልሞክረውም ብዬ ዛሬ ከጀሞ 1 ወደ ሜክሲኮ ሄጄ ነበር። ..ባስ ስቴሽኑ ጋ የደረስኩት ከጠዋቱ 12 ሰአት ...
22/02/2023

ሰሞኑን ሰው ሁሉ በ19 ሚሊዮን ብር ስለተገዛው አዲሱ ባስ ሲያወራ ለምን ሄጄበት አልሞክረውም ብዬ ዛሬ ከጀሞ 1 ወደ ሜክሲኮ ሄጄ ነበር። ..
ባስ ስቴሽኑ ጋ የደረስኩት ከጠዋቱ 12 ሰአት ሲሆን ከተደረደሩት አዲስ ባሶች ውስጥ አንዱን መርጩ ገባሁ። በር ላይ ሚኒ ስከርት የለበሰች አስተናጋጅ በፈገግታ ተቀብላኝ ጉንጬን ከሳመችኝ በኋላ ስልኳን ሰጥታኝ ወደ ውስጥ አስገብታ ወንበር አስያዘችኝ።..
በጣም ብርድ ስለነበር ከወንበሬ አጠገብ የነበረውን Heat የሚለውን በተን ክሊክ ሳደርገው ወዲያውን ከወንበሬ ዙሪያ ጠርዝ ላይ ነጭ ጋቢ ወጥቶ ሙሉ ሰውነቴን አለበሰው። በዚህ ተገርሜ እንደምንም ከጋቢ ውስጥ እጄን አውጥቼ ፊት ለፊቴ ያለውን ስክሪን ሳበራው መኪናው ላይ ስለተገጠሙት ቴክኖሎጂዎች የሚገልፅ ፅሁፍ መጣልኝ።..
ፅሁፍ ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ ክረምት ክረምት መንገዶች በጎርፍ ሲሞሉ ይሄ ባስ ወዲያውን ቅርፁን ወደ ዝርግነት በመቀየር ወደ መርከብነት የሚለወጥ ሲሆን በውስጡም መለስተኛ ኳስ ሜዳ እና የባስኬት ቦል ኮርቶች እንዲሁም ለፈረስ ግልቢያ የሚሆን ሰፊ ሜዳ ይዟል።..
ምናልባት ከቤቱ ተቻኮሎ ፊቱን ሳይታጠብ የመጣ ተሳፋሪ ካለ ባሱ የራሱን የፊት ሳሙና እና የጥርስ ብሩሽ ከኮልጌት ጋር እንዲሁም ከማይመለስ አንድ ፎጣ ጋር የሚያቀርብ ሲሆን ስቲም እና ሳውናም ከሾፌሩ ጀርባ ባለው ክፍል ውስጥ ዝግጁ ሆኖ ተሳፋሪዎቹን ይጠብቃል።..
በተጨማሪም መንገድ በሚዘጋበት ጊዜ ከጎን እና ከጎን ክንፎቹን በመዘርጋት ልክ እንደ ዴር 33 ከራዳር እይታ ውጪ መብረር የሚችል ሲሆን ምናልባት በሰማይ ላይ እያለ የሰማይ ትራፊክ መጨናነቅ ቢያጋጥመው እንኳን ከስሩ እሳት በመፍጠር ራሱን ወደ መንኮራኩነት በመቀየር ወደ ጨረቃ የሚያምዘገዝግ የሮኬት ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።..
ለባለስልጣኖች ራሱን የቻለ መኝታ ቤት ያለው ሲሆን ለሰፊው ህዝብ ደግሞ ትኬት ሳይቆርጥ የገባን ቆርጦ ከገባው የሚለይ ሴንሰር ተገጥሞለታል። የሚገርመው ትኬት ያልቆረጡትን ሰዎች በስም መለየት የሚችል ሲሆን አንዱ ተሳፋሪ ሳይቆርጥ ገብቶ ወዲያውኑ "ደጀኔ እባክህ ወይ ቁረጥ ወይ ውረድ አትሞላፈጥ" በሚል ድምፅ ተሳፋሪውን ሲያስጠነቅቅ በጆሮዬ ሰምቻለሁ።..
በመጨረሻም ሜክሲኮ ባስ ስቴሽን ደርሰን ስንወርድ ለሁላችንም የጫማ ማስጠረጊያ እና ለቀጣይ ታክሲ መሄጃ ስልሳ ስልሳ ብር የተሰጠን ሲሆን ሾፌሩን ጨምሮ ሁሉም የባሱ ሰራተኞች በእግራቸው የተወሰነ መንገድ ሸኝተውናል። በእኔ እይታ ይሄ ባስ 19 ሚሊየን ሲያንስበት እንጂ ከዚህም በላይ ይገባዋል። Thank you አዴክስ ጭሷ!

ዳጊ ነኝ ከገፈርሳ ወንዝ ማዶ 🙂😂

©Dagmawi Dagmawi

16/02/2023

የሚመጣው የኦርቶዶክስ ትውልድ

15/02/2023

ሙሸራው እስኪመጣ የምትቆይ ቤተክርስቲያን እናድርጋት-የጠፉትን በጎች ይሄው ይዤላችሁ መጥቻለሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

 በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩት በቀድሞ ስማቸው እነ አባ ሳዊሮስ በዛሬው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተው የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግበዋል።
15/02/2023


በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩት በቀድሞ ስማቸው እነ አባ ሳዊሮስ በዛሬው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተው የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግበዋል።

የነዐምን ዘለቀ መልክት👇
15/02/2023

የነዐምን ዘለቀ መልክት👇

 ስም:- ሙላቱ ጅማስልክ:- +251914271504አድራሻ:- ጎሃ ፅዮን
14/02/2023


ስም:- ሙላቱ ጅማ
ስልክ:- +251914271504
አድራሻ:- ጎሃ ፅዮን

Address

ON

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ye-Sheger Demtse - VOS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share